Karamara Medium Clinic

Karamara Medium Clinic Your good health is our ultimate mission

02/11/2023
1. ወባ ምንድን ነው?ወባ በጥገኛ ተሕዋስያን ምክንያት የሚመጣ በሽታ ነው። የበሽታው ምልክቶች ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ ማላብ፣ ራስ ምታት፣ የሰውነት መጓጎል፣ ማቅለሽለሽና ማስመለስ ናቸ...
24/10/2022

1. ወባ ምንድን ነው?
ወባ በጥገኛ ተሕዋስያን ምክንያት የሚመጣ በሽታ ነው። የበሽታው ምልክቶች ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ ማላብ፣ ራስ ምታት፣ የሰውነት መጓጎል፣ ማቅለሽለሽና ማስመለስ ናቸው። አንዳንድ ጊዜ ምልክቶቹ ከ48 እስከ 72 ሰዓት እየቆዩ በድጋሚ ይታያሉ፤ ይህን የሚወስነው ግለሰቡን ያጠቁት ተሕዋስያን ዓይነትና በበሽታው ተይዞ የቆየበት ጊዜ ነው።

2. ወባ የሚተላለፈው እንዴት ነው?
1.የወባ ተሕዋስያን፣ ፕላዝሞዲያ ተብለው የሚጠሩ ባለ አንድ ሴል ፍጥረታት ሲሆኑ ወደ ሰው ደም ውስጥ የሚገቡት አኖፊሊስ በምትባለው ሴት ትንኝ ንክሻ አማካኝነት ነው።
2.ተሕዋስያኑ የግለሰቡ ጉበት ሴሎች ውስጥ በመግባት ይራባሉ።
3.በጉበቱ ውስጥ ያሉት ሴሎች ሲፈነዱ ተሕዋስያኑ ይወጡና የግለሰቡን ቀይ የደም ሴሎች ይወርራሉ። ከዚያም ተሕዋስያኑ በቀይ የደም ሴሎቹ ውስጥ መባዛታቸውን ይቀጥላሉ።
4.ቀይ የደም ሴሎቹ በሚፈነዱበት ጊዜ ተሕዋስያኑ ይወጡና ሌሎች ቀይ የደም ሴሎችን ይወርራሉ።
5.በቀይ የደም ሴሎቹ ውስጥ የሚካሄደው ይህ ዑደት ይቀጥላል። ቀይ የደም ሴሎቹ በፈነዱ ቁጥር በበሽታው የተያዘው ሰው የወባ በሽታ ምልክቶቹ ይታዩበታል።

3. ራስህን መጠበቅ የምትችለው እንዴት ነው?
ወባ በተደጋጋሚ በሚከሰትበት አካባቢ የምትኖር ከሆነ . . .
• አጎበር ተጠቀም። አጎበሩ
o የተባይ ማጥፊያ የተረጨበት
o ምንም ቀዳዳ የሌለው
o በፍራሹ ዙሪያ የተጠቀጠቀ መሆን አለበት።
• ቤት ውስጥ የሚረጭ የተባይ ማጥፊያ ተጠቀም
• የሚቻል ከሆነ በበሮቹና በመስኮቶቹ ላይ እንደ ወንፊት ያለ መከለያ አድርግ፤ እንዲሁም ትንኞች እንዳያርፉ ሊከላከሉ ስለሚችሉ እንደ አየር ማቀዝቀዣ ያሉ መሣሪያዎችን ተጠቀም።
• ሰውነትህን ሙሉ በሙሉ የሚሸፍን ነጣ ያለ ቀለም ያለው ልብስ ልበስ።
• የሚቻል ከሆነ የወባ ትንኞች በብዛት ከሚገኙበት ጥሻ የሆነ አካባቢና ለትንኝ መራቢያነት አመቺ የሆኑ የታቆሩ ውኃዎች ካሉበት ቦታ ራቅ።
• በወባ ከተያዝክ በአፋጣኝ የሕክምና እርዳታ ለማግኘት ጥረት አድርግ።

www.jw.org/am/ላይብረሪ/መጽሔቶች/g201507/ስለ-ወባ-በሽታ-እውነታው/

Wishing every Muslim a happy Eid. EID MUBARAK 🎉
02/05/2022

Wishing every Muslim a happy Eid.

EID MUBARAK 🎉

Ramadan Mubarak 🌙 Wishing you and your family a blessed and Happy Ramadan !
01/04/2022

Ramadan Mubarak 🌙 Wishing you and your family a blessed and Happy Ramadan !

Your good health is our ultimate mission Address - Around Dire Dawa International stadium Phone - +251 25 111 1965 / +25...
29/03/2022

Your good health is our ultimate mission

Address - Around Dire Dawa International stadium
Phone - +251 25 111 1965 / +251 90 832 0174

Address

Greek Camp
Dire Dawa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Karamara Medium Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram