Adinas General Hospital Bahir Dar

Adinas General Hospital Bahir Dar The Hospital found infront of AWUSCOD,BahirDar, Ethiopia.

ሰራተኞቻችን ከባህርዳር ደም ባንክ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ደም በመለገስ ላይ!አዲናስ የጤናዎ ዋስ!ለመረጃስ .ቁ 0972 25 25 25
22/09/2025

ሰራተኞቻችን ከባህርዳር ደም ባንክ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ደም በመለገስ ላይ!
አዲናስ
የጤናዎ ዋስ!
ለመረጃ
ስ .ቁ 0972 25 25 25

ነጻ የዐይን ሞራ ግርዶሽ ሕክምና ጥሪ!የፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል"ላይት ፎር ዘወርልድ" ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ነጻ የዐይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና ሕ...
19/09/2025

ነጻ የዐይን ሞራ ግርዶሽ ሕክምና ጥሪ!

የፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል"ላይት ፎር ዘወርልድ" ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ነጻ የዐይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና ሕክምና ይሰጣል።

በመሆኑም ሕክምናው ከጥቅምት 3 እስከ 7/2018 ዓ.ም ባሉት ቀናት የሚሰጥ ይኾናል።

👉 ከመስከረም 26 እስከ ጥቅምት 2/2018 ዓ.ም ድረስ ደግሞ በፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የልየታ ሥራ ይሰራል።

መረጃውን Share በማድረግ ወገኖቻችን የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እናግዝ

በማህረሰብ ጤና አጠባበቅ አንጋፋውን የመካነ ገነት መረዳጃ ዕድር በመደገፋችን ይህን የውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥቶናል! የህብረተሰቡን ጤና በመጠበቅ አሁንም እንተጋለን!አዲናስየጤናዎ ዋስ!ለመረጃ ...
19/09/2025

በማህረሰብ ጤና አጠባበቅ አንጋፋውን የመካነ ገነት መረዳጃ ዕድር በመደገፋችን ይህን የውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥቶናል! የህብረተሰቡን ጤና በመጠበቅ አሁንም እንተጋለን!
አዲናስ
የጤናዎ ዋስ!
ለመረጃ 0972 25 25 25 ይደውሉ

EEG እና EMG ምርመራ በአዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል ለነርቭ እና ተያያዥ ችግሮች እንዲሁም ከጡንቻ ህመም ጋር ለተያያዙ ልዩ ልዩ ችግሮች! EEG- Electroencephalogram ኤሌክትሮኢን...
11/09/2025

EEG እና EMG ምርመራ በአዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል

ለነርቭ እና ተያያዥ ችግሮች እንዲሁም ከጡንቻ ህመም ጋር ለተያያዙ ልዩ ልዩ ችግሮች!

EEG- Electroencephalogram
ኤሌክትሮኢንሴፋሎግራም (ኢኢጂ) በአእምሮዎ ውስጥ ያለውን የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ የሚለይ ምርመራ ነው።
ኤሌክትሮኢንሴፋሎግራፊ (ኢኢጂ) ለተለያዩ ህመሞችን ለመለየት ትልቅ ጠቀሜታ አለው:

1. Diagnosis of Epilepsy: ሚጥል በሽታ ምርመራ
2. Monitoring Brain Function: የአንጎል ተግባርን ለመከታተል
3. Sleep Disorders Diagnosis: ለእንቅልፍ መዛባት ምርመራ
4. Prognostic Indicator: የአንጎል ጉዳት፣ በስትሮክ እና በኒውሮድጄኔሬቲቭ በሽታዎች ጭምር።
(Including traumatic brain injury, stroke, and neurodegenerative diseases.)

5. Medication Management: መድሀኒት ለመከታተል ፡- EEG መድሃኒቶችን በአንጎል እንቅስቃሴ ላይ ያለውን ተጽእኖ ለመከታተል፣ የመድሀኒት መጠንን ለማስተካከል ወይም እንደ አስፈላጊነቱ መድሃኒቶችን ለመቀየር ይጠቅማል።

Electromyography (EMG):

EMG በጡንቻ እንቅስቃሴ የሚመነጨውን የኤሌክትሪክ ግፊት ይለካል.

EMG የሚከተሉትን ጨምሮ የተለያዩ በሽታዎችን ለመመርመር ያገለግላል።

1. Peripheral Nerve Disorders: የነርቭ በሽታዎችን፡ የነርቭ መጎዳትን ወይም መጨናነቅን መለየት ይችላል።

2. Muscle Disorders: የጡንቻ ህመሞችን ለመለየት ያስችላል።

3. Motor Neuron Disorders: የሞተር ነርቭ በሽታዎችን፡ እንደ አሚዮትሮፊክ ላተራል ስክለሮሲስ (ALS) ያሉ የሞተር ነርቭ በሽታዎችን ለመመርመር ይረዳል።


#ባህርዳር
አዲናስ
የጤናዎ ዋስ!
ለበለጠ መረጃ :- በ0972 25 25 25 ይደውሉልን

እንዃን ለ2018 ዓ.ም አደረሳችሁ ! አዲሱ ዓመት የሰላም ; የጤና ; የዕድገት ዘመን እንዲያደርግላቹህ አዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል መልካም ምኞቱን ይገልፃል።አዲናስየጤናዎ ዋስ!ሰ.ቁ 0972 2...
10/09/2025

እንዃን ለ2018 ዓ.ም አደረሳችሁ ! አዲሱ ዓመት የሰላም ; የጤና ; የዕድገት ዘመን እንዲያደርግላቹህ አዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል መልካም ምኞቱን ይገልፃል።
አዲናስ
የጤናዎ ዋስ!
ሰ.ቁ 0972 25 25 25

የሆስፒታላችን ህንፃ ሥራ ከዚህ ደርሷል! በቅርብ ወራት እንገባለን! አድራሻው  9ኛ ፖሊስ አስፓልቱን እንደተሻገሩ  ኤፍራታ መግቢያ!ባህርዳር አዲናስየጤናዎ ዋስ!ስ.ቁ 0972 25 25 25
29/08/2025

የሆስፒታላችን ህንፃ ሥራ ከዚህ ደርሷል! በቅርብ ወራት እንገባለን! አድራሻው 9ኛ ፖሊስ አስፓልቱን እንደተሻገሩ ኤፍራታ መግቢያ!
ባህርዳር
አዲናስ
የጤናዎ ዋስ!
ስ.ቁ 0972 25 25 25

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ተማሪዎችን አስመረቀ*********************************************ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም  (ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) የባሕር ዳር ዩኒ...
26/07/2025

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ተማሪዎችን አስመረቀ
*********************************************
ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም (ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና የእንስሳት ህክምና ትምህርት ቤት በህክምና ዘርፍ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 93 የህክምና ዶክተሮች፣ 2 ስፔሻሊቲ፣ 2 የጤና ሳይንስ፣ 31 የእንስሳት ህክምና ዶክተሮችን ጨምሮ 37 የማዕረግ እና 1 የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን በድምሩ 166 ተማሪዎችን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መልካሙ አብቴ በተገኙበት በጥበብ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በደመቀ ሁኔታ አስመርቋል፡፡

በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ ለተመራቂዎች የፈተና ወንዞችን አቋርጣችሁ፤ የፅናት መስዋትነትን ተራራ ወጥታችሁ፤ ቀጣዩን የህይወት ምዕራፍ ለመጀመር ወሳኝ ቀን ላይ ስለደረሳችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ አክለውም የሀኪም ልብ ወደማገገሚያ መንገድ የሚያመራ መብራት ነው ያሉ ሲሆን ዛሬ ካለንበት ሁለንተናዊ የቀውስና ግጭት አዙሪት ለመውጣት ወደ ማገገሚያ የሚያመራው የሀኪም ልብ ዛሬ በፅኑ የሀገራችን ሁኔታ ውስጥ ባለንበት መከራ ለሁሉም መድሃኒት ለመሆን እና መድሃኒትነታችሁ በህክምና ተቋማት የተቀነበበ እና በእንስሳት ህክምና ብቻ የታጠረ ባለመሆኑ ሁለንተናዊ ምላሸ ለመስጠት በፅኑ መሰረት ላይ መቆማችሁን እንደ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እናምናለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ህንፃ በእጅ ይሰራል ቤት ግን በብርቱ ልብና ሩህሩህ ልቦች ይገነባል ያሉት ፕሬዚዳንቱ እነዚህ ወጣት ዶክተሮች እና የእንስሳት ሐኪሞች ከፍ እንዲሉ የሚያስችል የፍቅርና የድጋፍ የርህራሔን ቤት ገንብታችኋል ዩኒቨርሲቲው መስዋዕትነታችሁን ሳያመሰግን አያልፍም ሲሉ የተመራቂ ወላጆችን አመስግነዋል፡፡

ውድ ተመራቂዎች የተለያዩ የሙያ ዘርፍ ወክላችሁ ብትመረቁም የጋራ ተልዕኳችሁ ግን ህዝብን ማገልገል እና አመራር መስጠት ስኬታማ መሆን ብቻ ሳይሆን ተፅዕኖ ፈጣሪ እና የህይወት ዘመን ተማሪ እንድትሆኑ እና በቅንነት እና በርህራሄ ሀገራችሁን እና ህዝባችሁን እንድታገለግሉ ሲሉ ዶ/ር መንገሻ ለተመራቂዎች መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መልካሙ አብቴ በበኩላቸው የዛሬ ተመራቂ የህክምና ዶክተሮች የዓመታት ጽናትን ውጤት፣ ብርታትን፣ ጠንክሮ መስራትን፣ ትምህርትን፤ የለውጥ መሳሪያነት እና የወደፊት የሀገራችን የጤናውን ዘርፍ መፃኢ እድል መወሰኛ ጭምር ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በሀገራችን አሁን ላይ ጤናን መሰረት ባደረገ መልኩ እየተሠራ ባለበት ወቅት መመረቃቸው መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር እና ለጤናው ዘርፍ አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑንም ተናግረዋል።
በክህሎት እና በአመለካከት ቀርጾ እዚህ ደረጃ ላደረሳችሁ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አምባሳደር ናችሁ ያሉት ዶ/ር መልካሙ አብቴ ተመራቂዎች በቆይታቸው የጨበጡትን ክህሎት እና የቀሰሙትን ዕውቀት ተጠቅመው ሀገራቸውን እና ሕዝባቸውን በቅንነት እና በፍጹም ታማኝነት እንድታገለግሉ ሲሉ ለተመራቂዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም ከህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እንዲሁም ከእንስሳት ህክምና ትምህርት ቤት ተመራቂ ዶክተሮች ውስጥ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ዶ/ር ቤተልሄም እውነቱ እና ዶ/ር ደረበው መኩሪያ የዋንጫ፣ የሜዳሊያ እና የሰርተፊኬት ሽልማታቸውን ከእለቱ የክብር እንግዳ ከዶ/ር መልካሙ አብቴ እና ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ከዶ/ር መንገሻ አየነ እጅ ተቀብለዋል፡፡

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ
18/06/2025

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ

17/06/2025

........ ለክቡራን ደንበኞቻችን

ዩሮጋይናኮሎጂ ና ሪኮንስትራክቲቭ ፐልቪክ ሰርጀሪ ህክምና አገልግሎት በሰብ ስፔሻሊስት ሐኪም እየሰጠን እንገኛለን።
ስለሆነም የሚከተሉት እና ተያያዥ የጤና ችግር ካለበዎት ልናገለግለወት ዝግጁ ነን

1. የማህጸን መንሸራተት(መውጣት)
2. ሽንት አለመቆጣጠር
3. ሰገራ እና አየር አለመቆጣጠር
4. በወሊድም ሆነ ከወሊድ ውጭ የመራቢያ ብልት እና ፊንጢጣ ጉዳት
5. የሴቶች የዳሌ ወለል ህመም
6. የማህፀን/ብልት መላላት ችግር

ለበለጠ መረጃ 0972 25 25 25
አዲናስ
የጤናዎ ዋስ!

10/06/2025
የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ (Mpox) መተላለፊያ እና መከላከያ መንገዱ‎****‎የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ (Mpox) “ክሌድ 1” እና “ክሌድ 1ቢ” በሚባሉ በሁለት ዋነኛ የቫይረስ ዝርያዎች አማካይ...
10/06/2025

የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ (Mpox) መተላለፊያ እና መከላከያ መንገዱ
‎****
‎የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ (Mpox) “ክሌድ 1” እና “ክሌድ 1ቢ” በሚባሉ በሁለት ዋነኛ የቫይረስ ዝርያዎች አማካይነት ሲሠራጭ ቆይቷል።
‎“ክሌድ 1” የሚባለው የቫይረሱ ዓይነት በማዕከላዊ አፍሪካ በስፋት የሚገኝ ሲሆን፣ “ክሌድ 1ቢ” የተባለው ደግሞ ከ“ክሌድ 1” ኋላ እየተስፋፋ ያለ እና በጣም አደገኛ መሆኑ ይነገራል።

‎በፈረንጆቹ 2022 ቀለል ያለው እና በምዕራብ አፍሪካ የሚገኘው “ክሌድ 2” የተባለው የበሽታው ዝርያ በዓለም ዙሪያ በወረርሽኝ መልክ ተከስቶ እንደነበር መረጃዎች ያመላክታሉ።
‎በወቅቱ በሽታው ቫይረሱ ተከስቶባቸው የማያውቁት የአውሮፓ እና የእስያ አገራትን ጨምሮ 100 በሚጠጉ አገራት ውስጥ ተከስቶ ነገር ግን ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን በመከተብ ወረርሽኙ በቁጥጥር ስር ውሏል።

‎የበሽታው ምልክቶች

‎በዝንጀሮ ፈንጣጣ በተያዘ ሰው ላይ መጀመሪያ የሚታዩት ምልክቶች ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ እብጠት፣ ጀርባ ህመም እና የጡንቻ ህመምን ያካትታል።

‎ትኩሳት ከተከሰተ በኋላ ከፊት ጀምሮ ቀሪውን የሰውነት ክፍልን የሚያዳርስ ሽፍታ የሚከሰት ሲሆን፣ በአብዛኛው በእጅ መዳፍ እና በእግር መረገጫ ላይ ይከሰታል።

‎በሰውነት ላይ የሚያጋጥመው ሽፍታ በጣም የሚያሳክክ እና የሚቆጠቁጥ ሲሆን፣ በተለያዩ የለውጥ ደረጃዎች ውስጥ አልፎ በመጨረሻም እብጠት በመፍጠር ኋላ ላይም ይከስማል። ቁስለቱም ጠባሳን ትቶ ሊያልፍ ይችላል።

‎በሽታው በአብዛኛው ከሁለት እስከ ሦስት ሳምንት ባለው ጊዜ ውስጥ በራሱ የሚጠፋ ይሆናል።

‎በበሽታው የተያዘው ሰው በጣም የተጎዳ ከሆነ፣ ቁስለቱ አጠቃላይ ሰውነቱን፣ በተለይ አፍ፣ ዐይን እና የመራቢያ አካላት ላይ ከባድ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል።

‎የበሽታው ከሰው ወደ ሰው የመተላለፊያ መንገድ
‎በሽታው ቤተ ሙከራ ውስጥ በሚደረግ ምርመራ የሚገኝ ቫይረስ ሲሆን፣ በሰውነት ንክኪ ይተላለፋል።

‎የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወሲባዊ ግንኙነትን፣ የቆዳ ንክኪን እና በቅርብ ርቀት ላይ ሆኖ ማውራትን ወይም መተንፈስን ጨምሮ በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር በሚኖር የቀረበ ግንኙነት ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል።
‎የበሽታው ቫይረስ ወደ ሰውነት በቆሰላ ቆዳ፣ በመተንፈሻ አካላት፣ በዐይን፣ በአፍንጫ ወይም በአፍ በኩል ሊገባ ይችላል።

‎በቫይረሱ የተበከሉ የመኝታ አልባሳት፣ በልብሶች እና በፎጣዎች አማካይነት በሚኖር ንክኪም በሽታው ሊተላለፍ ይችላል።
‎ቫይረሱ ካለባቸው ዝንጀሮ እና አይጦችን ከመሳሳሉ ጋር የሚኖር ንክኪም ሌላኛው የበሽታው መተላለፊያ መንገድ ነው።

‎ከሁለት ዓመት በፊት የዝንጀሮ ፈንጣጣ በዓለም ዙሪያ በበርካታ ሀገራት ውስጥ በተከሰተበት ጊዜ ቫይረሱ በዋናነት በወሲባዊ ግንኙነት በሚፈጠር ንክኪ አማካይነት ነበር የተሠራጨው።

‎ባለፈው ዓመትም በዲሞክራቲክ ኮንጎ ውስጥ የተከሰተው የበሽታው ወረርሽኝ የተስፋፋው በወሲባዊ ግንኙነት በሚፈጠር ንክኪ ሲሆን፣ ነገር ግን በሌሎችም አካባቢዎች ተመሳሳይ ቫይረስ ሊገኝ ችሏል።
‎መከላከያ እና ህክምናው

‎የዝንጀሮ ፈንጣጣን ለማከም የተዘጋጀ ህክምና የታመሙ ሰዎችን ለማዳን በጣም ጠቃሚ ቢሆንም፣ ነገር ግን ህክምናው ምን ያክል ውጤታማ እንደሆነ የሚያሳይ ውስን ጥናት እንዳለ ነው የሚገለጸው።
‎የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝን፣ በሽታውን በመከላከል መቆጣጠር የሚቻል ሲሆን፣ ይህንንም ለማድረግ ተመራጩ መንገድ የመከላከያ ክትባት መስጠት ነው።

‎በአሁኑ ጊዜ ሦስት በሽታውን መከላከያ የክትባት ዓይነቶች ቢኖሩም፣ ክትባቶቹ የሚሰጡት ለበሽታው ተጋላጭ ለሆኑ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የቀረበ ንክኪ ላላቸው ብቻ ነው።

‎ይሁንና ያሉት የክትባት ዓይነቶች አዲስ ከተከሰተው የበሽታው ዝርያ አንፃር ምን ያክል የመከላከል አቅም አላቸው የሚለውን ለማወቅ ተጨማሪ ሙከራዎች ማድረግ ስለሚያስፈልግ፣ የዓለም ጤና ድርጅት ሁሉም ሰው መከተብ አለበት ብሎ አይመክርም።

‎ባለፈው ዓመትም የአፍሪካ ህብረት ለኮቪድ ተመድቦ ከነበረ ገንዘብ ላይ 10.4 ሚሊየን ዶላር ለሲዲሲ በመስጠት የዝንጀሮ ፈንጣጣን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት መደገፉን የቢቢሲ ዘገባ አመላክቷል።
‎የአፍሪካ ሲዲሲ እንደሚለው ካለፈው ዓመት ጥር መጀመሪያ አንስቶ እስከ ሐምሌ መጨረሻ ድረስ ባሉት ሰባት ወራት ውስጥ ከ14 ሺህ 500 በላይ በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዙ ሰዎች የተመዘገቡ ሲሆን፣ ከ450 በላይ ሰዎች ደግሞ በበሽታው ህይወታቸው አልፏል።

‎የበሽታው ክስተት 96 በመቶው በዲሞክራቲክ ኮንጎ ውስጥ የተመዘገበ ሲሆን፣ ጎረቤት ወደሆኑት እና የዝንጀሮ ፈንጣጣ እምብዛም ወደ ማይታወቅባቸው ቡሩንዲ፣ ኬንያ፣ ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ ተስፋፍቶ እንደነበርም ይታወሳል።

Dr. Mesfin Semunigus-- Pediatrician
(የህፃናት ስፔሻሊስት ሐኪም)

አዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል

09 72 25 25 25

Address

New Bus Station
Bahir Dar

Telephone

+251972252525

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Adinas General Hospital Bahir Dar posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Adinas General Hospital Bahir Dar:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram