እናት መካከለኛ ክሊኒክ / Enat Medium Clinic

እናት መካከለኛ ክሊኒክ / Enat Medium Clinic አላማችን ህሙማን መርዳት ነው!!

26/07/2025

(Mumps) ?
=======
✍ጆሮ ደግፍ መምፕስ (Mumps virus) በተባለ የቫይረስ ዓይነት የሚመጣ እና ፓሮቲድ የሚባለውን የምራቅ ማመንጫ እጢ የሚያጠቃ ተላላፊ በሽታ ነዉ፡፡

🔷 ልጆች በቂ የሆነ የመከላከያ አቂም ስለሌላቸው ይሄ በሺታ ብዙ ጊዜ ልጆች ላይ ይታያል ::

♦️ፓሮቲድ እጢ(Parotid gland) በቀኝና በግራ ጆሮአችን ስር የሚገኝ ምራቅ የሚያመነጭ እጢ ሲሆን በዚሁ ቫይረስ በሚጠቃበት ጊዜ ስለሚቆጣ ከጆሮአችን አካባቢ ሊያብጥ ይቺላል ::

✍አንዳንዴ እብጠቱ ከፍተኛ ከሆነ ጆሮን ወደ ላይ ገፍቶ ስለሚዘዉ በአማርኛ “ጆሮ ደግፍ” የሚል ስያሜ እነዲያገኝ ምክኒያት ሁኗል፡፡


=======
👉 በበሽታዉ ከተያዘ ሰዉ ጋር በሚኖር ንክኪ
👉 በትንፋሽ (በሳል በማስነጠስ ጊዜ)


========
♦️የጉንፋን ዓይነት ስሜትና መጠነኛ የሆነ የሰዉነት ሙቀት መጨመር ሲሆን ቀስ በቀስ ሙቀቱ ከፍተኛ ሊሆን ይችላል::

♦️ ከጆሮ ስር የሚከሰት እብጠት ና የህመም ስሜት

♦️ ልጆች ላይ የሚታይ የማልቀስና የመነጫነጭ

♦️ ራስ ምታት

♦️ የጡንቻ ህመም እና የድካም ስሜት

♦️ የምግብ ፍላጎት መቀነስ

♦️የሰውነት ሙቀት መጨመር(ትኩሳት)


========
👉የወንዶችን የዘር ፍሬ(testicle) በማጥቃት መጠኑ እንድቀንስ ያደርጋል እንድሁም ግዜያዊ መካንነት ያስከትላል
👉የሴቶችን የእንቁላል ማመንጫ(Ovary)ያጠቃል።
👉ቆሽትን በማጥቃት የቆሽት ብግነት(Pancreatitis) ያስከትላል።
👉የጆሮን የውስጥ ክፍሎች በማጥቃት ጊዜያዊ ወይም ቋሚ የመስማት ችግር ያስከትላል።
👉የአንጎል ህዋሳትን እና የአንጎልን አቃፊ በማጥቃት እና እራስን በማሳት እስከ ሞት ሊያደርስ ይችላል።

#ህክምናው
====
🔘 በቂ እረፍት መዉሰድ

🔘 ለሙቀትና የህመም ማስታገሻ መድሀኒት መዉሰድ

🔘 ተጨማሪ ፈሳሽ ነገሮች መዉሰድ

🔘 ይህ በሽታ መንስኤዉ ቫይረስ በመሆኑ ፀረ-ባክቴሪያ መድሀኒቶችን (antibiotics) መዉሰድ አያስፈልግም፡፡

🔘 ዋናው ህክምናዉ መሆን ያለበት ማስታገሻ መድሀኒቶችን (symptomatic treatment ) መውሰድ ነው ማለትም ለእብጠቱ፣ለሙቀቱና ለህመም ስሜቱን የሚቆጣጠሩ መድሃኒቶችን መውሰድ ይመከራል ፡፡

#ምንጮች (Sources)
1.CDC about mumps symptoms and complications)
2.National Institute of Health
3.Mediscape

፡፡

ጤና ነክ እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100076171566897
ቴሌግራም https://t.me/ba051219

🧬የቅድመ-ወር አበባ ቅምረ ህመም - Premenstrual syndrome (PMS) በዶ/ር በእምነት አየነውከወር አበባ በፊት እና ከኦቭሌሽን በኋላ (ከ5-7 ቀን) የሚከሰቱ ምልክቶች ሲሆኑ አብ...
29/06/2025

🧬የቅድመ-ወር አበባ ቅምረ ህመም - Premenstrual syndrome (PMS) በዶ/ር በእምነት አየነው
ከወር አበባ በፊት እና ከኦቭሌሽን በኋላ (ከ5-7 ቀን) የሚከሰቱ ምልክቶች ሲሆኑ አብዛኛውን ጊዜ የግለሰባዊ ግንኙነቶች እና መደበኛ እንቅስቃሴን ሲያስተጓጉል ይስተዋላል። የቅድመ-ወር አበባ (Premenstrual syndrome) ዓለም አቀፍ ስርጭት 47.8% ሲሆን 90% የሚሆኑት የመራቢያ ዕድሜ ላይ ያሉ ሴቶች በሕይወታቸው ውስጥ በሆነ ጊዜ ይጠቃሉ።
ይህ ሲንድሮም ትክክለኛ መንስኤ በትክክል ባይታወቅም እንቁላል ከወጣ በኋላ በሆርሞን ለውጦች ምክንያት እንደሚነሳሳ ይታመናል። ፕሮጄስትሮን ከ PMS ምልክቶች በስተጀርባ ያለው ዋና ምክንያት ነው።
🚦ምልክቶቹ
• ውጥረት ወይም ጭንቀት
• ድብርት
• ማልቀስ
• የስሜት መለዋወጥ እና ንዴት ወይም ቁጣ
• የምግብ ፍላጎት ለውጦች
• እንቅልፍ የመተኛት ችግር (እንቅልፍ ማጣት)
• ማህበራዊ ግንኙነትን ማቋረጥ
• ደካማ ትኩረት
• አጠቃላይ ህመም
• ማቅለሽለሽ
• ብጉር እና የአለርጂ ምላሾች
🎯መፍትሄ
• በቫይታሚን B6 ፣ ካልሲየም እና ማግኒዚየም የበለፀጉ ምግቦች ሊመከሩ ይችላሉ።
• ትራይፕቶፋን የያዙ ምግቦችን መመገብም ሊረዳ ይችላል። ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ የወተት ተዋጽኦዎች፣ አኩሪ አተር፣ ቱና እና ሼልፊሽ ናቸው።
• በወሩ ውስጥ ብዙ እንቅልፍ ለመተኛት ይሞክሩ።
• እንደ ውሃ ወይም ጭማቂ ያሉ ብዙ ፈሳሽ ይጠጡ። ለስላሳ መጠጦችን፣ አልኮልን ወይም በውስጡ ካፌይን ያለበትን (ቡና፣ ኮካ) ያስወግዱ።
• ቢያንስ በየ 3 ሰዓቱ የሚበላ ነገር ይኑርዎት። ነገር ግን ከመጠን በላይ አይብሉ።
• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ጡንቻን ማዝናናት እና የማያቋርጥ ማነቃቂያ መደጋገም ፣ ለምሳሌ በእያንዳንዱ እስትንፋስ ጊዜ “አንድ” የሚለው ቃል እየደጋገምን; ለ 10-20 ደቂቃዎች ልምምድ ማድረግ
• የግንዛቤ ባህሪ ሕክምና (Cognitive behavioral therapy) እና በሀኪም የሚታዘዙ መድሀኒቶችም ስለሚኖሩ አስጊ ደረጃ የሚደርስ (PMDD) ከሆነ ሀኪም ያማክሩ።
ለማማከርና ለህክምና ብቅ ይበሉ፣ በስልክም ያማክሩን!! በደስታ እናስተናግዶታለን!!
👇 መገኛችን
እናት መካከለኛ ክሊኒክ ዱራሜ
ዱራሜ አጠቃላይ ሆስፒታል ፊት ለፊት እንገኛለን
በዶ/ር አብነት አዳነ (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት) እና ሌሎች
ስልክ፡ 0913295363/ 0926268855
Telegram: https://t.me/+Wm5YIC1zUOMzMjE0
Facebook: https://www.facebook.com/share/1HwhaMdbcY/

Infantile colic (የጨቅላ ህፃን ቁርጠት) የእናት ጭንቀትስለ ጨቅላ ህፃን ቁርጠት ምን ያውቃሉ ??ቁርጠት (የህፃናት ኮሊክ) በተወሰነ ደረጃ ሚስጥራዊ የሆነ የስቃይ አይነት ነው፡፡ ቃ...
28/06/2025

Infantile colic (የጨቅላ ህፃን ቁርጠት) የእናት ጭንቀት
ስለ ጨቅላ ህፃን ቁርጠት ምን ያውቃሉ ??
ቁርጠት (የህፃናት ኮሊክ) በተወሰነ ደረጃ ሚስጥራዊ የሆነ የስቃይ አይነት ነው፡፡ ቃሉ ለማንኛውም ጤናማ ፣ ባግባቡ አየተመገበ ከ3 ሳምንታት ለሚበልጥ ግዜ በሳምንት ከ3ቀናት ለሚበልጥ ግዜ ለሚያለቅስ ህፃንን የሚመለከት ነው፡፡
ቁርጠት ቢያንስ ለ 3 ሳምንታት ያክል በሳምንት በላይ ለሆኑ ቀናት ከ3 ሰዓታት ለበለጡ ጊዜያት የጨቅላ ህፃን ማልቀስ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል ፡፡
ቁርጠት ህፃኑ በግዜው የተወለደ ከሆነ የ2 ሳምንታት እድሜ ሲሞላው የሚጀምር ሲሆን ግዜው ሳይደርስ የተወለደ ከሆነ ደግሞ ከ2 ሳምንታት በኋላ ሊከሰት ይችላል ፡፡
ይሁን እንጂ ብዙውን ጊዜ ከ3 ወይም ከ4 ወራት በኋላ በራሱ ግዜ ይተወዋል፡፡
አንዳንድ ጊዜ አራስ ልጆች ለሰዓታት ያለቅሱ እና ብስጩ ይሆናሉ ፡፡ አንድ ጨቅላ ህፃን ጤነኛ ሆኖ እያለ ለበርካታ ጊዜያት ብስጩ በጣም እየጮኸ የሚያለቅስ ከሆነ የምቾት ስሜት ሳይሰማው ሳምንቱን ሙሉ የሚያሳልፍ ከሆነ ፣ ቁርጠት የሚባለው ሁኔታ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡
የቁርጠት ምክንያት
የቁርጠት ትክክለኛው ምክንያት አይታወቅም ለዚህም ነው እርዳታ ለመስጠት የሚያስችል ግልፅ መንገድ የሌለው፡፡
- ብዙውን ጊዜ እየዳበሩ በሚሄዱ ጡንቻዎች አያደገ የሚሄድ የምግብ መፈጨት ስርዐት
- በተዋሲያን መጠቃት
- ጋዝ - ወተት ሲጠባ አብሮት ወደ ሆዱ የሚገባ አየር (ጋዝ)
- የጨጓራ ህመምን የሚያስከትሉ ወይም ደስ የማይል ስሜት የሚያስከትሉ ሆርሞኖች
- ስሜታዊ የሆነ ህፃን
- አሁንም በማደግ ላይ ያለ የነርቭ ስርዓት
መፍትሄ
ምግብ በሚመገብበት ወቅት በተቻለ መጠን ቶሎ ቶሎ እንዲያገሳ ሙከራ ማድረግ
ልጁን በሆዱ በታፋዎ ላይ አስተኝተውት ጀርባውን ማሸት
ልጅዎትን በዥዋዥዌ መቀመጫ ላይ / በህጻናት መኪና መቀመጫ ላይ ያስቀምጡት ፡፡ እንቅስቃሴው እንዲሻለው ያደርገዋል፡፡
- የልጅዎ የሙቀት መጠን ከፍ ማለት ፣ በደምብ ምግብ አለመውሰድ ፣ ተቅማጥ ፣ ትውከት ፣ እንቅልፍ አለመተኛት ካለው ወዲያውኑ የጤና ባለሙያ ጋር መውሰድ አስፈላጊ ነው፡
ለማማከርና ለህክምና ብቅ ይበሉ፣ በስልክም ያማክሩን!! በደስታ እናስተናግዶታለን!!
👇 መገኛችን
እናት መካከለኛ ክሊኒክ ዱራሜ
ዱራሜ አጠቃላይ ሆስፒታል ፊት ለፊት እንገኛለን
በዶ/ር አብነት አዳነ (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት)
ስልክ፡ 0913295363/ 0926268855
Telegram: https://t.me/+Wm5YIC1zUOMzMjE0
Facebook: https://www.facebook.com/share/1HwhaMdbcY/

"ልጆች የላም ወተት መች ነዉ መጀመር ያለባቸው?"በስራ ገበታ ሳለን ቀላል የማይባሉ እናቶች አዉቀውም ሆነ ሳያውቁ "የጡቴ ወተት በቂ ስላልሆነ የላም ወተት ተጨማሪ ጀምሬለታለው" ብለው ሳያበቁ...
26/06/2025

"ልጆች የላም ወተት መች ነዉ መጀመር ያለባቸው?"
በስራ ገበታ ሳለን ቀላል የማይባሉ እናቶች አዉቀውም ሆነ ሳያውቁ "የጡቴ ወተት በቂ ስላልሆነ የላም ወተት ተጨማሪ ጀምሬለታለው" ብለው ሳያበቁ ቱከት ተቅማጥ ታመው ማየት የተለመደ ነገር ነው ።
ልጆች የላም ወተት መች ነዉ መጀመር ያለባቸው? ጤናማ የሆነ የልጅ አመጋገብ ምንድነው?
ህፃናት የተስተካከለ አካላዊና አዕምሮዊ እድገት እንዲኖራቸዉ ጤናማ የአመጋገብ ዘዴ ጉልህ ድርሻ አለዉ፡፡ ይህ ጤናማ የሆነ የአመጋገብ ዘዴ ልጆቹን ከተለያዩ በሽታዎች እንደ ተቅማጥ ፣ የሳምባ ምች ፣ የጀሮ ምርቀዛ ('ኢንፌክሽን') እና ሌሎችንም ተላላፊ በሽታዎች በመከላከል ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅኦ አለዉ፡፡
ጤናማ የአመጋገብ ዘዴ የምንላቸዉ ምንድናቸው?
- የመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ዕድሜ
በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ህፃናት ያለምንም ተጨማሪ ምግብ የእናት ጡት ብቻ በቀን ከ8-12 ጊዜ እንዲወስዱ ይመከራል፡፡ጨቅላ ህፃናት ወዲያዉ በተወለዱ በ30 ደቂቃ ዉስጥ የእናት ጡት መጀመር አለባቸዉ፡፡
በተለምዶ በተለይ በገጠራማዉ አካባቢ እንዲሁም በከተማዎች አልፎ አለፎ ጨቅላ ህፃናት ወዲያዉ እንተወለዱ ከእናት ጡት በፊት የሚሰጡ (prelactal feeding) እንደ አብሽ ፣ ቅቤ ፣ ሻይ ፣ ዉሃ በስኳር የመሳሰሉትን መስጠት ለኢንፌክሽን ስለሚያጋልጣቸዉ ጎጂ ባህላዊ ልማድ ነዉ፡፡
- ከስድስት እስከ አስራ ሁለት ወራት ዕድሜ
በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ህፃናት ከየእናት ጡት በተጨማሪ ተጨማሪ ምግብ መጀመር አለባቸዉ፡፡
እድሜያቸዉ ከ 6-8 ወር ለሆኑ ህፃናት ተጨማሪ ምግቦችን በፈሳሽ መልክ (እንደ አጥሚት) በቀን ከ2-3 ጊዜ እንዲሁም ከ8-12 ወር ለሆናቸዉ በከፊል ጠጣር መልክ (እንደ ገንፎ) በቀን 4-5 ጊዜ መመግብ ያስፈልጋል፡፡
በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ጡት ማጥባት የሚቀጥል ሲሆን ነገር ግን የእናት ጡት ወተት መጠን እየቀነሰ የሚሄድበት ጊዜ ስለሆነ ለህፃናት የሚሰጠዉ ተጨማሪ ምግብ በዓይነትም በመጠንም በደንብ መጨመር አለበት፡፡ ተጨማሪ ምግቦችን በጠጣር መልክ (እንደ እንጀራ፣ ዳቦ፤ እንቁላል፣ ሥጋ፣ ወዘተ የቤተሰብ ምግቦችን) መጀመር ይቻላል፡፡

- ከስድስት ወር ቀደመው ሌላ ነገር ቢጀምሩ ምን የጤና ችግር ይገጥማቸዋል?
👌ልጆች ብዙ ወይም በቂ የእናት ጡት እንዳያገኙ ያደርጋቸዋል::
👌ልጆች ለተቅማጥ በሽታ እንዲጋለጡ ያደርጋቸዋል::
- ተጨማሪ ምግብ ከስድስት ወር አልፈው ቢጀምሩ እሳ?
👌 ልጆች የሚያስፈልጋቸውን ተጨማሪ ሀይልና ንጥረ ምግቦች እንዳያገኙ ያደርጋል፡፡
👌 ልጆች ለመቀጨጭና ለተለያዩ የማእድን እጥረት ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡
ልጆች የላም ወተት መች ነዉ መጀመር ያለባቸው?
- ህጻናትን ቶሎ የላም ወተት ማስጀመር ያለው የጤና ጉዳት
የአለም ጤና ዲርጅትና የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የተለየ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር የላም ወተት ከአንድ አመት በፊት መሰጠት የለበትም፡፡ ከአንድ አመት በፊት የላም ወተት የሚወስዱ ህፃናት በተለይም መጠኑ ከ20 ounce ወይም ግማሽ ሊትር በላይ ከሆነ የአንጀት መድማትና አይረን የተባለዉን ንጥረ ነገር ከአንጀት ወደ ደም እንዳይመጠጥ በማድረግ በአይረን እጥረት ምክንያት የሚከሰት የደም ማነስ (Iron deficiency anemia) ያመጣል፡፡
- የላም ወተት ለልጆች በቶሎ ማስጀመር የጤና ጉዳቶች
o ዝቅተኛ የአይረን መጠን ስላለው ለደም ማነስ ችግር ያጋልጣል
o ከፍተኛ የፕሮቲን ይዘት ስላለው ለአንደኛው የስኳር ህመም ያጋልጣቸዋል
o የህጻናት ሆድ ድርቀት
o የወተት አለርጂ
o ላክቶዝ ንጥረነገር በሰውነት ውስጥ አለመኖር በወተት ውስጥ ለሚገኘው የላክቶዝ ንጥረነገር መብላላት አለመቻል ያጋልጣቸዋል፡፡
o ተቅማጥ የመሳሰሉትን የጤና እክሎች ያመጡባቸዋል
አንብበው ሲጨርሱ ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር ያድርጉት
ዶ/ር መሐመድ በሽር የህፃናት ሐኪም እንደ ፃፈው!
🍀ጤና ይብዛሎ!🍀
🍀መልካም ጊዜን ተመኘሁ!🍀
🔊📍መልክቱ ከጠቀሞት ለወዳጆዎ ያጋሩ።
👇 ለበለጠ መረጃ
ለማማከርና ለህክምና ብቅ ይበሉ፣ በስልክም ያማክሩን!!
እናት መካከለኛ ክሊኒክ ዱራሜ
ዱራሜ አጠቃላይ ሆስፒታል ፊት ለፊት እንገኛለን
በዶ/ር አብነት አዳነ (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት)
ስልክ፡ 0913295363/ 0926268855
Telegram: https://t.me/+Wm5YIC1zUOMzMjE0
Facebook: https://www.facebook.com/share/1HwhaMdbcY/

"ትዳር ከመሰረትን 8 አመታት አሰቆጠርን። ልጅ ለመውለድ እስከ አሁን ድረስ ብንሞክርም አልተሳካልንም። ችግሩ ከእኔ ነው ወይስ ከባለቤቴ" የሚል ጥያቄ አንድ ታካሚ አንስቶልኝ ነበር።ስንቶቻችን...
25/06/2025

"ትዳር ከመሰረትን 8 አመታት አሰቆጠርን። ልጅ ለመውለድ እስከ አሁን ድረስ ብንሞክርም አልተሳካልንም። ችግሩ ከእኔ ነው ወይስ ከባለቤቴ" የሚል ጥያቄ አንድ ታካሚ አንስቶልኝ ነበር።
ስንቶቻችን ነን መካንነት (infertility) መፍትሄ ሊኖረው እንደሚችል ምናቀው?
(Infertility)ምንድን ነው?
-መካንነት የምንለው ጥንዶች አብረው እየኖሩ ምንም አይነት የወሊድ መቆጣጠሪያ ሳይጠቀሙ ለአንድ አመት ልጅ ለመመካንነትዉለድ ሞክረው ካልቻሉ ነው።
-መካንነት በተለየ መልኩ በታዳጊ ሀገሮች ይስተዋላል።
-እንደ የአለም የጤና ድርጅት (WHO) አገላለፅ ወደ 50 ሚሊዮን ጥንዶች በአለም አቀፍ ደረጃ ተጠቂ ናቸው።
በማን ችግር ምክንያት ሊፈጠር ይችላል?
-የመካንነት ችግር ብዙዎች የሚያስቡት በሴቷ ችግር ብቻ እንደሆነ ነው። ነገር ግን በእርስዎም ፣ ወይም በትዳር አጋርዎ ምክንያት ሊፈጠር ይችላል።
አይነቶቹስ?
1. አንደኛ ጀረጃ መካንነት (primary infertility) የምንለው ጥንዶች የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ አንድም ጊዜ ቢሆን ፅንስ መፍጠር ሳይችሉ ሲቀር ነው።
2.ሁለተኛ ደረጃ መካንነት (secondary infertility) የምንለው ከጊዜ በዃላ የሚከሰት ሲሆን ከዚህ በፊት ፅንስ መፍጠር ችለው በተለያየ ምክንያት ከዛ በዃላ ድጋሚ መፀነስ (መውለድ) ካልቻሉ ነው።
ምክንያቶቹስ?
-በሴት ምክንያት ፣ በወንድ ምክንያት ፣ በወንድም በሴትም ተጨባጭ የሆነ ምክንያት ያልተገኘላቸው ብለን ማየት እንችላለን።
1.በሴቶች ምክንያት ከሆነ ለምሳሌ በእድሜ መጨመር ምክንያት በተለይ ከ35 አመት በላይ እድሜ ፣ የማህፀን ቱቦ ኢንፌክሽን ፣ የማህፀን ቱቦ መጥበብ (መዘጋት) ፣ የማህፀን ጠባሳ ፣ የማህፀን አፈጣጠር ችግር ፣ ከእንቁላል ጋር የተያያዘ ችግር (polycystic ovarian syndrome) ፣ የሴቷ እንቁላል በቂ አለመሆን ፣ የሳንባ ነቀርሳ ፣ የማህፀን እጢ፣የአልኮል መጠጥ ፣ ሲጋራ ማጨስ ፣ አላሰፈላጊ ውፍረት ፣ ያልታከመ እና በተደጋጋሚ የሚከሰት የአባላዘር በሽታ ፣ የሆድ እና የመራቢያ አካል ቀዶ ጥገና እንደ ምክንያትነት ይጠቀሳሉ።
2.በወንድ ምክንያት ከሆነ ለምሳሌ የዘር ፍሬ መተላለፊያ መዘጋት ፣ በቂ የሆነ የዘር ፍሬ ህዋስ አለመኖር ፣ የሆርሞን መዛባት ፣ ሲጋራ ማጨስ ፣ አልኮል መጠጥ ፣ አላስፈላጊ ውፍረት ፣ አላስፈላጊ ጭንቀት ፣ የወንድ የዘር ህዋስ (s***m cell) አለመኖር ወይም ማነስ ፣ የሳንባ ነቀርሳ ፣ ኢነፌክሽን ፣ የአባላዘር በሽታ እንዲሁም በአደጋ ምክንያት ሊከሰት ይችላል።
3.በወንድም በሴትም ተጨባጭ የሆነ ምክንያት ያልተገኘላቸው (unexplained infertility) ሊኖር ይችላል።
ምርመራዎቹስ?
- ሀኪምዎት ተገቢውን ታሪክ ከወሰደ እና አካላዊ ምርመራ ካደረገልዎት በዃላ የተለያዩ ምርመራዎች ለምሳሌ ለወንዱም ለሴትም የተለያዩ የደም፣ የሽንት ምርመራ ከዛም ለወንድ የዘር ፈሳሽ ምርመራ (Semen analysis) ይታያል ከዛም አንደ አሰፈላጊነቱ karyotyping ፣ የሆርሞን ምርመራ (FSH, LH, PRL, testesterone)፣ x ray ፣ የሆድ ወይም የዘር ፍሬ አልትራሳውንድ ፣ CT scan
ለሴት ደግሞ HSG ፣ office hysterocopy ፣ የሆድ እና የመራቢያ አካል አልትራሳውንድ ፣ Endometrial biopsy ሊታዘዝ ይችላል።
በማህበረሰባችን የተሳሳቱ አመለካከቶች እና ተያያዥ ጉዳቶችስ ምንድን ናቸው?
-ልጅ ካልተወለደ ትዳር እንደማይባል ተደርጎ ማሰብ
-መካንነት ሲነሳ የሴቷ ችግር ብቻ እንደሆነ ማሰብ
-በማህበረሰባችን ውስጥ ህክምና ወይም መፍትሄ እንደሌለው ተደርጎ ማሰብ እና የግንዛቤ ማነስ
-ተያያዥ ጉዳቶች ለምሳሌ ስነልቦናዊ፣ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ያስከትላል።ለምሳሌ በጥነዶች መሀል የጥፋተኝነት ስሜት፣ራስን መውቀስ፣ እስከ ፍቺ የመድረስ ሁኔታ ይስተዋላል።
መፍትሄዎቹስ?
-የወር አበባ ኡደትን ጠብቆ የማይመጣ ከሆነ ባለሙያ በማማከር ማስተካከል
-የሰውነት ክብደትን ማስተካከል
-ሲገራ ፣ አልኮል መጠጥ ማቆም
-ጭንቀት መቀነስ
-ስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች የደም ስኳር መጠን መቆጣጠር
-በወንዱም በሴቱም ግልፅ የሆኑ የተረጋገጡ ምክንያቶች ካሉ ማከም፣ቀዶ ጥገና
-በቴክኖሎጂ የታገዘ ከማህፀን ውጪ የመካንነት ህክምና (IVF) ይህም ከሴቷ እንቁላል ፣ ከወንዱ የዘር ፈሳሽ ተወስዶ በቤተ ሙከራ ውስጥ ፅንስ እንዲፈጠር የማድረግ ህክምና ነው። የተፈጠረውን ፅንስ በሴቷ ማህፀን ውስጥ ይከተትና እንደ ማንኛውም እርግዝና ፅንሱን ተሸክማ ጊዜው ሲደርስ የምትወልድበት ህክምና ነው።
-የመሀፀን ኪራይ (Serrogacy) ይህ ህክምና በህጋዊ ስምምነት ፅንስ በሌላ ሰው ማህፀን ውስጥ እንዲያድግ ይደረግ እና ከተወለደ በዃላ የልጅ ባለቤት መሆን ማለት ነው።
-እኛ ሀገር ላይ ህክምናው በተወሰኑ የህክምና ቦታዎች ላይ በመሰጠት ላይ ይገኛል።
-ሌላዉ የመጨረሻ አማራጭ በማደጎ ልጅ ማሳደግ (Adoption) ነው።
🍀ጤና ይብዛሎ!🍀
🍀መልካም ጊዜን ተመኘሁ!🍀
ዶ/ር ኤርሚያስ ማሞ እንደጻፈው
🔊📍መልክቱ ከጠቀሞት ለወዳጆዎ ያጋሩ።
👇 ለበለጠ መረጃ
ለማማከርና ለህክምና ብቅ ይበሉ፣ በስልክም ያማክሩን!!
እናት መካከለኛ ክሊኒክ ዱራሜ
ዱራሜ አጠቃላይ ሆስፒታል ፊት ለፊት እንገኛለን
በዶ/ር አብነት አዳነ (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት)
ስልክ፡ 0913295363/ 0926268855
Telegram: https://t.me/+Wm5YIC1zUOMzMjE0
Facebook: https://www.facebook.com/share/1HwhaMdbcY/

24/06/2025
 (Hyperhidrosis)======= # አካል ብቃት እንቅስቃሴ ወይም ሙቀት ጋር ባልተገናኘ ሁኔታ ከመጠን በላይ ላብ ሲከሰት ነው።ጥናቶች እንደሚያሳዩት ዓለም ላይ ወደ 4.8% የሚጠጉ ሰዎች...
24/06/2025

(Hyperhidrosis)
=======
# አካል ብቃት እንቅስቃሴ ወይም ሙቀት ጋር ባልተገናኘ ሁኔታ ከመጠን በላይ ላብ ሲከሰት ነው።
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ዓለም ላይ ወደ 4.8% የሚጠጉ ሰዎች ይህ በሽታ አለባቸው።
hyperhidrosis ሁኔታዎች አሉ።
=====
1. (primary hyperhidrosi) እና
2. (Secondary hyperhidrosi) በመባል ይታወቃሉ።
1. (Secondary hyperhidrosis)
=======
☑️ምንም አይነት ጉልህ በሆነ በሽታ ምክንያት አይከሰትም።
☑️በዘር የመተላለፍ ባህሪ ያለው ነው።
☑️የሚከሰተውም የላብ እጢዎችን የሚቆጣጠሩ ነርቮች በሚኖራቸው ከመጠን በላይ መነቃቃት ምክንያት ነው።
☑️ብዙ ጊዜ የሚከሰተው በሰውነት ሙቀት መጨመር ወይም በማንኛውም የአካል እንቅስቃሴ ምክንያት አይደለም።
☑️በጭንቀት እና በፍርሀት ወቅት ይበልጥ ​​​​ይባባሳል።
2. (Secondary hyperhidrosis)
========
☑️ የሚከሰተው ሥር የሰደደ የጤና ችግር ሲኖር ነው።

☑️ዋና ዋና ምክንያቶችም የሚከተሉት ናቸው.
👉ለብዙ ጊዜ የቆየ የስኳር በሽታ
👉ዝቅተኛ የደም ስኳር መጠን (Hypoglycemia)
👉 በሴቶች የማረጥ ምልክት
👉አንዳንድ የቆዩ ኢንፌክሽኖች(ለምሳሌ ቲቢ)
👉 የሚረጭ የእንቅርት ዕጢ
👉 የልብ ድካም
👉 የነርቭ ሥርዓት መዛባት
#ምልክቶቹ
====
ከመጠን በላይ በላብ መጠመቅ:
☑️በጠንካራ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣
☑️ ፀሀይ ላይ በመንቀሳቀስ ወይም
☑️በጭንቀት ምክንያት ሊሆን ይችላል።
!
=====
☑️
🖊ከመጠን በላይ ላብ የሚሰቃዩ ሰዎች በተሰበሰበበት ወይም በማንኛውም ሌላ ማህበራዊ እድሎች ውስጥ ይሸማቀቃሉ።
☑️
🖊ከመጠን በላይ ላብ ያለው ቆዳ ከተለመደው ቆዳ በበለጠ ለቆዳ ኢንፌክሽን የተጋለጠ ነው።
☑️
🖊ከባድ ላብ ወደ ባክቴሪያ እና ቫይራል የቆዳ ኢንፌክሽን ሊመራ ይችላል።
☑️ (Bromhidrosis)
🖊ረቂቅ ተህዋሲያን ከላብ ጋር በሚገናኙበት ጊዜ ከሰውነት ውስጥ የሚወጣ መጥፎ ሽታ (ብሮምሂድሮሲስ) በመባል ይታወቃል።
🖊ይህ በዋነኝነት የሚከሰተው በብብት ፣ ብልት ፣ ጣቶች እና እግሮች ላይ ነው።
👨‍💻 ።
======
👉ላብ የእለት ተእለት እንቅስቃሴዎን የሚረብሽ ከሆነ።
👉ከመጠን በላይ ላብ በመኖሩ ምክንያት የስሜት መቃወስ እና ማህበራዊ ህይወት ላይ ተፅዕኖ ካሳደረ።
👉ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት የሌሊት ላብ እያጋጠመዎት ከሆነ።
👉ላብ ከሌሎች ምልክቶች ጋር አብሮ ከተከሰተ(ለምሳሌ: ከፍተኛ የሰውነት ሙቀት ፣ ምግብ መቀነሰ ፣ ክብደት መቀነስ....)

=====
ይህ ችግር የሚመጣባቸውን ውስብስብ የጤና ሁኔታዎች ለማወቅ እንደ የደም እና የሽንት ምርመራዎች ያሉ የላብራቶሪ ምርመራዎች ይከናወናሉ።
ለችግሩ መንስኤ የሆነውን ዋናውን ምክንያት መታከም አለበት።
🍀መልካም ጊዜን ተመኘሁ!🍀
🔊📍መልክቱ ከጠቀሞት ለወዳጆዎ ያጋሩ።
👇 ለበለጠ መረጃ
ለማማከርና ለህክምና ብቅ ይበሉ፣ በስልክም ያማክሩን!!
እናት መካከለኛ ክሊኒክ ዱራሜ
ዱራሜ አጠቃላይ ሆስፒታል ፊት ለፊት እንገኛለን
በዶ/ር አብነት አዳነ (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት)
ስልክ፡ 0913295363/ 0926268855
Telegram: https://t.me/+Wm5YIC1zUOMzMjE0
Facebook: https://www.facebook.com/share/1HwhaMdbcY/

👉 ቋቁቻ (Pityriasis versicolor) ምንድነው?ቋቁቻ የተለመደና በፈንገስ አማካኝነት የሚመጣ የቆዳ ህመም ነው👉 ምልክቶቹቋቁቻ በአብዛኛው ጀርባ ፣አንገት፣ደረትና የላይኛው የእጃችን ...
24/06/2025

👉 ቋቁቻ (Pityriasis versicolor) ምንድነው?
ቋቁቻ የተለመደና በፈንገስ አማካኝነት የሚመጣ የቆዳ ህመም ነው
👉 ምልክቶቹ
ቋቁቻ በአብዛኛው ጀርባ ፣አንገት፣ደረትና የላይኛው የእጃችን ክፍል አካባቢ ይወጣል
ጠቆር ያሉ (hyperpigmented) ፣ ነጣ ያሉ (hypopigmented) አንዳንዴም ቀላ ያሉ ክብ ወይም እንቁላል ቅርጽ(oval) ሽፍታዎች ሲኖሩት እነዚህ ሽፍታዎች ላይም ትንንሽ ቅርፊቶች ይታያሉ
ሽፍታዎቹን በጣታችን ስንለጥጠው ወይም ፋቅ ፋቅ ስናረገው ቅርፊቶቹ በደንብ ይጎላሉ
የተለመደ ባይሆንም አንዳንዴ የማሳከክ ስሜት ሊኖር ይችላል
👉 ምን አይነት ሰዎች ላይ ይከሰታል
በአብዛኛው በወጣትነት እና በጎልማሳነት የእድሜ ክልል ውስጥ ይከሰታል
👉 ለቋቁቻ የሚያጋልጡን ሁኔታዎች
- በተፈጥሮ ተጋላጭነት (genetic predisposition) ይህም በቤተሰብ አባላት ውስጥ እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል
- ሞቃታማ አካባቢ መኖር
- የበሽታ የመከላከል አቅም መዳከም
- እርግዝና
- ቆዳችን ወዛም ከሆነ
- Oily የሆኑ ቅባቶችን መጠቀም
- ከመጠን ያለፈ ላብ
👉 ቋቁቻ እንዴት ይታከማል?
ሽፍታው በቆዳ ሐኪም ታይቶ ከተረጋገጠ በኋላ ሐኪሙ በሚያዘው መሰረት በሚቀባ፣ በሻምፖ ወይም በሚዋጥ መድሀኒት ህክምናው ይሰጣል
ከህክምናው በኋላ ሽፍታው ላይ የነበሩት ቅርፊቶች ይጠፋሉ ይህም የህመሙን መዳን ያመለክታል
ነገር ግን ሽፍታው ወጥቶበት የነበረው ቦታ ወደ መደበኛው የቆዳችን ቀለም ለመመለስ ሳምንታትን/ወራትን ሊወስድ ይችላል
👉 ቋቁቻ ከሰው ወደሰው ይተላለፋል?
ቋቁቻ ከሰው ወደሰው አይተላለፍም
ለቋቁቻ መንስኤ የሆኑት የፈንገስ አይነቶች(በጥቅሉ Malassezia ተብለው ይጠራሉ) ከቆዳችን ጋር ተስማምተው የሚኖሩ (normal flora) ሲሆኑ ለህመሙ የሚያጋልጡን ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ወደ በሽታ አምጪነት የሚቀየሩ ናቸው፤ለዚህም ነው ህመሙ ደጋግሞ የሚከሰትብን
👉እንዴት እንከላከለው?
ቋቁቻ ደጋግሞ የሚከሰትብን ከሆነ እና በተለይም በሞቃታማ አካባቢ የምንኖር ከሆነ ከቆዳ ሐኪም ጋር በመመካከር ህክምናውን በሳምንት ወይም በሁለት ሳምንት ወይም በወር አንድ ጊዜ ለተወሰኑ ወራቶች በመውሰድ ቋቁቻ የሚመላላስበትን የጊዜ ፍጥነት መቀነስ ይቻላል
በተጨማሪም፡-
Oily የሆኑ ቅባቶችን አለመጠቀም
ከጥጥ የተሰሩ ልብሶችን መልበስ(በተለይ ከውስጥ የምንለብሳቸው)
ሰውነታችን ላይ የሚጣበቁ ልብሶችን አለማዘውተር
✔️ በመጨረሻም
ከቆዳ ሐኪም ውጪ የተሰሩ ቪድዮችን አይተን ወይም የቆዳ ሐኪም ሳናማክር መድሀኒቶችን ገዝተን ባለመጠቀም ቆዳችንን ከተጨማሪ ጉዳት እንከላከል‼️

ዶ/ር ዮሐንስ ታደሰ ፤ የቆዳና አባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት
🍀መልካም ጊዜን ተመኘሁ!🍀
🔊📍መልክቱ ከጠቀሞት ለወዳጆዎ ያጋሩ።
👇 ለበለጠ መረጃ
ለማማከርና ለህክምና ብቅ ይበሉ፣ በስልክም ያማክሩን!!
እናት መካከለኛ ክሊኒክ ዱራሜ
ዱራሜ አጠቃላይ ሆስፒታል ፊት ለፊት እንገኛለን
በዶ/ር አብነት አዳነ (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት)
ስልክ፡ 0913295363/ 0926268855
Telegram: https://t.me/+Wm5YIC1zUOMzMjE0
Facebook: https://www.facebook.com/share/1HwhaMdbcY/

የማህፀን ሞኝ እጢዎች (Uterine fibroids)በዶ/ር ዳዊት መስፍን፤ የማህፀንና ፅንስ ስኜሻሊስት💥 ትክክለኛ የአማርኛ ትርጓሜ ባይኖራቸውም Uterine fibroids የማህፀን ሞኝ እባጮ...
23/06/2025

የማህፀን ሞኝ እጢዎች (Uterine fibroids)
በዶ/ር ዳዊት መስፍን፤ የማህፀንና ፅንስ ስኜሻሊስት
💥 ትክክለኛ የአማርኛ ትርጓሜ ባይኖራቸውም Uterine fibroids የማህፀን ሞኝ እባጮች/እጢዎች ብንላቸው ካላቸው ባህሪ ጋር ያስኬዳል ብዬ አስባለሁ።
💥 የማህፀን ሞኝ እጢዎች (uterine fibroids) ከማህፀን የመሀከለኛው ክፍል ወይም ከማህፀን ጡንቻ ላይ የሚነሱ እጢዎች ናቸው።
💥 ብዙን ጊዜ እጢ ስንል በጭንቅላታችን የሚመጣው መጥፎና የካንሰርነት ባህርይ ያለው ነገር ቢሆንም እነኚህ uterine fibroids ወይም የማህፀን ሞኝ እባጮች ግን የካንሰርነት ባህሪ የሌላቸው እና ወደ ካንሰር የመቀየር እድላቸውም እጅግ በጣም አናሳ እና ጥናቶችም እንደሚያሳዩት በዚህ እጢ ከታከሙ 580 ሴቶች አንዷ ብቻ ይህ እጢ ወደ ካንሰር ሊቀየርባት እንደሚችል ያሳያሉ።
💥 የማህፀን ሞኝ እጢዎች (uterine fibroids) አንዲት ሴት በመውለጃ ዘመኗ ላይ የሚከሰቱ የእጢ አይነቶች ሲሆኑ በተለይ ደግሞ ከ 30 እስከ 40 አመት እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሴቶች ላይ አብዝተው ይከሰታሉ።
💥 እነኚህ እጢዎች ብዙን ጊዜ የህመም ስሜት ስለሌላቸው ነው እንጂ እስከ 70% የሚሆኑ ሴቶች ይህ እጢ በማህፀናቸው ላይ አለ ተብሎ ይታሰባል።
👉❓❓ይህ እጢ ለምን ይከሰታል❓❓
የማህፀን ሞኝ እጢዎች (uterine fibroids) ለምን እንደሚከሰቱ እርግጥ የሆነ ጥናት ባይኖርም መላምቶቹ ግን የሚያሳዩት በማህፀን ጡንቻ ውስጥ የሚገኙ የዘረመል ችግር ያለባቸው የጡንቻ ህዋሶች Estrogen የተሰኘው ንጥረ ነገር(hormone) ሲነካቸው ከቁጥጥር ውጪ በሆነ መንገድ ስለሚራቡ እና ወደ እጢነት ስለሚያድጉ ነው።
👉❓የዚህ እጢ ምልክቶች ምንድን ናቸው❓
💥 ባብዛኛው ጊዜ ምንም አይነት ምልክት የሌላቸው ሲሆን ለሌላ ህመም በሚደረግ የአልትራሳውንድ ምርመራ እንደ ድንገት ሊገኙ የሚችሉ እጢዎች ናቸው። ነገር ግን ከዛ ባለፈ ህመሙ የሚሰማቸው ሴቶች የሚከተሉትን ምልክቶች ሊያሳዩ ይችላሉ:-
🔑 የወር አበባ ለውጥ
📌 የወር አበባ መብዛት እና መቆየት ካለበት ጊዜ በላይ አሳልፎ ከቆየ
📌 የወር አበባ ህመም
📌 የደም ማነስ ምልክት:- ብዙ ደም ከመፍሰስ የመጣ
🔑 የወገብ ህመም እና ከእንብርት በታች የህመም ስሜት፣ በተለይ በግንኙነት ጊዜ ሊብስ የሚችል
🔑 ሽንት እንቢ ማለት ወይም ቶሎ ቶሎ ማለት
🔑 የሰገራ ድርቀት፣ እና የሆድ ህመም
🔑 በሆድ ላይ ቀስ ብሎ እየጨመረ የሚሄድ እብጠት ማስተዋል
🔑 በተደጋጋሚ ውርጃ መከሰት
🔑 እርግዝና እንዳይፈጠር መከልከል
👉❓እነኚህ እባጮች/እጢዎች መቼ ነው ህክምና የሚያስፈልጋቸው❓
💥 ብዙን ጊዜ ምንም አይነት ህመም ከሌላቸው በጊዜ ሂደት አንዲት ሴት ስታርጥ ወይም የወር አበባ ማየት ባቆመች ጊዜ መጠናቸው እየኮመሸሸ እና እያነሰ ስለሚመጣ በመድሀኒትም ሆነ በቀዶ ህክምና መታከም አያስፈልጋቸውም፤ ነገር ግን አንዲት ሴት :-
💥 በእጢው ምክንያት የመጣ የወር አበባ መዛባት ፣ በብዛት ካለ እና ደም ማነስ ካመጣባት
💥 ከፍተኛ የሆነ ህመም ካላት (ከእጢው ጋር የተገናኘ)
💥 እጅግ መጠኑ የበዛ እጢ ከሆነ
💥 እርግዝና ከከለከላት ወይም ደግሞ እርግዝና ተከስቶ ለውርጃ እንደምክንያት ከሆነ (ሌሎች እርግዝና የሚከለክሉ ወይም ውርጃን የሚያመጡ ነገሮች ሁሉ ከተጣሩ በውሀላ)
👉❓ሊሰጡ የሚችሉ ህክምናዎች❓
📌 የመድሀኒት ህክምና:- ይህ ህክምና የሚፈሰውን የደም መጠን ለመቆጣጠር የሚሰጥ ህክምና ነው።
📌 ኦፕሬሽን :- ይህ እጢውን በኦፕሬሽን የማውጣት ህክምና ሲሆን ፤ በተጨማሪ ግን የተለያዩ የኦፔሬሽ አይነቶችም ሊኖሩ ይችላሉ (በኛ ሀገር የማይሰሩም አሉ)
📌 ማህፀንን እስከነ እጢው ማውጣት:- ይህ ኦፕሬሽን ሴቲቱ ወልዳ የጨረሰች ከሆነች ወይም ደግሞ እጢውን ለማውጣት በሚደረግ ኦፕሬሽን ጊዜ ከፍተኛ ደም መፍሰስ ካለ ማህፀን ማውጣት የሴቲቱን ህይወት የሚያተርፍ አንዳች አማራጭ ሆኖ ሲገኝ የሚደረግ የኦፕሬሽን አይነት ነው።
🍀መልካም ጊዜን ተመኘሁ!🍀
🔊📍መልክቱ ከጠቀሞት ለወዳጆዎ ያጋሩ።
👇 ለበለጠ መረጃ
ለማማከርና ለህክምና ብቅ ይበሉ፣ በስልክም ያማክሩን!!
እናት መካከለኛ ክሊኒክ ዱራሜ
ዱራሜ አጠቃላይ ሆስፒታል ፊት ለፊት እንገኛለን
በዶ/ር አብነት አዳነ (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት)
ስልክ፡ 0913295363/ 0926268855
Telegram: https://t.me/+Wm5YIC1zUOMzMjE0
Facebook: https://www.facebook.com/share/1HwhaMdbcY/

22/06/2025
በእናት መካከለኛ ክሊኒክ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ያውቃሉ?የሚከተሉትን አገልግሎቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በሙያው አንቱታን ባተረፉ ባለሙያዎች ጋር እንደምንሰጥ ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው!!የHorm...
28/05/2024

በእናት መካከለኛ ክሊኒክ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ያውቃሉ?
የሚከተሉትን አገልግሎቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በሙያው አንቱታን ባተረፉ ባለሙያዎች ጋር እንደምንሰጥ ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው!!
የHormone ምርመራ
1. Serum Ɓ HCG
2. HbA1C
3. FSH
4. LH
5. Prolactin
6. TSH
7. T3
8. T4
9. CRP
ሌሎች ምርመራዎች
● Pathology services
● Dermatology services
●የመካንነት ምርመራና ህክምና /Infertility services
●የወንድ ልጅ ግርዛት /male circumcision
● Renal Function panel
● Liver Function panel እና ሌሎችንም ምርመራና ህክምና ያገኛሉ!!
እናት መካከለኛ ክሊኒክ
ዱራሜ ሆስፒታል ፊት ለፊት እንገኛለን
ለበለጠ መረጃ
0913295363 ይደውሉልን!!

Address

Durame

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when እናት መካከለኛ ክሊኒክ / Enat Medium Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to እናት መካከለኛ ክሊኒክ / Enat Medium Clinic:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram