01/12/2025
በአስተዳደሩ የማልበርግ ቫይረስ በሽታን ለመከላከል የሚተላለፉ የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክቶችን ህብረተሰቡ ተግባራዊ እንዲያደርግ የድሬደዋ ሀይማኖት ተቋማት ገባኤ ጥሪ አቅርበዋል።
የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ የማልበርግ በሽታ ምንነትና የመከላከያ መንገዶች ዙሪያ ለድሬደዋ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሥራ አስፈፃሚ የቦርድ አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ እና በአስተዳደር ደረጃ የተሠሩ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች በዝርዝር ቀርበዋል።
በቅርቡ በሀገራችን የደቡብ ክልል የተከሰተው የማርበርግ ቫይረስ ዙሪያ የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ለድሬደዋ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሥራ አስፈፃሚ የቦርድ አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥቷል።
በመድረኩ የሀይማኖት አባቶችም መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በአስተዳደሩ የማልበርግ በሽታን ለመከላከል እየተሠሩ የሚገኙ የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክቶችን የአስተዳደሩ ነዋሪዎች ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤው የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ በቅድመ ጥንቃቄ የሚተላለፉ መልዕክቶችን ሁሉም በየቤተ እምነቱ መልዕክት በማስተላለፍ ምእመኑ ጤናውን እንዲጠብቅ የአባትነት ሚናቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።
በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፋት የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዩሱፍ ሰኢድ እንዳሉት በአስተዳደሩ የማልበርግ በሽታን ለመከላከል የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች በስፋት እየተሠሩ መሆናቸውን ጠቁመው ህብረተሰቡ ማንኛውም የህመም ስሜት ሲሰማው በአቅራቢያው ወደሚገኝ ጤና ተቋም መሄድ እንደሚገባ ገልፀዋል።
በአስተዳደሩ ጤና ቢሮ የሚተላለፉ የመከላከያ የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክቶችን የአስተዳደሩ ነዋሪዎች ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ አቶ ዩሱፍ አፅንኦት ሰጥተዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን
22/03/2018