01/09/2025
👉GODOBBINO AMARA KALAQANTANO QUWA SA'INO MUNDEETE XIIWO
(PREECLAMPSIA)
✍️Tini xisso ama godobbu hunni ontu agani gedensaanni kalaqantannoha ikkanna, xissote reqecci assannori heeriro lawishaho, lakko godobburo onte agana wo'misekkinni Mundeete xiiwo quwa sa'ara dandiitanno.
✍️Wodanche, Ilate albaanni assi'nanni harunsonna kitibaatetete yannara ayee amano , reqecci assannori heero hoogo mundeete xiiwo bikkisiisira hasiissanno.
👉XISSOTE REQECCI ASSANNORI MAATI
✍️35 diri ale mine assira, woy umi qaaqqo godowa
✍️ Godombara albaanni heedhanno "giffiite"
✍️Albiidi ilara "gifiite" noosero, woy maatete giddo
✍️Du'mille quwa saino amuwira
✍️Lakko godowino amuwira
✍️Sukkaarete xisso noonsa amuwi
✍️Duucha galte soorriranno amuwi
✍️Mitto qaaqqo ille wole ilate mereero noohu lamala diro rooriro, w. k. l
👉QAAGGO, kuni qarri noo ama baalate qarru kalaqamanno yaa dikkkino.
👉XISSO LEELLISHANNOHE MALAATI
1. Kiniinetenni higgannokki umu xisso
2. kiniine adhiteenna higgannokki afalcho giira, roore qiniiteenni
3. ille tunsiisa, biso huxisa
4. foole tayisanna hawwunaatu gede asse huxisa
5. wayi shuma geesha aja
6. mundee du'nama, otoottote ragaanni
7. qaaqqu giddo lubbama
8. umu giddo mundee du'nama, woy biso paralyze ikma
9. biso fuuga, qaagge, mitte ama godobburo lekkase lamenti fuuggara dandiitano, gifiite kalaqantunsaro, albunna anga nafa gattukkinni fuuganno.
👉XISSO NOOHETA AFIRATTAHU
✍️xisso bandannihu, ogeeeyye yitanno garinni mundeete xiiwo bikkineeti, atewinni agarranniti fayyimate minira hara callate.
✍️Hedeweelcho fayyimate harunsora kitibaatete haroottawa, ikmara dandaannko
✍️Xisso batidhuro aliidi malaatta heedhanno, ollokke fayyimate ogeeyyera kuli
✍️Mundee du'nama, qaaqqu godo'la aguranna, ille tunsiisa heedhuro, ollokke fayyimate minira hari....hegersi tini gifiitete xisso lamalu agani albaanni dagguro, ate lubbono ikko qaaqqoho, dancha ikkannomkihura, ogeeyyete amaale macciishi.
✍️ xissote babbaxino deerri noose daafira, assinanni owaante hakkunni garinni babbaxitanno
👉XAGISI'NANNI GARA
✍️Ollonke xagisa amate woy qaaqqu keeraanchima agarate yanna uyinannikki loosooti.
✍️Faymate ogeye marfe qassanohe, qolteno qaaqqu humeetano ikko ateha badde xawissannohe.
✍️ Honse agana ikkihero (37 saaminte ) rakke ilshiishahera dandiitanno, kunino gamete marfe qasatenni woy dare ilshiishate
✍️GARGADHINANNI GARA
✍️Aleenni noo malaatta woy reqecci assannori heerirono mundeete xiiwo bikkisiisira
✍️ Qooxeessaho bikkaanchu dino yiniro, heeranno hospitaale woy fayyimate agarooshe hari
✍️Umi godowi yannara tini xisso heedhuro sasu aganinni hanaffe egemmata xagichi noohura fayyimate ogeeyye xa'mi
QAAGI, alba gifiite noohero tenne ilara kalaqamate kaayyo lowota ikkitinohura balaxxe qixaawo assiri, egeminanni xagicho adhi, mule mule buuxo assiri.
