16/02/2023
በወር አበባ (ሀይድ) ወቅት የሚሰማ ህም
🧚♀️ በዚህ ወቅት ሰውነትዎ ፕሮስታግላንዲን የሚባሉ ኬሚካሎችን ያመነጫል።እነዚህ ኬሚካሎች በምጥ ጊዜ የሚኖረው አይነት የማህጸን ቁርጠት ያመጣሉ። ይህ በወር አበባ ጊዜ የሚከሰት ህመም የጤና ባለሞያዎች ዲስመኖርያ( dysmenorrhea) በማለት ይጠሩታል።
🧚♀️ አንዳንድ የማህጸን በሽታዎች በወር አበባ ወቅት የሚኖረውን ህመም ያባብሱታል። ይህ ችግር ከሚያባብሱት መካከል ኢንዶመትርዮሲስ ፣ የማህጸን ኢጢ እና የማህጸን ኢንፌክሽን ተጠቃሽ ናቸዉ።
የህመም_ስሜቱ_ምን_የመስላል?
🧚♀️ ህመም ያላቸው ሴቶች የታችኛው የሆድ አከባቢ ቁርጠት ይኖራቸዋል። ቁርጠቱ ቀላል ወይም ከባድ ሊሆን ይችላል። በተጨማሪም የጀርባ ወይም በጭን አከባቢ ህመም ሊኖር ይችላል። ህመሙ ፔሬድ እንደጀመረ ወይም ከመጀመሩ ከጥቂት ሰአታት በፊት ሊጀምር ይችላል።
🧚♀️ አንዳንድ ሴቶች በተጨማሪ የሚከተሉት የህመም ስሜቶች ይታዬባቸዋል
● ማጥወልወል (ማቅለሽለሽ)
● ወደታች
● በጣም ከባድ የድካም ሰሜት
● ራስ ምታት
● ሆድ የመንፋት ስሜት
?
🧚♀️ አዎ የሚከተሉት በማድረግ ጥሩ ስሜት እንዲሰማዎ ማድረግ ይችላሉ።
🧚♀️ የወር አበባ መምጣት ምልክቶች እንደጀመሩ ወዲያውኑ የህመም ማስታገሻ ክኒኖችን መዋጥ ይጀምሩ። ከዚያም 2 ወይም ለ 3 ቀናት መውሰድዎን ይቀጥሉ።
🧚♀️ በታችኛው የሆድዎ አከባቢ ላይ የሞቀ ፓድ (የሞቀ ውሃን በሃላንድ ወይም ሌላ መያዣ በሙላት) ለተወሰኑ ደቂቃወች መያዝ
🧚♀️ በመደበኛነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ
ሃኪም መቸ ነው ማማከረ_ያለብኝ
ከስር የተዘረዘሩት ምልክቶች ከታዩብዎ ሐኪምዎን ወይም ነርስዎን ያማክሩ
● ህመሙ እየባሰ ከመጣ
● ህመሙ የህመም ማስታገሻ መድኃኒት ካላስታገሰው
● ህመሙ ከፐሬድ ውጪ የሚቀጥል ከሆነ
ላደርጋቸው_የሚገባኝ_ምርመራዎች_አሉን?
🧚♀️ የርስዎ እድሜ ፣ ሌሎች ተጨማሪ ምልክቶች እና ግለሰባዊ ሁኔታዎች መሰረት በማድረግ ምንአይነት ምርመራ ማድረግ እንዳለብዎት ሐኪምዎ ይወስናሉ።
🧚♀️ አብዛኛዎቹ ሴቶች የአካል ምርመራ ብቻ ያስፈልጋቸዋል። አንዳንድ ጊዜ ግን ተጨማሪ ምርመራዎች ሊያስፈልጉ ይችላሉ። ለምሳሌ ፦
● የማህጸን አልትራሳውንድ
● የአባላዘር በሽታዎች ምርመራ እና
● ላፓሮስኮፒ
ከሚያስፈልጉ ምርመራዎች ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው።
የፐሬድ ህመም ህክምናው ምንድን ነው ?
🧚♀️ ህክምናው በመንስኤው ላይ የተመሰረተ ነው።
አምባሰል መካከለኛ ክሊኒክ
ደሴ ቧንቧ ውሃ
ወደ ተስፋ ድርጅት መገንጠያ
📱0905-22-74-44