
29/02/2024
#ያሳዝናል😭
#በአዲስ አበባ ከተማ በግንባታ ተረፈ ምርት መደርመስ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ
#በአያት ሪል እስቴት በሚያስገነባዉ የቤት ግንባታ ላይ የኮንስትራክሽን ተረፈ ምርት ተንዶ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን አስታውቋል
#በአዲስ አበባ በአንድ ወር ውስጥ ብቻ በኮንስትራክሽን ስራ ላይ የዛሬዉን ጨምሮ የስድስት ሰዎች ህይወት አልፏል።
#በአዲስ አበባ ዛሬ የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ሲኤምሲ ሚካኤል ከቀኑ 5:09 ሰዓት ላይ አያት ሪል እስቴት በሚያስገነባዉ የቤት ግንባታ ላይ
#የኮንስትራክሽን ተረፈምርት ተንዶ እድሜዉ ሀያ ዓመት የሆነ የድርጅቱ ሰራተኛ ወዲያዉ ህይወቱ ማለፉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል
#የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የወጣቱን አስከሬን ከፍርስራሽ ዉስጥ አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል
#በአዲስ አበባ በኮንስትራክሽን የስራ ላይ አደጋ በአንድ ወር ዉስጥ የዛሬዉን ጨምሮ የስድስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ስድስት ሰዎችላይ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን ብስራት መዘገቡ ይታወሳል
#ምንጭ ፦ ET ነው
#ፔጃችንን በማድረግ #ቤተሰብ እንሁን
#ዮናስ ደምሴ ( የአይንዬ ልጅ )