Gondar Ayira General Hospital ጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል

  • Home
  • Ethiopia
  • Gondar
  • Gondar Ayira General Hospital ጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል

Gondar Ayira General Hospital ጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል አላማችን ህሙማን መርዳት ነዉ!!!

የጎንደር  አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል እና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በሁሉም አይነት  ህክምና ዙሪያ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ*የጎንደር  አይራ ጠቅላላ ሆስፒታ...
20/02/2026

የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል እና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በሁሉም አይነት ህክምና ዙሪያ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ
*
የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል እና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በጠቅላላ ቀዶ ጥገና ፣በአጥንት ስብራት ህክምና ፣በማህፀንና ፅንስ ፣ በህፃናት እና በሌሎች የህክምና ዘርፎች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የጋራ ስምምነት ዛሬ የካቲት 13/2018 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንንት ጽ/ቤት ተፈራርመዋል።

በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ገ/ዮሀንስ የሺነህ ፣ የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ሳሙኤል አጥቃቸዉ፣ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ጤና ምሪያ ሀላፊና የሆስፒታላችን የቦርድ አመራር አቶ ሰዒድ የሻዉ እና የሆስፒታል የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አስራት አፀደወይን፣የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ጌታው ብርሀን፣ የሆስፒታሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው በስምምነት ሰነዱ ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

ስምምነቱ በተለይ የቀዶ ጥገና (Back Log) ቁጥሩ ከፍተኛ ሲሆን ቀጠሮ ተሰጥቷቸው ለረጅም ጊዜ በወረፋ ላይ የሚገኙ ታካሚዎችን ምልልስ በመቀነስ፣ ፈጣን የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻል ሲሆን፣ በተለይ ለበርካታ ወራት የቀዶ ጥገና ህክምናዎችን የሚጠብቁ ታካሚዎችን ቁጥር ሆስፒታላችንን በመጠቀም በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ ታካሚወች ወረፋ ከመጠበቅ ይልቅ ቶሎ ህክምና እንዲያገኙ ያለመ ስለመሆኑ በመርሀ- ግብሩ ተገልጿል። በተጨማሪም ታካሚዎች በህመማቸው ላይ ተጨማሪ እንግልትና የኢኮኖሚ ጫና ሳይደርስባቸው ጥራት ያለው ህክምና እንዲያገኙ ለማድረግ የሚያሰችል መሆኑ በስምምነቱ ተጠቅሷል።

ሁለቱ ሆስፒታሎች ከዚህ ቀደምም በሰው ኃይል እና በህክምና ቁሳቁስ ግብዓቶች ላይ የመዋዋስና የመረዳዳት ስራዎችን ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን፣ የዛሬው ስምምነት ይህንን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግርና ህጋዊ ማዕቀፍ የያዘ እንደሆነ ከቀረበው ገለፃ ለመረዳት ተችሏል።

የታካሚዎችን እርካታ ይበልጥ ለማሳደግ ከሁለቱ ሆስፒታሎች ስምምነት ጎን ለጎን ጤና ጣቢያዎችን የመደገፍ፣የማብቃትና የማጠናከር ስራዎች እንደሚሰሩ ተጠቁሟል። ይህም ህብረተሰቡ በአቅራቢያው በሚገኙ የጤና ተቋማት ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል ተብሏል።

የሆስፒታሉ ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 13/2018 ዓ. ም

18/01/2026

የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ገ/ዮሐንስ የሽነህ ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ጎንደር ፤ ጥር 10/2018 ዓ/ም የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ገ/ዮሐንስ የከተራ እና የጥምቀት በዓላትን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አቶ ገ/ዮሐንስ በመልዕክታቸው ውድ የተቋማችን የክርስትና እምነት ተከታዮች፤ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል ።

የጥምቀት በዓል በታላቅ ድምቀትና መንፈሳዊ ስነስርዓት ከሚከበሩ ታላላቅ በዓላት አንዱ ነው። ይህ በዓል የትህትና፣ የፍቅርና የወንድማማችነት ተምሳሌት ነው።

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መሄዱ ታላቅ ትህትናን የሚያስተምር ሲሆን፤ እኛም በሥራችንና በማህበራዊ ህይወታችን በአገልግሎታችን ለአብሮነት ዝቅ ብለን ማገልገል እንዳለብን ትልቅ ትምህርት የምንወስድበት ነው ሲሉ ተናገረዋል።

የተከበራችሁ የሆስፒታላችን ባልደረቦች ፤የጥምቀት በዓል ከሃይማኖታዊ ፋይዳው ባሻገር፣ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት ጠብቀን ያቆየነውና በዓለም አቀፉ የዩኔስኮ ቅርስነት የተመዘገበ ታላቅ ብሔራዊ ሀብታችን ነው ብለዋል።

ይህ በዓል በተለይም በከተማችን በሚከበርበት ወቅት የህዝባችንን አንድነት፣ እንግዳ ተቀባይነትና ውብ ባህላችንን ለዓለም የምናሳይበት አጋጣሚ ነው።

የጥምቀት በዓል የሰላም፣ የፍቅርና የምሕረት በዓል ነው። ይህ በዓል በየዓመቱ በሚከበርበት ወቅት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ወደ አደባባይ የሚወጣበትና በጋራ የሚቆምበት በመሆኑ፣ የሕዝባችንን ጤንነት መጠበቅ ቀዳሚ ተግባራችን ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

በዓሉ በሰላም ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ በተቋማችን ለሚመጡ ታካሚወቻችን የተለመደዉን የህክምና አገልግሎት ከመስጠት ጎን ለጎን ድንገተኛ የጤና አክል ቢገጥም ሁሉም ባለሙያ የተለመደዉን እርብርብ እና ቲም አስፕሪት በመጠቀም አገልግሎት እንድንሰጥ እና ከዚህም ጎን ለጎን ተቋሙን ለመጎብኘት የሚመጡ እንግዶቻችን ካሉ ሁሉም የተቋሙ ባልደረባ የተሰሩ ስራወችን የማስተዋወቅ ሀላፊነቱን እንዲወጣ አደራ ብለዋል፡፡

በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የብልጽግና እና የአንድነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

#መልካም በዓል!
"የሆስፒታሉ ህዝብ ግንኙነት"

ቀን 16/04/2018ዓ/ም በዛሬዉ እለት በሆስፒታላችን በክልል ደረጃ ሁሉንም አቀፍ ድጋፍ  በተደረገዉ መሠረት በፕላን ኦፊሰር  Action plan ወጥቶሰፋ ያለ  ዉይይት ተደርጎባቸዋል።ክፍቶ...
25/12/2025

ቀን 16/04/2018ዓ/ም
በዛሬዉ እለት በሆስፒታላችን በክልል ደረጃ ሁሉንም አቀፍ ድጋፍ በተደረገዉ መሠረት በፕላን ኦፊሰር Action plan ወጥቶሰፋ ያለ ዉይይት ተደርጎባቸዋል።

ክፍቶችም ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል

በክፈተት የታዩ ( መስተካከል ያለባቸዉ)

1.ሆስፒታሉ ላይ የፀዳት ችግር መኖሩና 2.ለአገልግሎት እንቅፋት መሆኑ( ከበሩ ጀምሮ እስከ ወስጥ ድረስ የተጋነነ የጸዳት ችግር መኖሩ) ይህ ደግሞ ለታሚዎች ሌላ የጤና እክል ሊፈጥር እሚችል ስጋት መሆኑ
3.በሪፎርም ትግበራ ላይ ሁሉም ሰዉ እኩል ግንዛቤ ያለመኖሩ
4.የሆስፒታሉ እቅድ አስከታች ለሰራተኛዉ ያለመዉረዱና የስራ ክፍል አስተባባሪዎች አቅዱ በትክክል ለሰራተኛዉ ከማድረስ በኩል ዝቅተኛ አፈጻጸም መኖሩ(የግለሰብ እቅድ ለሁለም ሰራተኛ ያለማዉረድ ችግር)
5.ዲጅታላይዚሽን( ወረቀት አልባ) አገልግሎት ያለመጀመሩ
6.የታካሚ አልጋዎች አንሶላና ብርድልብስ አልባ መሆናቸዉ ይህ ደግሞ ለታከሚዎች ለተጨማሪ የበሽታ አይነት ለመጋለጥ ስጋት መሆኑ
7.የላዉንደሪና የምግብ ማብሰያ ማስኖች እርክክብ ያለመደረጉና ይህ ድግሞ አገልግሎቱን ሙሉ በመሉ ለመስጠት እንቅፋት መሆኑ
8.አዳዲስ የሆስፒታሉ እኒሸቲቦች(ሪፎርሞች)በእቅድ ያለመካተታቸዉ ዝቅተኛ አፈጻጸም ያላቸዉ መሆኑ
9.ዝቅተኛ የሆነ የላብላቶሪ ምርመራ አይነት መኖራቸዉ
10.ከፈተኛ የሆነ የባለሙያ እጥረት መከሰቱ ይህ ደግሞ የሆሰፒታሉን ስታዳርድ ለመፈጸም ትገዳሮት መሆኑ( የፈርማሲ ባለሙያ፤ጠቅላላ ሃኪም፤ነርስና ላብላቶሪ ባለሙያ)
11.የስራ ከፍል አስተባበሪዎች ለስራተኛዉ የግል እቅድ ያለመስጠታቸዉና ስራን እንደክፍል እየገመገሙ የድረጊት መራሃ ግብር ያለመዘጋጀታቸዉ
12.ካርድ ክፍል በር ያለመዘጋጀቱ ማለትም ክፍት መሆኑ ለካርዶች መጥፋት ስጋት መሆኑና ለህገመክ ካርዶች መጥፋት ስጋት መፈጠሩ
13.EHSIG, pt. seafty SBFR GGI ክሊኒካል ኦዲት ዝቅተኛ አፈጻጸም መኖራቸዉና ስራዉን የድርጊት መራሃግብር እያወጡ ያለመገምገም ችግር.
14.ወራሃዊ ሪፖረት ከተገመገመ በኃላ በተሰጠዉ ግብር መልስ መሰረት የስራ ክፍሎች የማስፈጸሚያ የድጊት መራሃ ግብር ያለማዉጣት ችግር
15.የተጠናከር DTC ያለመኖርና ጌዜዉን የጠበቀ ስብስባ ያለማድረግ ችግር
የመዳሀኒት ፤የስሪቨስ ክፍያ ኦዴቶችን ያለመስራት ችግር ተጠያቂነት አለማስፈን
ተቆራረጦ ያለመስራት ችግር
16.ሶሻል ኢንሹራንስ ስራተኛን ሙሉ በሙሉ ያለማስገባት ምዘገባዉን በተቀመጠዉ ግዜ ዉስጥ ያለመጨረስ
17.ሰራተኛዉን የማበረታታ ስራዓት ያለመዘርጋትና የስራ ክፈሎችን በስራቸዉ በየወሩ ያለማወዳደር ችግር
18. የሶሻል ስርቨስ አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ ስራ ያለመስጀመር
19.የህክምና እቃ እጥረት ለምሳሌ የኦርቶ ማተሪያል ጉድለት ይህ ደግሞ ያለዉን የሰዉ ሃይል ለመጠቀም ችግር መሆኑ
20.የዶፕለር አልትረሳዉንድ ያለመኖር ይህ ደግሞ የኢሚጅግ አገልግሎቱን ሙሉ እንዳይሆን ምክኒያት መሆኑ
21.የፈርኒቸር እጥረት( የታካሚ ወንበር፤ሽልፍ፤ድረቅ ወንበር)
ስለዚህ እያንዳንዱ የሆስፒታሉ ማህበረሰብ ፈፃሚ እንዲሆን የተቋሙ ስራ አስኪያጅ መልክታቸዉን አስተላልፈዋልበማስቀጠል ክፍተቶቻችን ላይ በመስራት ለዉጥ ለማምጣት ሁሉም ሰራተኛ እንዲተጋ አደራ በማለት የደገፉንን አካላት በተቋሙ ስም ምስጋና በማቅረብ ዉይይቱ ተቋጭቷል።

''የሆስፒታሉ ህዝብ ግንኙነት

ቀን 14/04/2018ዓ/ም በዛሬዉ እለት በሆስፒታላችን Good Governace Index በተመለከተ ዉይይት ተደረገ ከMinistry of health የመጡ ባለሙያወች ሁሉንም የስራ ክፍል አካታ...
24/12/2025

ቀን 14/04/2018ዓ/ም
በዛሬዉ እለት በሆስፒታላችን Good Governace Index በተመለከተ ዉይይት ተደረገ
ከMinistry of health የመጡ ባለሙያወች ሁሉንም የስራ ክፍል አካታች በሆነ መልኩ ሰፊ ድጋፎ አድርገዋል ::
ከድጋፍ በኋላም ሁሉም አስተባባሪወች እና Mgt በተገኙበት የተቋሙን ነባራዊ እና አሁናዊ ሁኔታ በሰፊዉ የተመለከተ ድጋፋዊ ሪፖርት በደጋፊዎች የቀረበ ሲሆን በጥንካሬ እና በክፍተት ተለይተዉ ከቀረቡ በኋላ በሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ገ/ዮሀንስ የሺነህ እና ከአብክመ ጤና ቢሮ ለድጋፍ በመጣዉ የፈዉስ ህክምና ተህድሶ ዳይሬክተር ወንድማችን አቶ ድንበሩ በአወያይነት የሀሳብ ልዉዉጥ ተደርጎ ጥንካሪያችን በማስቀጠል ክፍተቶቻችን ላይ በመስራት ለዉጥ ለማምጣት ሁሉም ሰራተኛ እንዲተጋ አደራ በማለት የደገፉንን አካላት በተቋሙ ስም ምስጋና በማቅረብ ዉይይቱ ተቋጭቷል።


''የሆስፒታሉ ህዝብ ግንኙነት''

"ትዉልድን በስነ ምግባር ተቋምን በአሰራር እንገንባ"    በሚል መሪ ቃል የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል  በአለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛ ጊዜ በአገራችን ለ21ኛ ጊዜ  የፀረ ሙስና ቀን በድም...
05/12/2025

"ትዉልድን በስነ ምግባር ተቋምን በአሰራር እንገንባ"

በሚል መሪ ቃል የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛ ጊዜ በአገራችን ለ21ኛ ጊዜ የፀረ ሙስና ቀን በድምቀት ተከበረ።

ህዳር 26/2018 ዓ.ም (የሆስፒታሉ ህዝብ ግንኙነት)

ሙስና በመንግስትና በህዝብ የተሰጠን ስልጣንና ኃላፊነትን ለግል ጥቅም ያለአግባብ መገልገል ነዉ።

ሙስና የስነ ምግባር ዝግጠት ሁኖ ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ሃብትና ንብረትን ከህዝብ ጉሮሮ መንጠቅ ማለት ነዉ።

በጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል በአለም አቀፍ ለ22ኛ ጊዜ በአገራችን ለ21ኛ ጊዜ "ትዉልድን በስነ ምግባር ተቋምን በአሰራር "በሚል መሪ ቃል የፀረ ሙስና ቀን በሆስፒታሉ ጠቅላላ የመንግስት ሰራተኛዉ በተገኙበት መድረክ በሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ገ/ዮሐንስ የሺነህ በመድረኩ ተገኝተዉ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት እንደአገር ክልል እየገጠመን ያለዉ አንዱ ፈታኝ ጉዳይ ሙስናና ብልሹ አሰራር መሆኑን ጠቁመዉ ሙስናን የሚፀየፍ የሚታገል ዜጋ መፍጠር እንደሚያስልግና የሚያመጣዉን ሁሉን አቀፍ አገራዊ ጉዳት በመረዳት ሁሉም ዜጋ ሙስናን መታገል ይገባል በማለት መድረኩን በይፋ ከፍተዋል።

የሆስፒታሉ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና መኮንን አቶ ቢሰጥ መለሰ የመወያያ ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት ከችግሩን አሳሳቢነት በመነሳት ስለሙስናና ብሉሹ አሰራርን ሁሉም የሆስፒታሉ ማህበረሰብ አካል ሊያወግዘዉና ከዚህ ድርጊት የተቆጠበ ዜጋ መፍጠር ለነገ የማይባል ስራ ነዉ ብለዋል።

ከቀረበዉ የመወያያ ሰነድ በመነሳት ከመድረኩ ታዳሚዎች ጥያቄዎች ሃሳብና አስተያየቶች ተሰንዝረዉ ሰፊ ዉይይት ተደርጎባቸዉ የጋራ ግንዛቤ ተይዟል።

አቶ ገ/ዮሐንስ በተጨማሪም እንዳብራሩት ለሙስናና ብልሹ አሰራር የችግሩም ባለቤትና የመፍትሄዉም አካል እኛዉ ነን ብለዉ ሙስና በሁሉም ዘርፍ የሚያመጣዉ ጉዳት የከፋ መሆኑን ሁሉም ዜጋ በመረዳት መታገልና ማስወገድ ይገባል በማለት ስለጉዳዩ አስከፊነት ሰፊ ትንታኔና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

እንደ ሆስፒታል ተጨባጭ ሁኔታ በተቋማችን በኩል የሚስተዋሉ የአሰራር ጉድለቶችን ከሰዉ ሀይል አያያዝና አስተዳደር አኳያ ፣ ከግዥ እና ስርዓት አኳያ፣ ከአሉባልተኛነት፣ የሆስፒታሉን መድሀኒቶች እና መሳሪያወች ከመጠቀም አኳያ ያሉ ክፍተቶችን በዘላቂነት ለማረም እና ከእጅ መንሻ የተላቀቀ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ዘመናዊ አሰራር ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ያስፈልጋል።

የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ገ/ዮሀንስ የሺነህ እና የሆስፒታሉ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና መኮነን አቶ ቢሰጥ መለሰ ከመድረኩ ለተነሱ ሃሳብና አስተያየቶች ምላሽ በሰጡበት ወቅት ስለሙስና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መቀዛቀዞች እንደነበሩ አንስተዉ አሁን ላይ በአገር አቀፍ ደረጃ ቀኑ እንዲከበር መደረጉ ጠቃሚ እንደሆነ እና የመንግስት ሰራተኛዉ ብልሹ አሰራሮች ለአገር እድገትና የሰላም ፀር መሆኑን በመታገልና ኃላፊነት ወስዶ ለማህበረሰባችን ፍትሀዊ በሆነ መልኩ እኩል ተጠቃሚነትን መሰረት አድርገን ሊሰራ ይገባል።

ሙስና እና ብልሹ አሰራር ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ያዛባል፤ የሀገር ልማትና እድገትን ይገታል። የዘላቂ ልማትና እድገት ተግዳሮት የሆነውን ብልሹ አሰራር በጋራ መከላከል ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም በማለት አብራርተዋል።
ትዉልድን በታነፀ ስነ ምግባር ተቋምን የሚለዉጥ አሰራር፣ የሙስና ስር መሰረቱ የስነ ምግባር ጉድለት ነዉ፣ራስን ማነፅ ተቋምን ማደስ፣በስነ ምግባር የተገነባ ትዉልድ ሙስናን ለመታገል የላቀ ኃይል ይኖረዋል የሚሉ መልእክቶች በመድረኩ ተነስቷል::

ሆስፒታላችን የህክምና ግብዓቶች ድጋፍ አገኘ፦መስከረም-29/2018ዓ.ም.የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ለተለያዩ የህክምና አገልግሎቶች የሚውሉ የተለያዩ የህክምና ግብዓቶች  ከጎንደር ዩኒቨር...
09/10/2025

ሆስፒታላችን የህክምና ግብዓቶች ድጋፍ አገኘ፦

መስከረም-29/2018ዓ.ም.

የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ለተለያዩ የህክምና አገልግሎቶች የሚውሉ የተለያዩ የህክምና ግብዓቶች ከጎንደር ዩኒቨርስቲ ኮምፕርሄሲቨ ሆስፒታል በድጋፍ አገኘ ፤ የተገኙት የህክምና ቁሳቁሶች ሆስፒታላችን ለሚሰጠው የህክምና አገልግሎት ጥራት ለማስጠበቅ እጅግ ወሳኝ ናቸው። በድጋፍ የተገኙት ግብዓቶች በገንዘብ ሲተመኑ ከ 5,000,000 ብር ከአምስት ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ሲሆኑ
11.Basin bowel wash #20
2.Bubble Humidifier #02
3.Pressure Regulator #02
4.instrument Tray #01
5.oxygen cylinder 50 liter #10
6.oxygen cylinder 40 liter #02
7.crile retractor #25
8.Bladder retractor #10
9.POP cutter Electrical #04
10.OR Light which is digital containing camera #04
11Portable oxygen cylinder 13 litter #01
ናቸው።
በመጨረሻም አንጋፋው የጎንደር ዩኒቨርስቲ ሆስፒታላችን ለተደረገልን ድጋፍ ልባዊ ምስጋና እያቀረብን ፤ ተግባሩን በማስተባበር ፣ በማስጨረስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለነበራቸው የሆስፒታሉ ስራ አስኪሂያጅ አቶ ገ/ዩሐንስ የሽነህ
ለተቋማችን ሹፌሮች ጌትነት ሀይሌ,ጌታቸዉ አለባቸዉ እና ለግርማ ምስጋናችን የላቀ ነው በርቱ ተበራቱ ማለት እንፈልጋለን።

'' ጥራት እና ፍትሃዊነት ያለው አገልግሎት ለደንበኞቻችን''

የአይራ ሆስፒታል ህዝብ ግንኙነት ክፍል

19/09/2025

ለመላው ኢ/ያን በሙሉ እንኳን ለ2018 ዓም የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም፣ በጤና፣ በፍቅር ፣ በአንድነት አደረሳቹህ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል አዲሱ ዓመት የሰላም ፣ የጤና እና የመተሳሰብ እንዲሆንላቹህ የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል መልካም ምኞቱን ይገልፃል፦ ሆስፒታላችን ወደ ስራ ከገባ ሁለት ዓመት የሆነው ሲሆን ለማህበረሰቡ የህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። አገልግሎቱንም በማሻሻል
1.ሁሉንም የእድሜ ክልል ያማከለ የተመላላሽ ህክምና አገልግሎት
2.የሁሉንም አይነት የተኝቶ ህክምና አገልግሎት
3.ቀላልና ከባድ ጠቅላላ የቀዶ ህክምና አገልግሎት በእስፔሻሊስት ሀኪሞች
4.የነብሰ ጡር እናቶች ቀዶ ህክምና አገልግሎት በእስፔሻሊስት ሀኪሞች
5.የ24 ሰዓት የማወለድ አገልገሎት
6.የነብሰ ጡር ክትትል እና የአልትራሳዉንድ አገልግሎት
7.የህጻናት ህክምና አገልግሎት በእስፔሻሊስት ሀኪሞች
8.የአልትራሳዉድና የራጅ አገልግሎት
9.የ24 ሰዓት የድንገተኛ ህክምና አገልገሎት
10.የ24 ሰዓት የፋርማሲ እና ላቦራቶሪ አገልገሎት
11.የውስጥ ደዌ ህክምናው እና ክትትል አገልገሎት በእስፔሻሊስት ሀኪሞች
12.የአጥንት ስብራት እና ተያያዥ ጉዳዮች ህክምና እና ክትትል አገልገሎት በእስፔሻሊስት ሀኪሞች
13.የአይንና ስነ አእምሮ ህክምና አገልገሎት
14.የቤተሰብ ምጣኔ
15.የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ልየታ አገልገሎት ከ2000,000 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎቱን እየሰጠ ሲሆን ሆስፒታላችን ከከተማው ማህበረሰብ በተጨማሪ ከአጎራባች ወረዳወች ለሚመጡ ታካሚዎቻችን አገግሎቱን በማሻሻል የሪፈራልና የጤና መድን አገልግሎት የጀመርን ሲሆን ከየትኛዉም የ አገሪቱ ክፍል መጣችሁበ መገልገል እንደምትችሉ ስናበስር በታላቅ ደስታ ነዉ።

አድራሻችን በጎንደር ከተማ አዘዞ ጠዳ ክፍለ ከተማ አይራ ቀበሌ ነዉ

መልካም አዲስ አመት

የሆስፒታሉ ህዝብ ግንኙነት

Address

Gondar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gondar Ayira General Hospital ጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category