Grand-mark medium clinic ግራንድ-ማርክ መካከለኛ ክሊኒክ

  • Home
  • Ethiopia
  • Jinka
  • Grand-mark medium clinic ግራንድ-ማርክ መካከለኛ ክሊኒክ

Grand-mark medium clinic ግራንድ-ማርክ መካከለኛ ክሊኒክ Better health Better tomorrow!

14/11/2025

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ (Marburg Virus Disease - MVD)

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ በሰው ልጆች ላይ የሚከሰት ከባድ እና ገዳይ የሆነ የቫይረስ ደም መፍሰስ ትኩሳት (Viral Hemorrhagic Fever) ነው። ይህ በሽታ እንደ ኢቦላ ቫይረስ ካሉ ተላላፊ በሽታዎች ጋር ተመሳሳይ ቤተሰብ አባል ነው።

መንስኤ
በሽታውን የሚያስከትለው የማርበርግ ቫይረስ ነው።
• የሌሊት ወፎች: ቫይረሱ በተፈጥሮ የሚገኘው የፍራፍሬ የሌሊት ወፎች (Rousettus fruit bats) በተባሉ እንስሳት ላይ ነው። በሽታውም ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሰው የሚተላለፈው የሌሊት ወፎች በሚበዙባቸው ዋሻዎች ወይም ማዕድናት ውስጥ ለረጅም ጊዜ በመቆየት ነው።
• ከሰው ወደ ሰው: በበሽታው ከተያዘ ሰው ደም፣ ፈሳሾች (መራቢያ አካላት፣ ትውከት፣ ሰገራ) ወይም በእነዚህ ፈሳሾች ከተበከሉ ቁሶች ጋር በቀጥታ ንክኪ ሲፈጠር ይተላለፋል።

ዋና ዋና ምልክቶች
ምልክቶቹ በድንገት ይጀምራሉ (ከ2 እስከ 21 ቀናት ባለው የክትባት ጊዜ ውስጥ)።
የመጀመሪያ ምልክቶች
° ከፍተኛ ትኩሳት
• ከባድ ራስ ምታት
• ከፍተኛ የሰውነት መዛል/ድካም
• የጡንቻ ህመም
• ከባድ ውሀማ ተቅማጥ፣ የሆድ ቁርጠት እና ማስታወክ
• የቆዳ ሽፍታ
• የደም መፍሰስ ምልክቶች (ከ5ኛው ቀን በኋላ): ከድድ፣ ከአፍንጫ፣ ከማህፀን፣ በሰገራ ወይም በትውከት ደም መፍሰስ።
• ግራ መጋባት፣ ንዴት እና ድንጋጤ።

ሕክምና አማራጭ
ለማርበርግ ቫይረስ በሽታ በአሁኑ ጊዜ የጸደቀ ልዩ መድሃኒት ወይም ክትባት የለም። ሆኖም የሚሰጠው ሕክምና: በዋነኛነት የህመምተኛውን ሕይወት ለመደገፍ እና ምልክቶችን ለማስታገስ ነው።

• በደም ሥር ፈሳሾችን (IV fluids) እና ኤሌክትሮላይቶችን በመስጠት ሰውነት ውሀ እንዳይደርቅ (Rehydration) መከላከል፡፡
• የህመም ማስታገሻዎችን እና ሌሎች ምልክት ተኮር ህክምናዎችን መስጠት።

መከላከል መንገዶች
• ከእንስሳት ንክኪ መራቅ: የሌሊት ወፎችንና የሌሊት ወፍ የሚበዛባቸውን ዋሻዎች/ማዕድናት ማስወገድ።
• ንጽህና መጠበቅ: እጅን በሳሙናና በውሃ አዘውትሮ መታጠብ ወይም የእጅ ማጽጃ (sanitizer) መጠቀም።
• የታመሙ ሰዎችን አለመንካት: በበሽታው የተጠረጠሩ ወይም የተረጋገጡ ሰዎችን የሰውነት ፈሳሽ (ደም፣ ፈሳሾች) ከመንካት መቆጠብ እና የቅርብ ንክኪን ማስወገድ።

• የጤና ባለሙያዎች ጥንቃቄ: የጤና ባለሙያዎች በሽተኛን ሲያክሙ ተገቢውን የጥበቃ ቁሳቁስ (PPE) መጠቀም እና የአደጋ ጊዜ መከላከያ ዘዴዎችን መከተል።

• አስከሬን አያያዝ: በበሽታው ለሞቱ ሰዎች አስከሬን ንክኪ ያለበት የቀብር ሥርዓት አለማድረግ፤ አስከሬን በልዩ ጥንቃቄ እና ክብር መቀበር።

ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱትን መንገዶች በመከተል ራሳችንን ከበሽታው መከላከል የምንችለው ሲሆን ከጤና ሚኒስቴርና ሌሎች አካላት የሚወጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ ይገባል!

05/08/2025

በክሊኒካችን free T3/T3 free T4/T4 TSH እና የመሳሰሉ እንደሚሰሩ ያውቃሉ? ከአላስፈላጊ እንግልትና ድካም ይገላገሉ!
Better health better tomorrow!

🚨 ከዚህ ቀደም በወጣው ማስታወቂያ መሰረት ባለሙያዎችን አወዳድረን መቅጠራችን ይታወቃል ስለሆነም 1ኛ በላብራቶሪ ቴክኖሎጂስት ወይም ቴክኒሽያን በከ 0 አመት የስራ ልምድ ጀምሮ መወዳደር የሚፈ...
14/06/2025

🚨 ከዚህ ቀደም በወጣው ማስታወቂያ መሰረት ባለሙያዎችን አወዳድረን መቅጠራችን ይታወቃል ስለሆነም 1ኛ በላብራቶሪ ቴክኖሎጂስት ወይም ቴክኒሽያን በከ 0 አመት የስራ ልምድ ጀምሮ መወዳደር የሚፈልግ በስልክ ቁጥር 0923440098 አልያም በአካል ተገኝቶ ማመልከት ይችላል !! ጂንካ

ከታች የተዘረዘሩትን የስራ መደብ መስስፈርቶችን የምታሟሉ በ ስልክ ቁጥር 0923440098 በመደወል እንዲሁም በዓካል በመምጣት መመዝገብ ይችላሉ!👇

ከታች የተዘረዘሩትን የስራ መደብ መስስፈርቶችን የምታሟሉ በ ስልክ ቁጥር 0923440098 በመደወል እንዲሁም በዓካል በመምጣት መመዝገብ ይችላሉ!👇
10/05/2025

ከታች የተዘረዘሩትን የስራ መደብ መስስፈርቶችን የምታሟሉ በ ስልክ ቁጥር 0923440098 በመደወል እንዲሁም በዓካል በመምጣት መመዝገብ ይችላሉ!👇

📝 ቅርበት (Intimacy):::::::::::::::ልጆች ከመብላት እና መጠጣት ባለፈ ከወላጆቻቸው(ከአሳዳጊያቸው) መቀራረብን ይሻሉ፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የወላጅ ልጅ ትስስር በተጠናከረ...
19/03/2025

📝 ቅርበት (Intimacy)
:::::::::::::::

ልጆች ከመብላት እና መጠጣት ባለፈ ከወላጆቻቸው(ከአሳዳጊያቸው) መቀራረብን ይሻሉ፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የወላጅ ልጅ ትስስር በተጠናከረ ቁጥር የልጆች የአእምሮ፣ የጤና፣ የስሜት፣ እና የመስተጋብር ክህሎታቸው ያድጋል፤ይበለፅጋል፡፡

በ Duke's University ለ30 አመታት የዘለቀ ተከታታይ ጥናት በልጅነታቸው በወላጅና ልጅ መካከል ጥብቅ የስሜት ትስስር ኖሯቸው ያደጉ ልጆች ከሌሎች ልጆች የተሻለ በራስ መተማመን ፣ ደስተኛ፣ በት/ቤት የተሻለ ውጤት ማግኘትና ችግር ቢገጥማቸው የመፍትሄ ሰዎች ሆነው ተገኝተዋል።

ምንም እንኳን ሁላችንም በተፈጥሮ የመቀራረብ አቅም (Potential intimacy) የተሰጠን ቢሆንም እንደ ችግኝ በመኮትኮት ማሳደግ የእያንዳንዳችን ድርሻ ነው፡፡

✅ በወላጅ እና በልጅ መካከል ያለውን ቅርርብ ለማሳደግ

1. አብሮ መጫወት
2. በጋራ መብላት
3. ልጆችን መስማት
4. ፍቅርን ማሳየት
5. ጤናማ እና ሚዛኑንን የጠበቀ ገደብ ማድረግ
6. በቤተሰብ የጋራ ጊዜ የማሳለፍ ልማድ ማዳበር

Grand-mark medium clinic

ክፍት የስራ ማስታወቂያ!ሰላም የግራንድ ማርክ ቤተሰቦች ከ ስር በፒክቸር እንደተገለፀው የ ግራንድ ማርክ መካከለኛ ክሊኒክ 👇👉በ ጠቅላላ ሀኪም👉ላብረቶሪ ቴክንሽያን/ ቴክኖሎጂስት👉በነርስ👉ፋርማ...
19/03/2025

ክፍት የስራ ማስታወቂያ!

ሰላም የግራንድ ማርክ ቤተሰቦች ከ ስር በፒክቸር እንደተገለፀው የ ግራንድ ማርክ መካከለኛ ክሊኒክ 👇
👉በ ጠቅላላ ሀኪም
👉ላብረቶሪ ቴክንሽያን/ ቴክኖሎጂስት
👉በነርስ
👉ፋርማሲ
👉ሪሴፕሽኒስት አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል!
ፈጥነው ይመዝገቡ!

#ሼር #ሼር #ሼር

 #ስለጤናዎየኩላሊት ህመም ምልክቶችየኩላሊት ህመም ምልክቶች ከሰው ወደ ሰው ይለያያሉ። መሰረታዊ የህመሙ ዓይነት እና እንደ ክብደቱ  የህመሙ ምልክት ይወሰናል። ምልክቶቹ ብዙውን ጊዜ ፣ ግልጽ...
17/03/2025

#ስለጤናዎ

የኩላሊት ህመም ምልክቶች

የኩላሊት ህመም ምልክቶች ከሰው ወደ ሰው ይለያያሉ። መሰረታዊ የህመሙ ዓይነት እና እንደ ክብደቱ የህመሙ ምልክት ይወሰናል። ምልክቶቹ ብዙውን ጊዜ ፣ ግልጽ ያልሆኑ እና አስደንጋጭ ያልሆኑ ናቸው። ስለሆነም በህመሙ የመጀመሪያዎቹ ደረጃዎች ህመም ስለመኖሩ ለመለየት አዳጋች ነው።
የኩላሊት ህመም በአብዛኛውን ጊዜ የሚታዩ ምልክቶች
• የፊት እብጠት

የፊት ፣ የሆድ እና የእግር እብጠት ብዙ ጊዜ የኩላሊት ህመም ማሳያ ነው። በኩላሊት ህመም ምክንያት የሚከሰት እብጠት አንድ ባህሪይ በመጀመሪያ ከዐይን ሽፋኖቹ በታች የሚስተዋል መሆኑ ነው ፡፡ ይህም በማለዳ በጣም ጎልቶ ይታያል፡፡ ነገር ግን እብጠት የግድ የኩላሊት መጎሳቆልን እንደማያመለክት ልብ ልንለው ይገባል። በተወሰኑ የኩላሊት ህመሞች ውስጥ መደበኛ የኩላሊት ሥራ ቢኖርም እብጠት ይከሰታል (ለምሳሌ ኔፍሮቲክ ሲንድሮም)። ከዚህም ጎን ለጎን መረዳት የሚያስፈልገው ከባድ ህመም ቢከሰትም በአንዳንድ ታካሚዎች ላይ እብጠት ላይታይ እንደሚችል ነው።

• የምግብ ፍላጎት ማጣት ፣ ማቅለሽለሽ ፣ ማስመለስ
የምግብ ፍላጎት ማጣት ፣ በአፍ ውስጥ ያልተለመደ ጣዕምና የምግብ መመገብ ደካማነት የኩላሊት ችግር ያለባቸው ሰዎች የሚያጋጥማቸው የተለመዱ ችግሮች ናቸው። የከፋ የኩላሊት ድክመት በሚኖርበት ጊዜ የማቅለሽለሽ ፣ ማስመልስ እና የአእምሮ ህመም የሚያስከትሉ መርዛማ ንጥረነገሮች መጠን እየጨመረ ይሄዳል።

• ከፍተኛ የደም ግፊት

የኩላሊት ችግር ያለባቸው ታካሚዎች ብዙውን ጊዜ የደም ግፊት ይኖራቸዋል። የደም ግፊት ችግር በወጣትነት ዕድሜ (ከ 30 ዓመት በታች) ከተገኘ ወይም በምርመራው ወቅት የደም ግፊት በጣም ከፍተኛ ከሆነ ምክንያቱ የኩላሊት በሽታ ሊሆን እንደሚችል መጠርጠር ያስፈልጋል።

• የደም ማነስ እና ድክመት

ቶሎ መድከም ፣ ማተኮር አለመቻል እና የቆዳ መገርጣት የደም ማነስ ችግር ያለበት ሰው የተለመዱ ምልክቶች ናቸው። አንዳንድ ጊዜ ሥር የሰደደ የኩላሊት መድከም የመጀመሪያ ደረጃዎች ላይ አንድ ሰው የሚያሳያቸው ብቸኛ ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ። የደም ማነስ ያለበት ሰው በመደበኛ ህክምና በተለምዶ በሚሰጡ መድኃቶች ካልዳነ፣ የኩላሊት ህመም እንዳለበት መጠርጠር ያስፈልጋል።
ከዚህም ተጨማሪ ምልክቶች -ዝቅተኛ የጀርባ ህመም ፣ አጠቃላይ የሰውነት ህመም ፣ እና የእግር ማሳከክ እና ህመም በኩላሊት ህመም ውስጥ ተደጋጋሚ የሚታዩ ምልክቶች ናቸው። በደንብ አለማደግ ፣የቁመት ማጠር እና የግር አጥንት ቀጥ አለማለት በልጆች ላይ የኩላሊት ህመም የሚያሳይ ነው።
የተለመዱ ምልክቶች

1. በሽንት መጠን መቀነስ ፣ በተለያዩ የኩላሊት ህመሞች ውስጥ በጣም የተለመደ ነው።

2. ሽንት በሚወገድበት ወቅት የሚያቃጥል ስሜት ፣ በተከታታይ መሽናት (ያልተለመደ ድግግሞሽ) እንዲሁም ደም ወይም መግል በሽንት ውስጥ ማየት የሽንት ቧንቧ ህመም የሚያሳዩ ምልክቶች ናቸው።

3. የሽንት ፍሰት መዘጋት ሽንትን ለማስተላለፍ ችግር ያስከትላል።

ምንም እንኳን አንድ ሰው ከላይ ከተዘረዘሩት ምልክቶች መካከል የተወሰኑት ሊያሳይ ቢችልም የግድ ሰውዬው በኩላሊት ህመም ተይዟል ማለት ግን አይደለም። ሆኖም እንደዚህ አይነት ምልክቶች ባሉበት ሁኔታ ሀኪምን ማማከር እና የኩላሊት ህመም እና ሌሎች ህመሞች መኖር ወይም አለመኖራቸውን በደም እና በሽንት ናሙና ምርመራዎች ማረጋገጥ የግድ ይላል።

ምንጭ:-- SPHMMC

12/03/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Yonatan Seid, Fikr Show, Getachew Ayalkbet

ነብስ ይማር!
04/02/2025

ነብስ ይማር!

04/02/2025

ሼር! ሼር!👇👇

ክፍት የስራ ማስታወቂያ LAB technologies / technician
በዲግሪ 0 አመት
በዲፕሎማ 1 አመት የስራ ልምድ ያለው በ comment ወይም inbox ያድርግልኝ!

Address

ጂንካ Jinka
Jinka

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Grand-mark medium clinic ግራንድ-ማርክ መካከለኛ ክሊኒክ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram