Dilla Health Center Official Information

Dilla Health Center Official Information Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dilla Health Center Official Information, Medical and health, Dilla Town, Dila.

09/08/2025
የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ የኤች አይ ቪና ቫይራል ሄፓታይትስ መከ/መቆ/ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የ2017ዓ.ም የ9 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ።ሰኔ 1/2017ዓ.ምዲላ፤በአፈጻጸም ግምገማው የሆ...
08/06/2025

የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ የኤች አይ ቪና ቫይራል ሄፓታይትስ መከ/መቆ/ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የ2017ዓ.ም የ9 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ።

ሰኔ 1/2017ዓ.ም
ዲላ፤

በአፈጻጸም ግምገማው የሆስፒታል ስራ አስኪያጆች/ Medical directors፣ የፀረ-ኤች አይ ቪ ክሊኒክ ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎች፣ የዘርፍ የመረጃ ባለሙያዎች፣ Adherence supporter and Case managers, የወረዳና ከተማ አ/ር ጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎችና የዘርፍ አስተባባሪዎች እናም ሌሎች በተገኙበት Review እየተካሄደ ይገኛል።

 /2017.ዓ.ምሀገር አቀፍ የኤችአይቪ ቅድመ መከላከል ክትባት pilot implentation  CAB_LA review metting በብሾፍቱ እየተካኤደ ይገኛል።በክልሉ በተሻለ ፕሮግራሞችን በማ...
20/05/2025

/2017.ዓ.ም

ሀገር አቀፍ የኤችአይቪ ቅድመ መከላከል ክትባት pilot implentation CAB_LA review metting በብሾፍቱ እየተካኤደ ይገኛል።

በክልሉ በተሻለ ፕሮግራሞችን በማሳካት እድል የተሰጠዉ የዲላ ጤና ጣቢያ በፈደራል ደረጃ የአፈፃጸም ግምገማ ላይ ተሳታፊ መሆኑን ገልጸዋል።

በማህበረሰቡ ከፍተኛ የሆነ የኤችአይቪ ስርጭትን ለመግታት ጤና ጥበቃ በሙከራ ደረጃ ያስጀመረዉን ኤችአይቪ ቅድመ መከላከል ክትባት /pilot implentation CAB_LA injection/ ያለዉን ይሄን ተግባር በመዉሰድ በማሳካት ህደት ላይ መሆኑን ነዉ የተነገረዉ።

በገጠሙ ተግዳሮቶችና በቀጣይ ድጋፍ በምያሻቸዉ ጉዳዮች ላይ ከጤና ጥበቃ ሚንስቴር ጋር እየመከረ ይገኛል።

ተጨማሪ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎች እንዲደርስዎ ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገጻችንን ሌሎችንም Join/Add ያድርጉ።

ቴሌግራም፦https://t.me/Dillahealthcenter1
Facebook Dilla Health Center Information official
ስለአብሮነትዎ እናመሰግናለን!

ባለፉዘ ጠኝ ወራት በጤና ተቋሙ የኤችአይቪና ቫሪያል ኤፓታይተስ መከላከል ስራዎች አመርቂ ዉጤት ማምጣቱን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለጸ። #ዲላ ጤና ጣቢያ:- ግንቦት 10/2017.ዓ.ምየደቡብ እትዮጵ...
18/05/2025

ባለፉዘ ጠኝ ወራት በጤና ተቋሙ የኤችአይቪና ቫሪያል ኤፓታይተስ መከላከል ስራዎች አመርቂ ዉጤት ማምጣቱን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለጸ።

#ዲላ ጤና ጣቢያ:- ግንቦት 10/2017.ዓ.ም

የደቡብ እትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የ supervision ቡድን የዜርፌ ብዙ ኤችአይቪ ኤድስ ሥራን በዲላ አስተዳደር የዲላ ጤና ጣቢያ ላይ ጉብኝት ባደረገበት ወቅት ነዉ ይሄን ለማየት የቻለዉ።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት በጤና ጣቢያዉ ጥራቱን የጠበቀ የ ሥራን በሁሉ አቀፍ ክፍሎች ከፍተኛ መሻሻል ማሳየቱንና በክልሉም የተሻለ አገልግሎት ከምሰጡ ጤና ተቋማት መሆን መቻሉን በጉብኝታቸዉ አንስተዋል።

ችግር ፈች ድጋፋዊ ክትትል አድርገው አመርቂ ዉጤት በታየባቸዉ ቦታዎች በመጠናከር ሌሎች ቦታዎች ላይም ትኩረት እንደረግም አሳስበዋል።

በፈደራል ብሎም በክልል ደረጃ ለምጀመሩ ፓይለት ተግባራት በማሳካት ጥሩ ስም ያለዉ ጤና ተቋም በመሆኑ ልመሰገን ይገባል ያሉ ስሆን በቀጣይም ለለሎች አመርቂ ዉጤት እንድያመጡ ማስተማሪያም አንደመሆን ነዉ የተናገሩት።

በመጨረሻም የማጠቃለያ ግብረ መልስ በጋራ በመሆን ባለሙያዎች በተገኘበት ግብረ መልስ ተሰቶ መጠናቀቁን የገለጸልን የዲላ ጤና ጣቢያ ነዉ።

ተጨማሪ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎች እንዲደርስዎ ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገጻችንን ሌሎችንም Join/Add ያድርጉ።

ቴሌግራም፦https://t.me/Dillahealthcenter1
Facebook Dilla Health Center Information official
ስለአብሮነትዎ እናመሰግናለን!

በሀሮሬሣ ጤና ጣቢያ ቀጠናዎች የቅዳሜና እሁድ የክትባት አሁናዊ ገጽታ በምስል።
18/05/2025

በሀሮሬሣ ጤና ጣቢያ ቀጠናዎች የቅዳሜና እሁድ የክትባት አሁናዊ ገጽታ በምስል።

በዲላ ከተማ አስተዳደር የተቀናጀ የኩፍኝ መከላከያ ክትባት ዘመቻ  በመጀመሪያ ቀን በተለያዩ  የክትባት መስጭያ ግዜያዊ ቦታዎቸ ላይ እየተሰጠ ነዉ።የሀሮሬሣ ጤና ጣቢያ የምስል ዜና!
14/05/2025

በዲላ ከተማ አስተዳደር የተቀናጀ የኩፍኝ መከላከያ ክትባት ዘመቻ በመጀመሪያ ቀን በተለያዩ የክትባት መስጭያ ግዜያዊ ቦታዎቸ ላይ እየተሰጠ ነዉ።

የሀሮሬሣ ጤና ጣቢያ የምስል ዜና!

 #የካቲት-11/2017.ዓ.ም ****የዲላ አጠ/ሆስፒታል ከጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ የኤች አይ ቪና ቫይራል ሄፓታይትስ መከ/መቆ/ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር  በአጠቃላይ  በዞኑ የፀረ ኤች አይ...
18/02/2025

#የካቲት-11/2017.ዓ.ም
****

የዲላ አጠ/ሆስፒታል ከጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ የኤች አይ ቪና ቫይራል ሄፓታይትስ መከ/መቆ/ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር በአጠቃላይ በዞኑ የፀረ ኤች አይ ቪ ሕክምና አፈጻጸም ላይ በ Catchment area meeting_ከባለድርሻ አካላት ጋር በመገምገም ላይ ያለ ሲሆን በካችመንት ውይይቱ ሁሉም ተቋማት ሪፓርታቸውን እንዲያቀርቡ በማድረግ አንዱ ከሌላኛው የተሻለ ልምድ የሚወስድበትንና እንደምሆን አሳዉቆዉናል ።

ተጨማሪ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎች እንዲደርስዎ ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገጻችንን ሌሎችንም Join/Add ያድርጉ።
_______

ቴሌግራም፦https://t.me/Dillahealthcenter1
Gmail:- dillahealthcenter147@gmail.com
Facebook:- Dilla Health Center Information official

ስለአብሮነትዎ እናመሰግናለን!

በዲላ ከተማ አስተዳደር የምገኘዉ የዲላ ጤና ጣቢያ( በተለምደዉ የሀሮሬሣ ጤና ጣቢያ) ላይ የvariaload Coverge ከፍ ለማድረግ በተሰራዉ ፕሮጀክት ዉጤት ማስመዝገቡን የጤና ጣቢያ ኤአር...
05/02/2025

በዲላ ከተማ አስተዳደር የምገኘዉ የዲላ ጤና ጣቢያ( በተለምደዉ የሀሮሬሣ ጤና ጣቢያ) ላይ የvariaload Coverge ከፍ ለማድረግ በተሰራዉ ፕሮጀክት ዉጤት ማስመዝገቡን የጤና ጣቢያ ኤአርቲ ፎካልና ተክንክ ክፍል አስተባባሪ አቶ ሱራፌል ተፈራ ገለጹ።

.ዓ.ም

በክልል እና ዞን ደረጃ የኤች አይቪ ኤድስ ህክምና ጥራትን ለማሳደግ የመድኃኒቱን ቁርኝት መከታተል ማለትም ቫሪያልሎድ ማወቅና መከታተል ወሳኝ መሆኑን ገልጸዉ ጤና ጣቢያዉ ዝቅተኛ አፈጻጸም ላይ እንደነበረና በተለያዩ መድረኩችም ስተች እንደነበረ ጤና ጣቢያ ኤአርቲ ፎካልና ተክንክ ክፍል አስተባባሪ አቶ ሱራፌል ተፈራ ገልጸዋል።

በዚህም ፕሮጀክት በመቅረስ ከስር መሠረቱ ችግሩን ለመፍታት የኳሊቲ ቲም በማቋቋም ወደስራ ማምራት አማራጭ መሆኑን የተረዱት አቶ ሱራፌል ተፈራ ላለፉት ስድስት ወራት ባደረጉት የፕሮጀክት ጥናትና ክትትል አመርቂ ዉጤት አምጥተዋል ነዉ ያሉት።

53% ላይ የነበረዉ አፈጻጸም በመያዝ በተደረገዉ የሶስት ወር ግምገማ ወደ 68% ከፍ ማድረግ መቻሉን አንስተዉ በቀጣን በነበረዉ ሶስት ወር አፈጻጸም ወደ 76% ከፍ ማድረግ መቻሉን አቶ ሱራፌል ተፈራ የገለጹት ይህ አፈጻጸም ለዞኑም ብሎም ለክልሉ ከፍተኛ ግበዓት መሆኑን አንስተዉ በተያዘዉ እቅድ መሠረት ፕሮጀክቱን 95% ማሳካት መቻሉን አቶ ሱራፌል ተፈራ አንስተዋል።

የነበሩ ተግዳሮቶች ይሄ ነዉ የማይባል ነዉ ያሉት አሰተባባሪዉ የግል አቅምንም በመጠቀም ዉጤት እንደመጣ ነዉ ያነሱት።

በቀጣይ ከዞንና ሌሎች ጤና ተቋማት ጋር በመሆን የተደረሰበትን ዉጤትና ተሞክሮ እንደምያጋራ ጤና ጣቢያ ኤአርቲ ክፍል ፎካልና ተክንክ ክፍል አስተባባሪ አቶ ሱራፌል ተፈራ ገልጸዋል።

በቅርቡ ለአጎራባች ጤና ተቋማት የልምድ ልዉወጥ መደረጉ ይታወቃል፤ በፈረንጆች ፋብራሪ 5 ድረስ ባለዉ አፈጻጸም ከ75% በላይ የቫሪያልሎድ አፈጻጸም መሆኑንም አንሰተዋል።



ተጨማሪ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎች እንዲደርስዎ ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገጻችንን ሌሎችንም Join/Add ያድርጉ።
___

ቴሌግራም፦https://t.me/Dillahealthcenter1
Gmail:- dillahealthcenter147@gmail.com
Facebook:- Dilla Health Center Information official

ስለአብሮነትዎ እናመሰግናለን!

QI project on Recieving HIV care service and Improvement of VL coverage  በጤና ጣበያ  ከተለያዩ ጤና ተቋማት ጋርና ሌሎች አካላት ጋር በመሆን ዉይይ...
01/01/2025

QI project on Recieving HIV care service and Improvement of VL coverage በጤና ጣበያ ከተለያዩ ጤና ተቋማት ጋርና ሌሎች አካላት ጋር በመሆን ዉይይት አካህዷል።

.ዓ.ም

የዲላ ጤና ጣቢያ አምስት ጤና ጣቢያዎችን በመያዝ በዘንድሮዉ ዓመት ለመስራት እቅድ ይዞ በጋራ ዉይይት አድርገዋል።

የተሰሩ መልካም ስራዎችን ሌሎች በማካፈል የጤናዉን ተደራሽነት ለማዝለቅና QI ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ መሻሻሎችን ማምጣት ያስፈልጋል ነዉ ያሉት አቶ ሱራፌል ተፈራ በጤና ተቋሙ በምሰጡ አገልግሎቶች ላይ ክትተልና ግምገባ ችግር ፈቺ ፕሮጀክቶችን በመስራት ለህዝብ ተጠቃምነትና አገልግሎት መሻሻል ይሰራል ብለዋል።

የዲላ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮናስ ዋቃየዉ በመክፈቻ ንግግራቸዉ በሁሉ አቀፍ የጤናዉን ስረዓት ለመገንባት በመረጃ የተደገፈ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ከትትል በማድረግ ለምድን በማካፈል ሌሎች የህዝብ መስጫ ጤና ተቋማትንም መገንባት አንደምያስፈልግ ገልጸዋል።

የVarialload coverage በክልል ደረጃ ዝቅተኛ መሆኑንና በዚህም ከፍ ለማድረግ በክልልና ዞን ከፍተኛ ደጋፍ የተደረገ ብሆንም ብዙም ፈቀቅ ያለ ዉጤት መምጣት አልቻለም ያሉት አቶ ሱራፌል ተፈራ የጥራት ቁጥጥርና እአርቲ ክፍል አስተባባሪ መሠረታዊ ችግሮችን በፕሮጀክት በቅረጽ የተሰራዉ ስራ ከፍተኛ ዉጤት እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል።

የ2016 ግማሽ ዓመት ከነበረበት 54% በተሰሩ ስራዎች አሁን ላይ 68% መድረስ መቻሉን እና በቀጣይ ቀሪ ከተያዘላቸዉ ግዜ ቀሪ አፈፃፀም ለማምጣት የተለያዩ ተገልጋዮችን ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን እና በዚህም ወደ 90% እና ከዛ በላይ ለማድረስ በየሳምንቱ ክትተል እያደረገ መሆኑን አክለዉ ገልጸዋል።

በዉይይት መድረኩ የጤና ጽ/ቤት የአራት አጎራባች ጤና ጣቢያዎችና (የኦዳያኣ፣ ጪጩ፣ አንዲዳ፣ ሲሶታ) የጤና ጣቢያዉ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።



ተጨማሪ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎች እንዲደርስዎ ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገጻችንን ሌሎችንም Join/Add ያድርጉ።
___

ቴሌግራም፦https://t.me/Dillahealthcenter1
Gmail:- dillahealthcenter147@gmail.com
Facebook:- Dilla Health Center Information official

ስለአብሮነትዎ እናመሰግናለን!

 /AIDS_News .ዓ.ምበኤችአይቪ/ኤድስ እና ቫይራል ሄፓታይተስ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ በክሊኒካል ሜንተርሽፕ ጋይድላይን ሪቫይታላይዜሽን (Clinical Mentorship Guideline...
22/12/2024

/AIDS_News
.ዓ.ም
በኤችአይቪ/ኤድስ እና ቫይራል ሄፓታይተስ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ በክሊኒካል ሜንተርሽፕ ጋይድላይን ሪቫይታላይዜሽን (Clinical Mentorship Guideline Revitalization) ላይ ከታህሣስ 11-12/4/ 2017 ዓ.ም ድረስ በወላይታ ሶዶ ሲካሄድ የነበረው ዎርክሾፕ መድረክ በስኬት ተጠናቀቀ
ክልላችን ከተመሠረተ ወዲህ በርካታ ተጨባጭ ለዉጦችን ማስመዝገብ ችለናል። በተለይ የኤችአይቪ ቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት እና በ2030 የተቀመጠዉን ዕቅድ ለማሳካት ከመቼዉም ጊዜ በላይ የተቀናጀ ሥራ ሲንሠራ እንደነበር መድረኩን የከፈቱት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ም/ኃላፊ እና የኤችአይቪ/ኤድስ እና ቫይራል ሄፓታይተስ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ማቴዎስ ጋርሾ በመልዕክታቸው አስቀምጠዋል።
ኤችአይቪ ቫይረስ ሥርጭት እንደ ሀገር እና ክልል እየቀነሰ ቢሆንም ይበልጥ ተጋላጭ በሆኑ የህብአተሰብ ክፍሎች በተለይ በወጣቶች እና ሴቶች አሁንም ከፍ ያለ አሀዝ እየተመዘገበ መሆኑን ገልጸዉ ይህንን ለመቀልበስ ተጋላጭነትን መሠረት ያደረገ የኤችአይቪ ምክርና ምርመራ፣ ህክምናና ክብካቤን ማጠናከር ተገቢ ነው ተብሏል።
ለዚህ ሥራ ቁልፍ ሚና መጫወት የሚችለዉ ክሊኒካል ሜንተርሽፕ ሥራን በስታንዳር መምራት ሲቻል ብቻ እንደሆነ ኃላፊው ገልጸዋል።
ክልሉ ውስጥ ባሉ 9 ሜንተር ፋስሊቲዎች እና 60 ገደማ ሜንቲ ፋስሊቲዎች ሜንተርሽፕ ጋይድ ላይንን መሠረት ያደረጉ እና በስታንዳርዱ መሠረት ብቻ ማከናወን ከቻሉ ከኤችአይቪ መከላከል፣ ክብካቤ እና ህክምና ጥራት ጋር የተያያዙ ችግሮችን በተሟላ መንገድ መፍታት እንጀሚቻል ያስቀመጡ ሲሆን በያዝነው በጀት ዓመት ይህንን ፕሮግራም ለማሳካት የሚመደቡ ዉስን ሀብቶች በዕቅድ መምራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
ኃላፊው መድረኩን ሲያጠቃልሉ የሚከተሉት ቁልፍ ጉዳዮችን ለተሳታፊዎቹ አንስተዋል፦
1. ክሊኒካል ሜንተርሽፕን ለማረጋገጥ የተቀመጡ ሦስቱ ምክረ-ሀሳቦች ያልተማከለ አስተዳደር፣ ቅንጅታዊ አሠራርና እና የሚመዘገቡ ዉጤቶች ቀጣይነት ማረጋገጥ ይገባል፣
2. ክሊኒካል ሜንተርሽፕ እና የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትልን ከዓላማና ዉጤት አንጻር ማየት ተገቢ ነው። ክሊካል ሜንተርሽፕ ከዓላማ አንጻር ሜንቲ ባለሙያዎች እና ፋስሊቲዎችን ማብቃት ስለሆነ ክህሎት ሽግግር ላይ አስምሮ መሥራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
3. Multidisciplinary Team (MDT) ተቋቁሞ እያንዳንዱን የኤችአይቪ ተግባር በተቀናጀ መንገድ እየገመገሙ መምራት ተገቢ መሆኑን አንስተው ቲሙ የሚመራበት TOR መዘጋጀት እንዳለበትም አሳስበዋል።
4. ሁሉም ተቋም Internal and external mentorship መሥራት ይኖርበታል። በሚያመጡት ዉጤት መሠረት እውቅና መርሃግብር ማዘጋጀት እንደሚገባ እና የሚፈለገዉን ዉጤት ያመጡ ከዓመት በኋላ መመረቅ እንደሚገባቸው ተመላክቷል።
5. የመረጃ ጥራት ችግሮች በአግባቡ እየተገመገሙ እና ችግሮች እየተፈቱ ለክልል ጤና ቢሮ ሪፖርት መደረግ እንዳለበት ተመላክቷል።
6. የክሊኒካል ሜንተርሽፕ ፕሮግራም ዝርዝር ዕቅድ በአጭር ጊዜ ተዘጋጅቶ ለክልል ጤና ቢሮ እንዲላክ እና ዕቅዱ ተገምግሞ ሲጸድቅ ተገበመዉ ሀብት እንደሚመደብ በመግለጽ መድረኩ ተደምድሟል።
መድረኩ ላይ የዞን ኤችአይቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ ዳይሬክተሮች፣ የሲዲሲ ፕሮጀክት አስተባባሪዎች፣ የዞንና የወረዳ ክሊኒካል ኦፊሰሮች፣ የአጠቃላይ እና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጆች፣ ሜዲካል ዳይሬክተሮች፣ የART ፎካሎች ፣ የላቦራቶሪ ክፍል ባለሙያዎችና ሌሎችም ተገኝተዋል።

የኤችአይቪ ስርጭት ለመከላከል ተግዳሮት እየሆነ ያለዉ ተሌግራም!  ድብቁ የወሲብ ገበያ: ቴሌግራም ያቀጣጠለው የወሲብ አብዮትቴሌግራም በሀገራችን ኢትዮጵያ ሰፊ ተጠቃሚዎች ካሉት መተግበሪያዎች ...
18/12/2024

የኤችአይቪ ስርጭት ለመከላከል ተግዳሮት እየሆነ ያለዉ ተሌግራም!



ድብቁ የወሲብ ገበያ: ቴሌግራም ያቀጣጠለው የወሲብ አብዮት

ቴሌግራም በሀገራችን ኢትዮጵያ ሰፊ ተጠቃሚዎች ካሉት መተግበሪያዎች አንዱ ነው። ቴሌግራም ጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎችን ከደንበኞች ጋር ለማገናኘት፣ ለትምህርትና ለመረጃ ልውውጥ አወንታዊ ሚናን ይጫወታል።

በአንጻሩ ደግሞ ላልተረጋገጡ መረጃዎችና የሤራ ትንተና፣ ማንነትን መሠረት ላደረጉ ጥቃቶች፣ ለህገወጥ ንግዶች፣ ለገንዘብ ማጭበርበርና ለመሳሰሉት ተጠቃሚዎችን ማጋለጡን የተለያዩ ሪፖርቶች ይጠቁማሉ።

ምንተስኖት ደስታ በሥነ-ሕብረተሰብ (ሶሲዮሎጂ) ከሐረማያ ዩንቨርስቲ የተመረቀ ሲሆን በአሁን ሰዓት በስንቅ ዩዝ ኢኒሼቲቭ ፕሮጀክት ማናጀር ሆኖ እየሰራ ይገኛል፡፡

በቴሌግራም ከሚታማባቸው ጉዳዮች አንዱ ስለሆነው ልቅ የወሲብ ገበያ ከኢትዮጵያ አንፃር የዳሰሰበትን ጹሑፍ በሐሳብ አለኝ ቅጽ 1 ዲጂታል መጽሔት ላይ አስነብቦናል።

ምንተስኖት በጹሑፉ በዚህ ላይ ከሚሳተፉ፤ ይኸው ተግባር ሱስ ከሆነባቸው ወጣቶችን ቃለመጠይቅ በማድረግና እና የተለያዩ ቻናሎችን በማጥናት ጥሩ ጹሑፍ አቅርቦልናል።

በዚህም፦

- ለዲጂታል ወሲብ አገልግሎቶች ከ500 - 3000 ብር እንደሚጠየቅ፤

- የህፃናት ወሲብ በሚያስደነግጥ ሁኔታ ተፈላጊ ስለመሆኑ፤

- ስለባህል ህክምናና ማስታወቂያዎቹ፤

- ከመንግስት እና ከቤተሰበሰ ስለሚጠበቀው ነገር በጹሑፉ አንስቷል።

👉ተጨማሪ ያንብቡ https://concepthub.net/article/4


ተጨማሪ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎች እንዲደርስዎ ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገጻችንን ሌሎችንም Join/Add ያድርጉ።
_______

ቴሌግራም፦https://t.me/Dillahealthcenter1
Gmail:- dillahealthcenter147@gmail.com
Facebook:- Dilla Health Center Information official

ስለአብሮነትዎ!

በዞኑ የቲቢ በሽታን ስርጭት ለመቀነስ እና መቆጣጠር የሚያስችል SWIF-TB የተሰኘ አዲስ ፕሮጀክት ይፋ ሆነሪች ኢትዮጵያ የተሰኘዉ  በዩኤስአይድ (USAID) እና ኢፊድሪ ጤና ሚኒስቴር ገንዘ...
14/12/2024

በዞኑ የቲቢ በሽታን ስርጭት ለመቀነስ እና መቆጣጠር የሚያስችል SWIF-TB የተሰኘ አዲስ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

ሪች ኢትዮጵያ የተሰኘዉ በዩኤስአይድ (USAID) እና ኢፊድሪ ጤና ሚኒስቴር ገንዘብ የሚደገፍ ፕሮግራም የቲቢ በሽታ ሰርጭት ለመቀነስ እና መቆጣጠር የሚያስችል SWIF-TB የተሰኘ አዲስ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሀግብር በዲላ ከተማ አካሂዷል።

እንደ ሀገር በቲቢ በሽታ ከፍተኛ ስርጭት በተለዩ አራት ክልሎች (ሲዳማ፤ ኦሮሚያ፤ ደቡብ አትዮጲያ፤ ማዕከላዊ ኢትዮጲያ) ውስጥ በሚገኙ ዞኖችና ወረዳዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የበሽታዉን ጫና እና ስርጭት ለመቀነስ ያተኮረ ፕሮጀክት መሆኑን ተገልጿል።

በመርሃግብሩ ላይ የተገኙት የክልሉ ጤና ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ መና መኩሪያ በUSAID በኩል የገንዘብና ቴክኒክ ድጋፍ መደረጉ የስርጭቱን ጫና ለመቀነስና በሽታውን ለመቆጣጠር ያግዛል ብለው የቲቢ ስርጭት ለመቀነስ የታቀደው አላማ ለማሳካት ከፍተኛ የባለሙያ ርብርብ እና የአመራር ክትትል እና ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ገልጿል።

በዞኑ ከፍተኛ የቲቢ በሽታ ስርጭት ምጣኔ እንዳለ መረጃ ያሳያል ያሉት የሪች ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ባለሙያ ዶ/ር ሂልና መከተ የስርጭት መጠኑን ለመግታት ከፍተኛ ቅንጅታዊ ስራ እንደሚጠብቅ ገልጿል።

የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አንዱአለም ማሞ ለፕሮጀክቱ ስኬት የዞኑ ጤና መምሪያ ከዞኑ አስተዳደር ጋር በመሆን በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አረጋግጠው ሁለም ማህበረሰቡና ባለድርሻ አካላት በንቃት በመሳተፍ የድርሻቸውን ልወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የSWIF-TB ፕሮጀክት የቲቢ ታማሚዎችን በመለየት፥ አክሞ ለማዳን እና ስርጭቱን ለመቆጣጠር እንዲሁም የተቋማትና የባለሙያውን አቅምን ለማጎልበት የጎላ እገዛ እንደሚኖረዉ ተገልጿል።

ፕሮጀክቱ በጤና ሚኒስቴር እና በUSAID በጋራ በሚመደብ በጀት የሚደገፍ ሲሆን ለቀጣይ አራት ዓመታት የሚቆይና ጌዴኦ ዞንን ጨምሮ በ11 ዞኖች በአጠቃላይ 87 ወረዳዎች ውስጥ ተግባራዊ የሚደረግ እና በቅንጀት በፌዴራል ጤና ሚኒስቴር፣ በክልልና በተዋረድ ባሉ ተቋማት እና REACH Ethiopia ከሚባል አጋር ድርጅት ጋር በመተባበር የሚተገበር መሆኑ ተመልክቷል።
@የጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን

ተጨማሪ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎች እንዲደርስዎ ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገጻችንን ሌሎችንም Join/Add ያድርጉ።

ቴሌግራም፦https://t.me/Dillahealthcenter1
Facebook Dilla Health Center Information official
ስለአብሮነትዎ!

Address

Dilla Town
Dila

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dilla Health Center Official Information posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram