Jimma Zone,Dedo Woreda,Dedo Hospital

Jimma Zone,Dedo Woreda,Dedo Hospital Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Jimma Zone,Dedo Woreda,Dedo Hospital, Jimma.

17/01/2023

✅ ‼

‼ለወጣቶች ታላቅ መልእክት ነው ሁሉን ሰው መውደድ እንጂ ሁሉን ጓደኛ ማድረግ አይቻልም ፤ ደግሞም ተገቢ አይደለም። #ሁሉን ሰው በእኩል ማየት እንጂ ለሁሉ ሰው ጓዳን መግለጥ ተገቢ አይደለም ፤ ደግሞም ጎጂ ነው።

#በሚጠሉህ መሐል ወዳጅህን እንደምታገኘው ፤ ከሚወዱህ መሐልም የሚጠላህን ታገኘዋለህ። ሁሉ ይወደኛል ብሎ የሚያስብ ጅል ብቻ ነው። ሁሉ ይጠላኛል ብሎ የሚያስብም ትላንትን ያልረሳ ነው።

#አንተ ቀድሞ ትጠላቸው የነበሩትን አሁን በጣም ትወዳቸዋለህ ፣ ቀድሞ በጣም ትወዳቸው የነበሩትን አሁን ባሰብካቸው ቊጥር ትታመማለህ። ሰዎችም እንዳንተ ናቸው።

#ሳያውቁህ ሊጠሉህ ይችላሉ፣ ጥላቻ ስሜት ነውና ስሜቱ ሲሄድ እንደገና ይወዱሃል። ይወዱህ የነበሩም ከዓይናቸው ጆሮአቸውን አምነው ሊርቁህ ይችላሉ። #የሄደው ይመጣል ፣ የመጣውም ይሄዳል። በዚህ ዓለም ላይና በሚመጣው ዓለም ቋሚው ነው።

#እግዚአብሔርን ከማያምኑና እናምናለን ከሚሉ ግብዞች ተጠንቀቅ። #ክርስቲያን ሁነው ጭካኔን የሚለማመዱ እንደ አርዮስ በልብ ክደው በአፍ የሚያምኑ ናቸው። የእነዚህ ሰዎች ወዳጅነት እንደ ፍግ እሳት ነው ፣ ውስጥ ውስጡን ሂዶ መጨረሻ ላይ ያቃጥላል።

ጻድቅ ለመምሰል ከሚሞክሩ ስጦም ውያለሁ፣ #ስጸልይ አድሬአለሁ ከሚሉ ፣ ለወሬ እየነቁ ለቃለ እግዚአብሔር ከሚተኙ ፣ ሌሎችን ሲኰንኑ ከሚውሉ ፣ ለመናገር እንጂ ለመስማት የተፈጠሩ ከማይመስላቸው ሰዎች ጋር ያለህን ወዳጅነት እንደገና መርምረው። #እነዚህ ሰዎች አንተን በተለያየ ነገር ተገዥአቸው ሊያደርጉህ ይፈልጋሉ። ድራማቸውን ከነቃህበት እንደ ጠላት ያዩሃል።

እንባ ሊያበዙ ፣ ተጎዳሁ የሚል ድርሰት ሊያነቡልህ ይችላሉ። የሚናገሩት የተጠና የመከራ ታሪክ አላቸው ፤ ተሳስተው ከሚጎዱህ አልመው የሚጎዱህ እነዚህ ናቸውና ተጠንቀቅ። የአየር ትራፊክ ሠራተኛ ብዙ አውሮፕላኖችን አየር ላይ ደርድሮ አንዱ አንዱን ሳያይ ሲያሳርፍና ሲያስነሣ እንደሚውል እነዚህ ሰዎችም የተለያዩ ወገኖችን ለተለያየ ጥቅም የሚጠቀሙ ስልታዊ ናቸው።

የሚደልሉላቸው ብዙ ሠራተኞች ፣ ጽድቃቸውን እያወሩ የሚከፈላቸው ሎሌዎች አሉአቸውና ተጠንቀቅ።

#የታወቁ ሰዎችን ለማወቅ አትጣር። ከሹም ጋር ለመታየት ጥረት አታድርግ። ከባለጠጎች ጋርም ጊዜ ለማጥፋት አትሻ። ዝነኞችንም በቤትህ ለመጋበዝ አትከጅል።

እነዚህ ሁሉ የነፋስ ጎረቤቶች ናቸውና ሲጠረጉ አብረህ ትጠረጋለህ። በእነዚህ መንደር ስላደረጉት ጀብዱ ስለሚፈጽሙት በቀል እንጂ ስለ ሕይወት አይወራምና ወዳጅነታቸውን አትውደደው። ደግሞም በሩቅም በቅርብም ውብ #እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን አትዘንጋ ።

በሥራ ሰነፎች የሆኑ ፣ በየቤቱ እየዞሩ በጸሎት ስም አድማ የሚረጩ ሰዎች አብረውህ ቢቆዩ እንኳ ስለ ሆዳቸው እንጂ ስለ ፍቅር አይደለምና ወዳጆችህን የሚያጠፉብህ እነዚህ ስለሆኑ በቶሎ ሸኛቸው።

#አለዝዘው የሚገድሉ ረጅም ሞት ማለት እነዚህ ናቸው። እምነት የሚመስል ግዴለሽነት ፣ ትዕግሥት የሚመስል ስንፍና እንዳላቸው ልብ በል። #ሥራ ስትላቸው ዋናው ጸሎት ነው የሚሉና ጸሎትን የስንፍና መጋረጃ ያደረጉ ናቸውና ከእነዚህ ዘባቾች ጋር ከቻልህ ጎረቤት አትሁን።

ገለባ እንደማይበቅል ሰነፍም ወዳጅ አይሆንም። አፈ ቅቤ የሆኑትን ተጠንቀቅ። #እግዚአብሔር ተናጋሪውን አሮንን ሳይሆን ኮልታፋውን ሙሴን እንደ መረጠ እወቅ። ተናጋሪ ሰው መጨረሻው ጥፋት ነው።

የሚያቆላምጡህን አትውደድ ፣ የስምህም ጥገኛ ሁነህ የሚያሞካሹህን አትጋብዝ። እነዚህ ሰዎች አዝማሪ ናቸውና ለሞቀበት የሚዘፍኑ ናቸው።

እኔ ብቻ ነኝ ያንተ ወዳጅ የሚሉህንም አትመን። እነዚህ ሰዎች አንተን በማምለክና አንተን የፈጠሩህ በሚመስል ስሜት ያበዱ ናቸው።

#በማምለክ ስሜታቸው ያለ አንተ የሚኖሩ አይመስላቸውም ፣ በመፍጠር ስሜታቸው እነርሱ ሳያውቁ ማንንም እንድትወድ አይፈቅዱም። እነዚህ ሰዎች ፍቅር በሚመስል ነገር በቅኝ የሚገዙህ ናቸውና ተጠንቀቅ።

ራስህን ነጻ ያወጣህ ቀን ለእኔ ካልሆነ ለማንም አይሁን በሚል ስሜት ሊያጠፉህ ይነሣሉ። የጅል ጠብ ማብቂያ የለውምና እባክህ ተጠንቀቅ።

#ለሚያደርሱብህ ጉዳትም ጸጸት አይሰማቸውም። ምክንያቱም በፈጠሩት ላይ የፈለጉትን የማድረግ ስሜት ስለሚሰማቸው ነው። ቆንጥር እንደያዘው ልብስ ቀስ ብለህ ተላቀቅ።

ሌሎችን የሚያዋርዱ ሰዎች አንተን እያከበሩህ ቢቀርቡ አትመናቸው። #ኃይለኛ ውሻ እንኳ የሚወድህ ለሌላ ውሻ ደግነት ስታደርግ ሲያይህ ነው። ይህ ሰው የእኛ ወዳጅ ነው ብሎ አላስቀርብ ያለ ውሻ ይቀርብሃል።

ይለዝብልሃል። ውሻ እንኳ በሌላ ውሻ ከለካህ አንተም ሰውን በሰው ለካው። #ባለጌ የሚሰድበውን ሲጨርስ ወዳንተ ይዞራል። ስድብ ሥራው ነውና። #በተሾምህበት ስፍራ አብሮ አደጎችህን ይዘህ አትሂድ።

በር ዘግተህ ካልሆነም ከአብሮ አደጎች ጋር አትጫወት። #ልክና ዕረፍት ያጣ ወዳጅነትን ተጠንቀቅ። እሳትን የሚያነደው እፍ እንደሆነ ሁሉ የሚያጠፋውም እፍ ነው። ያበዱለት ወዳጅነት አድራሻው እስኪጠፋ ብን ይላል ። ሁሉን በልክ አድርገው። የዓመቱን በዕለት አትሥራው ።

አሰቃቂ ነገርን በራሳቸው ላይ የሚናገሩትን ፣ ራሴን አጠፋለሁ የሚሉትን ሰዎች በጥንቃቄ ተመልከት። #አንዳንዶች ኑሮ ከፍቶባቸው እንዲህ ይላሉና እዘንላቸው።

ሌላውን እስረኛ ለማድረግና ሌላው ሲጨነቅ በመስተዋት እያዩ ለመሳቅ ፣ ሌላውን አንቅተው እነርሱ ለመተኛት እንዲህ የሚሉ ሰውን የኅሊና እስረኛ በማድረግ የሚረኩ ሰዎች እንዳሉ አትዘንጋ ።

#ርኅራኄህን ካገኙት በኋላ ያሰቃዩሃል ። እነዚህ ሰዎች በጣም ራስ ወዳድ ናቸውና ሁሉን ነገርህን እንዳያራቁቱብህ ተጠንቀቅ ።

#እነዚህ ሰዎች አንድ ቀን ቀድመው ባስመዘገቡት እብደት ቤትህንና ኑሮህን ሊያወድሙ ይችላሉ ።

#ለወዳጆችህ እኩል ፊት አሳይ ፣ ለአንዱ ትንሽ ለሌላው ብዙ ነገር አታድርግ። ፍቅር አነሰብኝ የሚለው ጠላትህ ይሆናልና ።

#እግዚአብሔር ከሌለበት ወዳጅነት እግዚአብሔር ያለበት በረሃ የተሻለ ነው ። ስሜትህን ሁሉ አትግለጥ ። ሁሉ በልቡ ይንቅሃል ፣ ወይም እንደ እብድ ያይሃል ።

። አንዳንድ ምሥጢር ሲገለጥ የነፋስ እርግዝና ነው። ነፋስ ሲያረግዙት ያስጨንቃል ፣ ሲወለድ ግን አይጨበጥም። #በሆንከው ደስ ይበልህ። ዕድገትህን ኑሮህን ቀባብተህ አታቅርብ።

እንደውም ተደስተህ ተርከው። የራቀህን ወዳጅ ምክንያቱን ባወቅሁት አትበል ። እርሱ የጨረሰበት ምክንያት አንተን ቂም ያስጀምርሃልና ። ደንበኛ እንኳ ሲሄድ አመስግኖ ነው ። ይህ ከደንበኛ ያነሰ ነውና ተወዉ ።

#የበታችነት ከሚሰማቸው ሰዎች ጋር አትዋል። ምልክታቸው የበላይነት ስሜት ይሰማቸዋል። ዓለም እየታመሰ ያለው በእነዚህ ሰዎች ነው። ዘሬ፣ክብሬ፣ስሜ የሚሉ እነዚህ ሰዎች ናቸው ።

#ጓደኛ አታብዛ መከራህ እንዳይበዛ !!

Address

Jimma

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jimma Zone,Dedo Woreda,Dedo Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram