Life Care Drug Store Assosa

Life Care Drug Store  Assosa Always there to care

05/05/2023

የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የፊት እና የአፍ ውስጥ የቀዶ ህክምና ተደራሽ ለማድረግ በማሰብ ከግንቦት 5 -12/2015 ዓ.ም ከካናዳ (ቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ) በሚመጡ የፊት እና የአፍ ውስጥ ቀዶ ጥገና (oral and maxilofacial surgery) ስፔሻሊስቶች ጋር በመተባበር የቀዶ ህክምና አገልግሎት ስለሚሰጥ የሚከተሉትን የህክምና አይነቶች ችግር ያለባችሁ ታካሚዎች እንድትመዘገቡ እና የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ እናሳውቃለን፡፡

መመዝገብ የሚችለው የህመም አይነቶች፦

- የመንጋጋ መገጣጠሚያ እና የአፍ አለመከፈት ችግር
- የፊት አካባቢ የነርቭ ህመም
- የፊት አካባቢ እና የአፍ ውስጥ እባጮች ካንሰርን ጨምሮ
- የምራቅ አመንጪ እጢዎች ህመሞች
- የፊት እና የመንጋጋ አጥንት ስብራት
- የፊት አጥንቶች እድገት አለመመጣጠን እና የፊት መጣመም ችግር
- የፊት እና የመንጋጋ አጥንቶች በተፈጥሮዊና በጉዳት የሚከሰቱ የገጽታ ችግሮች
-የከንፈር እና ላንቃ መሰንጠቅ ችግር

መመዝገቢያ ቦታዎች፦

በጥቁር አንበሳ ስፔሻሊዝድ ሆስፒታል ስኳር ማዕከል የጥርስ ህክምና ክፍል(1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር ቁ.14------+251913895471 ዶ/ር ፌቨን ወይም ዶ/ር ቀመር +251910056584
በአ.አ ዩኒቨርሲቲ የጥርስ ህክምና ማዕከል(6ኪሎ) -----0966138504 ዶ/ር ዘርሁን

02/05/2023

ለሴቶች የመካንነት ምርመራ መቼ ቢጀመር ይመከራል?

- ከ35 ዓመት በታች ሆና ያለምንም መከላከያ እስከ1 ዓመት ለማርገዝ ሞክረዉ ካልተሳካ ምርመራ መጀመር አለባት።

- ከ35 ዓመት በላይ ሆና እስከ6 ወር ሞክረዉ ካልተሳካ ምርመራ መጀመር አለባት።

- ከ40 ዓመት በላይ ከሆነች ወዲያዉ ምርመራ መጀመር አለባት።

ይደዉሉልን: 0945484848 / 0946484848

አድራሻ: ብስራተ ገብርኤል ደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ፊትለፊት።

ለበለጠ መረጃ ድረ ገጻችንን www.newleaffertility.org ይጐብኙ።.
https://vm.tiktok.com/ZMYGkQrPd/newleaf

https://www.facebook.com/100114186277691/posts/169495622672880/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6vnewleafet

Telegram: t.me/newleafcenterbot

02/05/2023
29/03/2023

አእምሮ ያለው ማንኛውም ሰው የአእምሮ ህመም ሊያጋጥመው ይችላል። የሌላቸው ሰዎች ግን አያሰጋቸውም።

📷 በአንድ ወቅት አማኑኤል ሆስፒታል

ያለ አእምሮ ጤና ፤ ጤና የለም!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

29/03/2023

የብዙ ህጻናትን ነፍስ የታደገው የልብ ሰብ-ስፔሻሊስቱ ሐኪም በፀና ታሟል

ዶ/ር አሊ ዳውድ ይባላል በጥቁር አንበሳ የህጻናት ልብ ማእከል Pediatric Interventional Cardiologist ነው። ትሁት ፣ ቀና እና በከፍተኛ ደረጃ የህጻናት የልብ ህክምናን በውጭ ሀገር ሰብስፔሻላይዝ አድርጎ በምጣት በማከም ላይ የሚገኝ ሲሆን ከቀናት በፊት ግን በሳንባ ካንሰር (Lung Cancer) እንደተጠቃ ሐኪሞቹ ባደረጉለት ምርመራ አረጋግጠዎል ።

ህክምናውንም ለማድረግ ወደ ውጭ ሀገር ባፋጣኝ መሔድ እንደሚኖርበት የጥቁር አንበሳ የሀኪሞች ቦርድ ወስኗል ለዚህም በርከት ያለ ገንዘብ እንደሚያስፈልገው ለመረዳት ችለናል።

ይህን እንቁ ሐኪም ተረባርበን ከፈጣሪ ጋር ጤናውን እንመልስ ዘንድ፣ ለቤተሰቡና ፣ ለ3ቱ ታዳጊ ልጆቹ እንዲሁም በሽህ ለሚቆጠሩ የልብ ታማሚ ሀጻናት ድጋሜ ተስፋ እንሁናቸዉ ስንል የእርዳታ እጃችሁንእንድትዘረጉ እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ: 1000533184271
Sofia Seid and/0r Ali Dawed

አዋሽ ባንክ: 013200510684101 Sofia Seid YIMER and/0r Ali Dawed Mohamed

Dr. Ali Dawed, 43 years old, is the only pediatric interventional cardiologist in Ethiopia who is currently working at the Cardiac Center in Addis Ababa.

He performs various advanced endovascular cardiac procedures for children born with serious congenital heart defects. He saved numerous lives and positively impacted the life of thousands of Ethiopian children.

Dr. Ali, who is a father of three children was recently diagnosed with lung cancer and is seriously ill. The Medical Board of Tikur Anbessa Specialized Hospital recommended treatment abroad.

Dr. Ali is a person who is very giving to others but now he is in need of our help to get the necessary treatment abroad and save his life. Please let’s lend him a hand and donate so that he can return to helping his family and patients.

For those who are living in the Diaspora, you can use the Gofundme account below!
Thank you

https://www.gofundme.com/f/doctor-alis-medical-support/donations?utm_campaign=p_cp+share-sheet&utm_content=undefined&utm_medium=copy_link_all&utm_source=customer&utm_term=undefined

27/03/2023

ቲማቲምን የመመገብ የጤና ጥቅሞች
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

• ቲማቲምን መመገብ ለቆዳ ጥራት ጠቃሚ ነው፡፡
ቲማቲም በውስጡ የያዘው ንጥረ ነገር ለቆዳ ተስማሚ የሆነ ሲሆን ቲማቲምን ልጦ የልጣጩን ውስጠኛ ክፍል በፊትዎ ላይ በመለጠፍ ለ10 ደቂቃ በማቆየት መታጠብ ንፁህና የሚያበራ ፊት እንዲኖርዎ ያደርጋል፡፡

• ቲማቲም የተለያዩ የካንሰር ዓይነቶችን ይከላከላል
ጥናቶች እንደሚያሳዩት በቲማቲም ውስጥ የሚገኘው ሊኮፒን የተባለ ንጥረ ነገር በፕሮስቴት ካንሰር፣የጨጓራ እና የአንጀት ካንሰርን የመከላከል አቅም አለው፡፡

• ጠንካራ አጥንት እንዲኖረን ያደርጋል
ቲማቲም በውስጡ ካልሲየም እና ቫይታሚን ኬን የያዘ ሲሆን ሁለቱም ንጥረ ነገሮች አጥንትአጥንት እንዲጠነክር ያደርጋሉ።

• ቲማቲም ለልባችን ጠቀሜታም አለው
ቲማቲም በቫይታሚን ቢ እና በፖታሺየም የበለፀገ ሲሆን ኮሌስትሮልን እና የደም ግፊትን የመቀነስ አቅምም አለው፡፡ ቲማቲምን በዕለት ተዕለት የምግብ ስርአትዎ ውስጥ ማስገባት ከድንገተኛ የልብ ሕመም እና ኮሌስትሮል እራስዎን ይከላከላሉ፡፡

• ለፀጉርዎ ጠቀሜታ አለው
በቲማቲም ውስጥ የሚገኘው ቫይታሚን ኤ ፀጉርዎን ጠንካራና ያማረ እንዲሆን ያደርጋል።

• ቲማቲም ለኩላሊት ጠጠር የመጋለጥ ዕድልዎን ይቀንሳል

• ለዓይንዎ ጥራት
በቲማቲም ውስጥ የሚገኘው ቫይታሚን ኤ ለዓይንዎ ጥራት እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ጥናቶች ይገልጻሉ፡፡

ጤና ይስጥልኝ

27/03/2023

ቦርጭን ለማጥፋት የሚጠቅሙ ምክሮች
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

በሰውነታችን ላይ የስብ መከማቸት ለተለያዩ የጤና ችግሮች እንደሚዳርግ የሚታወቅ ነው፡፡ ለምሳሌ፡

✔ ለልብ ሕመም
✔ ለስኳር ሕመም
✔ ለደም ግፊት መጨመር
✔ ለከፍተኛ ኮሌስትሮል

በአብዛኛው ስብ የሚከማችበት ቦታ ሆድ አካባቢ ሲሆን ይህም ቦርጭ ብለን የምንጠራው ነው፡፡ ቦርጭን ሊያመጡ የሚችሉ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

✔ ሊተኙ ሲሉ መመገብ
✔ ሰዓትን ጠብቆ አለመመገብ
✔ በሰውነታችን የሚገኙ ሆርሞኖች ለውጥ
✔ ጭንቀት
✔ ቅባት የበዛባቸው ምግቦችን መመገብ
✔ በተፈጥሮ የሚመጣ

► ቦርጭን ለማጥፋት

✔ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ አንድ ብርጭቆ ሎሚ ያለው ውኃን ጠዋት መጠጣት

✔ አረንጓዴ ሻይ መጠጣት፡- በውስጡ በያዘው ንጥረ ነገር ምክንያት አላስፈላጊ ስብን የማስወገድ አቅም እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

✔ ስብ የማቃጠል ችሎታ ያላቸው ምግቦችን መመገብ፡- እነዚህም እንደ ብሮክሊ፤ካሮት፤ጎመን ያሉ አትክልቶቸ፤ እንዲሁም እንደ ፖም፤ ሃብሃብ፤ ፓፓዬ ያሉ ፍራፍሬዎችን ማዘውተር

✔ ጤናማ የሆነ አመጋገብ እንዲኖረን ማድረግ ፡- የተመጣጠነ እና አትክልት የበዛበት የምግብ ባሕልን ማዳበር

✔ በቀን ውስጥ የምንጠጣውን የውኃ መጠን መጨመር

✔ ቁርስን በሚገባ መመገብ፡- ይህን ማድረግ የረሃብ ስሜት እንዳይሰማንና ማስታገሻ የሚሆኑ ተጨማሪ ስኳር እና ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች እንዳንመገብ ያደርጋል፡፡

✔ የአካል ብቀት እንቅስቃሴ ማድረግ፤ ዋና መዋኘትን ማዘውተር በቀን ለ30 ደቂቃ ያህል የእግር መንገድ መሄድ

✔ እንቅልፍ አለማብዛት
✔ ጭንቀት ማስወገድ
✔ ለስላሳ መጠጦችን አለማዘውተር ናቸው፡፡

ጤና ይስጥልኝ

14/10/2022

የማይግሬን ራስምታትን ለማስታገስ
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

1. የተረጋጋ እና ፀጥ ያለ ቦታ ይምረጡ

✔ በአካባቢዎ የሚገኝ መብራት ማጥፋት እና ከተቻለ እንቅልፍ መተኛት፣

✔ የሞቀ ወይንም የቀዘቀዘ ውኃን በላስቲክ በማድረግ በእራስዎ እና በአንገትዎ ላይ ማስቀመጥ፣ ይህ ማለት ደግሞ

• ቅዝቃዜው በማደንዘዝ ሕመም እንዳይሰማዎ ሲያደርግ ሙቀቱ ደግሞ የራስና የአንገት ጡንቻዎችን እንዲፈታቱ ያደርጋል

• ሕመም የሚሰማዎ ቦታ ላይ በቀላሉ ማሸት አንገትዎን እና ትከሻዎን ማሸት

✔ ገላዎን በሙቅ ውሀ መታጠብ

2. በቂ እረፍት ማድረግ

✔ መደበኛ የእንቅልፍ ሰዓት ይኑርዎ

✔ ሁሌም በተመሳሳይ ሰዓት የመተኛት ልምድ ያዳብሩ

✔ በቀን እንቅልፍ መተኛት ያስለመዱ ከሆነ ከ20-30 ደቂቃ ብቻ ቢሆን ይመከራል። ከዛ በላይ እንቅልፍ ከወሰዱ የለሊት እንቅልፍዎን ሊያዛባ ይችላል

✔ እንቅልፍዎ ያልመጣ ከሆነ እራስዎን አያስገድዱ መጽሐፍ በማንበብ ራስዎን ያድክሙ

3. አመጋገብዎን ያስተካክሉ

✔ መደበኛ የሆነ የምግብ ሰዓት ይኑርዎ

✔ ቁርስዎን መመገብ አይዘንጉ

✔ ማይግሬን ቀስቃሽ የሆኑ ምግቦችን ያስወግዱ (እንደ ቼኮሌት፣አይብ፣ቡና እና የአልኮል መጠጦች)

4. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የማይግሬን ራስ ምታትን ይቀሰቅሳል ነገር ግን ሐኪምዎን በማማከር ቀለል ያሉ እንቅስቃሴዎችን ያድርጉ

(ለምሳሌ እንደ ውሃ ዋና፤የእግር ጉዞ የመሳሰሉትን ማድረግ ይችላሉ)

5.ጭንቀትዎን ይቆጣጠሩ

ጭንቀት የማይግሬን ራስ ምታትን ይቀሰቅሳል፡፡ በዕለት ተዕለት የኑሮ ሁኔታዎች የሚያጋጥሙንን አስጨናቂ ነገሮች መከላከል ባይቻልም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በመፈፀም መቀነስ ይችላሉ።

✔ ቀለል ያለ የኑሮ ዘይቤ ይኑርዎ

✔ ጊዜዎን በአግባቡ ይጠቀሙ

✔ የዕረፍት ጊዜ ይኑርዎ

✔ ለነገሮች በጎ አመለካከት ይኑርዎ

✔ ራስዎን ዘና ያድርጉ

6. የራስ ምታትዎን በተመለከተ የግል ማኅደር ይኑርዎ

✔ በግል ማኅደር መመዝገብ ራስምታትዎን የሚያስነሳውን ሁኔታ ለማወቅ እና ምን እንደሚያስታግስልዎም ለማጤን ይረዳል፡፡

ጤና ይስጥልኝ

 #የጥንቃቄ  #መልክት! ሼር ይደረግ!!!የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በቅርቡ በጋምቢያ ለህጻናት  #ሞት ክስተት በሆኑት አራቱ የመድኃኒት ምርቶች ሁኔታ እና በአለም ጤና ድርጅት ...
14/10/2022

#የጥንቃቄ #መልክት! ሼር ይደረግ!!!

የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በቅርቡ በጋምቢያ ለህጻናት #ሞት ክስተት በሆኑት አራቱ የመድኃኒት ምርቶች ሁኔታ እና በአለም ጤና ድርጅት በተሰጠው መረጃ መሰረት ሁኔታውን በቅርበት በመከታተል ላይ ይገኛል፡፡

አራቱ ምርቶች Promethazine Oral Solution, Kofexmalin Baby Cough Syrup, Makoff Baby Cough Syrup እና Magrip N Cold Syrup ናቸው፡፡የእነዚህ ምርቶች አምራች የሆነው በህንድ ሀገር የሚገኘው Maiden Pharmaceuticals ነው። አምራች ድርጅቱ ምርቶችን ወደ ኢትዮጵያ #ለማስገባት #እውቅና #ያልተሰጠው ፤ #ምርቶቹም #ያልተመዘገቡ ከመሆናቸውም በላይ በየትኛውም #ህጋዊ በሆነ መልኩ #ወደ #ኢትዮጵያ #ያልገቡ መሆናቸውን ያሳውቃል፡፡ነገር ግን በተለያየ መልክ ህጋዊ ባልሆነ መልኩ ቢገባ እንኳን በሚል አስፈላጊውን የሰርቬይላንስ እና ክትትል ስራዎች እያከናወነ ይገኛል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ከእነዚህ ከላይ ከተዘረዘሩት የመድኃኒት አይነቶች በተጨማሪ በአምራች ድርጅቱ የተመረቱ ሌሎች መድኃኒቶችም ላይ ክትትል እያደረገ ይገኛል፡፡

ባለስልጣኑ በየጊዜው ወቅታዊ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ የሚያቀርብ መሆኑን እየገለጽን #መረጃዎችን #ለመጠቆም ወይም #ለመስጠት #በነጻ #ስልክ #መስመር #8482 መጠቀም ህብረተሰባችን #ጥቆማ #መስጠት #እንደሚችል በአክብሮት ያሳውቃል፡፡

Address

Assosa, Infront Of Blendana (ብሌንዳና ፊትለፊት)
Asosa

Telephone

+251917179689

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Life Care Drug Store Assosa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Life Care Drug Store Assosa:

Share