አሴር የቤት ለቤት ህክምናና እንክብካቤ -ሐዋሳ/Asher Home Based Health Care-Hawassa

  • Home
  • Ethiopia
  • Awassa
  • አሴር የቤት ለቤት ህክምናና እንክብካቤ -ሐዋሳ/Asher Home Based Health Care-Hawassa

አሴር የቤት ለቤት ህክምናና እንክብካቤ -ሐዋሳ/Asher Home Based Health Care-Hawassa ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ዶክተሮችና ነርሶች የቤት ለቤት ህክምና

ዶ/ር ዘላለም ብለው ይደውሉ( 0913247243)። አገልግሎቱን ልምድ ባላቸው ዶክተሮችና ነርሶች ብቻ ያገኛሉ
23/12/2025

ዶ/ር ዘላለም ብለው ይደውሉ( 0913247243)። አገልግሎቱን ልምድ ባላቸው ዶክተሮችና ነርሶች ብቻ ያገኛሉ

09/01/2024
02/01/2022
19/12/2021

ምች የሚባል በሽታ ግን ምንድነው ?
( ምች በፀሐይ ይመጣል ወይስ አይመጣም?)

🔘 ምች የሚባለው በሽታ በእንግሊዘኛው herpes labialis የሚባለው ሲሆን ዋናው የበሽታው ምልክት ደሞ ሄድ መጣ የሚሉ ትናንሽ ዉሃ የቋጠሩ በከንፈር ዙሪያ የሚወጡ ቁስሎች ናቸዉ።

የምች መንስኤው ምንድነው?

የበሽታው ዋናው መንስኤው herpes simplex የሚባለው ቫይረስ ሲሆን በመሳሳም ወይም በ ሌሎች አካላዊ ግንኙነቶች አማካኝንት ከአንድ ሰዉ ወደ ሌላዉ ሰዉ በቀላሉ የሚተላለፍ ነው ::

ምልክቶቹ

- የመጠቅጠቅና የማሳከክ ስሜት
- ዉሃ የቋጠሩ ቁስሎች
- ትኩሳት
-የራስ ምታት
- የጡንቻ ላይ ህመም
-የአንገት ላይ ንፍፊትቶች እብጠት

-ለምች የሚያጋልጡ ነገሮች ምንድናቸው?

1. ለፀሃይ ብርሃን መጋለጥ

ፀሐይ ብርሃን ለብቻው ምች አያመጣም።
ነገር ግን ምች የሚያመጣው ቫይረስ (herpes simplex 1) ቀድሞ ይዞን እራሱ ነርቭ ህዋሶች ዉስጥ ይደብቃል ።

የፀሐይ ብርሃን ዉስጥ ባለው ultraviolet የሚባለው ጨረር ደሞ ሊነሳሳው (re activate ሊያረገው) እና ከተደበቀበት የነርቭ ስር ዉስጥ በ መውጣት ድጋሚ ወደ ቆዳ አካባቢ በመሄድ ሄድ መለስ የሚል ቁስል ሊያመጣ ይችላልይችላል
2. ቅባት ያለዉ ምግብ መመገብ
3. ጭንቀት
4. ኤች አይ ቪ ኤድስ
5. የካንሰር ህክምና
6. የወር አበባ ዑደት ጊዜ የሆርሞን መለዋወጥ

የጤና ባለሙያ ማማከር ያለብን መቼ ነው ?

- የበሽታ መከላከል ብቃት መቀነስ/የተዳከመ ከሆነ
- ቁስሉ በሁለት ሳምንት ጊዜ ዉስጥ ካልዳነ
- የህመሙ ምልክቶች ከፍተኛ ከሆኑ
- ህመሙ በተደጋጋሚ ከተከሰተ
-በአይን የመቆጥቆጥ ስሜት ሲሰማ

ሕክምናውስ ምንድን ነው?
-ጸረ- ቫይረስ መድሃኒት እና የህመም ማስታገሻ መድሐኒት መዉሰድ
- በቫይታሚንሲ የበለጸጉ እንደ ሎሚ፣ብርቱካን እና ፓፓያ ያሉ ምግቦችን
-በቀዝቃዛ ዉሃ በተነከረ ጨረቅ ወይም በበረዶ ቁራጭ በቀን ዉስጥ ለተወሰኑ ጊዜያት ከ5-10 ደቂቃ በቦታዉ ላይ መያዝ
- የአእምሮ ዉጥረትን/ ጭንቀትን መቅነስ
- ዳማከሴ (Ocimum Lamiifolium) የተባለዉ ተክል ቅጠል በማሸት ቁስሉ ላይ ማድረግ/መቀባት

( በነገራችን ላይ ዳማከሴ በተወሰነ ደረጃ ቢሆንም ቫይረስን የመቆጣጠር እና የማጥፋት ባህሪ እንዳለው ብዙ ጥናቶች ጠቁመዋል ።)

-ዉሃ የቋጠረ ቁስል ባለበት ወቅት የቆዳ ለቆዳ ንክኪ እንዳይኖር መከላከል፤
- ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ የሚዛመተዉ በሚያዥበት/ዉሃ በሚቋጥርበት ጊዜ ስለሆነ ሌላዉን የሰዉነት ክፍልዎን እንዳይነኩ መጠንቀቅ :- በተለይ አይንንና የብልት አካብቢ ለቫይረሱ በጣም ተጋላጭ ስለሆኑ ላለመንካት መጠንቀቅ፤
- የመገልገያ ዕቃዎችን በጋራ ያለመጠቀም፡- እንደ ፎጣ፣ መመገቢያ ዕቃዎችንና የመሳሰሉትን
-የእጅን ንፅህና መጠበቅ፡- ሌላ ሰዉ ከመንካት በፊት እጅዎን በደንብ ይታጠቡ ።

መልዕክቱን ሌሎችም ያዳርሱ።
ዶር ፋሲል መንበረ
የሕጻናት ስፔሻሊስት ሐኪምና ረዳት ፕሮፌሰር
T.me/eahci

 • የጀርባ ህመም በአለማችን ከ5 ሰዎች 3 ሰዎችን ያጠቃል። ብዙ ሰዎችን ከስራቸው ሳይቀር የሚያስተጐጉልና ወደ ህክምና ቦታ እንድመላለሱ የሚያደርግ ከባድ ችግር ነው።• በተለያየ አደጋ፡ አግ...
07/12/2021



• የጀርባ ህመም በአለማችን ከ5 ሰዎች 3 ሰዎችን ያጠቃል። ብዙ ሰዎችን ከስራቸው ሳይቀር የሚያስተጐጉልና ወደ ህክምና ቦታ እንድመላለሱ የሚያደርግ ከባድ ችግር ነው።

• በተለያየ አደጋ፡ አግባብ ባልሆነ የአካል እንቅስቃሴ፡ በተዛባ አቀማመጥና አተኛኘትና በተለያዩ ህመሞች ችግሩ ይፈጠራል።

• የጀርባ ህመም በማንኛውም የእድሜ ክልል ቢፈጠርም በእድሜ የገፉ፡ እርጉዞችና የነርቭ ኢንፌክሽን ያለባቸው ላይ ጎላ ያለ ነው።

• ቀድሞ ይሰሩት የነበረ ከባድ ስራ፡ የድስክ መንሸራተትና የጀርባ ላይ አደጋ እድሜ ሲጨምር የጀርባ ህመም እንድባባስ ያደርጋሉ።

• ጀርባ ከአጥንት፡ ከጅማት፡ ከጡንቻ፡ ከነርቭ፡ ከደም ቱቦና ከሌሎችም የተዋቀረ ነው።


• የድስክ መንሸራተት
• የተዛባ የሰውነት ቁመና
• አደጋ ወይም ምት
• የጀርባ ውልቃትና ወለምታ
• የጅማት መጨማደድናመለጠጥ
• የድስክ ጉዳት
• ስብራት
• መውደቅ
• ከባድ ነገሮች በዘፈቀደ ማንሳት፡ ማውጣት፡ ማውረድና ማንቀሳቀስ
• የድስክ መጉበጥና ማበጥ
• የነርቭ መጐዳት
• የጅማት ኢንፌክሽን
• የአጥንት መሳሳት
• የኩላሊት ችግር
• ለብዙ ሰአት መቀመጥና መቆም
• ብዙ ሰአት ኮምፒውተር ላይ ማታኮር
• ብዙ ሰአት በጀርባና በደረት መተኛት
• የጀርባ ካንሰር
• የዳሌ አጥንት ዙሪያ ኢንፌክሽን
• የነርቭ ኢንፌክሽን


• የስራ አይነት
• እርግዝና
• እርጅና
• ዘር
• ማጤስ
• ውፍረት
• የአጥንት መሳሳት
• የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ


• የደርባ ቁርጥማትና ህመም
• ክብደት መቀነስ
• ትኩሳት
• እብጠት
• የእግር ህመምና እብጠት
• የጉልበት ህመም
• ለመሽናት መቸገር
• መደንዘዝ
• ሽንትና ሰገራን መልቀቅ
• መጥፎ የጀርባ ስሜት
• መልፈስፈስ
የጀርባ ህመም ሲሰማዎት ፈጥነው የጤና ባለሙያ ያማክሩ። የጀርባ ህመም እንዳያጠቃዎት ከላይ የተዘረዘሩትን ምክንያቶች ተረድተው ከእነዚህ ምክናየቶች እራሰዎትን ያርቁ። ይጠንቀቁ።

#ወደህክምና ቦታ ሄደው ባለሙያ ሲያማክሩ በተለያየ መንገድ ምርመራ ስለሚደረግለዎት የችግሩ መጠንና ስፋት ተለይቶ ስለሚታወቅ ችግሩ እንዳይባባስና በቀላሉ እንድያገግሙ ይረዳዎታል።

#ህክምናው
• ብዙ ጊዜ እረፍት ማድረግ ይመከራል። ዋናውም መፍትሔ ነው።



1. ህመም ማስታገሻ መጠቀም
2. ምቅ ያለ ውሀ በፕላስቲክ ከረጢት አድርጎ ጀርባ ላይ ማድረግ
3. በረዶ በፕላስቲክ ከረጢት አድርጎ ህመም ያለበት ቦታ ላይ ማድረግ
4. ጀርባን መታሸት

#በጤና ባለሙያ ከታዩ በኋላ እንደ አስፈላጊነቱ መድሐኒት፣ ስፖርት እና ፊዚዎቴራፒ ይታቀዝለዎታል።

#አስታውሱ:
• በጀርባዎ እና በደረተዎ ከቻሉ አይተኙ። መጠነኛ የአካል እንቅስቃሴ ያስፈልገዎታል። ክብደት ቀንሱ። የጤና ምርመራ ያድርጉ።
Share

ሙሉ ጤንነት ከፈለጋችሁ . . . 1.  ለመንፈሳዊ ጤንነት - ፈጣሪን ፍሩ! በየእለቱ ጸሎት አድርጉ!2.  ለአካላዊ ጤንነት - ወደሰውነታችሁ ስለምታስገቡት ነገር ተጠንቀቁ! የአካል ብቃት እን...
26/11/2021

ሙሉ ጤንነት ከፈለጋችሁ . . .

1. ለመንፈሳዊ ጤንነት - ፈጣሪን ፍሩ! በየእለቱ ጸሎት አድርጉ!

2. ለአካላዊ ጤንነት - ወደሰውነታችሁ ስለምታስገቡት ነገር ተጠንቀቁ! የአካል ብቃት እንቅስቃሴን አድርጉ!

3. ለማሕበራዊ ጤንነት - ራስ-ተኮር አትሁኑ! ትክክለኛ የተግባቦት ክህሎትን አዳብሩ!

4. ለስነ-ልቦና ጤንነት - ራሳችሁን ተቀበሉ! ራሳችሁን ከሌላው ሰው ጋር አታነጻጽሩ!

5. ለስሜት ጤንነት - የምታሰላስሉትን ሃሳብ በቁጥጥር ስር አውሉ! ትክክለኛውን ስሜት በትክክለኛው ጊዜ፣ ቦታና መጠን መግለጽን ተማሩ!

Dr.Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me

26/11/2021



• ቶንሲል(Tonsil)የጉሮሮ የኋለኛ ክፍል ላይ የሚገኙ ትንንሽ ስጋ መሳይ የሰውነት አካል ናቸው። እነዚህ የሰውነት አካል ክፍል በበሽታ አምጭ ተዋህስያን ሲጠቁና ሲመረዙ የቶንሲል ኢንፌክሽን(Tonsillitis) ይባላል።

ማንኛውሜ ሰው ቶንሲል የሚባል የሰውነት አካል ከምላሱ ቀጥሎ ከጉሮሮ ኋላ ቀኝና ግራ ላይ አለው።

• ቶንሲል በሽታ አምጭ ተዋህስያን ወደታችኛው የመተንፈሻ አካል ክፍል እንዳይወርድ የማጣራትና የመከልከል ስራ በመስራት ሳንባንና የታችኛውን የመተፈሻ ቱቦ ይጠብቃል።

• የነዚህ የሰውነት አካል ክፍል መቆጣትና ማበጥ፣ መቅላት፣ የእንጥል ማበጥ መጐዝጐዝና መቆጣት፣ በአፍ መተንፈስ አለመቻል፣ የጉሮሮ ህመም፣ የቶንሲል በነጭ ወይም በቢጫ መሳይ ዝልግልግ ፈሳሽ መሸፈን፣ እራስ ምታት፣ የምግብ ፍላጎት መውረድ፣ የጆሮ ህመም፣ በአንገትና አገጭ ዙሪያ ያሉ እጢዎች ማበጥ፣ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ ለመናገር መቸገር፤ የአንገት እንቅስቃሴ መገደብና የመሳሰሉት ሲታዩ በተለምዶ ቶንሲል በሳይንሱ ደግሞ #የቶንሲል ኢንፌክሽን(Tonsillitis) ይባላል።

በተለይ በህፃናት ላይ የሆድ መነፋት፣ ማስታወክ፣ ማቅለሽለሽ፣ ጡት አለመጥባትና ትኩሳት ተጨማሪ ምልክቶች ናቸው።

• የቶንሲል ኢንፌክሽንን የአጭር ጊዜ፣ የሚደጋገምና የረጅም ጊዜ ተብሎ በሶስት ይከፈላል።

የቶንሲል መቆጣት በዋናነት (ስትሪፕቶ ኮከስ) በሚባል የባክቴሪያ ዝርያ የሚመጣ ሲሆን በተጨማሪም በሌሎች ባክቴሪያና በቫይረስ ይከሰታል።

• የጤና ባለሙያውና ልምዱ ያላቸው ሰዎች ምልክቶቹን በማየት የቶንሲል ኢንፌክሽንን ማወቅ ቢችሉም በፍጥነት ወደህክምና ተቋም በመሄድ ተገቢውን ምርመራና ህክምና ማግኘት ወሳኝ ነው።

የቶንሲል ኢንፌክሽን በጊዜው ካልታከመ የሚከተሉትን ተጨማሪ በሽታዎች ያመጣል።
• በቶንሲል ዙሪያ መግል መቋጠር
• የመካከለኛው የጆሮ ኢንፌክሽን
• የሳይነስ ኢንፌክሽን
• የኩላሊት ኢንፌክሽን
• የልብ ችግርና ሌሎችንም ችግር ያስከትላል።

የቶንሲል ኢንፌክሽን በቤት ውስጥ የግል እንክብካቤ፣ በመድሀኒትና ከዛም ከባሰ አንጥልንና ቶንሲልን በመቁረጥ ይታከማል።

• በቤት ውስጥ በቂና ብዙ እረፍት በመውሰድ፡ ለስለስ ያሉ ምግቦችን በመመገብ፡ ሞቅ ያለ ውሀ ላይ ጨው ጨምሮ ጉሮሮ ውስጥ በማኩረፍረፍ ወይም መጉመጥመጥና ህመም ማስታገሻ በመውሰድ ችግሩን መቀነስና እንዳይደጋገም ማድረግ ይቻላል።
• #በተለምዶ ቀዝቃዛ ውሀ መጠጣት ለቶንሲል ኢንፌክሽን ይዳርጋል የሚባለዉ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን እንደውም በተቃራኒው በጣም የቀዘቀዘና በመጠኑ የሞቀ ውሀ የቶንሲል ኢንፌክሽንን ይከላከላል።
• ንፅህናን በመጠበቅ(እጅን በስርአቱ በመታጠብ)፡ ከማንም ጋር ምግብ መጠጥ መገልገያ እቃዎችንና የጥርስ ቡርሽ ባለመጋራትና በጉሮሮና በቶንሲል ኢንፌክሽን ከተጠቃ ሰው ጋር ግንኙነትን በመቀነስ የቶንሲል ኢንፌክሽንን መከላከል ይቻላል።

  ኩላሊትዎ ሽንት ለመስራት ከደማችን ውስጥ ቆሻሻ እና ፈሳሽ ያስወግዳል ፤አንዳንድ ጊዜ የተወሰኑ ቆሻሻዎች ሲበዙ እና በደምዎ ውስጥ በቂ ፈሳሽ በማይኖርበት ጊዜ እነዚህ ቆሻሻዎች በኩላሊቶችዎ...
18/11/2021



ኩላሊትዎ ሽንት ለመስራት ከደማችን ውስጥ ቆሻሻ እና ፈሳሽ ያስወግዳል ፤አንዳንድ ጊዜ የተወሰኑ ቆሻሻዎች ሲበዙ እና በደምዎ ውስጥ በቂ ፈሳሽ በማይኖርበት ጊዜ እነዚህ ቆሻሻዎች በኩላሊቶችዎ ውስጥ ሊከማቹ እና ጠጠር ሊፈጥሩ ይችላሉ ፡፡
👉አጋላጭ ሁኔታዎች
ከዚህ በፊት የኩላሊት ጠጠር ከነበረቦት
በቂ ውሃ ካልጠጡ
በፕሮቲን ፣ በሶዲየም እና ወይም በስኳር የበለፀገ አመጋገብ የሚያዘወትሩ ከሆነ
ከመጠን በላይ ክብደት ካሎት
የፖሊሲስቲክ የኩላሊት በሽታ ካለብዎት
እንደ ዳዩሬቲክስ ያሉ መድሃኒቶችን የሚጠቀሙ ከሆነ

👉ምልክቶቹ
ከጎድን አጥንቶች በታች ከባድ ህመም
በሽንት ጊዜ ህመም ወይም ማቃጠል ስሜት
ቀይ ወይም ቡናማ የሽንት ቀለም
መጥፎ ሽታ ያለው ሽንት
የማያቋርጥ ፍላጎት መሽናት ፣ ከተለመደው ብዙ ጊዜ መሽናት ወይም በትንሽ መጠን መሽናት
ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ
ትኩሳት እና ብርድ ብርድ ማለት
👉ህክምና
የምርመራዎ ውጤት የኩላሊት ጠጠርዎ ትንሽ መሆኑን ካሳየ የህመም ማስታገሻ መድሃኒት መውሰድ እና ጠጠሩን በሽንት ቧንቧዎ በኩል ለማውጣት የሚያግዙ ብዙ ፈሳሽ መጠጣት
ሊቶትሪፕሲ ፤ይህ ህክምና የኩላሊት ጠጠርን ወደ ትናንሽ ቁርጥራጮች በመከፋፈል ማስወጣት ነው

👉መከላከያ መንገዶች

በየቀኑ በቂ ፈሳሽ መጠጣት ፤በቀን ከስምንት እስከ 12 ብርጭቆ ውሃ መጠጣት (የኩላሊት በሽታ ካለብዎ እና ፈሳሾችን መገደብ ከፈለጉ በየቀኑ ምን ያህል ፈሳሽ እንደሚያስፈልጎት ሐኪምዎ ይጠይቁ)
በአመጋገብዎ ውስጥ ሶዲየም እና የእንስሳት ፕሮቲን (ስጋ ፣ እንቁላል) መገደብ ጥራጥሬዎች ያሉ እንስሳ ያልሆኑ የፕሮቲን ምንጮችን ይምረጡ
የጨው መጠን ይቀንሱ
በሞቃት እና ደረቅ የአየር ንብረት ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ ወይም ብዙ ጊዜ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ከሆነ በቂ ሽንት ለማምረት እንኳን የበለጠ ውሃ መጠጣት ይኖርብዎታል።

አድራሻችን

ሀዋሳ 0913421022/0965410000

በባዶ ሆድ ውሃ የመጠጣት የጤና ጥቅሞች********************************1. በባዶ ሆድ ውሃ መጠጣት አንጀትን በማጽዳት ለሰውነታችን ጠቃሚ የሆኑ የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን በቀ...
15/11/2021

በባዶ ሆድ ውሃ የመጠጣት የጤና ጥቅሞች
********************************
1. በባዶ ሆድ ውሃ መጠጣት አንጀትን በማጽዳት ለሰውነታችን ጠቃሚ የሆኑ የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን በቀላሉ እንዲመጥ ይረዳናል፡፡

2. አዲስ የደም እና የጡንቻ ሴሎች እንዲመረቱ ያደርጋል።

3. ክብደትን ለመቀነስ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ጠዋት ከእንቅልፍዎ ሲነሱ ቀዝቃዛ ውሃ መጠጣት ሜታቦሊዝምን ያፋጥናል፡፡

4. ሲያዩት የሚያምርና ጤናማ የሆነ ቆዳ እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ ውሃ በደም ውስጥ የሚገኙ መርዛማ ነገሮችን ጠራርጎ በማስወጣት ቆዳችን ንጹህ፣ ለስላሳና አንጸባራቂ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡

5. የሊምፍ ሥርዓታችን (Lymph System) የተመጣጠነ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ እነዚህ ዕጢዎች የዕለት ከዕለት ተግባራችንን በትክክል እንድንወጣ፣ የሰውነታችን ፈሳሽ የተመጣጠነ እንዲሆን እና ኢንፌክሽንን እንድንዋጋ ይረዱናል፡፡

✔ውሃን በመጠቀም የሚደረግ ህክምና

በአሁኑ ጊዜ ከወደ ጃፓን የመጣ አዲስ ልምድ አለ ጃፓኖች በሚመገቡበት ጊዜ ትኩስ ሻይ ይጠጣሉ ይህም ምንም የጎንዮሽ ጉዳት የሌለው ህክምና ሲሆን ይህ ህክምና ከጠዋት ጀምሮ ቀኑን ሙሉ በተወሰነ የጊዜ ልዩነት ውሃ መጠጣትን ያካትታል፡፡ ይህም ህክምና በሚጀምሩበት ሰሞን በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት የሚያጋጥም ሲሆን በጃፓን የህክምና ማህበር ከብዙ በሽታዎች የመፈወስ አቅሙ 100% መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

ከነዚህም በሽታዎች መካከል የራስ ህመም፣ አጠቃላይ የሰውነት ህመም፣ የልብ ህመም፣ አርትራይተስ፣ ለፈጣን የልብ ምት፣ ለሚጥል በሽታ፣ ለአስም፣ ቲቢ፣ መንጋጋ ቆልፍ፣ ለኩላሊትና ሽንት በሽታ፣ ማስመለስ፣ ጨጓራ፣ ተቅማጥ፣ ለሆድ ድርቀት፣ ለሁሉም የአይን በሽታ፣ ለካንሰርና የወር አበባ ችግር፣ ለጆሮ አፍንጫና ጉሮሮ ህመሞች ፈውስ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

✔ቀዝቃዛ ውሃ መጠጣት

ምግብ በምንመገብበት ጊዜ ቀዝቃዛ ውሃ መጠጣት የራሱ የሆነ የጐንዮሽ ጉዳቶች አሉት፡፡ በተመገቡት ምግብ ውስጥ የሚገኝው ዘይት እንዲወፍር ያደርገዋል፤ ይህ ማለት የምግብ ስልቀጣ ሥርዓትን ከማዘግየቱ በተጨማሪ ምግብን ከሚፈጨው አሲድ ጋር ግጭት ይፈጥራል፤ አንጀታችን ምግብን በፍጥነት ይመጣቸዋል፣ ወደ ስብ(ፋት) ይቀይራቸዋል ስለዚህ ከምግብ በኋላ ያልቀዘቀዘ ወይም ትንሽ ለብ ያለ ውሃ ወይም ሾርባ ይጠቀሙ፡፡

✔ህክምናው እንዴት ይተገበራል (የህክምናው ዘዴ)

1. ጠዋት ጥርስዎን ከመፋቅዎ በፊት 160 ሚ.ሊ. በሚይዝ ብርጭቆ አራት(4) ብርጭቆ ውሃ ይጠጡ፡፡
2. ጥርስዎን ይቦርሹ ወይም ያጽዱ ነገር ግን ለ 45 ደቂቃ ምንም ዓይነት ምግብ ወይም ውሃ እንዳይወስዱ፡፡
3. ከ 45 ደቂቃ በኋላ ምግብ መመገብ ወይም ውሃ መጠጣት ይችላሉ፡፡
4. ቁርስ፣ ምሳ ወይም እራት ከበሉ ከ 15 ደቂቃ በኋላ ለሁለት(2) ሠዓት ያክል ምንም ዓይነት ምግብ ወይም ውሃ አይውሰዱ፡፡
5. ዕድሜያቸው የገፋና የታመሙ ሰዎች ከትንሽ ውሃ በመጀመር 4 ብርጭቆ ውሃ ላይ እንዲደርሱ ይመከራል፡፡
6. ይህ ህክምና በህመም ላይ የሚገኙ ወይም የታመሙ ሰዎችን የመፈወስ አቅም አለው፡፡

✔ከዚህ በታች የተዘረዘሩት እንደየበሽታዎ ለምን ያህል ቀን ህክምናውን መውሰድ እንዳለብዎ ያሳያል፦

1. ለደም ግፊት ሰላሳ(30) ቀናት
2. ለጨጓራ ህመም አስር(10) ቀናት
3. ለስኳር ህመም ሰላሳ(30) ቀናት
4. ለሆድ ድርቀት አሥር(10) ቀናት
5. ለቲቢ ዘጠና(90) ቀናት ናቸው።

ውሃ ህይወት ነው!
ሌሎችም ያንብቡት፤ በተን በተን አድርጉት፡

ጤናዎን በቤትዎ ሆነው መጠበቅ እንደሚችሉ ያውቃሉ? አሴር የቤት ለቤት ህክምና አገልግሎት ድርጅት በአይነቱ ልዩ የሆነና የእርስዎን የጤና ፍላጎት የሚያሟላ የተሟላ የህክምና አገልግሎት ይዞ ወደ...
13/10/2021

ጤናዎን በቤትዎ ሆነው መጠበቅ እንደሚችሉ ያውቃሉ?

አሴር የቤት ለቤት ህክምና አገልግሎት ድርጅት በአይነቱ ልዩ የሆነና የእርስዎን የጤና ፍላጎት የሚያሟላ የተሟላ የህክምና አገልግሎት ይዞ ወደ ቤትዎት መጥቷል።

ድርጅታችን ልምድ ያላቸውንና ከፍተኛ የሙያ ሰነምግባር የተላበሱ የህክምና ዶክተሮች ፣
ነርሶች ፣ ፊዚዮቴራፒስቶች ፣ የስነ ምግብ አማካሪዎች እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አሰሪዎችን በማሰማራት
1. አጠቃላይ የጤና ምርመራ
2. የነርሲንግ አገልግሎት
3. የፊዚዮቴራፒ አገልግሎት
4. የላብራቶሪ አገልግሎት
5. እንዲሁም የኮቪድ-19 ምርመራና ህክምና የትም ሳይጉላሉ በቤትዎ ይሰጥዎታል።
6.የ ኦክሲጂን አቅርቦት በሲሊንደር እናቀርባለን።

በተጨማሪም የሚወዷቸው ቤተሰብዎን ጤና በቅድሚያ ለመንከባከብ የሚያስችልዎት መደበኛ የጤና ምርመራ ጥቅሎችን አዘጋጅተንልዎታል። ለተጨማሪ መረጃና አገልግሎታችንን ለማግኘት

0913421022/0965410000

ሐዋሳ ;ሰፈረ ሰላም ዮሐንስ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ላይ ያገኙናል ።

Address

Hawassa
Awassa

Telephone

+251913421022

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አሴር የቤት ለቤት ህክምናና እንክብካቤ -ሐዋሳ/Asher Home Based Health Care-Hawassa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share