KT ZHD_Health promotion and communication

KT ZHD_Health promotion and communication Halaba Zone_Health Department

16/06/2024
24/01/2023

ለተቋማዊ መርህ ቃል ማስተካከያ እንዲደረግ ማሳሰቢያ ተሰጠ።

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ስር ባሉ በሁሉም ጤና ሴክተር መዋቅሮች ላለፉት ጊዜያት በተለያዩ ጉዳዮችና በደብዳቤዎቻችን ስንጠቀምበት የነበረዉ "አንድም እናት በወሊድ ምክኒያት መሞት የለባትም" የምለዉ መፈክር "መከላከል በምንችላቸዉ ምክኒያቶች የሚከሰቱ የእናቶችን ሞት በጋራ እንግታ" or "Let's end preventable maternal death together" በምል የተቀየረ መሆኑን የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ዳንኤል አሳውቀዋል።

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ቃጫ ቢራ ወረዳ ምስራቅ ሌሾ ቀበሌ በዶ/ር ተሾመ አለምቦ ለሚቋቋመው ዶ/ር ተሾመ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታ ሥራ ማስጀመሪያ የመሠረት ድንጋይ ተጣለ።የመሠረት ድን...
21/01/2023

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ቃጫ ቢራ ወረዳ ምስራቅ ሌሾ ቀበሌ በዶ/ር ተሾመ አለምቦ ለሚቋቋመው ዶ/ር ተሾመ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታ ሥራ ማስጀመሪያ የመሠረት ድንጋይ ተጣለ።

የመሠረት ድንጋዩ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ክልል የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ባዩሽ ተስፋዬ እና በከምባታ ጠምባሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ መለሠ አጭሶ ተጥሏል።

Congratulations all!!!

Our zonal Medical tourisim, quality care and private public, partineship should be shifted one step Ihead. Share the experience and let's stand together for our community health!!!!

የወባ በሽታን ለመከላከል ሁል ጊዜ በመኝታ ዙሪያ የአልጋ አጎባር በአግባቡ መጠቀም ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ተገለፀ።በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ስር በዱራሜ ከተማ አስተዳደር በአጎበር ስ...
19/01/2023

የወባ በሽታን ለመከላከል ሁል ጊዜ በመኝታ ዙሪያ የአልጋ አጎባር በአግባቡ መጠቀም ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ተገለፀ።

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ስር በዱራሜ ከተማ አስተዳደር በአጎበር ስርጭትና አጠቃቀም ዙርያ የቅድመ የኦሬንቴሽን መድረክ ተካሄደ።

በመድረኩም በአጎበር አጠቃቀም፣ ስርጭት፣በወባ መከላከያ ዘዴዎች፣በወባ ትንኝ ባህርያት እንዲሁም አገራዊ የአጎባር ሥርጭት ስልቶች፣ የባለድርሻ አካላት ኃላፊነት እና ተግባር ዙርያ እንዲሁም በሌሎችም ርዕሶች ላይ የዞኑ የጤና መምሪያ የወባ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ተሰማ ታረቀኝ በኩል
ለተሳታፊዎች ቀርቦ ዉይይት ተደርጓል።

መድረኩን የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ያስጀመሩት የላሎ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተሰማ ተሾመ እንደገለፁት አጎባርን በአግባቡ በመጠቀም ከበሽታው መከላከል እንደሚገባ ጠቁመው ከዚህ ዉጪ አጎባር ከዓላማው ውጪ በሚጠቀሙ አካላት ተገቢውን እርምጃ በመዉሰድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል።

አክለውም የአጎባር ሥርጭቱ በዋናነት በሽታው የሚበዛባቸው አከባቢዎች ቅድምያ በመስጠት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ህብረተሰቡም አጎበርን በተገቢው መንገድ በመጠቀም ከበሽታው መከላከል እንደሚያስፈልግ በኦሬንቴሽን መድረኩ ላይ ተገልጿል።

በመድረኩም የከተማው አመራር አካላት፣የቀጠና አመራሮች፣የጤና ጽ/ቤት ማኔጅመንት አባላት ፣ሁሉም የከተማው ኤክስቴንሽን አባላት፣የዞኑ ጤና መምርያ የዘርፉ ባለድርሻ አካላትን ጨምሮ የሚመለከታቸው ባለድርሻዎች ተሳታፊ መሆናቸውን የዱራሜ አስተዳደር መንግስት ኮሚዪኒኬሽን ዘግቧል።

የጤና ሴክተር ትራንስፎርሜሽን ፅቅዶችን በውጤታማነት ለማሳካት የመልካም ተሞክሮ ልምድ ልዉዉጥ  ማካሄድ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ተገለፀ፡፡በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ በቀን 25/4/201...
04/01/2023

የጤና ሴክተር ትራንስፎርሜሽን ፅቅዶችን በውጤታማነት ለማሳካት የመልካም ተሞክሮ ልምድ ልዉዉጥ ማካሄድ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ተገለፀ፡፡

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ በቀን 25/4/2015 ዓ/ም የዞኑ ጤና መምሪያ ከተላያዩ የተመረጡ ጤና ጣቢዎች ከተዉጣጡ ኃላፊዎችና የሆስፒታል ኃላፊዎችና ከዉስን ወረዳና አብዛኞቹ ከተማ አስተደዳር ጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎች፤ እንድሁም የዞን ጤና መምሪያ የማኔጅመንት አባላት ተሳታፊ ተጋባዦች ባሉበት በዋሰራ ካቶልክ ጤና ጣቢያ የልምድ ልዉዉጥ ተደረገ።

ይህንን መድረክ የመሩት የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ዳንኤል የልምድ ልውውጥ አስፈላጊነቱንም ስገልጹ አብዛኞዎቹ የመንግስት ጤና ተቋማት መንግስት በርካታ የአሰራር ህደቶችንና ብቁ ባለሙያዎችን ቀጥሮ ስራዉን እንዲከናወን እያደረገ ቢሆንም ከነባርና ቁርጠኛ ሁነዉ በህሙማን አያያዝ ስርዓትና ድስፒሊን፣ የላቀ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት፣ የህክምና ማዕከላትን ንጹህ አድሮጎ በመያዝና ለተገልጋይ የመንፈስ እርካታና ከተላላፊ በሸታ ምንጭ እንዳይሆኑ በማድረግ ከፍተኛ ተምሳሌት ከሆኑት ጤና ጣቢያዎች አንዱ የሆነዉን የዋሰራ ካቶሊክ ጤና ጣቢያን መጎብኘትና ለሌሎች አስተማሪ የሆኑ ስራዎችን በጉብኝቱ ወቅት ለማየት እንደተቻለ ገልፀዋል፡፡

በተጎበኘዉ ዋሰራ ካቶልክ ጤና ጣቢያ የነፍሰጡር እናቶች የሚሰጠዉ የቅድመ ወሊድ ህክምና ክትትል፣ በእርግዝና ምክንያት የሚከሰቱ የጤና መቃወስን ልየታ ስርዓትና ከተለዩም በኋላ የክትትል አግባብ፣ በቅድመ ወሊድ ወቅት ለእናት ተገቢ ምርመራዎችን በበቂ ሁኔታ ማድረግ፣ ከጤና ጣቢያዉ አቅም በላይ ሲሆን ወደ ሆስፒታል የመላክ ሁኔታ፣ የህጻናት ክትባት አሰጣጥና የክትባት የቅዝቃዜ ሠንሰለት አያያዝ፣ የወላዶች ህክምና አሰጣጥና አያያዝ፣ የላቦራቶሪ ምርመራ ክፍል አሰራር፣ የመድሃኒት አቅርቦትና መድኃኒት ለታካሚዎች ከተዘዘላቸዉ በኋላ የሚጠበቀዉን ምክር አሟልተዉ ከማማከር አንጻር ያሉትን መልካም ተሞክሮዎችን ጎብኝዎቹ ልምድ ልዉዉጥ አድርገዉ እንደ መልካም ተሞክሮ ለማየት ችለዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጤና ጣቢያዉ ከግቢ ንጽህና አያያዝ፣ የህክምና ክፍሎ ንጽህና አያያዝ እና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን ከበሽታ አምጪ ህዋሳት ነጻ የማድረግን /sterilization / ሂደት፣ የታካሚዎች መረጃ አያያዝ ማለትም ከካርድ ክፍል አንስቶ ያለዉ ነገር እንከን የማይወጣለት እንደሆነ በጉብኝቱ ወቅት ለማየት ተችሎአል፡፡

