Federal police Harar General Hospital

  • Home
  • Federal police Harar General Hospital

Federal police Harar General Hospital ይህ የፌደራል ፖሊስ ሐረር ጠቅላላ ሆስፒታል ገፅ ነው።

የመድሃኒት ፈንድ አቅርቦት ኤጀንሲ አዲስ የኢንቬንተሪ ሲስተም ተግባራዊ አደረገ፡፡ሲስተሙ በተለይም የጤና ተቓማት ያለምንም  ድካም እና እንግልት በኢንተርኔት አማካኝነት በቀጥታ በመግባት  በፈ...
29/09/2018

የመድሃኒት ፈንድ አቅርቦት ኤጀንሲ አዲስ የኢንቬንተሪ ሲስተም ተግባራዊ አደረገ፡፡
ሲስተሙ በተለይም የጤና ተቓማት ያለምንም ድካም እና እንግልት በኢንተርኔት አማካኝነት በቀጥታ በመግባት በፈለጉት ቅርንጫፍ የሚፈልጉትን መድሃኒት ወይም እቃ መኖሩን እና አለመኖሩን ማረጋገጥ ያስችላል፡፡

BID
12/06/2017

BID

ድሉ የእኛ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካም ጭምር ነው!CongratulationDr. Tedros Adhanom Director-General, World HealthOrganization (WHO)ዶክተር ቴድሮስ ...
23/05/2017

ድሉ የእኛ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካም ጭምር ነው!
Congratulation
Dr. Tedros Adhanom Director-General, World Health
Organization (WHO)
ዶክተር ቴድሮስ አድሓኖም የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነትን አሸነፉ
መላው የኢትዮጵያ የሀገራችን ህዝቦች እንኳን ደስ ያላችሁ እንኳን ድስ
ያለን።

Cirvical CA
14/05/2017

Cirvical CA

የማህፀን በር kanesre(cervical cancer)
ማንኛውም ግብረ ስጋ ፈፅማ የምታውቅ
ሴት ለማህፀን በር የቅድመ ካንሰር
መንስዔ ለሆነው በሂውማን
ፓፒሎማቫይረስ ኢንፌኪሽን የመጋለጥ
ዕድል አላት፡፡ ከ30-45 ዕድሜ ክልል
ውስጥ ያሉ ሴቶች የማህፀን በር ቅድመ
ካንሰር ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራል
የሚለው ፓዝ ፋይንደር ኢንተርናሽናል
ኢትዮጵያ ነው፡፡ የማህፀን ካንሰር
በአብዛኛው የ “ሂውማን ፓፒሎማቫይረስ
ኢንፌክሽን” ለረጅም ጊዜ በሰውነት
ውስጥ በመቆየት በሚያደርገው ሂደት
የሚከሰት ነው፡፡ ምናልባት አንዲት ሴት በግብረ ስጋ ግንኙነት
ጊዜ በሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ ቫይረሱን ብታገኘው እስከ
ቅድመ ካንሰር ምልክት ለመድረስ ቢያንስ በአማካኝ ከ10-15
ዓመታት ይፈጃል፡፡ በ15 ዓመቷ የግብረ ስጋ ግንኙነት ብትጀምር
እስከ 30 እና 35 ዕድሜዋ ድረስ ላይታወቅ ይችላል፡፡ የቅድመ
ካንሰር ምልክት በሰውነቷ አንድ ጊዜ ከታየ በማህፀን በር ላይ
ከተከሰተ በኋላ ቅድመ ካንሰሩ ወደ ካንሰር ለመለወጥ ከ10-15
ዓመት ይፈጃል፡፡ ስለዚህ የካንሰርን ሁኔታ በምናይበት ጊዜ
በቫይረሱ አማካኝነት ተለውጦ በማህፀን ውስጥ የማህፀን
ክፍሎች ላይ ለውጥ አምጥቶ፣ ቫይረሱ የማህፀን ግድግዳ
ክፍሎችን በመበከል ወደ ቁስለት፤ ያ ቁስል ደግሞ ከማህፀን
ባሻገር ወደ ደም በመግባት ወደ ሰውነት ውስጥ መተላለፍ
የሚችልበት ነው፡፡በአሁኑ ወቅት ገዳይ ከሆኑት የሴቶች
በሽታዎች ውስጥ የማህፀንና ጡት ካንሰር የመጀመሪያዎቹን
ደረጃዎች ይይዛሉ፡፡ ቀደም ሲል የማህፀን ካንሰር የሀብታሞችና
በኢኮኖሚ የዳበሩ አገሮች ብቻ ችግር ተደርጎ ይታይ ነበር፡፡
ትልቁ ችግር የነበረው ይሄንን በሽታ ለማወቅ የሚቻልበት
መንገድ ውስን ከመሆኑ የተነሳ ሰዎች እየታመሙ ይሞቱ ነበር፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከአሜሪካ መንግስት በሽታ መከላከልና
መቆጣጠሪያ(CDC) በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የማህፀን ካንሰር
መከላከል ፕሮግራም የጀመረ ሲሆን ፓዝ ፋይንደር
ኢንተርናሽናል ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ ከሌሎች ድርጅቶችና
ክልሎች ጋር በመሆን ይሄንን ፕሮግራም ጀምረዋል፡፡ ፕሮግራሙ
በመጀመሪያ ደረጃ በተመረጡ 14 ሆስፒታሎች ላይ በተለይም
ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ሴቶችን ከካንሰር
ለመጠበቅ የመከላከል ሥራ የሚሰራ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም
ማንኛውም ሴት ይህንኑ ምርመራ ለማድረግ እንድትችል
ያደርጋታል፡፡ ዶ/ር መንግስቱ አስናቀ የፓዝፋይንደር
ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ፕሮግራም ተጠሪ እና የተቀናጀ
የቤተሰብ የጤና ፕሮግራም ዳይሬክተር ስለጉዳዩ ማብራሪያ
ሰጥተዋል፡፡
ህክምናው እንዴት ይሰጣል? በማህፀን በር ላይ የአሲቲክ አሲድ
የተባለ ፈሳሽ በመቀባት የቅድመ ካንሰር ምልክቱን ማየት
ይቻላል፡፡ ምልክቱ ካለ በቀዘቀዘ ካርቦንዳኦክሳይድ ይጠረጋል፡፡
በሚጠረግበት ጊዜ ችግሩ ወደ ካንሰርነት እንዳይለወጥ
ያደርገዋል፡፡ አንዳንድ የቅድመ ካንሰር ምልክቶችን ጥንካሬ
ስላላቸው በቀዘቀዘ ክራዮቴራፒ (Cryo ማሽን ይባላል)
የህክምና ዘዴ ለመጥረግ ያስቸግራል፡፡ እነዚህን ምልክቶች
ከመጀመሪያው ቴክኖሎጂ በተለየና (LEEP፤ በተባለ ቴክኖሎጂ
አቃጥሎ እንዲወጣ ማድረግ ይቻላል፡፡ ቅድመ ካንሰር ወደ
ካንሰርነት ሲለወጥ እንዴት ይታወቃል? በሂውማን ፓፒሎማ
ቫይረስ ኢንፌክሽን ያለባቸው በቀጥታ ወደ ቅድመ ካንሰር ፤
ቅድመ ካንሰር ያላቸው ሁሉ ወደ ካንሰር ይለወጣል ማለት
አይደለም፡፡ በተወሰነ ደረጃ በሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ
ኢንፌክሽን ያለባቸው ሰዎች (በኢንፌክሽኑ የተያዙ ሰዎች) ችግሩ
ወደ ቅድመ ካንሰርነት ይቀየራል፡፡ ይሄም ለመታየት ከ10-15
ዓመት ይፈጃል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ምንም ነገር ማድረግ
አይቻልም፡፡ ቫይረሱን ለማከምም ሆነ ሌላ ህክምና ለማድረግ
ጊዜው አይደለም፡፡ የቅድመ ካንሰር ምልክቱ ከታየ ግን ማከም
ይቻላል፡፡ ከቅድመ ካንሰር ወደ ካንሰር ለመለወጥ አሁንም
ከ10-15 ዓመት ጊዜ ይወስዳል፡፡ ቅድመ ካንሰሩን ማከም
ከቻልን ግን ወደ ካንሰር እንዳይሄድ አቆምነው ማለት ነው፡፡
ከቅድመ ካንሰር፤ ወደ ካንሰር ከተቀየረ ደግሞ ለካንሰር
የሚደረጉ ህክምናዎች አሉ፡፡ ምናልባት ካንሰሩ በማህፀን
የተወሰኑ ክፍሎች ላይ ብቻ የሚታይ ከሆነ ችግሩ የታየበት
የማህፀኑን ክፍል ብቻ እንዲወጣ ይደረጋል፡፡ በአካባቢው ባሉ
ቦታዎች ተራብቶም እንደሆነ እነዛ እጢዎች አብረው
የሚወጡበት ሁኔታ አለ፡፡ ወደ ደም ውስጥ ከገባ በኋላ
የሚሰጠው ህክምና የመድሃኒት የቀዶ ጥገና ወይንም የጨረር
ህክምና ነው፡፡ ይሄ የሚሆነው አሁን በምንላቸውን
ቴክኖሎጂዎች ሳንጠቀም ከቀረን ነው፡፡ አሁን የምንላቸውን
ቴክኖሎጂዎች ቅድመ ካንሰር ህክምናና ምርመራ ካደረግን ግን
እዛ ደረጃ ላይም ሳይደርሱ ካንሰሩን ለመከላከል ይቻላል፡፡
ዕድሜያቸው ከ30-40 ላሉ ሴቶች የቅድመ ካንሰር ምርመራ
ካደረጉ እና ችግር እንዳለባቸው ካወቁ በነዚህ ህክምናዎች
በሽታው ወደ ካንሰርነት እንዳይቀየር መከላከል ይቻላል
የሚባለውም ለዚህ ነው፡፡ ቢቻልና አመቺ ቢሆን የግብረ ስጋ
ግንኙነት ከመጀመሩ በፊት ክትባት መውሰድ ቫይረሱን
ለመከላከል ትልቅ ጠቀሜታ አለው፡፡ ሆኖም ክትባቱ ከአቅም
አንፃር አስቸጋሪ ነው፤ ለምሳሌ በአሜሪካ ክትባቱን አንዴ
ለመውሰድ እስከ 250 ዶላር ያስከፍላል፡፡ ይሄ በእኛ አቅም
የሚቻል አይደለም፡፡ ክትባቱ ወደ አገር ውስጥ ገብቶ
አገልግሎት ላይ ይዋል ቢባል መሰጠት ያለበት የግብረ ስጋ
ግንኙነት ላልጀመሩ ሰዎች እንጂ ለጀመሩ ሰዎች አይደለም፡፡
ምክንያቱም የግብረሥጋ ግንኙነት የጀመሩ ሴቶች ቫይረሱ
በሰውነታቸው ውስጥ ሊኖር ስለሚችል ነው፡፡ ከክትባቱ ውድነት
አንፃርና በአሁኑ ሰዓት በሽታው ካንሰር ደረጃ ሳይደርስ መከላከል
የሚቻልበት ቴክኖሎጂዎች ስላሉ እነዚህን መጠቀም
ይመረጣል፡፡
የቅድመ ካንሰር መከላከያው አዲስ ቴክኖሎጂን በማስተዋወቁ
ረገድ በህክምና ተቋማት ውስጥ ምን እየተሰራ ነው? በአዲሱ
ቴክኖሎጂ አንድ ሴት ምርመራውን አግኝታ ‹‹ምንም ነገር
የለብሽም›› ወይንም ‹‹ምልክት ያሳያል›› ተብላ ቀጠሮ
ተሰጥቷት ‹‹ሌላ ጊዜ ነይ›› የምትባልበት አይደለም፡፡
ምርመራውን ምልክት ከታየ እዛው ቦታ ላይ ህክምናውን
ታገኛለች – ዋን ስቶፕ ዲያግኖሲስ ትሪትመንት (በአንድ ቦታ
የሚፈልጉትን አግኝቶ መውጣት እንደማለት ነው) ከዚህ በፊት
የነበሩት ምርመራዎች የማህፀን ካንሰር በአብዛኛው ይሰራ
የነበረው ከማህፀን በር ላይ ፈሳሽ ተጠርጎ ተወስዶ (ቁስለቱ
ካለ ከቁስለቱ ላይ) ተወስዶ በፓቶሎጂ(ከተጠረገው ቁስል ላይ
ያለውን ሴል) በመመርመር የካንሰር ምልክት አለ የለም
የሚለውን ለማወቅ የሚካሄድ የምርመራ ዘዴ ነበር፡፡ ለዚህ
ምርመራ በመጀመሪያ በሙያው ክህሎት ያላቸው ሰዎች
ያስፈልጋሉ፡፡ የምርመራ ውጤቱንም ወዲያው ማወቅ
አይቻልም፡፡ ከ10-15 ቀን ወይም ከዛም በላይ ቆይቶ በቀጠሮ
ነበር፡፡ ይሄ ደግሞ ውድና ጊዜ የሚጠይቅ ነው፡፡ በዚህ አዲስ
ቴክኖሎጂ ግን አሲቲክ አሲድ በሚቀባበት ጊዜ የቀለምና
የማህፀን በር ላይ ለውጥ ያመጣል፡፡ ያ ለውጥ ከቅድመ
ማህፀን ካንሰር ጋር ከተመሳሰለ፣ ህክምናው ወዲያውኑ እዛው
ይሰጣል፡፡ በነገራችን ላይ አሲቲክ አሲድ ስንል በየመንደሩ
የሚሸጠው አቸቶ አይደለም ለራሱ ተብሎ የሚዘጋጅ አለ፡፡
ህክምናው በሰለጠነ ባለሞያ ለምሳሌ በአሁኑ ጊዜ በአዋላጅ
ነርሶችና በነርሶች እየተሰጠ ነው፡፡ በክራዮቴራፒ(Cryo)
የሚጠረገውን የፅንስና የማህፀን ሀኪሞች እና ሌሎች ሀኪሞች
ይሰሩታል፡፡ ቴክኖሎጂው እየተሻሻለ መምጣቱ ረጅም ጊዜ
የመጠበቅን ነገር እና ሌሎችንም ተጓዳኝ ችግሮችን ይፈታል፡፡
ይህንን ሕክምና ለማግኘት የህብረተሰቡ ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ
እየጨመረ ነው፡፡ ሴቶች ተራ ጠብቀው አገልግሎቱን ለማግኝት
ይፈልጋሉ፡፡ የገንዘብ ድጋፉ የተሰጠው ከኤችአይቪ ጋር በተያያዘ
የጤና ችግር ላለባቸው ሴቶች በመሆኑ ህክምናውን መስጠት
በተጀመረባቸው ሆስፒታሎች በአብዛኛው ከኤችአይቪ ጋር
የሚኖሩ ሴቶችን ለማዳረስ ተሞክሯል፡፡ ይሁን እንጂ አሁን
ሁሉም ሴቶችም ምርመራውን ለማግኘት የሚችሉበትን መንገድ
በማመቻቸት ላይ ነው፡፡
ህክምናው ከኤችአይቪ ጋር በሚኖሩ ሴቶች ላይ ብቻ
እንዲያተኩር የተደረገበት ምክንያት ምንድነው? የቅድመ ካንሰር
ኤችአይቪ በደማቸው ያለ ሴቶች ላይ ከታየ ወደ ካንሰርነት
የመለወጡ ሁኔታ በጣም አጭር ጊዜ ስለሆነ እና ኤችአይቪ
በደማቸው ያሉ ሴቶችን በፍጥነት ገዳይ ከሆኑ በሽታዎች
የማህፀን ካንሰር አንዱ በመሆኑ ነው፡፡ የረጅም ጊዜ ኬር
ከምንለው አንዱ ለሴቶች በተለይ ሰርቫይካል ካንሰር (የማህፀን
በር) ካንሰርን መከላከል አንዱና ትልቁ ነው፡፡ መታመምንና
ሞትን የመቀነስ አቅሙከፍተኛ ነው፡፡ HIV በደማቸው ውስጥ ያሉ
ሴቶች የሰውነታቸው የመከላከል ሃይል በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡
ኤችአይቪ በደሙ ያለበት ሰው ሁሉ ቅድመ ካንሰር አለበት
ማለት አይደለም፡፡ ቅድመ ካንሰር ያለው በሙሉም ካንሰር
አለበት ማለትም አይደለም፡፡ የቅድመ ካንሰር ህክምና
ለመስጠት የተለየ ሞያ ወይም ሥልጠና ያስፈልጋል? እ.ኤ.አ
በ2010 ሚያዚያ ወር ከስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ ጋር በተፈጠረ
ትብብር የመጀመሪያዎቹ ሰልጣኞች ከአምስት ሆስፒታሎች
ተመርጠው ሰለጠኑ ወደየመጡበት ሄደው ለስድስት ወራት
ሰለጠኑ፡፡ ከዚያም ተመልሰው መጥተው የአሰልጣኝነት ስልጠና
እንዲሰለጥኑ ተደረገ፡፡ እነዚህኛዎቹ ደግሞ በዘጠኙም ክልል
ባሉ ሆስፒታሎች እየሄዱ ስልጠና እንዲሰጡ ተደርጐ ወደ
ሥራው ተገባ፡፡ ጉዳዩ በፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንደ
አንድ ጉዳይ ታይቶ በመንግስት ዕቅድ ውስጥ ገብቷል፡፡ ቅድመ
ምርመር ማድረጉ ወደ ጤና ጣቢያዎች ቢወርድ ውጤታማ
ሊሆንና ብዙዎች ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡
ፕሮግራሙ ከተጀመረ ወዲህ ምን ያህል ሴቶች ምርመራውን
አገኙ ምን ያህሉስ የቅድመ ካንሰር ምልክት ተገኘባቸው?
በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ 10 ሺህ ሴቶች ተመርምረው ወደ 1
ሺህ የሚጠጉ ሴቶች የቅድመ ካንሰር ምልክቱ ተገኝቶባቸው ወደ
98ፐርሰንት ትሪትመንት አግኝተዋል፡፡ ሌሎቹ ከቅድመ ካንሰር
ያለፈ በመሆኑ በኦፕሬሽንና በመሳሰሉት ህክምና ማግኘት
ነበረባቸው፡፡ ከተመረመሩት ውስጥ 90 በመቶ የሚሆኑት በአንድ
ወር ጊዜ ውስጥ ምልክቱ ጠፍቶአል፡፡ ‹‹አንዲት ሴት ለምርመራ
መጥታና ቅድመ ካንሰር ምርመራው ተደርጎላትና ታክማ፤ ከአንድ
ወር በኋላ መጥታ አሁን ምንም ምልክት የለሽም ተብላ ፊቷ
ላይ የሚታየውን ደስታ ከማየት የበለጠ ምንም የሚያስደስት
ነገር የለም›› የቅድመ ካንሰር የነበረባቸው ሴቶች ህክምናውን
ሳያገኙ ቢቀሩ ኖሮ ወደ ካንሰር ሊያድግ ይችል ነበር፡፡
ከምርመራው በፊት ካውንስሊንግ ይሰጣል፤ በአዲስ አበባና
በክልሎች ህክምናው የት የት ቦታ ይሰጣል? ምርመራውን
ለማድረግ መጀመሪያ ካውንስሊንግ አለው፡፡ ከ30 ደቂቃ እስከ
አንድ ሰዓት ባለው ጊዜ ድረሰወ ካውንስሊንጉ ሊፈጅ ይችላል፡፡
ምልክቶቹ ከተገኙ ሊሰጥ የሚችለውን መፍትሄ ምንድን ነው
የሚለውን ጭምር የሚያካትት ነው፤ በአዲስ አበባ ጳውሎስ
ሆስፒታል፣ ሚሊኒየም ህክምና ትምህርት ቤትና ዘውዲቱ
መታሰቢያ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና ይሰጣል፡፡ በክልሎች
ደግሞ ይርጋለም፣ ወላይታ ሶዶ ሪፈራል ሆስፒታሎች አዋሳ፣
ባህርዳር ፈለገ ህይወት፣ ጎንደር፣ ደብረ ማርቆስና ደሴ ሪፈራል
ሆስፒታሎች፤ መቀሌ፣ አድዋ፣ አክሱም፣ ማይጨው ለምለም
ካርል ሆስፒታሎች፤ ነቀምት፣ አሰላ፣ ቢሾፍቱ ሆስፒታሎች
ውስጥም ይሰጣል፡፡ አራት ክሊኒኮች ከኢትዮጵያ ቤተሰብ
መምሪያ ጋር በመተባበር ህክምናውን እንዲጀመሩ ድጋፍ
ተደርጐላቸዋል፡፡ ጦር ሃይሎች ሆስፒታልም እንዲጀመር ድጋፍ
ተደርጓል፡፡ አንድ ክራዮቴራፒ(Cryo) ማሽን ዋጋው 40 ሺ ብር
ነው፡፡
የቅድመ ካንሰር ምርመራውን አድርጋ ህክምናውን ያገኘች ሴት
በሽታው ድጋሚ እንደማይከሰት ምን ያህል እርግጠኛ ትሆናለች?
ቅድመ ካንሰርን ማከም ከተቻለ ካንሰርን መከላከል ይቻላል፡፡
ወደ ካንሰር ከተለወጠ በኋላ ግን ያለው አማራጭ ከፍተኛ
ህክምና ነው ይህ ደግሞ የሚሰጠው በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል
ነው፡፡ ከህሙማኑ መብዛት የተነሣ የሚሰጠው የዓመት ወይም
የስምንት ወር ቀጠሮ ነው፡፡ አንዳንዶች ቀጠሮአቸውን እየጠበቁ
ሳይደርስ ይሞታሉ፡፡ ቅድመምርመራው ይሄን ቁጥር ለመቀነስ
ያረዳል፡፡ ቅድመ ካንሰር ህክምና ያደረገች ሴት ከዓመት በኋላ
መጥታ ምርመራ በማድረግ ምንም ነገር እንደሌለ እርግጠኛ
ሆና ትሄዳለች፡፡ አብዛኞቹ ማለትም ከ90 ፐርሰንት በላይ ያህሉ
ኔጌቲቭ ይሆናሉ፡፡ በአንድ ዓመት ውስጥ መጥታ አሁን ምልክቱ
ካላትና እንደገና ለመጥረግ ጠንካራ ከሆነ ሊፕ የሚባለው
ህክምና ይሰራላታል፡፡
አንዲት ሴት ቢያንስ አንድ ጊዜ የቅድመ ካንሰር ምርምራ
ካደረገች ከካንሰር ለመጠበቅ ዋስትና ይሆናታል፡፡
አብዛኛዎቻችን የበሽታ ምልክት ከታየብን በኋላ ነው ወደ ጤና
ተቋማት መሄድ የምናዘወትረው ይህ ግን አግባብ አይደለም፡፡
በተለይ ካንሰር ምልክት የለውም፡፡ ከ30-35 ባለው ዕድሜ
ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶች ምርመራ ማድረጉ ምልክት የሌለውን
ነገር በማወቅ ከችግሩ ራስን ለመጠበቅ እንዳችሉ
ያደርጋቸዋል፡፡

RH..
26/02/2017

RH..

Rh-Incompatablitiy ሾተላይ
ሾተላይ ምንድን ነው?
(በዶ/ር ቤቴል ደረጀ- የማህጸን እና የጽንስ ስፔሺያሊስት)

ሾተላይ በመባል የሚታወቀው ክስተት ብዙ ጊዜ አንዲት እናት ከመጀመሪያ እርግዝናዋ በኃላ በተደጋጋሚ የሚከሰት የጽንሱ መጥፋት ነው።

ይህ ለምን ይሆናል?

የሰዎች ደም በአራት መደብ ይከፈላል(A, B, AB, O) እነዚህ ደግሞ እያንዳንዳቸው በሁለት አበይት መደብ ይከፈላሉ፡ አር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) እና አር ኤች ኔጋቲቭ(Rh-)። ለምሳሌ፦ የአንድ ሰው የደም ዓይነት A+ ወይም A- ሊሆን ይችላል። የሰው ማንነቱ ከእናቱና ከአባቱ በሚወስደው የዘር-መል ይወሰናል። የደም ዓይነትም በዚሁ መልክ እንወስዳለን። ከአር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) አባት እና ከአር ኤች ኔጋቲቭ(Rh-) እናት የሚፈጠር ጽንስ አር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) የመሆን እድሉ የሰፋ ነው።

ሾተላይ የሚከሰተው አንዲት ሴት የደም ዓይነቷ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) ሆኖ ከዚህ በፊት አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +) የሆነ ደም ወደ ሰውነቷ ሲገባ ደሟ ውስጥ አር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) የሆኑ የደም ህዋሶችን የሚያጠፋ ንጥረ-ነገር በደሟ ውስጥ ይመረታል። ይህ ንጥረ-ነገር አንዴ ከተመረተ በደሟ ውስጥ እስከ ህይወቷ ፍጻሜ ድረስ ይኖራል።
በመሆኑም በማህጸንዋ ውስጥ የያዘችው ጽንስ የደም ዓይነቱ አር ኤች ፖዘቲቭ ከሆነ የተመረተው ንጥረ-ነገር ጽንሱን እንደ ባእድ አካል ስለሚቆጥረው ያጠቃዋል። በዚህም ምክንያት በተደጋጋሚ የምትይዘው ጽንስ የደም ዓይነቱ አር ኤች ፖዘቲቭ ከሆነ አስፈላጊውን ህክምና ካልተደረገላት ይሞትባታል። የደም ዓይነቱ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) ከሆነ ግን በጤና ይወለዳል። ይህ እንዲሆን ግን
የአባትየው የደም ዓይንት አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) መሆን አለበት?

ሕክምናው
1. የደም ዓይነቷ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) የሆነች እናት ሕክምናዋ በሆስፒታል ውስጥ መሆን አለበት።

2. በደሟ ውስት ያለውን የንጥረ-ነገር መጠን መለካትና የጽነሷን የጉዳት መጠን በማየት ብዙ ሳይጎዳ እንዲወለድ ማድረግ።

3. በሀገራችን በቅርቡ የተጀመረው ጽንሱ በማህጸን ውስጥ እያለ ደም በመለገስ እንዲያድግና እንዲወለድ ማስቻል። እንዴት እንከላከለው?

1. ማንኛዋም ሴት ከማርገዟ ወይም ማንኛውንም ደም ከመውሰዷ በፊት የደም ዓይነቷን ማወቅ አለባት።

2. የወንድ አጋሯን የደም ዓይነት ማወቅ አለባት።
3. እርግዝና አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +) ከሆነ አጋሯ ከተፈጠረ መጀመሪያ በሚደረግላት
ምርመራ (indirect coomb’s test) ንጥረ-ነገሩ አለመመረቱን ያረጋግጣል። እዳይመረት
የሚከላከል መድኃኒት (Anti-D) 7ተኛ ወሯ ላይ ይሰጣታል። ከወለደች በኃላ የልጇ የደም
ዓይነት አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +) ከሆነ በድጋሚ መድኃኒቱ ይሰጣታል።

4. እርግዝናው ከማህጸን ውጭ ወይም በውርጃ ቢያበቃም መከላከያውን መድኃኒት መውሰድ አለባት።

ጽሑፉን ከወደዱት(Like) በማድረግ ለሌሎችም (share)ያድርጉት፡፡
ሌሎች ምርጥ ምርጥ መረጃዎች እንዲደርስዎ ፔጁን ላይክ ያድርጉ።እናመሰግናለን።

ከፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተሰጠ ወቅታዊ የአተት መግለጫየአጣዳፊ ተቅማጥና ትዉከት ተላላፊ በሽታ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሕብረተሰቡ ተግባራዊ ምላሽ ወሳኝ ነዉ!!! የአጣዳፊ ተቅማጥና ት...
19/08/2016

ከፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተሰጠ ወቅታዊ የአተት መግለጫ
የአጣዳፊ ተቅማጥና ትዉከት ተላላፊ በሽታ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሕብረተሰቡ ተግባራዊ ምላሽ ወሳኝ ነዉ!!!
የአጣዳፊ ተቅማጥና ትዉከት ተላላፊ በሽታ ስርጭትን ለማቆም አሁንም የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከአ/አበባ ከተማ አስተዳደርና ከክልሎች ጋር በመሆን ሕብረተሰቡን በንቃት እንዲሳተፍ በማድረግ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዉ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ የታማሚዎች ቁጥር እየቀነ ሲሆን በአንዳንድ ክልሎች በተለይም በአማራ ክልል ባህርዳር ሁሪያ እና በመቀሌ ከተማ በዚህ ሳምንት በሽታዉ መከሰቱ ቃዉቋል፡፡ በአዲስ አበባ የታማሚዎች ቁጥር የመቀነስ አዝማሚያ እያሳየ ቢሆንም ሁሉም አካባቢዎች ከበሽታዉ ነፃ እሰኪሆኑ ቀጣይነት ያለዉ የግል የአካባቢና የምግብ ንፅህና ላይ አትኩሮ በግል በቤተሰብና በመኖሪያ አካባቢ መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡
በአዲስ አበባና በስታዉ በተከሰተባቸዉ በአንዳንድ የከክልል አካባቢዎች ለአጣዳፊ ተቅማጥና ትዉከት ህክምና አገልግሎት በተዋቀሩ የህክምና ጣቢያዎች ታማሚዎች የህክምና አገልግሎት እያገኙ ወደየቤታቸዉ እየተመለሱ ነዉ፡፡
ቀደም ብሎ እንደተገለፀዉ በአዲስ አበባ የበሽታዉ መነሻ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ወንወዞችና ምንጮች በበሽታ ሃምጪ ተህዋሲያን የተበከሉ በመሆኑ ይህን ተከትሎ በህገወጥ እየታረዱ የሚቀርብ ስጋና የአትክልት ዉጤቶችን በወንዞቹ እየታጠቡና እየተነካኩ የሚቀርቡ በመሆናቸዉ እነኝህን አቅርቦቶች በጥሬያቸዉ የተመገቡ ሰወች ለበሽታዉ መጋለጣቸዉ እንደሆነ ይታወሳል፡፡
አሁን ባለዉ መረጃ የበሽታዉ መቀነስ ምክንያት ሕብረተሰቡ በግልና በአካባቢ ንጽኅና እደረገ ያለዉ ጥረትና በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የፍልሰታ ፆም ምክንያት ከስጋ አጠቃቀም መቀነስ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ይገመታለል፡፡
በመሆኑም ከፆሙ መፈታት ጋር ተያይዞ በሚኖረዉ የስጋ አጠቃቀም ጥንቃቄ ያልተሞላበት ከሆነ የታማሚዉ ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል የባለሙያዎች ከፍተኛ ስጋት አለ፡፡
ይህንን መሰረት በማድረግ የህገወጥ እርድ፣ የልኳንዳ ቤቶች የምግብ ቤቶች ቁጥጥር ተጠናክሮ የቀጠለ ስለሆነ ሕብረተሰቡ በቁጥጥሩ ስራ ላይ ከፍተኛ ድጋፉን እንዲሰጥ፣ በማንኛዉም መልኩ ስጋንም ሆነ አትክልትን በጥሬዉ ከመመገብ እንዲቆጠብና አብስሎ በትኩሱ ብቻ በመመገብ እራሱንና ቤተሰቡን ከበሽታዉ እንዲከላከል፣
በሌላ በኩል በተበከሉ የወንዝ ፣የምንጭ የቦይ ወራጅ ዉሃ ዉሃዎችን በመጠቀም ምግብ የሚያዘጋጁ፣ የምግብ እቃዎችን ልዩ ልዩ የቤት መገልገያ ቁሳቁሶችን መኪናን ጨምሮ የሚያጥቡ የሚያሳጥቡና የተበከሉ ፍሳሾችን ረግጠዉ ሳያጸዱ ወደ መኖሪያ ቤታቸዉ የሚገቡ ሰወችና ቤተሰቦች ለበሽታው እንዳይጋለጡ ከዚህ አይነት ድርጊት እንዲቆጠቡና ለማንኛዉም ነገር የታከመ ወይም የፈላ ዉሃ መጠቀማቸዉን እንዲያረጋግጡ፣
በጥቅሉ፡-
• ሕብረተስቡ በአዲስ አበባ የሚገኙ የወንወዝ ዉሃዎችን በምንም መልኩ ከመጠቀም እንዲቆጠብና
• ከሚጠረጠሩ አካባቢዎች የሚገኝን ዉሃ አፍልቶ ወይም አክሞ ብቻ እንዲጠቀም፣
• የስጋ ዉጤቶችን በዱለት፣ በሰንበርና ምላስ፣ በክትፎና በጥሬ ስጋነት ከመመገብ እንዲቆጠብና ንጽህናቸዉን ጠብቆ አብስሎ በትኩሱ ብቻ እንዲመገብና
• እንደዚሁም የአትክልት ዉጤቶችን ከዝግጅት እስከ ማዕድ አፍ እስኪገባ ንጽህናቸዉን ጠብቆ አብስሎ በትኩሱ ብቻ እንዲመገብና
• በአዲስ አበባ የሚገኙ ወንዞችን ምንጮችን እንዲሁም የቦይ ወራጅ የጎርፍ ዉሃን ለመኪናና ለልዩልዩ ቁሳቁስ እጥበት ከመጠቀም እንዲቆጠብ፡፡
በሽታዉን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሕብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ወሳኝ እንደመሆኑ የመከላከል ስራዎችን ተግባራዊ በማድረግ ከበሽታው ምልክት ዉስጥ ማስታወክና ማስቀመጥ ወይም ከሁለቱ አንዱ እንኳን የታየበት ሰዉ ከተገኘ ወዲያወኑ በአስቸኳይ በአቅራቢያ ወደሚገኝ ጤና ተቋም እንዲሄድና ህክምና እንዲያገኝ የታማሚዉ ቤትና አካባቢ በባራኪና እንዲጸዳ በማድረግ በሽታውን ከራሱ ከቤተሰቡና ከአካባቢዉ በመከላከል እንዲቆጣጠር የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በድጋሚ ያሳስባል፡፡

vcy
03/08/2016

vcy

Vaccancy Anouncement
03/08/2016

Vaccancy Anouncement

Address

Harar

Telephone

+251256661985

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Federal police Harar General Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your practice to be the top-listed Clinic?

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram