09/05/2025
==================================
Tajaajilli Maadaallii Barnootaa fi Qormaata Biyyaalessaa Sagantaa Qormaata Biyyaalessaa Kutaa 12ffaa ifoomse.
Sagantaa kanas gabatee armaan gadii kana irraa ilaaluun ni danda'ama👇
Barattootni keenya dubbisatti jabaadhaa.
Our Students, be study hard
" ✓"
የ2017 ትምህርት ዘመን ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት መርሃ ግብር ተገለጸ፡፡
ፈተናው ከሰኔ 23/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ/ም የሚሰጥ ሲሆን በወረቀት የሚፈተኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 21 እና 22/2017 ዓ/ም እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 29 እና 30/2017 ዓ/ም ወደሚፈተኑበት ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ይሆናል፡፡ በበይነ መረብ የሚፈተኑ ተፈታኞች ከመኖሪያ ቤታቸው በየቀኑ እየተመላለሱ በተመደቡበት መፈተኛ ማዕከል የሚፈተኑ ሲሆን ዝርዝር መርሃ ግብሩ በሚከተለው ሠንጠረዥ ተገልጿል፡፡
የፈተናው ይዘት በተማሪው መጽሐፍ ላይ ያተኮረ በመሆኑ እያንዳንዱ ተፈታኝ በትምህርት ቤቱ የተማረበትን የተማሪ መጽሐፍ መሠረት አድርጎ ተገቢ የሆኑ አጋዥ መጽሐፍትን ለበለጠ እውቀትና መረዳት በመጠቀም እንዲዘጋጅ እናበረታታለን፡፡ በፈተና ወቅት ለፈተና ስርቆትና ኩረጃ የሚውሉ ማንኛውንም ቁሳቁሶች መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡ ዝርዝሩ በቀጣይ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
ግንቦት 01/2017 ዓ/ም