ከጉብኝቱ በኋላም ከተሳታፊዎች በተሰጠዉ አስተያየቶች ጤና ጣቢያዉ በዞኑ ዉስጥና ዉጭ ላሉት ጤና ድርጅቶች እንደ ልምድ ልዉዉጥና የመልካም ተሞክሮ ማዕከል መሆን እንደሚችልና ከጤና ጣቢያዉ ባለሙያዎች ለስራ ባለቸዉ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት፣ በቡድን ስሜት የመስራት ሂደት፣ ለግቢዉ ጽዳት የተቀጠሩት ሰራተኞች ቢኖሩም የየክፍሉ ሰራተኛ ለያንዳንዱ ክፍል ንጽህና አያያዝ የሰጡትን ትኩረት እጅግ አድንቀዋል፡፡

በማጠቃለያዉም የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ዳንኤል ሁሉም የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ወደየመዋቅሮቻቸዉ ስመለሱ ይህንን መልካም ተሞክሮ በየጤና ጣቢያዎቻቸዉና በየሆስፒታሎቻቸዉ እንዲያሰፉና ባለሙያዎች በመልካም ስነምግባር የተሞሉ ሲሆኑ በርካታ ተግባራትን ማሳካት እንደሚቻልና ለሁሉም ተግባር ቁልፍ ጉዳይ ብሩህ አመለካከት ይዞ ወደ ተግባር መግባትና ተገልጋይ ተኮር የሆነ የባለሙያ ተነሳሽነት መኖር እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ኮሚዩኒኬሽን ፎካል ባለሙያ

ፊስቱላ ምንድን ነው?ፊስቱላ በብልትና በሽንት ፊኛ ወይም በሰገራ መውጫ (ዳንዳኔ) መካከል የሚፈጠር ቀዳዳ ሲሆን ተጠቂዎች ሽንት ወይም አይነምድርን አሊያም ሁለቱንም መቆጣጠር ይሳናቸዋል፡፡የተ...
12/10/2022

ፊስቱላ ምንድን ነው?

ፊስቱላ በብልትና በሽንት ፊኛ ወይም በሰገራ መውጫ (ዳንዳኔ) መካከል የሚፈጠር ቀዳዳ ሲሆን ተጠቂዎች ሽንት ወይም አይነምድርን አሊያም ሁለቱንም መቆጣጠር ይሳናቸዋል፡፡
የተራዘመና የተሰናከለ ምጥ ያጋጠማት እናት በሰለጠነ ባለሙያ ካልታገዘች ምጡ ከተለመደው ጊዜ በላይ ሊቆይ ይችላል፡፡ ምጡ በተራዘመ ወቅት የህፃኑ ጭንቅላት በማህፀን በር ለመውጣት በሚደረገው ግፊት ምክንያት የፊኛ ከረጢትና የሰገራ መውጫ (ዳንዳኔ) ላይ ከፍተኛ ጫና በመፍጠር የደም ዝውውር እንዲቋረጥና በአከባቢው የሚገኙትን ስስ ክፍሎች (ቲሹዎች) እንዲጎዱና እንዲበሱ ያደርጋል፤ የፊስቱላ ህመም/ችግር የሚባለውም ይህ ነው፡፡

ፊስቱላ የሚከሰትባቸውን ምክንያቶችና የሚያደርሰውን ጉዳት ያውቃሉ?

ፊስቱላ የሚከሰትባቸው ምክንያቶች፡
ዋና ምክንያት
በጤና ተቋማት በሰለጠነ ባለሙያ አለመውለድና በድንገተኛ ቀዶ ህክምና የማዋለድ አገልግሎት በበቂ ደረጃ ያለማግኘት ሲሆን፤
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትም ለፊስቱላ መከሰት አስተዋጽኦ ሊያደርጉ የሚችሉ ምክንያቶች ናቸው፡-
ያለእድሜ ጋብቻ
ወሲባዊ ጥቃት
የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለሴቶች ቁመት ማጠርና አነስተኛ ዳሌ እንዲፈጠር መንስኤ ይሆናል፡፡
በመሆኑም በልጅነታቸው በቂ ምግብ የማያገኙ ሴቶች ለፊስቱላ የመጋለት እድላቸው ከፍ ይላል፡፡
በተጫማሪም ድህነት፣ ትምህርት ያለማግኘት እና በቂ የጤና አገልግሎት በማይገኝባቸው የገጠር አከባቢዎች መኖር ለችግሩ ተጋላጭነት የሚዳርጉ ሁኔታዎች ናቸው፡፡

ፊስቱላ በሴቶች የሚያደርሰው ጉዳት ምንድን ነው?

በፊስቱላ ህመም የሚሰቃዩ ሴቶች በርካታ የሆኑ የጤና፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ያጋጥሟቸዋል፡፡
ሴቶች ሽንትና አይነ ምድር መቆጣጠር በላመቻላቸው በሚፈጠር መጥፎ ጠረን የተነሳ ከትዳር አጋሮቻቸው መለያየት
ከማህበረሰቡና ከቤተሰብ መገለል
ድብርት/ድባቴ ህመም
በሽንት ምክንያት የቆዳ ማሳከክ
የኩላሊት ቁስለት፣ መጎዳትና የሽንት ቱቦና ፊኛ ጠጠር
የማህፀን ጠባሳና በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ የህመም ስሜት
የወር አበባ መጥፋት
መካንነት
የአግር መስነፍ
የምግብ እጥረት፡- በፊስቱላ ጉዳት ምክንያት ተጠቂዎቹ ምግብና ፈሳሽ ለመውሰድ ያላቸው ፍላጎት ይቀንሳል፤ በዚህም ምክንያት የምግብ እጥረት ጉዳት ያጋጥማቸዋል፡፡

ይሁን እንጂ በተራዘመ ምጥ አማካይነት የሚፈጠረውን ፊስቱላ መከላከልና ከተከሰተም ችግሩን በህክምና ማዳን ይቻላል፡፡ ችግሩ ያጋጣማቸው ሴቶች በአፋጣኝ ህክምና መከታተል ከቻሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ቀድሞ ህይወታቸው ሊመለሱ ይችላሉ፡፡
ህክምናውም ለዚሁ በተዘጋጀ ልዩ የህክምና ማዕከል ውስጥ ይሰጣል፡፡

ፊስቱላ ያጋጠማት ሴት የህክምና አገልግሎት እንድታገኝ ማመቻቸት

በፊስቱላ ህመም የሚሰቃዩ ሴቶችን በመለየት ወደ ህክምና የማድረስና ተገቢውን ህክምና እንዲያገኙ የማድረግ ሥራ በተፋጠነ ሁኔታ መሰራት የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡

በተለይም ከጤና ኤክስቴንሽንና ከልማት ቡድኖች/አንድ ለአምስት ትስስሮች ጋር በቅንጅት ችግሩ ያለባቸውን ሴቶች በመለየት የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ማመቻቸት ይጠበቅባቸዋል፡፡

የመረጃው ምንጭ: ከታች በፎቶ የተጠቀሰው ማኑዋል ነው።

የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ኮሚዩኒኬሽን ክፍል

አስደሳች ዜና እንኳን ደስ አላችሁ ደስ አለን!!የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ዳንኤል በ2014 በጀት ዓመት ዞኑ በክልሉ ካሉ አቻ ዞኖች ላስመዘገበው የላቀ እቅድ አፈጻ...
17/09/2022

አስደሳች ዜና እንኳን ደስ አላችሁ ደስ አለን!!
የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ዳንኤል በ2014 በጀት ዓመት ዞኑ በክልሉ ካሉ አቻ ዞኖች ላስመዘገበው የላቀ እቅድ አፈጻጸም በቅድሚያ በዓመቱ በሁሉም ነገር መከናወንን የሰጠን ኢግዚአብሄርን እያመሰገንኩ የውጤቱ ባለቤት የሆናችሁ የጤና መምሪያ ማነጅሜንት አባላትና እስታፍ በሙሉ፣ የየወረዳና ከተማ አስተዳደር ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ የሆስፒታሎች ማነጅሜንት አባላትና ባለሙያዎች እና ጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች በሙሉ፣ ለህዝባችሁ ላደረጋችሁት እንቅስቃሴ እጅግ በጣም አመሰግናቾኃለሁ። ለዚህ የላቀ ስኬት ስላበቃችሁ ልዩ ክብርና ምስጋና ይገባችኃል። ቀጣይም ለበለጠ እንትጋ፣ ህዝባችንን የጤናው አገልግሎት ባለቤት እናድርግ በማለት የእንኳን ደስ አላችሁ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። ቀጣዩ ጊዜም ብሩህ 2015 አመት እንዲሆንላችሁ ተመኝተዋል።
አቶ ወንድሙ ዳንኤል የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ

ለ2015 እንቁጠጣሽ የዘመን መለዋወጫ በዓል እንኳን በጤናና በሰላም አደረሳችሁ ተባለ።የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ዳንኤል ለጤናው ሴክተር በህብረተሰቡ ጤና ላይ ተዕዕ...
10/09/2022

ለ2015 እንቁጠጣሽ የዘመን መለዋወጫ በዓል እንኳን በጤናና በሰላም አደረሳችሁ ተባለ።
የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ዳንኤል ለጤናው ሴክተር በህብረተሰቡ ጤና ላይ ተዕዕኖአቸውን የሚያሳርፉ የጤና
ችግሮችን በመከላከል፣ ጤናን የማበልጸግና የጤና ልማት ግቦችን ለማሳካት ጤናማ፣ ምርታማና የበለፀገ ህብረተሰብ ተፈጥሮ የማየትን ራዕይ እውን ለማድረግ መምሪያው ተጠናክሮ ይሰራል ብለዋል፡፡
ከዚህም አንፃር አንድ ሃገር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕቅዶችን ለማሳካት በመጀመሪያ ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ መፍጠር ወሳኝ መሆኑን ታላሚ ያደረጉ ተግባራት በትኩረት በመተግበር ላይ እንደሚገኝ አንስተዋል ፡፡
በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ የሚከሰቱ የተለያዩ ድንገተኛ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን መከላከል ሲከሰቱም ፈጥኖ በቦታው በመገኘት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት የህብረተሰብ ጤና ስጋት ወደ ማይሆኑበት ደረጃ ለማድረስ ጤና ተቋም የድንገተኛና ሠው ሠራሽ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊት አስቀድሞ በመለየት የመከላከልና የአየር ንብረት ለውጡን ተከትለው ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና ተግዳሮቶች ቅድሚያ ትኩረት በመስጠት የመከላከል ስራዎችን በማጠናከር ህብረተሰቡ ይህንን ታሳቢ ባደረገ መልኩ በባለቤትንት የመከላከል ስራውን ማገዝ ይገባዋል ብለዋል፡፡
የእንቁጣጣሽ በዓል ስናከብር የአየር ንብረት ለውጡን ተከትለው ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና ተግዳሮቶች ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ፣ተላላፊና ፣ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የወረርሽኝ ክስተቶችን በህብረተሰቡ ላይ ሊያደርሱ የሚችሉትን ፣የጤና ፣ የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጫናና ተፅዕኖ ለመቀልበስ የሚያስችሉ ተግባራት ላይ በጋራ በመረባረብ ከወራርሽኝ የፀዳች ኢትዮጵያን ለትውልድ እናውርስ ዘንድ በተቀናጀ መንገድ ልንረባረብ ይገባል።

በዞናችን የደረጃው የሚንገኝ ጤና ባለሙያዎች ባገባደድነው ዓመት የዞናችን ህዝቦች ጤናቸው ተጠብቆ በልማት ስራዎች ላይ እንድሆኑ የተሰራዉ ስራ አድናቆት ሊሰጠው ይገባል። በአንዳንድ ወረዳዎች ማህበረሰባችንን የተፈታተነው የወባ በሽታ በተደረገው ብርቱ ርብርብ ከፍተኛ ጉዳት ሳያስከትል መቆጣጠር የተቻለበት ዓመት ነበር። ለዚህም ምስጋና ይገባችዃል። በተቋሞቻችን በሀገራዊና ዓለማቀፋዊ ምክንያቶች የተፈጠረው የተወሰኑ ግብዓቶች እጥረት ብፈታትነንም ተገልጋዩ ህዝባችን በራሱ ላደረገው ትብብር ሊመሰገን ይገባል።
መላው ሴክተራችን አመራሮችና ባለሙያዎች፣ ዛሬ ከትላንት በእጅጉ ይለያልና አድሱ አመት የህዝባችንን የጤና ተስፋ የሚናድስበት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና ፍትሃዊነት የሚናሳልጥበት፣ ተቋሞችንን የግብአት አቅርቦት የምናድስበት፣ ሁላችንም በርህራዬና በብቃት ለማገልገል ቃለችንን የሚናድስበት፣ አኗኗር ዘይቤ መቀየርን ተከትለው የመጡ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች (ደም ግፊትና ስኳር) ከህዝባችን ጋር በመተባበር በልዩ ትኩረት የምንሰራበት ዓመት እንድሆን እየተመኘሁ ጥሪዬንም በዚህ አጋጣሚ ለማስተላሐፍ እወዳለሁ ብለዋል።
መልካም አድስ ዓመት
የዜጎች ጤና ለሀገር ብልፅግና!!!

አቶ ወንድሙ ደንኤል
የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ስር በሀደሮ ከተማ የክረምት የወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ የደም ልገሳና አረንጓደ አሻራ ችግኝ ተከላ ተካሂዷል ።በተፈጥሮ ወ...
27/07/2022

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ስር በሀደሮ ከተማ የክረምት የወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ የደም ልገሳና አረንጓደ አሻራ ችግኝ ተከላ ተካሂዷል ።

በተፈጥሮ ወይም በሰው ሠራሽ አደጋ ምክንያት በተያያዘ ሊከሰት የሚችለውን የደም እጦት ለመታገዝ በከተማ አስተዳደሩ የዘንድሮው የክረምት የወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራ በይፋ የተጀመረ ሲሆን በፕሮግራሙ ከተሳታፊዎች አንድም እናት በደም እጦት ምክንያት መሞት የለባትም በሚል ሀሳብ 08 ዩኒት ደም በአንድ ቀን የማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ብቻ መለገስ ተችሏል። ይህም የሰብአዊ በጎ ተግባር ለተከታታይ ሁለት ወራት ከሐምሌ እስከ ነሐሴ 2014 ድረስ ተጠናክሮ እንደምቀጥል የከተማው ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወጋየሁ ቃሎሬ ገልፀዋል። ከዚሁም ጎን ለጎን ጥላማና ፍራፍሬ በርካታ ጥቅም የሚሰጡ ችግኞችን በግቢው በመትከል ማህበረሰቡ የምግብ ዋስትና በማረጋገጥና የተመጣጠነ ምግብ ለማግኘት የበኩሉን ጥረት ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል።

አሁኑኑ ደም ይለግሱ፤ ችግኝ ይትከሉ፤ ሕይወትን ያድኑ፤ ከምግብ እጥረት የሚከሰቱ በሽታዎችንም ይከላከሉ!!!!

የከምባታ ጠምባሮ ጤና መምሪያ ኮሚዩኒኬሽን ክፍል

የአረንጓዳ አሻራችንን ለጥለና ለምግብነት የሚዉሉ ችግኞችን በጤና ተቋማት በመትከልና በማንከባከብ በሽታን ብቻ ሳይሆን አስተሳሰብ ጭምር መታከም እንዳለበት ተገለፀ። የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና ...
25/07/2022

የአረንጓዳ አሻራችንን ለጥለና ለምግብነት የሚዉሉ ችግኞችን በጤና ተቋማት በመትከልና በማንከባከብ በሽታን ብቻ ሳይሆን አስተሳሰብ ጭምር መታከም እንዳለበት ተገለፀ። የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ዳንኤል በዛሬው ዕለት (18/11/2014) በዶ.ር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል ግቢ ለጥላና ለምግብነት የሚዉሉ ችግኞችን በመትከል አረንጓደ አሻራችንን በማሳረፍ ህብረሰቡ ወደ ጤና ተቋማት ስመጣ በሽታን ብቻ ሳይሆን አስተሳሰቡን ጭምር እንድታከም ማድረግ አለብን ስሉ በዕለቱ ከሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የዞን ጤና መምሪያ እና የዶ/ር ቦጋለች ገ/መ/አ/ሆስፒታል እስታፍ በተገኙበት አሳስበዋል። በዚሁ መነሻ ሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ ጤና ተቋማት አረንጓደ አሻራችንን በማሳረፍ ተገቢውን እንዲፈፀም አሳስበዋል።

ዛሬ የምስራች ከቀዲዳ ጋማላ ወ /ጤ/ጥ ቤት የምስራች ላውጋችሁ።በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ስር ባለው የቀዲዳ ጋሜላ ወረዳ አር በየቦታው ከሚፀዳዳበት ወደ ጉድጓድ ከዚያ ወደ ተለምዶ መ...
23/07/2022

ዛሬ የምስራች ከቀዲዳ ጋማላ ወ /ጤ/ጥ ቤት የምስራች ላውጋችሁ።
በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ስር ባለው የቀዲዳ ጋሜላ ወረዳ አር በየቦታው ከሚፀዳዳበት ወደ ጉድጓድ ከዚያ ወደ ተለምዶ መጸዳጃ ከዚያ ወደ ተሻሻለ የሚጠረግ መጸዳጃ ከዚያ ወደ ተሻሻለ የሚታጠብ እስላቭ ዛሬ ደግሞ ጉልበትና ገንዘብ ቆጣቢ ወደሆነው ዘመናዊ ሳቶፓ የሚባል መፀዳጃ ቤት ለመጠቀም ተሸጋግረን
በ12/11/2014 በጆሬ ቀበሌ በዚሁ የሳቶፓ አሰራርና አጠቃቀም ግንዛቤ ማስጨበጫና ሰርቶ ማሳያ ስልጠና ላይ የቀበሌ ዋና አስተዳዳሪዎች፣ ሴቶች ጉዳይ፣ ጤና ኤክስቴንሽኖች፣ የእስላብ አምራች ማህበር አባላት፣ የጤና ጽ/ቤት ባለሙያዎች፣ የመ/ኮምንኬሽን በለሙያዎች፣ ከምባታ ማህበረሰብ ሬድዮ ባለሙያዎችና ሌሎችም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በድምሩ ከ70 በላይ አካላት በተነኙበት ገራሚ ስራ የተሰረውን እንኩ ከታች ተመልከቱ!

Address

Durame

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when KT ZHD_Health promotion and communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to KT ZHD_Health promotion and communication:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram