
04/02/2023
እርሶንና እና ቤተሰብዎን ብሎም አስታማሚዎን ከእንግልት ሊያድን የጤና መድህን አገልግሎት አለውሎት ይላል!
ስለ ጤና መድህን ግንዛቤ እንዲኖርዎ ይፈልጋሉ? አዎን
ጤና መድን ዓይነቶች የጤና መድን አገልግሎት ሁለት ዓይነት የመድህን ዓይነቶችን ይዞ በኢትዮጵያ ጤና መድን ኤጀንሲ የሚሰራ እና የሚመራ ነው።
አንደኛው የተጀመረው ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት (CBHI) ሲሆን ፤ሁለተኛው ደግሞ ማህበራዊ ጤና መድህን (SHI) ይሰኛል።
ባህሪያቸው ምን ይመስላል?
1) የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን (CBHI) ምንድን ነው?
የማህበረሰብ አቀፍ ማለት በአንድ አካባቢ ተመሳሳይ የሆነ የአኗኗር ዘይቤ የሚከተል፣ መደበኛ ገቢ የሌለው የኅብረተሰብ ክፍል ነው።
መደበኛ ገቢ የሌለው ሲባል በተለይ የገጠሩ ማህበረሰብ ተጠቃሽ ነው። በገጠር የሚኖረው ማህበረሰብ በአብዛኛው በግብርና የሚተዳደር በመሆኑ ያመረተውን በመሸጥ የሚተዳደር ነው።
በተጨማሪም የተለያዩ የዕጅ ባለሙያዎች መደበኛ ያልሆኑ ሥራዎችን በመስራት በሚያገኙት ገቢ የሚተዳደሩትን ጭምር የሚያካትት ነው።
በሚሰራው አነስተኛ ሥራ ትርፍና ኪሳራ አለው ሊባል የማይችል በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን ሊጠቃለል ይችላል።
2) የማህበራዊ የጤና መድህን፡- ይህ የጤና መድን ሥርዓት በግልም ሆነ በመንግሥት ተቀጥሮ የሚሰራና ወርሃዊ ደመወዝ የሚከፈለውን የማህበረሰብ ክፍል የሚያካትት ነው።
በትምህርት ደረጃውም፣ በግንዛቤውም፣ በቋሚ ገቢውም፣ በአኗኗር ዘይቤውም ተመሳሳይነት ያላቸውን የሚያካትት ነው።