AWDAT Multi Speciality Clinic

AWDAT Multi Speciality Clinic Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from AWDAT Multi Speciality Clinic, Medical and health, Bahir Dar.

05/10/2020

The virus is a major cause of liver cancer and can lead to people needing a liver transplant.

Today is World Elder Abuse Awareness Day.Violence against older people, who are already bearing the brunt of this pandem...
15/06/2020

Today is World Elder Abuse Awareness Day.

Violence against older people, who are already bearing the brunt of this pandemic, has risen sharply since the beginning of the COVID-19 pandemic and imposition of lockdown measures.

15/06/2020

ወሲባዊ እና ፆታን መሠረት ያደረገ ጥቃት ምንድን?መጠኑስ?

ወሲባዊ ጥቃት ምንድን ነው?
ማንኛውም አይነት ከፈቃድ ውጭ በማስገደድ በማስፈራራት እና በመደለል በግለሰብ ላይ አካላዊ አእምሮአዊ እንዲሁም ስነልቦናዊ ጉዳት የሚያሰከትል ወሲባዊ ድርጊት ወይም ሙከራ ማለት ነው፡፡

ወሲባዊ ጥቃት የት ይፈጸመል
በማንኛውም ቦታ
የህጻናት ጾታዊ /ወሲባዊ ጥቃት ደረጃዎች
1.ፆታን መሰረት ያደረገ ወሲብ ነክ የቃላት ትንኮሳ/ማሸማቀቅ
3. ወሲባዊ የሆነ የአካል ጉንተላ
4. የወሲብ ምስል ወይም አካልን ማየት /ማሳየት
5. አስገድዶ መድፈር

ወሲባዊ ጥቃት በማን ይፈጸማል

ከተጠቂ ጋር የትኛውም ዓይነት ዝምድና ባላቸው ግለሰቦች ሊፈፀም ይችላል፡፡ በብዛት ቅርብ በሆኑ የቤተሰብ አባላት ይፈጸማል።

አሃዛዊ የጾታዊ/ ወሲባዊ ጥቃት መረጃዎች

የአለም ጤና ድርጅት ከሦስት ሴቶች መካከል ቢያንስ አንዷ በህይወት ዘመኗ ቢያንስ አንድ ጊዜ ለወሲባዊ እና ፆታን መሰረት ላደረገ ጥቃት ተጋለጣለች ይላል፡፡
እኤአ በ 2018 በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚኖሩ ሴቶች ውስጥ 50% የጾታ/ ወሲባዊ ጥቃት ሰለባ ነበሩ ፡፡ በዚህ ጥናት 13% የሚደርሱት የሀገራችን ሴቶች የመደፈር አደጋ እንደደረሰባቸው ያሳያል። ይህም ኢትዮጵያ ወሲባዊ እና ጾታዊ ጥቃት እጅግ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ከደረሰባቸው ግንባር ቀደም ሀገራት ተርታ ትመደባለች ፡፡

08/06/2020
በ ኢትዮጵያ በ Covid 19 የሟቾች ቁጥር 11 ደርሷል..
31/05/2020

በ ኢትዮጵያ በ Covid 19 የሟቾች ቁጥር 11 ደርሷል..

የልጆች   አመጋገብበ ዶ/ር አላምረዉ አለባቸዉ(የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት)ህፃናት የተስተካከለ አካላዊና አዕምሮዊ  እድገት እንዲኖራቸዉ  ጤናማ  የአመጋገብ ዘዴ ጉልህ ድርሻ አለዉ፡፡ይህ ጤ...
23/05/2020

የልጆች አመጋገብ
በ ዶ/ር አላምረዉ አለባቸዉ(የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት)
ህፃናት የተስተካከለ አካላዊና አዕምሮዊ እድገት እንዲኖራቸዉ ጤናማ የአመጋገብ ዘዴ ጉልህ ድርሻ አለዉ፡፡ይህ ጤናማ የሆነ የአመጋገብ ዘዴ ልጆቹን ከተለያዩ በሽታዎች እንደ ተቅማጥ፣የሳምባ ምች፣የጀሮ ኢንፌክሽን እና ሌሎችንም ተላላፊ በሽታዎች በመከላከል ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅኦ አለዉ፡፡
ጤናማ የአመጋገብ ዘዴ የምንላቸዉን በዕድሜ ከፍሎ ማየቱ ጠቃሚ ነዉ፡፡
1) የመጀመሪያዎቹ 6 ወራት
በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ህፃናት ያለምንም ተጨማሪ ምግብ የእናት ጡት ብቻ በቀን ከ8-12 ጊዜ እንዲወስዱ ይመከራል፡፡ጨቅላ ህፃናት ወዲያዉ በተወለዱ በ 30 ደቂቃ ዉስጥ የእናት ጡት መጀመር አለባቸዉ፡፡በተለምዶ በተለይ በገጠራማዉ አካባቢ ጨቅላ ህፃናት ወዲያዉ እንተወለዱ ከእናት ጡት በፊት የሚሰጡ (prelactal feeding) እንደ አብሽ፣ቅቤ፣ሻይ፣ዉሃ በስካር የመሳሰሉትን መስጠት ለ ኢንፌክሽን ስለሚያጋልጣቸዉ ጎጂ ባህላዊ ልማድ ነዉ፡፡
2) ከ ስድስት እስከ አስራ ሁለት (6-12 ወር)
በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ህፃናት ከየእናት ጡት በተጨማሪ ተጨማሪ ምግብ መጀመር አለባቸዉ፡፡እድሜያቸዉ ከ 6-8 ወር ለሆኑ ህፃናት ተጨማሪ ምግቦችን በፈሳሽ መልክ(እንደ አጥሚት) በቀን ከ2-3 ጊዜ እንዲሁም ከ8-12 ወር ለሆናቸዉ በከፊል ጠጣር መልክ(እንደ ገንፎ) በቀን 4-5ጊዜ መመግብ ያስፈልጋል፡፡
3) ከ1-2 ዓመት
በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ጡት ማጥባት የሚቀጥል ሲሆን ነገር ግን የእናት ጡት ወተት መጠን እየቀነሰ የሚሄድበት ጊዜ ስለሆነ ለህፃናት የሚሰጠዉ ተጨማሪ ምግብ በዓይነትም በመጠንም በደንብ መጨመር አለበት፡፡ተጨማሪ ምግቦችን በጠጣር መልክ(እንደ እንጀራ፣ዳቦ፤እንቁላል፣ሥጋ፣ወዘተ የቤተሰብ ምግቦችን) መጀመር ይቻላል፡፡
4) ከ 2ዓመት በኋላ
በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ጡት ማጥባት ምንም ጥቅም ስለሌለዉ ህፃናት ከ እናት ጡት ወተት ዉጭ የሆነ አመጋገብ መቀጠል አስፈላጊ ነዉ፡፡
ተጨማሪ ምግብ የምንለው ለህጻናት ከእናት ጡት በተጨማሪ ከስድሰት ወር ጀምሮ የምንሰጣቸው ምግብ ማለት ነው፡፡ ተጨማሪ ምግብ የእናት ጡት አያካትትም ነገር ግን ከእናት ጡት ጋር ለልጁ ተጨማሪ የምግብ አማራጭ ነው፡፡
ተጨማሪ ምግብ ልጆች ስድስት ወር ሲሞላቸው ነው የሚጀመረው ምክንያቱም የእናት ጡት ልጆች ስድስት ወር ሲሞላቸው ሙሉ ለሙሉ ልጆች የሚያስፈልጋቸውን ንጥረ ምግቦችን ማሞላት ስለማይችል ተጨማሪ ምግብ ያስፈልጋቸዋል፡፡
እንዲሁም የህጻናቱ አንጀት ስድስት ወር ሲሞላቸው ምግብ ለመፍጨት ዝግጁ ይሆናል፡፡
ተጨማሪ ምግብን ልጆች ቀደም ብለው ወይም ቆየት ብለው ቢጀምሩ ምን ችግር አለው
ሀ)ከስድስት ወር ቀደመው ቢጀምሩ
 ልጆች ብዙ ወይም በቂ የእናት ጡት እንዳያገኙ ያደርጋቸዋል
 ልጆች ለተቅማጥ በሽታ እንዲጋለጡ ያደርጋቸዋል
ለ)ከስድስት ወር አልፈው ቢጀምሩ
 ልጆች የሚያስፈልጋጨውን ተጨማሪ ሀይልና ንጥረ ምግቦች እንዳያገኙ ያደርጋል፡፡
 ልጆች የመቀጨጭ ለተለያዩ የማእድን እጥረት ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡
ልጆችን እስከ ሁለት አመታቸው ድረስ ጡት መጥባታቸው ጠቀሜታው
 የእናት ጡት ለልጆች ዋነኛው የሀይልና የንጥረ ምግብ ምንጭ ሆኖ ያገለግላል እስከ ሁለት አመታቸው
 ከ ስድስት እስከ አስራ ሁለት (6-12 ወር)የእናት ጡት ግማሽ ያክሉን ለልጆች የሚያስፈልጉ ነገሮች ያቀርባል፡፡
 ከ አስራ ሁለት እስከ ሃያ አራት(12-24 ወር) የእናት ጡት 1/3 ያክሉን ለልጆች የሚያስፈልጉ ነገሮች ያቀርባል፡፡
 ልጆች እስከ ሁለት ዓመታቸው የእናት ጡት ሲጠጡ ከበሽታ እንዲሁም ከመቀጨጭ(malnutrition) የመጋለጥ እድላቸው ይቀንሳል፡፡
 ጡት ማጥባት በእናት በልጁ መሀከል ፍቅርንና መቀራረብን(mother-child bond) ያዳብራል ወይምያጠናክራል፡፡

የላም ወተት መቸ እንጀምራለን?
የአለም ጤና ዲርጅትና የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የተለየ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር የላም ወተት ከ አንድ አመት በፊት መሰጠት የለበትም፡፡ከ አንድ አመት በፊት የላም ወተት የሚወስዱ ህፃናት በተለይም መጠኑ ከ 20 ounce ወይም ግማሽ ሊትር በላይ ከሆነ የአንጀት መድማትና አይረን የተባለዉን ንጥረ ነገር ከ አንጀት ወደ ደም እንዳይመጠጥ በማድረግ በአይረን እጥረት ምክኒያት የሚከሰት የደም ማነስ(Iron deficiency anemia) ያመጣል፡፡
ለልጆች የተመጣጠነ ተጨማሪ ምግብ እንዴት እናዘጋጃለን
ምግብ አንድ፡ የልጆች ገንፎ አዘገጃጀት
ሀ) የሚያስፈልጉ ነገሮች
( በመጀመሪያ አጃ፣ገብስ፣ በቆሎ፣ ስንዴ፣ጤፍ፣ ዳጉሳ፣ ማሽላ፣ ሽንብራ፣ባቄላ፣ አቾሎኒ፣ ሱፍ፣ ምስር፣ አደንጎሬ፣ አኩሪ አተር እና አብሽ አንድ ላይ አስፈጭተን ዱቄት እናዘጋጃለን፡፡)
ቦሎቄ ፣ ቲማቲም፣ቅቤና አዮዲን ያለበት የደቀቀ ጨው
ለ) አዘገጃጀት
በመጀመሪያ ቦሎቄ ማታ ውሃ ውስጥ ነክሮ ወይም ዘፍዝፎ ማሳደር
ቀጥሎ ቦሎቄውን በውሃ መቀቀል እና ሲበስል ቅርፊቱን መላጥና መዳጥ
ከዛም ቲማቲም መቀቀልና መላጥ ከዛም በቀጣጭኑ መክተፍና ፈሳሽ እስከሚሆን መቀጥቀጥ
ውሃ አፍልተን ከዛም ከብዙ አይነት ተፈጭቶ የተዘጋጀውን ዱቄት መክተት(ከግማሽ ስኒ ከፍ ያለ መጠን ያድርጉ)
እያማሰልነው ከዛም የተፈጨውን ቲማቲም መክተት ከዛም ቅቤውን ከዛም የተዳጣውን ቦሎቄ ጨምሮ ማማሰል ከዛም ልክ ልናወርደው ስንል አዮዲን ያለበት የደቀቀ ጨው መጨመርና ማውረድ ከዛም በማንኪያ ልጆችን መመገብ፡፡
ምግብ ሁለት የድንች ገንፎ በካሮት በእንቁላል የበለጸገ
ሀ) የሚያስፈልጉ ነገሮች
አንድ ትልቅ ድንች
አንድ እንቁላል
ሁለት ትንንሽ ካሮት
አንድ የሻይ ማንኪያ ቅቤ
አዮዲን ያለበት የደቀቀ ጨው
ለ) አዘገጃጀት
ድንችና ካሮቱን በደንብ ማጠብ
ከዛም ድንችና ካሮቱን መላጥ እና መክተፍ ከዛም መቀቀል
ትንሽ ዘይት መጥበሻ ላይ ማድረግ ድንችና ካሮቱን መጨመር ከዛም መጥበሻው ላይ መዳጥ ስንድጠው ግን መጥበሻውን ከእሳት ላይ እያወረድን መሆን አለበት፡፡
ከዛም እንቁላሉን መጨመር ከዛም በደንብ ማማሰል
ከዛም አንድ የሻይ ማንኪያ ቅቤ መጨመርና አዮዲን ያለበት የደቀቀ ጨው ጨምረን ማውረድ፡፡

ለልጆቻችን የተመጣጠነ ምግብ በመስጠት ጤናማና ብሩህ አዕምሮ ያላቸዉን ህፃናት ለሀገር ማበርከት የሁሉም ወላጅ ግዴታ ነዉ!!!

18/05/2020

የአስም በሽታ

የአስም በሽታ ሳንባችንን የሚጎዳ የህመም አይነት ሲሆን በዓለማችን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የበሽታው ተጠቂዎች ይገኛሉ፡፡

የአስም ህመም በአብዛኛው ከልጅነት ጀምሮ በመከሰት ደረጃ በደረጃ እያደገ የሚሄድ የመተንፈሻ አካል ህመም ቢሆንም አልፎ አልፎም ቢሆን እድሜ ከገፋ በኋላም የሚጀምር የህመም አይነት ነው፡፡

ለአስም በሽታ መከሰት ምክንያት የሚሆኑ መንስኤዎች በትክክል ያልተወቁ ሲሆን እስካሁንም ድረስ በሽታው ሙሉ በሙሉ ሊፈውስ የሚችል መድሃኒት አልተገኘም፡፡

በአብዘኛው አንድ የቤተሰብ አባል የበሽታው ተጠቂ ከሆነ በዘር የመተላለፍ ባህሪም አለው፡፡
የአስም በሽታ የሚያጠቃው የሳንባችንን የአየር ቧንቧዎች ሲሆን እነዚህን ቧንቧዎች በማጥበብ እና በቂ አየር ወደ ሳንባችን እንዳይገባና እና እንዳየወጣ በማድረግ እስከ ሞት ሊያደርስ ይችላል፡፡

የአስም በሽታ ምልክቶች
1.ሳል ፡- በተለይም በምሽት ግዜ የሚበረታ
2.ትንፋሽ (አየር) ማጠር
3.የደረት መጨምደድ ወይም መውጋት
4.ደረት አካባቢ በምንተነፍስበት ወቅት የሚሰማ ሲር ሲርታ (Wheezing)
የአስም በሽታን ሊቀሰቅሱ ከሚችሉ ነገሮች ውስጥ አንዳንዶቹ ከዚህ በታች ተጠቅሰዋል ነገር ግን ከሰው ሰው ሊለያዩ እንደሚችሉ መገንዘብ ያስፈላጋል፡፡

1.ሲጋራ ማጤስ
ሲጋራ ማጤስ የጤና ጠንቅ መሆኑ ይታወቃል፡፡በተለይም ለአስም በሽታ ተጠቂዎች ማጨስም ሆነ ሲጋራ የሚጤስበት አካባቢ መሆን በሽታው እንዲቀሰቅስ እና እንዲያገረሽ ያደርጋል፡፡

2.የአየር ብክለት
ከተለያዩ ፋብሪካዎች እና ተሽከርካሪዎች ከሚለቀቁ በካይ ጭሶች እና የአካባቢን አየር ከሚበክሉ ሽታዎች ካላቸው ቆሻሻዎች ተጋላጭነትን ማስወገድ አሊያም መቀነስ ያስፈልጋል፡፡
ይህ ጉዳይ በግለሰብ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በከተማ እና በሃገር ደረጃ ሊሠራበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

3.በረሮዎች
ጥናቶች እንደሚመለክቱት ከሆነ በረሮዎች እና የሚያመነጩት ብናኝ ለአስም በሽታ መቀስቀስ ምክንያት ናቸው፡፡ በረሮዎች በአብዛኛው በቤታችን የሚገኙ እና ለጤና ጠንቅ ስለሚሆኑ ማስወገድ ተገቢ ነው፡፡

4.የቤት እንስሳት
የቤት እንስሳትን በመኖሪያ ከማኖር ይልቅ ከመኖሪያ ቤት ውጪ ቤት መስራት እና ንጽህናቸውን ጠብቆ ማኖር ያስፈልጋል፡፡
እነዚህ እንስሳት ብናኝ ስለሚኖራቸው ለአስም ህመም መቀስቀስ ምክንያት ይሆናሉ፡፡

5.ከዚህ በተጨማሪ እንደ ጉንፋን ፣ የተለያዩ የሳንባ ህመሞች (ኢንፌክሽኖች) ፣ ቅዝቃዜ ፣ የአየር ለውጥ እና የተለያዩ መኣዛ ያላቸው ሽቶዎች የአስም በሽታን ሊቀሰቅሱ እና እንዲያገረሽ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡

ሁሉም የአስም በሽታ ተጠቂዎች የህክምና መድሃኒት መውሰድ አይጠበቅባቸውም፡፡ የአስም በሽታን ከላይ የተዘረዘሩትን የበሽታው ቀስቃሽ የሆኑ ነገሮችን በማስወገድ እና የአካል ብቃት እንቀቅስቃሴ በማድረግ መቆጣጠር ይችላል፡፡
የአስም ህክምና መከታተል የጀመረና መድሃኒት የሚወስድ የበሽታው ተጠቂ ሃኪም በሚያዘው መንገድ መድሃኒቶቹን በአግባቡ እና በትክክል መውሰድ ይኖርበታል፡፡

ወላጆች አስም በሽታ ተጠቂ ከሆኑ ልጆች በሚወልዱበት ግዜ የህክምና ምርመራ እንዲዲርጉ እና በሃኪሞች የሚሰጡ ምክሮችን መከታተል ተገቢ ነው፡፡

መልካም የጤና ግዜ ይሁንልዎ

ስለ ምትከታተሉን ከልብ
አናመሰግናለን

በ ዶ /ር አላምረው አለባቸው
የህፃናት ስፔሻሊስት

11/05/2020
10/05/2020

የእናት ስጦታዋ

አዘጋጅ ፡ ዶ/ር አቤንኤዘር እሸቱ
ጠቅላላ ሀኪም

አርታኢ ፡ ዶ/ር ንጉሤ ጫኔ
የህፃናት እስፔሻሊስት ሐኪም

ከውልደት ጀምሮ እስከ እውቀት እና እርጅና ያለን አመጋገብ ከተለያየ በሽታ የመከላከል ጥቅም እንዳለው ብዙዎች ይስማማሉ። የስኳር፣ የግፊት፣ የልብ፣ የውፍረት እና የካንሰር በሽታዎችን አመጋገብን በማስተካከል መቀነስ ወይም ማስቀረት ይቻላል። ለዚህም ነው ብዙ የሰለጠኑ ሃገራት የበሽታዎችን ስርጭት እና ጉዳት እያጠኑ በየ 5 እሰከ 10 ዓመት ልዩነት የአመጋገብ መመሪያ ለዜጎቻቸው ያወጣሉ እንደ ሁኔታውም ማስተካከያ በየወቅቱ ያደርጋሉ ።
የእናት ጡት ወተት ከጥንት ጀምሮ ለህጻናት አቻ የሌለው ምቹ እና አስተማማኝ የመጀመሪያ የህጻናት ምግብ መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም ዘመናዊነት ሲጫነን እናቶች ለማጥባት በስራ መብዛት የጊዜ ማጣትም፣ የኑሮ ጭንቀት፣ እና የአቻ ተጽእኖ ሲደራረብባቸው ጡት የማጥባት ፍላጎትና ክህሎት እየቀነሰ መምጣቱን አንዳንድ ጥናቶች ያመለክታሉ። ጡት ማጥባት የራሱ የሆነ ክህሎት አለው።ጡት በምናጠባ ጊዜ የልጅ አስተቃቀፍ እና ጡት አጎራረስ ዘዴ ህጻኑ የተሻለ ጡት እንዲያገኝ እና በአግባቡ እንዲያድግ እናትም የተሻለ እርካታ እንዲኖራት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
ውጤታማ ጡት የማጥባት ዘዴ የራሱ የሆነ አቀማመጥ፣ አስተቃቀፍ እና ጡት አጎራረስ አለው። ይህ ክህሎት እናት የጡት ጫፍ ህመም እንዳይሰማት እና እንዳትነከስ ሲረዳ ህፃኑ ደግሞ የሚፈልገውን የወተት መጠን እንዲያገኝ ስለሚያግዝ አዲስ ለወለዱ እናቶች ማስተማር ከጤና ባለሙያ ይጠበቃል ።

፩ . የጥሩ አስተቃቀፍ ምልክቶች signs of good positioning
፩ . የህፃኑን ጭንቅላትና ሙሉ ዳሌ አንድ መስመር ላይ ማድረግ
፪ . የጡትን ጫፍ እና የህፃኑን አፍንጫ ማቃረን
፫ . ህፃኑን ወደ ጡት ማስጠጋት
፬ . የህፃኑን ሙሉ ሰውነት ደግፎ መያዝ

፪ . የጥሩ ጡት አጎራረስ ምልክቶች /signs of good attachment

፩ .የህፃኑን ከንፈር በጡት ጫፍ መንካት
፪ . ህፃኑ አፉን በደንብ እስኪከፍት መጠበቅ
፫ . የጡት ጫፍን ወደ ታችኛው ከንፈር አዘቅዝቆ ማጉረስ
፬ . ህጻኑ በደንብ ጡት መያዙን ማረጋገጫ ምልክቶች
-አፍ በደንብ መከፈት ፣ የስረኛው ከንፈር ወደ ውጭ መገልበጥ
-የአገጩ ጡትን መንካት፣ ጥቁሩ የጡት ክፍል አብዛኛው ከህፃኑ አፍ በላይ መሆኑ ናቸው።

፫ . የመጥባቱ ውጤታማነት ምልክቶች

፩. አጠባቡ ዝግ ያለ፣ተመሳሳይ እና ጥብቅ መሆንና አጭር እረፍት መውስዱ
(slow, regular and deep sometimes pausing)
፪. በየጊዜው በቂ የሆነ ክብደት እና እድገትን መጨመር
፫. ከጠቡ በኋላ በቂ እረፍት እና እንቅልፍ ይተኛሉ

፬ . ጡት የማጥባት ጥቅሞች
ጡት ማጥባት ለእናትም ለህጻንም ወደር የማይገኝለት ብዙ ጥቅም አለው።

ሀ. ለእናት ያለው ጠቀሜታ
፩ .ከሚገዙ የተዘጋጁ የወተት አይነቶች ይልቅ ርካሽ መሆኑ
፪ . ሁሌም መገኝቱ
፫ . ለእናት ልጅም በራስ መተማመን እና የአእምሮ እርካታ ማጎናፀፍ
፬ . ከወሊድ በኋላ ባሉት ጥቂት ቀናት እና ሳምንታት የእናትን የመድማት አደጋን ይቀንሳል።
፭ . በትክክል የምታጠባ እናት እስከተወሰነ ጊዜ እንደ ተፈጥሮ የወሊድ መቆጣጠሪያነት ያገለግላል
፮ . እናት ላይም ይሁን ህጻናቱ ላይ አላስፈላጊ ክብደትን ይቀንሳል
፯ . በእናትና ልጅ መካከል ልባዊ እና ስሜታዊ ትስስርን ይጨምራል
፰ . የእንግዴ ልጅ ቶሎ እንዲወጣ ያግዛል
፱ . የጡት እብጠትን እና ኢንፌክሽን ይከላከል
፲. የጡት ና የመሃፀን ካንሠርን ይቀንሳል

ለ. የእናት ጡት ወተት ለህፃናት ያሉት ጥቅሞች

፩ . ሙሉ በሙሉ አልሚነት አለው
፪ . በቀላሉ መፈጨትና መመጠጥ
፫ .ንፁህና በማንኛውም ጊዜ ለመስጠት ምቹና የተመጣጠነ ሙቅት አለው።
፬ . ፀረ ጀርም አለው
፭ . የተቅማጥ በሽታን፣ የጆሮ ኢንፌክሽን የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ፡የደም በባክቴሪያ መበከልን ይከላከላል
፮ . የስውነት አንዳንድ ነገሮችን አለመቀበል ይቀንሳል reduces incidence of allergies
፯ . የአገጭና የጥርስ እድገትን ያግዛል
፰ . የአእምሮ ብስለት እና እድገትን ያፋጥናል
፱ .ተጨማሪ ምግብ እስኪጀመር ድረስ ለህፃኑ የሚያስፈልገውን ያህል በቂ የውሃ ይዘት አለው።
፲. የስኳር ህመም የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል
፲፩. የአንጀት የደም ካንሰርን ይከላከላል
፲፪. የተሻለ የእውቀት አድማስ፣ የመግባባት ችሎታ እና የማስታወስ ችሎታ ያጎናፅፋል።
፲፫ . የህጻናት በምግብ እጥረት መጎዳት እና ሞትን ይቀንሳል

እውነታዎች

፩ አንድ ህፃን በተወልደ አንድ ሰዓት ሳይሞላው ጡት መጥባት አለበት።
፪ አንድ ህፃን ተወልዶ ሰድስት ወር እስኪሞላው የእናት ጡት ወተት ብቻውን መስጠት በቂ ነው።
፫ እንገር የሚባለው ቢጫ ወተት ህጻናቱ እንደተወለዱ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናቶች ውስጥ የሚገኝ ሲሆን
ብዙ ጥቅሞች አሉት ፦ በፕሮቲን የበለፀገ ነው፣ፀረ ባክቴሪያዎች አሉት
እና በሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራል። እንገር የመጀመሪያው የተፈጥሮ ክትባት እንደሆነም ይታመናል።

፬ ጡት በቀን ውስጥ ከ8-12 ጊዜ መጥባት አለባቸው። ቢያንስ በየሦስት ሰዓት ልዩነት መጥባት ይኖርባቸዋል።
በመጀመሪያ ጥቂት ቀናት ያለው የወተት መጠን አነስተኛ ቢሆንም ለህጻናት በቂ መሆኑ ይታወቃል። ጡት በደንብ መመንጨት የሚጀምር በተወለዱ ከ2-5 ቀናት ውስጥ ነው። ይህ የሚሆነው ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ጡት በበቂ ሁኔታ ከተጠባ ብቻ ነው።
ስለዚህ ሁለቱንም ጡት በየተራ እስከመጨረሻው እንዲጠቡ ያደርጉ። በየመሀሉ ደግሞ ማስገሳት እና ጡት እንደገና መሞከር ያስፈልጋል።

ጡት ማጥባት የሚከለክሉ ምክንያቶች

፩. እናት በጠና የታመመች እና ጡት አልቦ ለመስጠት ጤንነቷ የማይፈቅድ ከሆነ
፪. እናት የጡት ካንሰር ታማሚ ከሆነች
፫. እናት የኤች.አይ.ቪ ታማሚ ሆና ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ጡት አላጠባም ብላ ከወሰነች
፬. ቲቢ/የሳንባ ነቀርሳ በአክታ የተገኘባት እናመድሃኒት በጀመረች ሁለት ሳምንታት ውስጥ ጡት ማጥባት የለባትም።
፭. የካንሰር መድሃኒት ወይም የጨርራ ህክምና የምትወስድ እናት።
፮. እናት ታማ የምትወስደው መድሃኒት ጡት ማጥባት የሚከለክል ከሆነ

ይህ ጽሁፍ መታሰቢያነቱ ዘጠኝ ወር አርግዘው አራት ዓመት አጥብተው ለወግ ለማረግ ላበቁን እናቶቻችን ሁሉ ይሁን።

Address

Bahir Dar

Telephone

+251933333326

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AWDAT Multi Speciality Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram