Debreberhan Comprehensive Specialized Hospital

Debreberhan Comprehensive Specialized Hospital This is the official page for Debre Birhan comprhensive specialized Hospital.

Like it you will get reliable information about Hospital sevice and related issues .

09/05/2026
አስደሳች ዜና ለአካባቢው ነዋሪዎች!የደብረ ብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከአሜሪካው ኪውር ብላይንድነስ (Cure Blindness) ጋር በመተባበር ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 7/2018 ዓ....
09/05/2026

አስደሳች ዜና ለአካባቢው ነዋሪዎች!

የደብረ ብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከአሜሪካው ኪውር ብላይንድነስ (Cure Blindness) ጋር በመተባበር ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 7/2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ነፃ የዓይን ቀዶ ህክምና ዘመቻ አዘጋጅቷል።

የሚሰጡ የህክምና አገልግሎቶች፦

🌾የዓይን ሞራ ግርዶሽ መግፈፍ

🌾የዓይን ቆብ ቅንደላ (Trichiasis)

🌾እና ሌሎች ተያያዥ የዓይን ቀዶ ህክምናዎች።

በመሆኑም በሰሜን ሸዋ ዞን እና በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ስር በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች የቅድመ ልየታ (Screening) መርሃ ግብር ወጥቷል።

ይህ ችግር ያለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በወጣው ፕሮግራም መሰረት ተገኝተው የነፃ ህክምናው ተጠቃሚ እንዲሆኑ፣ መረጃውን ለሚመለከታቸው ወገኖች በማድረስ ሁላችሁም የበኩላችሁን እንድትወጡ ሆስፒታሉ ጥሪውን ያስተላልፋል።

29/11/2025

የደብረብረሃን ኮም/ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአይን ሞራ ችግር ላለባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች Cure Blind project ከሚባል ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የነፃ የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና በዘመቻ እየሠጠ ይገኛል።

👀👀ከሰኞ እስከ አርብ በድምሩ 1,804 የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና የተሰጠ ሲሆን የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና እስከ እሁድ (21/03/2018 ዓ.ም)ድረስ ይቀጥላል።

ህዳር 19/2018ዓ.ም
ደብረብረሃን

የደብረብረሃን ኮም/ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአይን ሞራ ችግር ላለባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች Cure Blind project ከሚባል  ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የነፃ የአይን ሞራ ግርዶሽ...
27/11/2025

የደብረብረሃን ኮም/ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአይን ሞራ ችግር ላለባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች Cure Blind project ከሚባል ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የነፃ የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና በዘመቻ እየሠጠ ይገኛል።

👀👀ከሰኞ እስከ ሐሙስ በድምሩ 1,417 የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና የተሰጠ ሲሆን የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና እስከ እሁድ (21/03/2018 ዓ.ም)ድረስ ይቀጥላል።

ህዳር 18/2018ዓ.ም
ደብረብረሃን

የደብረ ብርሃን ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከህዳር 15 ቀን 2018 ጀምሮ ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና ከኪዩር ብላይንድነስ ጋር በመተባበር እየሰጠ ይገኛል።👁👁👁 ሰኞ፡ 333👁👁...
26/11/2025

የደብረ ብርሃን ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከህዳር 15 ቀን 2018 ጀምሮ ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና ከኪዩር ብላይንድነስ ጋር በመተባበር እየሰጠ ይገኛል።

👁👁👁 ሰኞ፡ 333

👁👁👁 ማክሰኞ፡ 344

👁👁👁 እሮብ፡ 357

በድምሩ 1,034 ታካሚዎች በሦስት ቀናት ውስጥ ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና አግኝተዋል።

አብዛኛዎቹ ታካሚዎች በዕድሜ የገፉ ሰዎች ናቸው፡፡ ቃለ መጠይቅ ከተደረገላቸው ታካሚዎች መካከል አንድ ግለሰብ ላለፉት 4ዓመታት ምንም ነገር ማየት ባለመቻሉ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ለማድረግ ተቸግረው እንደነበር እና ለረጅም ጊዜ ከቤት እንደማይወጡ ተናግረዋል፡፡

የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና የተደረገላቸው ሁሉም ህሙማን ለደብረ ብርሃን ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ ለኪዩር ብላይንድነስ እና አገልግሎቱን በመስጠት ላይ ላሉት ባለሙያዎች በሙሉ አመስግነዋል።

Debre Birhan Comprehensive Specialized Hospital staff conducted a community service at 'Habesha Haregawi,' a cleaning ca...
17/04/2025

Debre Birhan Comprehensive Specialized Hospital staff conducted a community service at 'Habesha Haregawi,' a cleaning campaign led by the Environmental Health Department. Mrs. Wude and Haregewein facilitated the involvement of various teams, including cleaners, nurses, and administrative staff.

06/03/2025
ነፃ_ሕክምና 🌾🌾🌾የደብረ ብርሃን ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከcure blindness project(CBP) ከሚባል ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ከመጋቢት 22-27/017 ዓም ድ...
03/03/2025

ነፃ_ሕክምና

🌾🌾🌾የደብረ ብርሃን ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከcure blindness project(CBP) ከሚባል ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ከመጋቢት 22-27/017 ዓም ድረስ ለተከታታይ ስድስት ቀናት የሚቆይ የነጻ የአይን ሞራ ግርዶሽ እና የአይን ቆብ ቅንደላ ህክምና ስለሚያካሂድ የህክምናዉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከዉዲሁ መልእክታችንን እያስተላለፍን የልየታ ፕሮግራም ከዚህ በላይ በሰንጠረዥ የተያያዘ ሲሆን በፕሮግራሙ መሰረት እና በየአቅራቢያችሁ በሚገኘው ጤና ተቋም ልየታ እንዲደረግላችሁ እናሳስባለን፡፡

🌾🌾🌾የደ/ብርሃን አጠቃላይ ሆስፒታል
ሊንኩን በመክፈት በመጫን አዳድ መረጃዎች ማግኘት ትችላላችሁ

እድሜ ጠገቡ ደብረ ብርሃን ሆስፒታል እስከ መቼ ይሆን የአልጋ ችግሩ የሚቀጥለው???
18/06/2023

እድሜ ጠገቡ ደብረ ብርሃን ሆስፒታል እስከ መቼ ይሆን የአልጋ ችግሩ የሚቀጥለው???

Address

Debre Birhan

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debreberhan Comprehensive Specialized Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share