Adare Health Center አዳሬ ጤና ጣቢያ

Adare Health Center አዳሬ ጤና ጣቢያ This is Adare Health Center's official page.

የአዳሬ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በዛሬው ዕለት ባዘጋጀው የሰራተኞች ፎረም ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የጤና ጣቢያውን የ 2016 በጀት ዓመት አፈፃፀምና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ገመገ...
22/08/2024

የአዳሬ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በዛሬው ዕለት ባዘጋጀው የሰራተኞች ፎረም ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የጤና ጣቢያውን የ 2016 በጀት ዓመት አፈፃፀምና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ገመገመ።
በመድረኩም የሀዋሳ ከተማ አስ/ጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ ማራዶና ዘለቀ ፣ የመምሪያው ማኔጅመንት አባላት እና ተወካዮች፣ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳዳሪ አቶ አምራች እና የክፍለ ከተማው አመራሮች፣ የዳካ እና የፍላደልፊያ ቀበሌ ስራስኪያጆች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ከቀረበው ሪፓርት መነሻ ሰፊ ውይይት ማድረግ ተችሏል።
በተጨማሪም በተቋሙ በ2016 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የስራ ክፍሎች እና ባለሙያዎች የማበረታቻ ሽልማትና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
ነሀሴ 16/2016
አዳሬ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ

29/09/2022

የማይግሬን ራስምታትን ለማስታገስ
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

1. የተረጋጋ እና ፀጥ ያለ ቦታ ይምረጡ

✔ በአካባቢዎ የሚገኝ መብራት ማጥፋት እና ከተቻለ እንቅልፍ መተኛት፣

✔ የሞቀ ወይንም የቀዘቀዘ ውኃን በላስቲክ በማድረግ በእራስዎ እና በአንገትዎ ላይ ማስቀመጥ፣ ይህ ማለት ደግሞ

• ቅዝቃዜው በማደንዘዝ ሕመም እንዳይሰማዎ ሲያደርግ ሙቀቱ ደግሞ የራስና የአንገት ጡንቻዎችን እንዲፈታቱ ያደርጋል

• ሕመም የሚሰማዎ ቦታ ላይ በቀላሉ ማሸት አንገትዎን እና ትከሻዎን ማሸት

✔ ገላዎን በሙቅ ውሀ መታጠብ

2. በቂ እረፍት ማድረግ

✔ መደበኛ የእንቅልፍ ሰዓት ይኑርዎ

✔ ሁሌም በተመሳሳይ ሰዓት የመተኛት ልምድ ያዳብሩ

✔ በቀን እንቅልፍ መተኛት ያስለመዱ ከሆነ ከ20-30 ደቂቃ ብቻ ቢሆን ይመከራል። ከዛ በላይ እንቅልፍ ከወሰዱ የለሊት እንቅልፍዎን ሊያዛባ ይችላል

✔ እንቅልፍዎ ያልመጣ ከሆነ እራስዎን አያስገድዱ መጽሐፍ በማንበብ ራስዎን ያድክሙ

3. አመጋገብዎን ያስተካክሉ

✔ መደበኛ የሆነ የምግብ ሰዓት ይኑርዎ

✔ ቁርስዎን መመገብ አይዘንጉ

✔ ማይግሬን ቀስቃሽ የሆኑ ምግቦችን ያስወግዱ (እንደ ቼኮሌት፣አይብ፣ቡና እና የአልኮል መጠጦች)

4. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የማይግሬን ራስ ምታትን ይቀሰቅሳል ነገር ግን ሐኪምዎን በማማከር ቀለል ያሉ እንቅስቃሴዎችን ያድርጉ

(ለምሳሌ እንደ ውሃ ዋና፤የእግር ጉዞ የመሳሰሉትን ማድረግ ይችላሉ)

5.ጭንቀትዎን ይቆጣጠሩ

ጭንቀት የማይግሬን ራስ ምታትን ይቀሰቅሳል፡፡ በዕለት ተዕለት የኑሮ ሁኔታዎች የሚያጋጥሙንን አስጨናቂ ነገሮች መከላከል ባይቻልም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በመፈፀም መቀነስ ይችላሉ።

✔ ቀለል ያለ የኑሮ ዘይቤ ይኑርዎ

✔ ጊዜዎን በአግባቡ ይጠቀሙ

✔ የዕረፍት ጊዜ ይኑርዎ

✔ ለነገሮች በጎ አመለካከት ይኑርዎ

✔ ራስዎን ዘና ያድርጉ

6. የራስ ምታትዎን በተመለከተ የግል ማኅደር ይኑርዎ

✔ በግል ማኅደር መመዝገብ ራስምታትዎን የሚያስነሳውን ሁኔታ ለማወቅ እና ምን እንደሚያስታግስልዎም ለማጤን ይረዳል፡፡

ጤና ይስጥልኝ

09/09/2022
09/08/2022

እርግዝናን የመከላከያ መንገዶችና እውነታቸው
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

ያልተፈለገ እርግዝናን ለመከላከልና ራስዎን ከአባላዘር በሽታዎች ለመጠበቅ ሲባል የተለያዩ መንገዶችን ይጠቀሙ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የእነዚህን መከላከያዎች እውነታዎች አውቆና ተረድቶ ጥቅም ላይ ማዋል እጅግ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብዬ ስለማስብ ይህን ጽሑፍ አዘጋጅቼላችኋለሁ፡፡

1) በወር አበባ ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ቢደረግ እርግዝና ይከሰት ይሆን?

የወር አበባን በምታይ ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የምታደርግ ሴት የማርገዝ ዕድሏ የቀነሰ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ግን አይከሰትምለማለት አይቻልም፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት የወር አበባ ከማለቁ በፊት እንቁላል ሊፈጠር ስለሚችልና ወይንም ደግሞ የወንድ ዘር በማኅፀን ውስጥ እስከ 3 ቀን ወይንም ከዚያ በላይ የሚቆይበት አጋጣሚ ስለሚኖር ነው፡፡

2) ጡት ማጥባት እርግዝናን ይከላከላል?

ጡት ማጥባት የእንቁላል መፈጠርን የሚከላከል ቢሆንም የሚቆይበት ጊዜ ግን ለጥቂት ወራት ብቻ ስለሆነ ሰውነት ወደቀድሞ ሁኔታው በሚመለስ ጊዜ የማርገዝ ዕድልም አብሮ ስለሚመለስ ጡት ማጥባት እርግዝናን የሚከላከልብት ጊዜ ውስን መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

3) የመጀመሪያ ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ ላልተፈለገ እርግዝና ያጋልጣል?

አዎን! ለመጀመሪያ ጊዜ የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ላልተፈለገ እርግዝና ላያጋላጥ ይችላል ብለው የሚያስቡ አንዳንዶች ያሉ ቢሆንም ይህ ከእውነት የራቀ ነው፡፡ በመጀመሪያ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት ሕመምና ደም መፍሰስ ሊያጋጥም የሚችል ቢሆንም እርግዝናን ከመከላከል ጋር ግን ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌለው መሆኑን ተገንዝቦ ተገቢውን ጥንቀቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

4) የወሊድ መቆጣጠሪያዎች ምን ያህል እርግዝናን ይከላከላሉ?

የወሊድ መቆጣጠሪያዎች በትክክለኛው መንገድ ከተተገበሩ ከ90% በላይ የሚሆን የመከላከያ አቅም ያላቸው ሲሆን ተአቅቦ ግን ጥርጥር የሌለው አማራጭ ነው፡፡ የወሊድ መቆጣጣሪያ ለመጠቀም በሚታሰብ ጊዜ የትኛውን ዓይነት እንደምንመርጥና አጠቃቀሙን በተመለከተ ሐኪምዎን ማማከር ተገቢ ነው፡፡

5) በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ ሁለት ኮንዶሞች ደርቦ መጠቀም በእርግጥ እርግዝናን የበለጠ ይከላከላል?

አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ሁለት ኮንዶምን ደርቦ በመጠቀም የበለጠ ጠቀሜታ እንዳለው ያስባሉ ይህ ግን እጅግ የተሳሳተ እና ከእውነት የራቀ ሲሆን ይባስ ብሎ በሚፈጠረው ፍጭት (Friction) ምክንያት የኮንዶም መቀደድ በማስከተል ላልተፈለገ እርግዝና ለአባላዘር በሽታ የመጋለጥን ዕድል በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል፡፡ ስለዚህ ሁለት ኮንዶሞችን ደርቦ መጠቅም አይመከርም፡፡

6) የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎችን መውሰድ ወዲያውኑ እርግዝናን ይከላከላል?

የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች አጠቃቀም እና የሚወሰዱበትን ጊዜ በሚገባ ማወቅ እርግዝናን ለመከላከል ጠቃሚ ነው፡፡ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎችን የወር አበባ በመጣ ከመጀመሪያው ቀን እስከ አምስተኛው ቀን ውስጥ መጀመር ወዲውኑ ከአልተፈለገ እርግዝና የሚከላከል ሲሆን፣ ከዚያ ጊዜ ውጭ ከመጀመሩ ግን ወዲያውኑ የመከላከል አቅም ስለማይኖረው ኮንዶምን መጠቀም አስፈላጊ ይሆናል፡፡

7) ሁሉም የወሊድ መቆጣጠሪያዎች ከአባለዘር በሽታዎች ይከላከሉ ይሆን?

ከወሊድ መቆጣጠሪያዎች ውስጥ ኮንዶምን መጠቀም ብቻ ከአባላዘር በሽታ ራስን መከላከል የሚቻልበት ዋነኛው መንገድ ነው፡፡

8) የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች የሰውነት ክብደት ይጨምራሉ?

አንዳንድ ሴቶች የሰውነት ክብደት መጨመርን እንዳስከተለባቸው የሚናገሩ ሲሆን ምክንያቱም የምግብ ፍላጎትን መጨመርን ማስከተሉና ፈሳሽ በሰውነታችን እንዲቀመጥ ማድረጉ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ስለዚህም የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች መጠነኛ የሚባል የሰውነት ክብደት መጨመርን ያስከትላሉ፡፡

9) የወሊድ መቆጣጠሪያን መጠቀም መሃንነትን ያስከትላል?

አያስከትልም! ሆርሞኖችን በውስጣቸው የያዙ የወሊድ መቆጣጠሪያዎች ለረጅም ጊዜ ከተወሰዱ መሃንነትን ያስከትላሉ ተብሎ የሚታሰብ ቢሆንም እነዚህን የወሊድ መቆጣጠሪያዎች መካንነትን እንደማያስከትሉ ሊያውቁት የሚገባ እውነታ ነው፡፡

10) ኮንዶምን በሌሎች ቁሳቁሶች መተካት ይቻላል?

በፍፁም አይቻልም! በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ ኮንዶምን በሌሎች እንደ ላስቲክ፣ ፈኛ፣እና የመሳሰሉ ቁሳቁሶች ተክቶ መጠቀም በፍፁም ተገቢ ያልሆነ ድርጊት እና ከአልተፈለገ እርግዝናም ሆነ ከአባላዘር በሽታም በጭራሽ እንደማይከላከል ሊያውቁት ይገባል፡፡

እባክዎን ለወዳጅዎ ያካፍሉ!

ጤና ይስጥልኝ

05/08/2022

የጨጓራ ህመምተኞች ሊመገቧቸው የሚችሉ የምግብ አይነቶች፡፡
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

* የጨጓራ ህመም ሊከሰትባቸው ከሚችሉባቸው መንገዶች መካከል

1. ባክቴርያ
2. ከፍተኛ አልኮል መጠጦችን መውሰድ
3. ለረዥም ግዜ የሚወሰዱ አንዳንድ መድሃኒቶች
4. የምንመገባቸው የምግብ አይነቶች

ወደ ጤና ማእከል በመሄድ ከምናገኛቸው የጨጓራ ህመም መድሀኒቶች በተጨማሪ የአመጋገብ ሁኔታችንን ማስተካከል ከህመሙ ፋታ እንድናገኝ ይረዳናል፡፡

* የጨጓራ ህመምተኞች ሊመገቧቸው የሚችሉ የምግብ አይነቶች በጥቂቱ:-

1. ፍራፍሬ ፡- ፍራፍሬዎች ለጤና ጠቃሚ የሆኑ ቫይታሚኖች ፣ ፋይበር እና አንቲ ኦክሲደንቶችን ስለሚይዙ በእለት ተእለት የምግብ ፕሮግራማችን ላይ ማካተት ጠቃሚ ነው፡፡
እንደ ፖም እና ሃብሃብ የመሳሰሉት ፍራፍሬዎች ለጨጓራ ህመምተኞች ተስማሚ የምግብ አይነቶች ሲሆኑ እንደ ብርቱካን ያሉት ደግሞ እንዲወሰዱ አይመከርም

2. አትክልት ፡- የተለያዩ የአትክልት አይነቶችን መመገብ ለጨጓራ ህመምተኞች ተስማሚ ሲሆን በምግብ አዘገጃጀት ላይ የሚጨመሩ እንደ ነጭ ሽንኩርት እና የተለያዩ ማጣፈጫ ቅመሞች ግን እንዲወሰዱ አይመከርም፡፡

3. ወተት እና የወተት ተዋጽኦ ፡- የጨጓራ ህመም ላለባቸው ሰዎች ወተት እና የወተት ተዋጽኦ ተስማሚ የሆኑ ሲሆን ጥቂት የሚባሉ ሰዎች ላይ ግን ህመሙን ሊያባብሱ ይችላሉ ፡፡ ስለዚህም የሚስማማቸው ሰዎች ብቻ እንዲወስዱ ይመከራል፡፡

4. ስጋ ዶሮ እና አሳ ፡ - እነዚህ ምግቦች የጨጓራ ህመምተኞች ሊመገቧቸው የሚችሉ ሲሆን የማጣፈጫ ቅመሞች እና ቅባት ሳይኖርባቸው መመገብ ይቻላል ፡፡

5. በቀን ውስጥ የሚመገቡትን የምግብ ዓይነቶች ወደ ዳቦ፣ አጃ፣ ሩዝ፣ ድንች፣ ገብስ፣ ፓስታ፣ ማኮሮኒ ማዞር ለጤና ተመራጭ ነው፡፡

6. ፈሳሽ በሚገባ መውሰድ የጨጓራ ህመምን በከፍተኛ ሁኔታ ያስታግሳል፡፡ ንጹህ ውሀ መጠጣም ለሰውነታችን እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡

እንደ ቡና ሻይ እና ለስላሳ እንዲሁም የአልኮል መጠጦች የጨጓራ ህመም ያለባቸው ሰዎች እንዲወስዷቸው አይመከርም፡፡

ጤና ይስጥልኝ!

03/08/2022

B is preventable & treatable!

✅ Mother-to child-transmission must be eliminated.

✅ Children should be vaccinated against within 24 hours of birth & complemented by at least 2 additional doses a month apart. 👶🏿

02/08/2022

ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የስኳር ሕመም ምልክቶች
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

1) ከተለመደው ጊዜ በተለይ ውሃ መጠማትና በተደጋጋሚ የውኃ ሽንት መምጣት፡፡

የስኳር ሕመም ለኩላሊት ችግር በማጋለጥ ቀዳሚ ደረጃን የሚይዝ ሲሁን በደምውስጥ የሚገኝ የስኳር መጠን መጨመር የኩላሊት ሥራ ያዛባል፡፡

2) የድካም ስሜት መሰማት

የስኳር ሕመም ከፍተኛ የድካም ስሜትን ያስከትላል፡፡ የሰውንት ክብደት መጨመር በራሱ ለስኳር ሕመም ከማጋለጥ ባለፈ የድካም ስሜት እንዲበረታ ያደርጋል፡፡

3) የዓይን ችግር

ማናኛውም ዓይነት የዓይን ችግር የስኳር ሕመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ጊዜ ሳይሰጡ ወደ ሕክምና ቦታ በመሄድ ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
የስኳር ሕመምተኞች ለግላውኮማ የመጋለጥ ዕድላቸው ስለሚጨምርና በካታራክት (በዓይን ሞራ) ሊጠቁ ስለሚችሉ የዓይን ሕመም ከተሰማ ወደ ሕክምና ቦታ መሄድ ይመከራል፡፡

4) የእግር መደንዘዝ

የስኳር ሕመም የነርቭ ጉዳትን ያስከትላል፡፡ ይህም ጉዳት በአብዛኛው የሚከሰተው በእጃችንና በእግራችን ላይ ባሉ ነርቮች ላይ ነው፡፡ በነርቭ ወይንም በደም ሥር ላይ የሚደርስ ጉዳት የእግር መደንዘዝ ቀጥሎም የሕመም ስሜትን ያስከትላል፡፡ ሕመሙ በጊዜ ብዛት እየባሰ የሚሄድ ሲሆን መጠጥ እና ሲጋር ማጨስ ሕመሙን ያባብሰዋል፡፡

5) የቆዳ ላይ ኢንፌክሽንና በቶሎ የማይድን ቁስለት

የስኳር ሕመም ቆዳችንን ጨምሮ ማንኛውንም የሰውነት ክፍላችንን ሊጎዳ ይችላል እንዲያውም የስኳር ሕመም ያለበት ሰው በቀላሉ በባክቴሪያ እና በፈንገስ የሚመጣ ለቆዳ ላይ ኢንፌክሽን ያጋልጣል እነዚህም ኢንፌክሽኖች ቁስለትን ያስከትላሉ በቶሎ ሊድኑም አይችሉም፡፡

ጤና ይስጥልኝ

አዳሬ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ባለሙያዎች ከክኒካል ሴሽን በኋላ
20/07/2022

አዳሬ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ባለሙያዎች ከክኒካል ሴሽን በኋላ

Address

Hawassa Industrial Park
Awassa

Telephone

+251916785785

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Adare Health Center አዳሬ ጤና ጣቢያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Adare Health Center አዳሬ ጤና ጣቢያ:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram