24/11/2024
💥 ቫይታሚን ዲ ምንድን ነው❓
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
👉ቫይታሚን ዲ ለጤናማ አጥንቶች እና ጡንቻዎች እድገት እንዲሁም ለተለያዩ ጥቅሞች የሚዉል ለአጠቃላይ ጤና አስፈላጊ የሆነ ንጥረ ነገር ሲሆን
🦴🦴 ቫይታሚን ዲ በደም ውስጥ ያለውን የካልሲየም መጠን ይቆጣጠራል ይህም ለአጥንታችን መዋቅር አስፈላጊ ነው።
⛅ ቫይታሚን ዲ ከየት ነው የምናገኘው❓
✅ዋናው የቫይታሚን ዲ (90%) በፀሐይ ብርሃን እርዳታ በቆዳ ውስጥ ይሠራል
የቫይታሚን ዲ እጥረት መንስኤው ምንድን ነው❓
☁️ ዝቅተኛ የቫይታሚን ዲ (የቫይታሚን ዲ እጥረት) በሰውነት ውስጥ የሚከሰተው በቂ የፀሐይ ብርሃን ባለመኖሩ ነው:: ይህም ብዙውን ጊዜ ደመናማ የአየር ሁኔታ እና ረዥም የክረምት ወራት ባላቸው አገሮች ላይ የተለመደ ነው ::
👰♂️ጠቆር ያለ የቆዳ ቀለም ያላቸው እንዲሁም አብዛኛው የሰውነት ክፍላቸውን በባህላዊ ልብሶች የሚሸፍኑ ለቫይታሚን ዲ እጥረት ይበልጥ የተጋለጡ ናቸው።
🤱የቫይታሚን ዲ እጥረት ካላቸው እናቶች የተወለዱ ሕፃናት በተወለዱበት ጊዜ የቫይታሚን ዲ መጠናቸው ዝቅተኛ ሊሆን ይችላል::
🤱የእናት ጡት ወተት ለህፃናት ምርጥ ምግብ ቢሆንም፣ ለህፃናት የሚያስፈልገውን በቂ የቫይታሚን ዲ መጠን በውስጡ የለም::
👨🦽የመንቀሳቀስ ችሎታቸው ውስን የሆኑ ለምሳሌ.
በዊልቸር የሚሄዱ ሰዎች የቫይታሚን ዲ እጥረት የተጋለጡ ናቸው::
➡️ በቂ ቫይታሚን ዲ ከሌለ ምን ይከሰታል?
🔶ብዙ ሰዎች ምንም ምልክት ላይኖራቸው ይችላል
🔶የድብርት ; አቅም ማነስ ; በተደጋጋሚ ለቀላል ኢንፌክሽን መጋለጥ
🔶 የፀጉር መነቃቀል ; የጀርባ እና የጡንቻ ህመም
🔶ከባድ የቫይታሚን ዲ እጥረት በልጆች ላይ ሪኬትስ (Rickets) እና በአዋቂዎች ኦስቲኦማላሲያ (Osteomalacia)በመባል የሚታወቀው ለስላሳ አጥንት ሊፈጥር ይችላል::
🔶ምልክቶቹ የአጥንት/ መገጣጠሚያ ህመም (ብዙውን ጊዜ በእግሮች ላይ), ደካማ ጡንቻዎች እና በልጆች ላይ የእግር አጥንት መዛነፍ ( Bowlegs) ናቸው::
🔶በጣም አልፎ አልፎ በከባድ የቫይታሚን ዲ እጥረት ካልሲየም በጣም ዝቅተኛ በሆነበት ጊዜ የጡንቻ መኮማተር ምልክቶች ሊከሰቱ ይችላሉ።
🔶የረጅም ጊዜ የቫይታሚን ዲ እጥረት, ለአጥንት መሳሳት (ኦስቲዮፖሮሲስ) የመፈጠር እድልን ይጨምራል
🔶ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ ጥናቶች ፣ የቫይታሚን ዲ እጥረት ከ ካንሰር፣ ሳንባ ነቀርሳ፣ የስኳር በሽታ እና የልብ ሕመም ካሉ የጤና ችግሮች ጋር እንደሚያያዝ ይገለፃሉ::
↪️ የቫይታሚን ዲ እጥረት እንዴት ይገለጻል?
🔹የማነስ ምልክቶች እና ለጉድለት የሚያጋልጡ ምክንያቶች ካሉ የቫይታሚን ዲ መጠንን ለማረጋገጥ የደም ምርመራ ይደረጋል።
👉ለቫይታሚን ዲ እጥረት ሕክምናው ምንድነው?
💊ሕክምናው በተለያየ መልኩ የሚዘጋጁ የቫይታሚን ዲ መድሃኒት መውሰድ ነው::
🐬በ ቫይታሚን ዲ የበለፀጉ ምግቦችን መብላት ሌላው አማራጭ ነው
⚕️በተጠቀሰው መጠን ከተወሰደ በቫይታሚን ዲ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ማግኘት በጣም የተለመደ ባይሆንም
🚫ከመጠን በላይ መውሰድ በሚከሰትበት ጊዜ ምልክቶቹ በደም ውስጥ ያለው የካልሲየም መጠን መጨመር ምልክቶች ናቸው እነዚህም ማቅለሽለሽ, ማስታወክ, ጥማት መጨመር, መጠኑ የበዛ ሽንት መሽናት እና ራስ ምታት ናቸው::
❗በዚህም ምክንያት በተለያየ መልኩ ተዘጋጅተው እና ከሀኪም ትእዛዝ ዉጪ የሚወሰዱ የቫይታሚን ዲ ምርቶች ለ Vitamin D Toxicity ስለሚያጋልጡ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል
ፋሚሊ መካከለኛ ክሊኒክ - ቡታጅራ
➡️➡️➡️አድራሻ :ቡታጅራ ከተማ አስተዳደር አጠገብ
📲 0979- 58 -81- 48
1. https://t.me/familiyclinicbutajira
2. facebook.com/Familyclinicbutajira
3. tiktok.com/.kamilaumer