የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ Aari Zone Health Department ትክክለኛው ገጽ

  • Home
  • Ethiopia
  • Jinka
  • የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ Aari Zone Health Department ትክክለኛው ገጽ

የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ Aari Zone Health Department ትክክለኛው ገጽ የዜጎች ጤና ለሀገር ብልጽግና በሚል መሪህ የጤና ሥርዓቱን አጠናክሮ ማስቀጠል

በኣሪ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ በድሉ ባጊማስ የተመራ ቡድን  በደቡብ ኣሪ ወረዳ የ5ኛው ዙር ፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የመስክ ምልከታ እና ድጋፍ በማድረግ የጋዜር ማህበረሰብ ፋርማሲ ግንባታ ያ...
03/05/2026

በኣሪ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ በድሉ ባጊማስ የተመራ ቡድን በደቡብ ኣሪ ወረዳ የ5ኛው ዙር ፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የመስክ ምልከታ እና ድጋፍ በማድረግ የጋዜር ማህበረሰብ ፋርማሲ ግንባታ ያለበትን ደረጃ ምልከታ አድርገዋል ።

ጂንካ_ሚያዝያ 25/2018(ኣዞጤመ)

በደቡብ ኣሪ ወረዳ የ5ኛ ዙር የፖሊዮ ዘመቻ ሥራ ያለበትን ደረጃ በወረዳው በመገኘት ድጋፍና ክትትል በግብረሃይል ያደረጉ ሲሆን በጌታመር ክላስተር አይካመር ቀበሌ በመገኘት የክትባት ቲሞችን ያበረታቱ ሲሆን መስተካከል ያለባቸውን እንድስተካከሉ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።

የበተሰብ አባላት በክትትሉ ወቅት የፖሊዮ ክትባት እና የወባ ጉዳይ በተመለከተ ምልከታ በማድረግ አስተያየት ተሰጥተዋል ።

የጋዜር ማህበረሰብ ፋርማሲ ግንባታ ያለበትን ደረጃ ምልከታ ያደረጉ ሲሆን የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ በድሉ ባጊማስ ቀሪ የፊንሽንግ ስራዎች በፊጥነት እስከ ግንቦት አጋማሽ እንድጠናቀቅ ለግንባታ ማህበሩ አሳስበዋል ።

የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ሚከተሉትን ገጾች Follow በማድረግ እንድከታተሉን እንጋብዛለን ።

ተለግራም https://t.me/AariZoneHealthDepartment

tiktok.com/

https://www.facebook.com/profile.php?id=61565064929502

03/05/2026
ተደራሽነት እና ጥራት ሥራ ልዩ ትኩረት በመስጠት ቀሪ ቀናት ሊሰራ ይገባል አሉ የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ በድሉ ባጊማስ የ5ኛ ዙር ፖሊዮ ዘመቻ ሁለተኛ  ቀን አፈጻጸም በተገመገሙበት ...
03/05/2026

ተደራሽነት እና ጥራት ሥራ ልዩ ትኩረት በመስጠት ቀሪ ቀናት ሊሰራ ይገባል አሉ የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ በድሉ ባጊማስ የ5ኛ ዙር ፖሊዮ ዘመቻ ሁለተኛ ቀን አፈጻጸም በተገመገሙበት ወቅት ተናገሩ።

ጂንካ_ሚያዝያ 25/2018(ኣዞጤመ)

በኣሪ ዞን በሁሉም ቀበሌያቶች ቤት ለቤት የተጀመረው አምስተኛው ዙር የፖሊዮ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ሁለተኛ ቀን አፈጻጸም ተገምግሟል ።

በሁለተኛ ቀን ከምጠበቀው 27,323 በማከናወን 119% ሕጻናትን ተደራሽ ማድረግ የተቻለ ሲሆን ከአጠቃላይ ዕቅድ አንጻር 48,533 ሕጻናትን የክትባት አግልግሎት በመስጠት 53% ተደራሽ ማድረግ ተችሏል።

ተቀናጅተው ከሚሰሩ ተግባራት መካከል የቆልማማ እግር 3 እና የማህጸን ውልቃት የተገኘ ሲሆን ከአምስት ዓመት በታች የምግብ ዕጥረት ልየታ 62.8% መድረስ ተችሏል ።

የነፈሰጡር እና አጥቢ እናቶች የምግብ ዕጥረት ልየታ 41.2% መለየት ተችሏል ።

የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የመምሪያ ኃላፊ አቶ በድሉ ባጊማሶ የክትባት ተደራሽነት እና ጥራት ሥራዎች በልዩ ትኩረት እንድሰራ አሳስበው የክላስተር ደጋፊዎች ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር ተግባራት እንድመራ እና የተሰጡ ግብረመልሶች እንድተገበሩ በመግለፅ አጠቃለዋል ።

መከተብ የሕጻናት መብት ስሆን ማስከተብ የወላጅ ግደታ ነው።

የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ገጾች እንድትከታተሉን እንጋብዛለን

ተለግራም https://t.me/AariZoneHealthDepartment

tiktok.com/

https://www.facebook.com/profile.php?id=61565064929502

የ5ኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የመጀመሪያው ቀን አፈጻጸም 93% ሕጻናት መከተብ መቻሉ ተገለጿል ።ጂንካ_ሚያዝያ 24/2018(ኣዞጤመ)  የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ የመጀመሪያ ቀን የዘመቻውን አ...
02/05/2026

የ5ኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የመጀመሪያው ቀን አፈጻጸም 93% ሕጻናት መከተብ መቻሉ ተገለጿል ።

ጂንካ_ሚያዝያ 24/2018(ኣዞጤመ)

የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ የመጀመሪያ ቀን የዘመቻውን አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት 22,915 ሕጻናት ለመከተብ ታቅዶ 21,210 በመከተብ 93% ሕጻናትን ከፖሊዮ መከላከል መቻሉን ተመላክቷል።

የተቀናጁ አግልግሎቶችም መከናወናቸውን ተገልጿል ። ዝርዝር መረጃዎችን በቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/AariZoneHealthDepartment
ማግኘት የምችሉ መሆኑን እንገልፃለን ።

የፈደራል ፣የክልል እና አጋር አካላት በመጀመሪያ ቀን ባደረጉት ክትትል የተገኙ ግኝቶች ግብረ መልስ ሰጥተዋል።

በቀረበው ሪፖርት መነሻነት የፖሊዮ አፈጻጸም በመጀመሪያ ቀን 93% የተከናወነው በወረዳ ደረጃ የማካካሻ ሥራዎች እንድሰሩ እና ተቀናጅተው የሚሰሩ ተግባራት ሳይዘናጉ በልዩ ትኩረት እንድመራ እንድሁም በሱፔርቫይዘሮች የተነሱ ጉድለቶች ታርመው የቀን አፈጻጸም በወቅቱ በተደራጀ መልኩ እንድላክ በማሳሰብ የጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ በድሉ ባጊማሶ መድረኩን አጠቃለዋል ።

መከተብ የሕጻናት መብት ስሆን ማስከተብ የወላጅ ግደታ ነው።

በተጨማሪም
https://t.me/AariZoneHealthDepartment
tiktok.com/
https://www.facebook.com/profile.php?id=61565064929502

በኣሪ ዞን ጂንካ ከተማ የ5ኛ ዙር ፖሊዮ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ማስጀመሪያ  ተከናውኗል ።  ሚያዝያ 23/2018(ኣዞጤመ)      በማስጀመሪያ መርሐግብር ላይ የክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲ...
01/05/2026

በኣሪ ዞን ጂንካ ከተማ የ5ኛ ዙር ፖሊዮ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ማስጀመሪያ ተከናውኗል ።

ሚያዝያ 23/2018(ኣዞጤመ)

በማስጀመሪያ መርሐግብር ላይ የክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ አጉነ አሾለ፣ የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ በድሉ ባጊማስ፣ የጂንካ ከተማ ክቡር ከንቲባ አቶ ደግፌ ጌታቸው ፣ የጂንካ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ግርማ ገብሬ እና የክልል የዞን እንድሁም የጂንካ ከተማ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የገርተጵ ቀበሌ ማህበረሰብ በተገኙበት ፕሮግራሙን በይፋ አስጀምረዋል ።

ዘመቻው ለቀጣይ አራት ቀናት የሚቀጥል በመሆኑ ማሕበረሰቡ ከአምስት ዓመት በታች ዕድሜው የሆነ ህጻናት በሙሉ በማስከተብ ኃላፊነት እንድወጡ መልዕክት ተላልፏል ።

መከተብ የህጻናት መብት ሲሆን ማስከተብ የወላጆች ግደታ ነው።

የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ
ጂንካ

01/05/2026
በኣሪ ዞን 5ኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት ከነገ ጀምሮ በዘመቻ ቤት ለቤት እንደሚሰጥ ተገለጸ ጂንካ_ሚያዝያ 22/2018   5ኛ ዙር የልጅነት ልምሻ ክትባት ከነገ ሚያዚያ 23/2018 ዓ/ም ጀምሮ ...
30/04/2026

በኣሪ ዞን 5ኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት ከነገ ጀምሮ በዘመቻ ቤት ለቤት እንደሚሰጥ ተገለጸ
ጂንካ_ሚያዝያ 22/2018

5ኛ ዙር የልጅነት ልምሻ ክትባት ከነገ ሚያዚያ 23/2018 ዓ/ም ጀምሮ በኣሪ ዞን በሁሉም ከተማ አስተዳደርና በወረዳዎች የምሰጥ ስሆን በዚህም ከ91 ሺህ በላይ ህጻናት የፖሊዮ ክትባት እንደሚያገኙ ተገልጿል።

በዚህም የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ የኃላፊ ተወካይ አቶ ታገል ደጉ በዞኑ ባሉ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት ክትባቱ በዘመቻ እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

ይህ ክትባት ለአራት ተከታታይ ቀናት በዘመቻ ቤት ለቤት የሚሰጥ ሲሆን ህፃናት ጤነኛ የአካል አቋም እንዲኖራቸው የሚረዳ ክትባት በመሆኑ ቤተሰቦች ልጆችን በተገቢው ማስከተብ እንዳለባቸው ገልፀዋል።

በመደበኛው የክትባት መርሀ ግብር ተደራሺ ያልሆኑ ወይም ጀምረው ያቋረጡ እድሜያቸው ከ5 አመት በታች የሆኑ ህፃናትን መለየት እና መከተብ እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።

በተጨማሪም ቆልማማ እግር ( Club foot ) ፣ የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ( cleft Lip and palate ) ችግር ያለባቸው ልጆች መለየትና ህክምና እንድያገኙ ማድረግ

ፍስቱላ ( የማህፀን መሸንቆር ) እና የማህፀን ውልቃት ያለባቸው እናቶችን መለየትና ህክምና እንድያገኙ ማድረግ

የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያለባቸው ህፃናት ፣ ነፍሰ ጡር እና አጥቢ እናቶች መለየትና ህክምና አገልግሎት እንድያገኙ ማድረግ

አያይዘውም ከፖሊዮ ክትባት ጎን ለጎን ተቀናጅተው የሚሰሩ በአግባቡ እንድከናወኑ እና የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ማህበረሰቡን በማስተባበር ወባ በሽታን ለመከላከል የሚያግዙ ተግባራትን የወባ መራቢያ ስፍራዎችን ማጽዳትና ያቆሩ ውሃዎችን የማፋሰስ ሥራ እንዲሰሩም አሳስበዋል ።

በመጨረሻም ክትባቱ ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ በመሆኑ ሁሉም ህፃናት የዚህ ክትባት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ወላጆችና አሳዳጊዎች ተገቢውን ትኩረት እንድያደርጉ ጥሪ አስተላልፈዋል ።

ከዞን ማዕከል ለወረዳዎች ድጋፍ የሚያደርግ ቡድን በODK የተደገፈ ሱፐርቪዥን ለመሥራት የተመደቡ ሲሆን ጥራት ያለው ሥራ ሊሰራ እንደምገባ ተመልክቷል ።

የዘመቻው ቅድሜ ዝግጅት ተግባራት በሁሉም መዋቅር ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገምግሟል ።

ህጻናት የመከተብ መብት ሲኖራቸው ወላጆች የማስከተብ ግደታ አለባቸው!!

የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ
ጂንካ

አስፈላጊውን መረጃ ለሚመለከታቸው የማህበረሰብ ክፍል በመስጠት የአይን ሕመም ተጠቂዎች ህክምና እንድያገኙ እንድደረግ እናሳስባለን ።
29/04/2026

አስፈላጊውን መረጃ ለሚመለከታቸው የማህበረሰብ ክፍል በመስጠት የአይን ሕመም ተጠቂዎች ህክምና እንድያገኙ እንድደረግ እናሳስባለን ።

መከተብ የልጆች መብት ማስከተብ የወላጆች ግዴታ ነው!የአፍሪካ የክትባት ሳምንትከሚያዚያ 16-22/2018 ዓ.ም
27/04/2026

መከተብ የልጆች መብት ማስከተብ የወላጆች ግዴታ ነው!
የአፍሪካ የክትባት ሳምንት
ከሚያዚያ 16-22/2018 ዓ.ም

የወባ በሽታ ለመከላከልና ቁጥጥር ሥራዎች ለማጠናከር  የባለሙያው እና የአመራሩ ቁርጠኝነት  እንደሚያስፈልግ የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ  አቶ በድሉ በጊማሶ በIMS/PHOC ግምገማ ወቅት ተ...
25/04/2026

የወባ በሽታ ለመከላከልና ቁጥጥር ሥራዎች ለማጠናከር የባለሙያው እና የአመራሩ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ በድሉ በጊማሶ በIMS/PHOC ግምገማ ወቅት ተናገሩ፡፡
ሚያዝያ 17/2018 (ኣዞጤመ)

የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና የጤና ተግባራትን በማስተባበሪያ ማዕከሉ የሳምንት 16 ት/2026 ሪፖርቱን ገምግሟል፡፡

ከቀረበው ሪፖርት አንጻር የወባ ጫና በዚህ ሳምንት ከዎባ ኣሪ ወረዳ በስተቀር በሁሉም ወረዳ እና ከተማ አስተዳደሮች ጭማሪ የተመዘገበ ሲሆን በጂንካ ከተማ አስተዳደር እና በደቡብ ኣሪ ወረዳ በከፍተኛ ደረጃ የጨመረ ሲሆን እንደ ዞን ከባለፈው ሳምንት ጋር ሲነጻጸር በ526(41%) ከፍ ያለ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል ፡፡

በጂንካ ከተማ አሰተዳደር ፤በጋዘር ከተማ እና በደቡብ ኣሪሪ ወረዳ ወባን የመከላከል ስራ ማህበረሰቡን በማስተባበር እየተሰራ ሲሆን በዚህም መሰረት ቤት ለቤት አሳሳ እና ቅኝት ስራ 4993 ቤቶች በላይ ተደራሽ በማድረግ 559 የወባ ምልክት ትኩሳት ያለቸውን ልየታ በማድረግ ወደህክምና ማዕከል በማቆራኘት እንድታከሙ ተደርጓል ።

3862 ካሬ ሜትር ውሃ ያቆረ ቦታ በህበረተሰብ ተሳፍፎ ማዳፈንእና ማፋሰስ የተሰራ ቢሆንም አሁን ያለውን የወባ በሽታ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የህብረተሰብ ተሳትፎን በሁሉም ወባማ ቀበሌያት በማጠናከር እንዲሁም አመራሩም ቁርጠኛ በመሆን ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋት አሁን የጀመርነውን የወባ መከላከል ስራ አጠናክርን መቀጠል አንዳለብን የአሪ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ በድሉ ባጊማሶ በማሳሰብ መድረኩን አጠቃለዋል ፡፡
ለሎች ሳምንታዊ አፈጻጸም እና ተግባራት በመገምገም አቅጣጫ ተቀምጧል ።

የዜጎች ጤና ለሀገር ብልጽግና
የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ
ጂንካ _2018

"ወባን ለማጥፋት እንነሳ፣ አሁንም እንችላለን!"የዓለም ወባ ቀን!ሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም
25/04/2026

"ወባን ለማጥፋት እንነሳ፣ አሁንም እንችላለን!"

የዓለም ወባ ቀን!
ሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም

Address

South Ethiopia
Jinka

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ Aari Zone Health Department ትክክለኛው ገጽ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share