Paulos Primary Hospital Awash 7 kilo

Paulos Primary Hospital Awash 7 kilo Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Paulos Primary Hospital Awash 7 kilo, Hospital, Afar Awash 7, Awash.

07/12/2024
ከወትሮ በተለየ የዉሃ መጥማትና ዉሃ ሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት ካለብዋ፣የክብደት መቀነስ፣ የድካም ስሜት በተደጋጋሚ መከሰት ፣ሰዉነትዎ ላይ ቁስል ኖሮት ቶሎ ያለመዳን ችግር ከገጠመዎ፣ የአፍ መድ...
07/12/2024

ከወትሮ በተለየ የዉሃ መጥማትና ዉሃ ሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት ካለብዋ፣የክብደት መቀነስ፣ የድካም ስሜት በተደጋጋሚ መከሰት ፣ሰዉነትዎ ላይ ቁስል ኖሮት ቶሎ ያለመዳን ችግር ከገጠመዎ፣ የአፍ መድረቅ ስሜት መኖር፣ እይታዎ ላይ ብዥ የማለት ስሜት መከሰት ከገጠመዎ፣የረሃብ ስሜት ቶሎ ቶሎ መሰማትና የመሳሰሉት የህመም ምልክቶች ከታየብዎ የስኳር ህመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል የህክምና ባልሙያዎ ጋ በመቅረብ የስኳር ህመም ምርመራ ያድርጉ።
የምንሰጣቸዉ አገልግሎቶች
*ጠቅላላ የቀዶ ህክምና
* የህጻናት እና እናቶች ክትትል
* የወሊድ አገልግሎት በGynacolgist
* የተሟላ የላብራቶሪ አገልግሎት
* የራጅ ምርመራ
* የጥርስ ህክምና
* የአይን ህክምና

አድራሻችን፦ አፋር ክልል አዋሽ 7 ከፓርክ ሆቴል ገባ ብሎ
*0222413285
*0924960000

30/11/2024
26/11/2024
25/11/2024

የኩላሊት መድከምን እንዴት መከላከል ይቻላል?

ኩላሊት ቆሻሻንና የማይፈለግ ( ትርፍ) ፈሳሽን ከደምዎ ዉስጥ በማጣራት በሽንት በኩል እንዲወገድ የሚያደርግ አካል ነዉ። ኩላሊት መስራት ስታቆምና ተግባፘን በአግባቡ መከወን ሲያቅታት የኩላሊት መድካም (kidney failure) ይከሰታል።

የኩላሊት መድከምን ለመከላከል የሚከተሉትን ምክሮች ይተግብሩ
1. የደም የስኳር መጠንዎን መቆጣጠር:- የስኳር ህመም ለልብ ህመም እና ለኩላሊት ድካም የመጋለጥ እድልን ይጨምራል።

2. የደምግፊትዎን መቆጣጠር፦ከፍተኛ የደም ግፊት ለልብ ህመምና ለኩላሊት መድከም የመጋለጥ እድልን ይጨምራል።

3. ጤናማና የተመጣጠነ የሰዉነት ክብደት አንዲኖርዎ ማድረግ፦ ከመጠን በላይ መወፈር ከኩላሊት መድከም ጋር ለተያያዙ እንደ የስኳር በሽታ እና የደም ግፊት ላሉ በሽታዎች የመጋለጥ እድልዎን ይጨምራል።

4. ጤናማ አመጋገብ መመገብ፦ ዝቅተኛ የስኳርና የስብ (ኮሌስትሮል) እንዲሁም ከፍተኛ ፋይበር፣ ጥራጥሬ አትክልት እና ፍራፍሬ ምግቦችን መመገብ የሰዉነት ክብደት መጨመርን ይከላከላል።

5. የጨዉ መጠንን መቀነስ፦ ጨዉ አብዝቶ መጠቀም ለደምግፊት እንዲጋለጡ ያደርጋል።

6. ዉሃ በበቂ መጠን መጠጣት፦ የፈሳሽ እጥረት ሲከሰት ወደ ኩላሊትዎ የሚሄደዉ የደም መጠን እንዲቀንስ ያደርጋል

7. አልኮሆል አለመጠጣት ወይም የአልኮሆል መጠንን መመጠን፦ መጠጥ የደም ግፊት መጠንን ይጨምራል

8. ሲጋራ አለማጨስ ፤ እያጨሱ ከሆነ ማቆም ፦ ሲጋራ ማጨስ ወደ ኩላሊትዎ የደም ፍሰትን ይቀንሳል፤ የኩላሊት ህመም ባለባቸው ወይም በሌላቸው ሰዎች ላይ ኩላሊት እንዲጎዳ ያደርጋል።

9. ያለሀኪም ትእዛዝ የሚወሰዱ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን ይቀንሱ፦ከፍ ባለ መጠን በሚወስዱበት ወቅት እንደ አስፕሪን ፣ ኢቡፕሮፌንና ናፕሮክሲን ያሉ ስቴሮይድ ያልሆኑ ፀረ-ብግነት መድኃኒቶች (NSAIDs) ወደ ኩላሊትዎ የሚሄደውን የደም ፍሰት መጠን ይቀንሳሉ፤ ይህም ኩላልትን ሊጎዱ ይችላሉ ።

10. ጭንቀትን መቀነስ፦ ጭንቀትን መቀነስ የደም ግፊትዎ እንዲቀንስ ያደርጋል

11. በመደበኛነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድራግ፦ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድራግ ጭንቀትን ለመቀነስ፣ የስኳር በሽታንና የደም ግፊትን ለመቆጣጠር እንዲሁም ጤናማ የሰዉነት ክብደት እንዲኖርዎ ያደርጋል።

Address

Afar Awash 7
Awash

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Paulos Primary Hospital Awash 7 kilo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category