EDEN MCH JIMMA

EDEN MCH JIMMA A Commitment to Quality

Hello our valued customers we are happy to share with you that we have started to give service with digital x ray with a...
22/02/2025

Hello our valued customers we are happy to share with you that we have started to give service with digital x ray with a comment by radiologists.
https://t.me/xray1edenclinic

Our OPD at Eden Clinic
29/06/2024

Our OPD at Eden Clinic

14/06/2024
27/02/2024
18/02/2024
10/02/2024

***የሳንባ ካንሰር ምንድን ነው?***
=============

የሳንባ ካንሰር ማለት በሳንባ ውስጥ የሚገኙ ህዋሳት ከመደበኛ ዕድገታቸውና ቁጥራቸው ውጪ ጤናማ ባልሆነ መልኩ መባዛት ነው፡፡ የሳንባ ካንሰር ከሳንባ ተነስቶ ወደ አንጎል እንዲሁም ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ሊሰራጭ ይችላል፡፡

የሳንባ ካንሰር ምን ያህል ተስፋፍቶ ይገኛል?

• የሳንባ ካንሰር በዓለም አቀፍ ደረጃ በብዛት የሚከሰት ካንሰር ነው፡፡
• የሳንባ ካንሰር በዓለም አቀፍ ደረጃ በገዳይነቱ ቀዳሚ ነው፡፡
• የሳንባ ካንሰር በኢትዮጵያ በወንዶች ዘንድ በብዛት ከሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች ስድስተኛው ነው፡፡

የሳንባ ካንሰር ዋና ዋና አጋላጭ ሁኔታዎች

1. ማጨስ፡- ለሳንባ ካንሰር ዋነኛ አጋላጭ ሁኔታ ነው፡፡ የትምባሆ ምርቶችን መጠቀም ለሳንባ ካንሰር የመጋለጥ ዕድልን ይጨምራል፡፡ በማንኛውም የዕድሜ ክልል ማጨስን ማቆም በሳንባ ካንሰር የመጋለጥ ዕድልን ሊቀንስ ይችላል፡፡ ደባል አጫሾችም ለሳንባ ካንሰር የተጋለጡ ናቸው፡፡

2. የስራ ቦታ፡- በብዛት ከሚታወቁ የስራ ቦታ አጋላጭ ሁኔታዎች ውስጥ እንደ አስቤስቶስ፣ ሲሊካ፣ ራዶን፣ ከባድ ብረቶች፣ ፖሊሳይክሊክ፣ እና ሃይድሮካርቦን የመሳሰሉ ኬሚካሎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

3. የአየር ብክለት፡- በቤት ውስጥ እንዲሁም ከቤት ውጪ የሚኖር የአየር ብክለት ለሳንባ ካንሰር ተጋላጭ ያደርጋል፡፡ በተለይም በቂ አየር በሌላቸው ቤቶች ውስጥ ከሰል፣ እንጨት እና ሌሎች ለማገዶ የምንጠቀማቸው ነገሮች የሚያወጡት ጭስ ሴቶችን ይበልጥ ተጋላጭ ያደርጋቸዋል፡፡

4. የቤተሰብ ሁኔታ፡- የሳንባ ካንሰር በቤተሰብ ውስጥ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍ ያለ ነው፡፡

5. የጨረር ህክምና፡- በተደጋጋሚ በደረት ላይ የሚደረግ የጨረር ምርመራ በሳንባ ካንሰር የመጋለጥ ዕድልን ከፍ ያደርጋል፡፡ ስለሆነም ከላይ የተዘረዘሩትን አጋላጭ ሁኔታዎች መቀነስ ወይም ማስወገድ የሳንባ ካንሰርን ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡

የሳንባ ካንሰር ዋና ዋና ምልክቶች

 ለረጅም ጊዜ እየተባባሰ የሚሄድ ወይም በቀላሉ የማይጠፋ ሳል፣
 የደረት ህመም
 የትንፋሽ ማጠር
 ስንተነፍስ ድምጽ መኖር
 ደም የቀላቀለ አክታ
 በብዛት የሚሰማ የድካም ስሜት
 ባልታወቀ ምክንያት ክብደት መቀነስ
 በተደጋጋሚ ለሳንባ ምች መጋለጥ ወ.ዘ.ተ.

በይበልጥ ቅድመ-ምርመራ (ልየታ) ማድረግ ያለባቸው እነማን ናቸው?

ዕድሜያቸው 40 አመትና ከዚያ በላይ የሆኑና ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ማለትም፡-
 አጫሾች ወይም ለሲጋራ ጭስ ተጋላጭ የሆኑ፣
 የመተንፈሻ አካላት ህመሞች (የሳንባ ምች፣ ስር የሰደደ የመተንፈሻ አካላት ህመም፣ በሳንባ ቲቢ ምክንያት የመጣ ጠባሳ፣ እንዲሁም ሌሎች ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ የመተንፈሻ አካላት ህመሞች)
 የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ታማሚዎች
 ከዚህ በፊት በካንሰር ህመም የተያዙ፣
 ለተለያዩ ኬሚካሎች ተጋላጭ በሚያደርጉ የስራ ቦታዎች ውስጥ የሚሰሩ፣
 ከቤተሰብ አባላት ውስጥ የሳንባ ካንሰር ታማሚ ከነበረ ወይም ካለ፡፡

የሳንባ ካንሰር ምርመራ

የሳንባ ካንሰር ምርመራ ከሳንባ ውስጥ ናሙና በመውሰድ የሚካሄድ ሲሆን በሳንባችን ውስጥ የሚኖር እብጠት ወይም የተለየ ለውጥ በምስል ማለትም (የደረት ራጅ ወይም ሲቲ ስካን) በመመልከት ምርመራ ማካሄድ ይቻላል፡፡

የሳንባ ካንሰር ሕክምና

የሳንባ ካንሰር እንደ ካንሰር አይነቱ እንዲሁም እንደሚገኝበት የስርጭት ደረጃ በብዙ መንገዶች ይታከማል፡፡ ይህም፡-
• በቀዶ ሕክምና፣
• በኬሞቴራፒ፣
• በጨረር ሕክምና እና
• በሌሎች ዘመናዊ ህክምናዎች ወይም በእነዚህ ሕክምናዎች ጥምረት መታከም ይችላል

10/02/2024

የጡት ካንሰር

ጡት ካንሰር በዓለማችን በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በአብዛኛው ከ50 ዓመት በላይ በሆኑ ሴቶች ላይ የሚከሰት ቢሆንም በወጣት ሴቶች ላይም የመከሰት እድል አለው፡፡

የጡት ካንሰር አጋላጭ ምክንያቶች

✳️እድሜ እድሜ አየገፋ ሲመጣ በጡት ካንሰር የመያዝ እድልም ይጨምራል
✳️ሴት መሆን ሴት መሆን በራሱ ከወነዶች ይልቅ ለጡት ካንሰር የጋልጣል
✳️በዘር፡ ይህ የካንሰር አይነት በዘር የመተላለፍ ባህሪ ያለው ሲሆን በካንስር ህመሙ የተጠቃው የቤተሰብ አባል እናት ፣ እህት ወይንም ሴት አያት ከሆኑ የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ ይሆናል፡፡
✳️ከዚህ ቀደም የጡት ካንሰር ህመም የነበረባቸው
✳️ልጅ ያልወለዱ ሴቶች ወይም የመጀመሪያ ልጃቸውን እድሜያቸው ከ30 ዓመት በላይ ከሆኑ በኋላ የወለዱ ሴቶች
✳️ጡት ያለማጥባት
✳️ከዚህ ቀደም ጡት አካባቢ የጨረር ህክምና የወሰዱ ከሆነ
✳️ከፍተኛ የአልኮል መጠን ያላቸውን መጠጦች ማዘውተር እና ሲጋራ ማጨስ

የጡት ካንሰር ምልክቶች ምንድናቸዉ?

♦️በጡት ላይ የሚከሰት አብዘኛውን ጊዜ ህመም የሌለው እብጠት
♦️ደም የቀላቀለ ፈሳሽ ከጡት መዉጣት
♦️የጡት ቆዳ ወደ ዉስጥ መሰርጎድ
♦️የጡት ወይም የጡት ጫፍ ህመም
♦️የጡት ጫፍ ወደ ዉስጥ መግባት
♦️የጡት ቆዳ ቀለም ወደ ቀይነት ማድላት
♦️የጡት ቆዳ መሻከር (የብርቱካን ቆዳ ልጣጭ ይመስል)
♦️የብብት ንፊፊት መጠን መጨመር ወይም እርስ በርስ መያያዝ
♦️የሁለቱ ጡት መጠን እኩል ያለመሆን እና የታመመዉ ማበጥ … ይገኙበታል።

የጡት ካንስር ቅድሚያ ካልተደረሰበት እና ህክምና ካላገኘ ወደ ጉበታችን እንዲሁም ወደተለያዩ የሰውነት ክፍሎች በመሰራጨት እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችል የህመም አይነት ሲሆን በሀገራችን ኢትዮጵያም እየተበራከተ ያለ የህመም አይነት ነው፡፡

በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን ማናኛውም አይነት የህመሙ ምልክቶች የታዩት ሠው ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ በቶሎ መፍትሄ ማግኘት ይኖርበታል፡፡
የጡት ካንሠር እንደየደረጃው በቀዶ ጥገና ኬሞ ትራፒ የተለያዩ ኪንን አና ታርጌትድ ቴራፒ የጨር ህክምና መታከም ይችላል:: ደረጃው ሳይጨምር በጊዜ መገኘቱ ደግሞ ከሁሉ የበለጠ የተሻለ የህክምና ውጤት ያስገኛል::

13/01/2024

Check out Tafese Dejene's video.

Address

Jimma

Telephone

+251471112057

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EDEN MCH JIMMA posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to EDEN MCH JIMMA:

Share