✍️Godowakira albaanni gifiite heedhuro, ogeeyye uyitanno kiniine garunni egemmi.
"Mitte amano godowinni heedhe lubbama dinose."
Dr. Adane C.(GP)
Amaaru afiinni konni woroonni noo borro
Nabbabbe, Galateemmo!
በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የደም ግፊት ምንድን ነው?
👉 እንደ ዶክተር ተፈራ ገለጻ፤ የደም ግፊት ከእርግዝና ጋር በያያዘ ከዋና ዋና የእናቶች እና የጨቅላ ሕጻናት ሞት ምክንያቶች መካከል አንዱ ነው።
ከደከም መፍሰስ በመቀጠል ለእናቶች ሞት ምክንያት መሆኑን ገልጸው፤ እንዲያውም በአንዳንድ ሆስፒታሎች ለእናቶች ሞት ቀዳሚው ምክንያት ሆኖ የሚገኝበት ጊዜ እንዳለ ለኢዜአ ገልጸዋል።
👉 በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ3 እስከ 5 በመቶ ያህሉ ለዚህ በሽታ ተጋላጭ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።
👉 በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የደም ግፊት እርጉዝ በሆነች ወይም በአራስ ሴት አካል ውስጥ ያሉ ክፍሎች ላይ እክል የሚፈጥር እና ከፍተኛ የደም ግፊት የሚያስከትል ህመም መሆኑንም ያስረዳሉ።
👉 ይህ በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የደም ግፊት ከእናት በተጨማሪ በጽንስ ላይ የተለያዩ ችግሮችን የሚያስከትል መሆኑን ይገልጻሉ።
በመሆኑም በጊዜ ታውቆ ሕክምና ካልተደረገ ከፍተኛ የጤና መቃወስ ከማስከተል ባለፈ የእናትንም ሆነ የጽንሱን ሕይወት እስከማሳጣት ሊያደርስ ይችላል ብለዋል።
ከእርግዝና ጋር የተያያዘ የደም ግፊት መቼ ይከሰታል?
👉 አብዛኛውን ጊዜ ከ20 ሳምንታት በኋላ እንደሚከሰት የሚናገሩት ዶክተር ተፈራ፤ አልፎ አልፎ ልጅ ከተወለደ በኋላም ሊከሰት እንደሚችልም አመላክተዋል።
መንስኤዎቹ ምንድን ናቸው?
👉 እስከ አሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥናቶች ቢደረጉም አንዳንድ ሴቶች ለምን በእርግዝና ወቅት የደም ግፊት እንደሚያጋጥማቸው በውል የታወቀ ነገር አለመነሩን ጠቅሰዋል።
ለበሽታው ተጋላጭነትን ከሚጨምሩ ምክንያቶች መካከል፦
• የመጀመሪያ እርግዝና ሲሆን፤
• ቀደም ሲል በእርግዝና ጊዜ የደም ግፊት የታየባቸው ወይም በቤተሰብ ውስጥ ተመሳሳይ ታሪክ ያላቸው፤
• ከዚህ በፊት የደም ግፊት፣ የኩላሊት ወይም ሁለቱም ህመሞች የነበረባቸው፤
• ዕድሜያቸው ከ20 በታች ወይም ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ እናቶች፤
• እርግዝናው መንታ ወይም ከዚያ በላይ ሲሆን፤
• እንደ ስኳር ዓይነት ተጓዳኝ ህመም ያለባቸው፤
• ከመጠን በላይ የሰውነት ክብደት (ውፍረት) ፤
አንዲት ነፍሰጡር ደም ግፊት ቢኖርባት በልጇ ላይ ምን ሊያስከትል ይችላል?
• የልጁ ክብደት ከእርግዝና ጊዜው ጋር ሲታይ የቀነሰ ወይም የቀጨጨ ይሆናል ይላሉ ዶክተር ተፈራ።
• ያለጊዜ መወለድና ተጓዳኝ ችግሮች እንዲሁም ጽንሱ በማህጸን ውስጥ እንዳለ ሊሞት ይችላል ሲሉ አብራርተዋል።
ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
👉 የበሽታው የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ምንም ዓይነት ምልክት እንደማይታይ ገልጸው፤ ነገር ግን በምርመራ ጊዜ የግፊት ከፍ ማለት (≥140/90) ሲኖር፤ ይህም ቢያንስ በአራት ሠዓት ልዩነትና በሰባት ቀን ውስጥ ተለክቶ እንዲሁም በሽንት ምርመራ ውስጥ ያለው ፕሮቲን መጠን መጨመር ያሳያል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ግፊቱ አደገኛ (ከፍተኛ) ደረጃ ላይ ሲደርስ ከታች የተጠቀሱትን ምልክቶች ያሳያል ብለዋል።
• ከባድ የራስ ምታት፤
• የዕይን ብዥ ማለት ወይም የዕይታ መጋረድ፤
• ትንፋሽ ማጠር ወይም ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ቶሎ ቶሎ መተንፈስ፤
• በቀኝ የጡት ሥር ከባድ ማቃጠል ወይም የህመም ስሜት፤
• ከፍተኛ የደም ግፊት (≥160/110) እንዲሁም የፊት እና የእጆች ወይም የተጋነነ የእግር እብጠት መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የደም ግፊትን ለመከላከል ምን ይደረግ?
• ዶክተር ተፈራ እንደሚሉት፤ ሁሉም ነፍሰጡር እናቶች የቅድመ ወሊድ ክትትል እንዲያደርጉ ማበረታታት ይገባል፤
• ደም ግፊት ያለባት እናት ለመጸነስ ስታስብ የጤና ባለሙያ ማማከር እና የቅድመ እርግዝና ምርመራ ማድረግ ይኖርባታል፤
• ክብደቷ ከተገቢው በላይ ከሆነ ከእርግዝና በፊት መቀነስ ይጠበቅባታል፤
• የስኳር ህመም ያለባት እናት ከማርገዟ በፊት የስኳር ቁጥጥሩ ጥሩ መሆን ይኖርበታል፤
• በእርግዝና ወቅት ለደም ግፊት የተጋለጡ እናቶችን ለመለየትና የመከሰት ዕድሉን ለመቀነስ የቅድመ ወሊድ ክትትል በመጀመሪያ ሦስት ወር መጀመር እንደሚያስፍልግም መክረዋል።
• ከዚህ በፊት በእርግዝና ወቅት ግፊት ከነበራት አስፕሪን በመጀመሪያዎቹ ከ3 እስከ 4 የእርግዝና ወራት መጀመር አለባት ብለዋል የሕክምና ባለሙያው።
የሐኪም ምክር…..
👉 በእርግዝና ወቅት ከፍተኛ የደም ግፊት ጥንቃቄ የተሞላበት ክትትል፣ ፈጣን ምርመራ እና የአደጋ ስጋትን ለመቅረፍ እና የእናትን እና የሕጻኑን ደኅንነት ለማረጋገጥ ውጤታማ ሕክምና ይጠይቃል።
👉 መደበኛ የቅድመ ወሊድ እንክብካቤ፣ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ምርጫዎች እና በጤና አጠባበቅ ባለሙያዎች ምክር የሚሰጡ የሕክምና ጣልቃ ገብነቶች ከዚህ ሁኔታ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮችን በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ።
👉 መንስኤዎቹን በመረዳት፣ ምልክቶችን በማወቅ፣ ችግሮችን በመፍታት እና ሊከሰቱ የሚችሉትን አደጋዎች በመገንዘብ፣ ነፍሰጡር እናቶች በዚህ ወሳኝ የሕይወት ምዕራፍ ውስጥ ጤንነታቸውን እና የልጃቸውን ጤንነት ለመጠበቅ ንቁ እርምጃዎችን መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።
SOURCE👉👉 ENA
Call now to connect with business.