
16/08/2025
ከ 2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የሕክምና መገልገያ ቁሳቁሶች እና የመድሀኒት ድጋፍ ለኦቶና ሆስፒታል ተደረገ
ነሐሴ 10/2017 ዓ.ም
*******************************
ግምቱ ከ 2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን የህክምና መገልገያ ቁሳቁስ ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ንግስት እሌኒ መሃመድ መታሰቢያ ኮምፕርሔንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ ኦቶና ኮምፕርሔንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ድጋፍ ተደርጓል።
በወላይታ ሶዶ ዩኒበርሲቲ ኦቶና ኮምፕርሔንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒተ ላይ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ድንገተኛ የእሳት አደጋ በመከሰቱ ምክኒያት በሆስፒታሉ ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ንግስት እሌኒ ኮምፕርሔንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታልም ጉዳት የደረሰበትን ኦቶና ሆስፒታልን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ርብርብ የበኩሉን እንደሚወጣ መናገሩ የሚታወስ ሲሆን በዛሬውም እለት የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳዊት ሃዬሶ፣ የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት አባላት፣ የን/እ/መ/መ/ኮ/ስ/ሆስፒታል ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ይድነቃቸው ደዳቸው እና የን/እ/መ/መ/ኮ/ስ/ሆስፒታል ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ለኦቶና ኮምፕርሔንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ድጋፍ ተደርጓል።
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳዊት ሃዬሶ በንግግራቸው፦
በድንገት የተከሰተው የእሳት አደጋ የፈጠረው ውድመት ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ሆስፒታሉ ቀደም-ሲል ወደሚሰጠው የህክምና አገልግሎት እንዲመለስ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የበኩሉን ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል ጠቅሰው ሁላችንም በጋራ እና በአንድነት ከተባበርን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሆስፒታሉን መልሰን ማቋቋም እንችላለን ብለዋል።
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጉቼ ጉሌ እንደገለጹት፦ በእሳት አደጋው ምክኒያት የተስተጓጎለውን የህክምና አገልግሎት መልሶ ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸው በዛሬው እለትም ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ላደረገው የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶችና የመድሀኒት ድጋፍ ከፍ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የን/እ/መ/መ/ኮ/ስ/ሆስፒታል ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ይድነቃቸው ደዳቸው እንደተናገሩት፦ በኦቶና ሆስፒታል ላይ የደረሰው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ያደረሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ሆስፒታሉን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት ጋር በመነጋገር ይህን ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸው በቀጣይም ሆስፒታሉን ለማቋቋም በሚደረግ ርብርብ ድጋፋቸው እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
ነሐሴ 10/2017 ዓ.ም
ዘገባው በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ን/እ/መ/መ/ኮ/እ/ ሆስፒታል ህዝብ ግንኙነት ነው!!!
Let Your light shine in the Society!!