Kembata Tembaro zone health dep't Health communication

  • Home
  • Kembata Tembaro zone health dep't Health communication

Kembata Tembaro zone health dep't Health communication የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ኮሚዩኒኬሽን

29/04/2023

I f you are interested , refer this published study.

Womens_Experiences_and_Reasons_for_Preferences_to_Home_Delivery_A_Phenomenological_Qualitative_Study_in_Tembaro_District_Southern_Nations_Nationalities_and_Peoples_Region_SNNPR_Ethiopia

በጤናው ዘርፍ ጥራት ያለው መረጃ ከሌለ ጥራት ያለው አገልግሎት የለም መርዕ ተግባራዊ ማድረግ በጤናው ሴክተር ጉልህ ሚና እንደሚጫወት ተገለፀ።  በጤናው ዘርፍ ጥራት ያለው መረጃ ከሌለ ጥራት ...
03/04/2023

በጤናው ዘርፍ ጥራት ያለው መረጃ ከሌለ ጥራት ያለው አገልግሎት የለም መርዕ ተግባራዊ ማድረግ በጤናው ሴክተር ጉልህ ሚና እንደሚጫወት ተገለፀ።

በጤናው ዘርፍ ጥራት ያለው መረጃ ከሌለ ጥራት ያለው አገልግሎት የለም መርዕ ተግባራዊ ለማድረግ በተዘጋጀው ውይይት መረጃ በጤና ተቋማት እና በፕሮግራም ክፍሎች መረጃን ለውሳኔ መጠቀም የመረጃን አብዮት ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ‹‹ጥራት ያለው መረጃ ከሌለ ጥራት ያለው አገልግሎት የለም›› በሚል የጤና መረጃ ሳምንት ቀን ተከበረ፡፡

የግሉን ጤና ዘርፍ የጤና መረጃ ተሳትፎ አቅምና ተጠያቂነት ማሳደግ በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የሀገር አቀፍ የመረጃ ሳምንት ከመጋቢት 18-22/2015 መነሻ በማድረግ የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡

በመድረኩ ላይ‹‹ጥራት ያለው መረጃ ከሌለ ጥራት ያለው አገልግሎት የለም›› በሚል የጤና መረጃ ሳምንት በመረጃ ላይ ለውጥን ለማምጣት ታላሚ ያደረገ መሆኑን ተገልጿል፡፡

መድረኩ ከዞኑ ጤና መምሪያ ባለሙያዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የተከበረ ሲሆን

የመረጃ ጥራት ላይ ችግሮችን ለማስተካከል ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ኃላፊነት መወጣት እንዳለባቸው የተገለፀ ሲሆን ቀጣይ የተሻለ ለዉጥ ለማስመዝገብ በሁሉም መዋቅሮች ለተግባራዊነቱ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ በማሳሰብ የዕለቱ ውይይት ተጠናቅቋል።

የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ኮሚዩኒኬሽን

ማህበረሰቡ የሚፈልገውን የጤና አገልግሎት ለሁሉም ለማዳረስ አዲሱ የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖታ ካርታ አተገባበር ዙሪያ በየደረጃው በቂ ግንዛቤ መፍጠር ለትግበራው ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ተገለፀ። ...
02/04/2023

ማህበረሰቡ የሚፈልገውን የጤና አገልግሎት ለሁሉም ለማዳረስ አዲሱ የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖታ ካርታ አተገባበር ዙሪያ በየደረጃው በቂ ግንዛቤ መፍጠር ለትግበራው ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ተገለፀ።

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ስር በአዲሎ ዙሪያ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት አዲሱን የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖታ ካርታ ትግበራ ማጠናከሪያ ግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ

በሸሸራ ጤና ጣቢያ ሁሉም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት

በተላይም የጤና ኬላዎች በመስፈርቱ መሠረት እንደገና ማጥራት፣ የፍኖታ ካርታ አተገባበር መመሪያ፣ የጤና ኬላ ሪፎርም ስታንዳርዶች ትግበራ፣ በጤና ጣቢያዎች የጤና ኤክስቴንሽን ዩኒት ማደራጀትና ማጠናከር እንዲሁም የተዋሃዱ ጤና ኬላዎች ባሉበት ጤና ጣቢያና ቀበሌ ደረጃ የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆች አተገባበር ዙሪያ

ሰፋ ያሉ ዝርዝር ጉዳዮች ከወረዳው ጤና ፅ/ቤት በቅርቡ በክልሉ ጤና ቢሮ የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖታ ካርታ ማጠናከሪያ ስልጠና በሀላባ ዞን ቁሊቶ ከተማ ወስዳው በተመለሱ ባለሙያዎችና የጤ/ፅ/ቤት ኃላፊዎች አማካይነት ቀርቦ

በተሳታፊዎቹ ለተነሱ ጥያቄዎች በቂ ምላሽ ተሰጥቶ ቀጣይ የሚተገብሩትን አክሽን ፖይንቶችን በማዘጋጀትና ለመተግበር የድርሻቸውን ለመወጣት በመስማማት ተጠናቅቋል።

የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ኮሚዩኒኬሽን

እናቶች ህይወት እየሰጡ በደም እጦት ህይወታቸውን እኛ እያለን ማጣት የለባቸውም በሚል የግል ውሳኔ ተማሪዎችና መምህራን ደማቸውን በመለገስ አርኣያ መሆናቸው ተገለፀ።በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና ...
02/04/2023

እናቶች ህይወት እየሰጡ በደም እጦት ህይወታቸውን እኛ እያለን ማጣት የለባቸውም በሚል የግል ውሳኔ ተማሪዎችና መምህራን ደማቸውን በመለገስ አርኣያ መሆናቸው ተገለፀ።

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ስር በዱራሜ ከተማ አስ/ር በህጋ አዳሪ ት/ቤት ተማሪዎችና መምህራን አንድም እናት በወሊድ ሳቢያ በሚፈጠር የደም እጦት መሞት የለባትም በሚል በግላቸው ውሳኔ ደም ለመለገሰ ተስማምተው በአንድ ቀን ብቻ 34 ዩኒት ደም በመለገስ ለሌሎች አከባቢ ተማሪዎችና መምህራን አርአያ መሆናቸውን በተግባር ማረጋገጣቸው በምድር ላይ ታላቅ በጎ ሥራ በመሆኑ እጅግ ልመሰገኑ እንደሚገባ የዱራሜ ከተማ አስ/ር ጤና ፅ/ቤት ዘግቧል።

የከምባታ ጠምባሮ ጤና መምሪያ ኮሚዩኒኬሽን

አዲሱ የአጠቃላይ ጤና ኬላ የጤና አገልግሎት እንዲሰጥ የታቀደው ጤና ኬላ ይህ ከታች የሚትመለከቱት ስሆን በሁሉም ወረዳዎች ቀጣይ 2016 ዓመት በአንድ ወረዳ በአንድ ዓመት 01 ለመገንባት ባጀ...
20/03/2023

አዲሱ የአጠቃላይ ጤና ኬላ የጤና አገልግሎት እንዲሰጥ የታቀደው ጤና ኬላ ይህ ከታች የሚትመለከቱት ስሆን በሁሉም ወረዳዎች ቀጣይ 2016 ዓመት በአንድ ወረዳ በአንድ ዓመት 01 ለመገንባት ባጀት በማስያዝ ከጤና ጣቢያ ራቅ ባለ አከባቢ ከሚገኙና መስፈርቱን የሚያሟላ ጤና ኬላ ወደ ሁሉ አቀፍ ጤና አገልግሎት ሰጪነት ለመቀየር የሁሉም ወረዳ ጤና ፅ/ቤት ኃላፊዎችና ዋና አስተዳዳሪዎች እንዲትረባረቡ እናሳስባለን።

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ስር በዱራሜ ከተማ አስተዳደር በዱራሜ ጤና ጣቢያ ባለው የቤተሰብ ጤና ቡድን በላሎና ዘራሮ ቀበሌ በተጋላጭነትና በኢኮኖሚ ዝቅተኛ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ...
20/03/2023

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ስር በዱራሜ ከተማ አስተዳደር በዱራሜ ጤና ጣቢያ ባለው የቤተሰብ ጤና ቡድን በላሎና ዘራሮ ቀበሌ በተጋላጭነትና በኢኮኖሚ ዝቅተኛ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች አስቀድሞ ሊየታ ከተሠራ በኃላ ተገቢው የጤና አገልግሎት በጤና ጣቢያ ደረጃና ቤት ለቤት ድረስ በመሄድ የህክምናና የጤና ማጎልባት ተግባራት አገልግሎት እየተሠጠ ይገኛል።

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ስር በቀዲዳ ጋሜላ ወረዳ በአድሱ  ጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታ ዙርያ ግንዛቤ ማስጨበጨ ስልጠና በሚመለከታቸው አካላት በበቂ ሁኔታ የተሰጠ ሲሆን ተሳታፊዎችም ጤ/ኤክስቴ...
20/03/2023

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ስር በቀዲዳ ጋሜላ ወረዳ በአድሱ ጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታ ዙርያ ግንዛቤ ማስጨበጨ ስልጠና በሚመለከታቸው አካላት በበቂ ሁኔታ የተሰጠ ሲሆን

ተሳታፊዎችም ጤ/ኤክስቴንሽኖች፣ የወረዳው ፊት አመራር፣ የወረዳው ካብኔ አካላት፣ የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች፣ የጤ/ጣ ኃላፊና ትስስር ፎካሎች እና ሌሎችም ተግባሩ የሚመለከታቸው አጋሮች በድምሩ ከ80 በላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል።

ተሳታፊዎቹም አስተየየት ሰጥተው ለአፈጻጻሙ ሁላችንም የድርሻችንን መወጠት አለብን ብለዋል ::

የወረዳው ጤና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዛቸውም ጎበና መድረኩን የመሩት ስያጠቃልሉ በተሻሸለው ጤና ኬላዎች መሰረት ህብረተሰባችንን ተጠቃሚ ለማድረግ በየደረጃው ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል በማለት አጠቃለዋል::

This is Very Inspiring Public health service expansion acoording to public interest.
20/03/2023

This is Very Inspiring Public health service expansion acoording to public interest.

በየጊዜው የስራ አፈፃፀም ያለበትን ደረጃ በመገምገም ጠንካራ ጎኖችን የማስቀጠልና ሊሻሻሉ የሚገቡ ጉዳዮችን ፈጥኖ በማረም የጤናውን ሴክተር ትራንስፎርሜሽን ዕቅዶችን ለማሳካት መረባረብ እንደሚገ...
13/03/2023

በየጊዜው የስራ አፈፃፀም ያለበትን ደረጃ በመገምገም ጠንካራ ጎኖችን የማስቀጠልና ሊሻሻሉ የሚገቡ ጉዳዮችን ፈጥኖ በማረም የጤናውን ሴክተር ትራንስፎርሜሽን ዕቅዶችን ለማሳካት መረባረብ እንደሚገባ ተገለፀ።

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ስር የሚገኘው የጠምባሮ ወረዳ በጤናው ዘርፍ የ2015 ዓ.ም የሰባት ወራት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የተግባራት አፈጻፃም ግምገማ ላይ የወረዳው አስፈጻሚ አካላት፣ ጤና ጽ/ቤት የማኔጅመንት አካላት ፣ የጤና ጣቢያ ኃለፊዎች፣ የጤና ኤክሰቴንሽን ባለሙያዎችና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካለት በተገኙበት በጥልቀት መገምገሙ ተገልጿል።

የዕቅድ አፈጻጸም መድረኩን የመሩት የጤና ጥባቃ ጽ/ቤት ኃለፊ አቶ ታደሰ መኩሪያ የመድረኩ ዋናው ዓላማ ባለሙያው በፕሮግራሙ አፈጻጸም ያጋጠሙትን ተግዳራቶች በራሱ እንዲለይና ችግሮችን ለመፍታት ምን ማድረግ እንዳለበት ማንም ተነግሮለት ሳይሆን በራሱ የመፍትሄ ባለቤት እንዲሆን ለማብቃት የተዘጋጀ የጋራ መድረክ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በመድረኩ መክፈቻ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የወረዳው ዋና አስተዳደር አቶ አበራ አርፍጦ እንደገለፁት በእናቶችና በህፃናት በተለያ መልኩ በአየር መዛባት ምክንያት የሚስተዋሉ ወቅታዊ በሆነው በሽታ ከመከላከል የተሰሩ ሥራዎች አፈፃፀም ተጠናክሮ እንዲቀጥል በጤናው ዘርፍ ጤናማና አምራች ዜጋ በመፍጠርና በተሰማራንበት በማንኛውም ሙያ መስክ በቅንነት ህብረተሰቡን ማገልገል ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ገልፀዋል።

በመድረኩ ታዳሚዎችም በሽታን መከላከልና ጤናን ማጎልበት ላይ ያተኮረው የጤና ፖሊሲያችን የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሙን መተግበር ከጀመረ ወዲህ የማህበረሰቡን የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት በወሳኝ መልኩ በመቀየር ረገድ ጉልህ ድርሻ እንደነበረው ገልፀው በቀጣይ ቀሪ ተግባራትን ለማጠናከር የተሻለ መድረክ መሆኑን ገልፀዋል።

የወረደው የጤናው ዘርፍ ባለፉት ሰባት ወራት በዕቅድ የተያዙትን ተግባራት በተገቢው ሁኔታ ሪፖርት ቀርቦ ከተገመገመ በኋላ ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት እንዳይደገሙ ለማድረግ ጠንካራ ስራ እንደሚሠሩና በጥንካሬ የተለዩ አፈጻጸሞችን ደግሞ ወደ ሁሉም ቀበሌዎች እንዲሰፉ ለማድረግ የሚያስችል አቅጣጫ በማስቀመጥ እንደተጠናቀቀ የጠምባሮ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት አሳውቋል።

የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ኮሚዪኒኬሽን

እናቶች  በደም እጦት ህይወት እየሰጡ ህይወታቸውን ማጣት የለባቸውም በሚል አቋም የመንፈሳዊ ኮንፊራንስ ተሰብሳቢዎች ደማቸውን በመለገስ አርኣያ መሆናቸው ተገለፀ።በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መም...
11/02/2023

እናቶች በደም እጦት ህይወት እየሰጡ ህይወታቸውን ማጣት የለባቸውም በሚል አቋም የመንፈሳዊ ኮንፊራንስ ተሰብሳቢዎች ደማቸውን በመለገስ አርኣያ መሆናቸው ተገለፀ።

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ስር በቀን 02/06/2015 በዱራሜ ከተማ አስ/ር አንድም እናት በደም እጦት ምክንያት ህይወት እየሰጠች ህይወቷን ማጣት የለባትም በሚል በአንድ ቀን ብቻ በተደረገዉ መንፈሳዊ ኮንፍራንስ ላይ ከተሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎች 75 ዩኒት ደም መሰብሰብ ተችሏል።

የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ዳንኤል ህበረተሰቡ በደም እጥረት የሚከሰተዉን የእናቶችን ሞት ለመከላከል የሚያደርገዉ ትብብር የሚያስደንቅ መሆኑን ተናግረዋል።

አክለውም ሁሉም አካባቢ ይህንን ልምድ ወስዶ ተግባራዊ ማድረግ እንዳለበት አሳስበው ለተደረገው መልካም ተግባር በዞኑ ጤና መምሪያ ስም ምስጋናቸውን ገልፀዋል።

መከላከል በምንችላቸዉ ም፦ኒያቶች የሚከሰተውን የእናቶችን ሞት በጋራ እንከላከል!!!

የከምባታ ጠምባሮ ጤና መምሪያ ኮሚዩኒኬሽን ፎካል ባለሙያ

02/02/2023

በደቡብ ክልል ዕድሜያቸው ከ12_23 ወራት ላሉ ህፃናት የፀረ አንጀት ጥገኛ ትላትል መከላከያ መድሃኒት እደላ በተመረጡ ወረዳዎች ሊጀመር መሆኑ ተገልጿል
በደቡብ ክልል በተመረጡ 7 ወረዳዎች ዕድሜያቸው ከ12_23 ወራት ላሉ ህፃናት የፀረ አንጀት ጥገኛ ትላትል መከላከያ መድሃኒት እደላ የሙከራ ትግበራ ይፍዊ የማስጀመሪያ መርዓ ግብር በሀላባ ከተማ ተካሄዷል
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ የእናቶችና ህፃናት ጤናና ስርዓተምግብ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፍዬ ሌጆሶ በመልዕክታቸው የሆድ ጥገኛ ትላትሎች ህፃናትንና አዋቂዎችን የሚያጠቁ ቢሆንም በአብዛኛዉ በህፃናት ላይ እንደሚበዛ አውስተዋል ፡፡
ከዚህ ቀደም እድሜያቸው ከ5_19 ዓመት ለሞላቸው ህፃናቶችና እንዲሁም እድሜያቸው ከ15_49 ዓመት ለሚገኙ ሴቶች ይሠጥ የነበረው መድሃኒት በተመረጡ ወረዳዎች ላይ የሙከራ ትግበራው ዕድሜያቸው ከ12 -23 ወራት ያሉ ሕጻናት ተደራሽ እንደሚደረጉ በማንሳት ከዚህ ቀድም ሲከናወኑ የቆዩ ልምድና ተሞክሮዎችን በማካተት ለውጤታማነቱ የጋራ ርብርብ ሊደረግበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ የእናቶችና ህፃናት ጤናና ስርዓተምግብ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ወ\ሮ ገነት ላቀው በበኩላቸው ንጽህናው ያልተጠበቀ ምግብ መመገብ፣ በግልና አካባቢ ንጽህና ጉድለትና በባዶ እግር መሄድና የመሳሰሉት በሽታው እንዲከሰት የሚያደርጉ ዋነኛ ምክንያቶች መሆናቸው ተናግረዋል።
በሽታው የልጆችን አካላዊና አዕምሯዊ እድገት በማቀንጨር አምራችና ጤናማ ዜጋ እንዳይሆኑ ያደርጋልም ይሁን እንጂ የአንጀት ጥገኛ ትላትሎች መከላከያ መድሃኒት እደላ ውጤታማነት በህጻናት አስተዳደግና የመማር ማስተማር ሂደት ላይ ለያጋጥሙ የሚችሉ ተጽዕኖዎችን ለመግታት ያሥችላል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ከመድረኩ አሳቦች ተነስተው ውይይት የተካሄደባቸው ሲሆን የአንጀት ጥገኛ ትላትል ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት በስፋት የሚከሰት የጤና ችግር መሆኑን ይህም በተለይ የግልና የአካባቢ ንጽሕና ጉድለት ፣ የንጹህ ውሃ አቅርቦት ችግር መኖር በተግዳሮትነት እንደሚወሳ አንስተው ይህንንም ተግዳሮት ለመቅረፍ በተለይም በህጣናት ሁለንተናዊ እድገት ላይ የሚያመጣውን ተፅህኖ ለመመከት የፀረ አንጀት ጥገኛ ትላትል መከላከያ መድሃኒት እደላውን የተሳካ ለማድረግ በዘርፉ የተቀመጡ አደረጃጀቶችን በመጠቀም በጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ባሳተፈ መልኩ ተግባራት እንደሚፈፀሙ ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
የአንጋጫ ወረዳም ለዚህ ሙከራ ፕሮግራም ተጠቃሚ ለመሆን ስለባቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ።

በሁሉም የጤና አገልግሎት ዘርፎች ደረጃውን የጠበቀ እና ጥራት ያለው አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ።የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤ...
01/02/2023

በሁሉም የጤና አገልግሎት ዘርፎች ደረጃውን የጠበቀ እና ጥራት ያለው አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ።

የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ስድስት ወራት የጤና ልማት ሥራዎች እቅድ አፈፃፀም ግምገማና ምክክር መድረክ ተካሄደ።

በሽታን መከላከል የሚያስችሉ የጤና ልማት ሥራዎችን በጥራትና በፍትሃዊነት ተደራሽ በማድረግ ጤናማና አምራች ዜጋን ለመፍጠር ትኩረት ሠጥቶ እየሠራ መሆኑን የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ዳንኤል ገለፁ።

መድረኩን የመሩት የመምሪያው ኃላፊ አቶ ወንድሙ ዳንኤል ጤናው የተጠበቀና አምራች ዜጋን ለመፍጠር በሽታን መከላከል የሚያስችል የጤና ልማት ሥራዎች ለህብረተሰቡ በጥራትና በፍትሃዊነት ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን አብራርተዋል።

ለፍትሃዊ ተጠቃሚነትና ለመልካም አስተዳደር ችግር የሚሆኑ ሙስናን እና ብልሹ አሠራርን በማረምና በማስወገድ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የዘርፉ የሥራ ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎች፣ ባለድርሻ አካላትና ማህበረሰቡ ተቀራርቦና ተቀናጅቶ መስራት እንዳለበት አቶ ወንድሙ ዳንኤል አክለው አሳስበዋል።

አቶ ወንድሙ ዳንኤል አያይዘውም በጤና ተቋማት በየዘርፉ የሚሠጠው ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ከቁጥር ባሻገር ደረጃውን የጠበቀ ጥራት ያለው እና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆን አለበት ብለዋል።

የየዘርፉ የሥራ ሂደት አስተባባሪዎች የበጀት ዓመቱን የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበው ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በግማሽ ዓመቱ የጤና ልማት ሥራዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በተደረገው ርብርብ የታዩ ጠንካራ አፈፃፀሞች ይበልጥ አጠናክሮ በማስቀጠል እና የታዩ ክፍተቶችን በማረም በቀጣይ አገልግሎቱን በጥራትና በፍትሃዊነት ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት ተሠጥቶ መሠራት እንዳለበት አቅጣጫ በማስቀመጥ የግምገማው መድረክ ተጠናቅቋል።

በመድረኩ የመምሪያው ማናጅመንት አባላትና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ኮሚዩኒኬሽን ፎካል ባለሙያ

የወባ ኬዞችን በመፈተሽ ወባን የማስወገድ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለፀ።በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ስር በሁሉም መዋቅሮች ለሚገኙ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የወባ ፍተሻ ...
24/01/2023

የወባ ኬዞችን በመፈተሽ ወባን የማስወገድ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለፀ።

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ስር በሁሉም መዋቅሮች ለሚገኙ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የወባ ፍተሻ ተሃዲሶ ስልጠና በሁለት ዙር የሚሰጥ በክላስቴር ደረጃ በዳምቦያ፣ በሀዳሮና ዱራሜ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል።

ስልጠናው ጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የወባ በሽታን ለማስወገድ ለሚሠሩ ተግባራት ዙሪያ የተሻለ ግንዛቤና ልምድ ልውውጥ ለማድረግ እንደሚያግዛቸው ተጠቅሷል።

24/01/2023

ለተቋማዊ መርህ ቃል ማስተካከያ እንዲደረግ ማሳሰቢያ ተሰጠ።

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ስር ባሉ በሁሉም ጤና ሴክተር መዋቅሮች ላለፉት ጊዜያት በተለያዩ ጉዳዮችና በደብዳቤዎቻችን ስንጠቀምበት የነበረዉ "አንድም እናት በወሊድ ምክኒያት መሞት የለባትም" የምለዉ መፈክር "መከላከል በምንችላቸዉ ምክኒያቶች የሚከሰቱ የእናቶችን ሞት በጋራ እንግታ" or "Let's end preventable maternal death together" በምል የተቀየረ መሆኑን የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ዳንኤል አሳውቀዋል።

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ቃጫ ቢራ ወረዳ ምስራቅ ሌሾ ቀበሌ በዶ/ር ተሾመ አለምቦ ለሚቋቋመው ዶ/ር ተሾመ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታ ሥራ ማስጀመሪያ የመሠረት ድንጋይ ተጣለ።የመሠረት ድን...
21/01/2023

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ቃጫ ቢራ ወረዳ ምስራቅ ሌሾ ቀበሌ በዶ/ር ተሾመ አለምቦ ለሚቋቋመው ዶ/ር ተሾመ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታ ሥራ ማስጀመሪያ የመሠረት ድንጋይ ተጣለ።

የመሠረት ድንጋዩ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ክልል የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ባዩሽ ተስፋዬ እና በከምባታ ጠምባሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ መለሠ አጭሶ ተጥሏል።

Congratulations all!!!
Our zonal Medical tourisim, quality care and private public, partineship should be shifted one step Ihead. Share the experience and let's stand together for our community health!!!!

የወባ በሽታን ለመከላከል ሁል ጊዜ በመኝታ ዙሪያ የአልጋ አጎባር በአግባቡ መጠቀም ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ተገለፀ።በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ስር በዱራሜ ከተማ አስተዳደር በአጎበር ስ...
18/01/2023

የወባ በሽታን ለመከላከል ሁል ጊዜ በመኝታ ዙሪያ የአልጋ አጎባር በአግባቡ መጠቀም ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ተገለፀ።

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ስር በዱራሜ ከተማ አስተዳደር በአጎበር ስርጭትና አጠቃቀም ዙርያ የቅድመ የኦሬንቴሽን መድረክ ተካሄደ።

በመድረኩም በአጎበር አጠቃቀም፣ ስርጭት፣በወባ መከላከያ ዘዴዎች፣በወባ ትንኝ ባህርያት እንዲሁም አገራዊ የአጎባር ሥርጭት ስልቶች፣ የባለድርሻ አካላት ኃላፊነት እና ተግባር ዙርያ እንዲሁም በሌሎችም ርዕሶች ላይ የዞኑ የጤና መምሪያ የወባ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ተሰማ ታረቀኝ በኩል
ለተሳታፊዎች ቀርቦ ዉይይት ተደርጓል።

መድረኩን የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ያስጀመሩት የላሎ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተሰማ ተሾመ እንደገለፁት አጎባርን በአግባቡ በመጠቀም ከበሽታው መከላከል እንደሚገባ ጠቁመው ከዚህ ዉጪ አጎባር ከዓላማው ውጪ በሚጠቀሙ አካላት ተገቢውን እርምጃ በመዉሰድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል።

አክለውም የአጎባር ሥርጭቱ በዋናነት በሽታው የሚበዛባቸው አከባቢዎች ቅድምያ በመስጠት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ህብረተሰቡም አጎበርን በተገቢው መንገድ በመጠቀም ከበሽታው መከላከል እንደሚያስፈልግ በኦሬንቴሽን መድረኩ ላይ ተገልጿል።

በመድረኩም የከተማው አመራር አካላት፣የቀጠና አመራሮች፣የጤና ጽ/ቤት ማኔጅመንት አባላት ፣ሁሉም የከተማው ኤክስቴንሽን አባላት፣የዞኑ ጤና መምርያ የዘርፉ ባለድርሻ አካላትን ጨምሮ የሚመለከታቸው ባለድርሻዎች ተሳታፊ መሆናቸውን የዱራሜ አስተዳደር መንግስት ኮሚዪኒኬሽን ዘግቧል።

The first private Hospital inauguration in Kambat Tembaro zone Kachabira Woreda In Misrak Lesho will be done in the pres...
17/01/2023

The first private Hospital inauguration in Kambat Tembaro zone Kachabira Woreda In Misrak Lesho will be done in the presence of Elders of Kambata as well as Goverment officials plus highly educated Kambats Doctors and professor on 13/05/15 E.C

Congratulation

በማህበረሰብ የጤና መድህን አፈፃፀም የሀዳሮ ከተማ አስተዳደር 1ኛ ደረጃ በመውጣት የተሻለ አፈፃፀም ስላስመዘገበ ዋንጫና ሴርቲፍኬት ተሸላሚ ሆነ። በክልላዊ ማዐጤመ ንቅናቄ መድረክ በ2014 በ...
14/01/2023

በማህበረሰብ የጤና መድህን አፈፃፀም የሀዳሮ ከተማ አስተዳደር 1ኛ ደረጃ በመውጣት የተሻለ አፈፃፀም ስላስመዘገበ ዋንጫና ሴርቲፍኬት ተሸላሚ ሆነ።

በክልላዊ ማዐጤመ ንቅናቄ መድረክ በ2014 በጀት አመት አፈፃፀፈም የሀደሮ ከተማ አስተዳደር 100% በማስመዝገብ በክልሉ ካሉት ወረዳዎች 1ኛ በመሆን ክርስታል ዋንጫና ሰርቲፊኬት እወቅና ተሰጥቶታል።

አቶ ወንድሙ ዳንኤል የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ እንደገለፁት ለተመዘገበው ውጤት፣ እውቅናና ሽልማት ስኬት አስተዋፅኦ ላበረከቱት አካላት በሙሉ የሁላችንም ርብርብ ውጤት በመሆኑ እንኳን ደስ አለን ደስ አላችሁ ብለዋል!!!

አክላውም ለመላው የዞናችን የጤናው ሴክተር አመራሮችና ባለሙያዎች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል!!

ለበለጠ ስኬት እንትጋ!!

የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጤና መምሪያ ኮሚዩኒኬሽን ፎካል ባለሙያ

Address

SNNPR, Ethiopia

SBCC

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kembata Tembaro zone health dep't Health communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your practice to be the top-listed Clinic?

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram