Central Ethiopia Region Yem Zone Saja General Hospital

Central Ethiopia Region Yem Zone Saja General Hospital Saja General Hospital is Committed to provide Quality Healthy Care Up On Communicable and Noncommunicable Diseases in Hospital care.

18/09/2025
የሳጃ አጠቃላይ ሆስፒታል የክረምት በጎ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል...(ሳጃ፤ጳጉሜ 5/2017 ዓ.ም)በዛሬው ዕለት የሳጃ አጠቃላይ ሆስፒታል ከጤና አገልግሎት ጎን ለጎን ለሳጃ ከተማ አስተዳደር ቀጠ...
10/09/2025

የሳጃ አጠቃላይ ሆስፒታል የክረምት በጎ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል...

(ሳጃ፤ጳጉሜ 5/2017 ዓ.ም)

በዛሬው ዕለት የሳጃ አጠቃላይ ሆስፒታል ከጤና አገልግሎት ጎን ለጎን ለሳጃ ከተማ አስተዳደር ቀጠና ሶስት ለሚገኙ ተማሪዎች እና ለቤተሰብ የሚሆን የትምህርት ቁሳቁሶች፣ የንፅህና መጠበቂያዎች እና የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል::

ሆስፒታሉ በርካታ ማህበራዊ አገልግሎት እየሰጠ ከመሆኑ በተጨማሪ ተመሣሣይ ድጋፎችን ወደፊት ማድረጉንም ይቀጥላል።

ምንጭ፦የሆስፒታሉ ማህበራዊ አገልግሎት ክፍል

በየም ዞን በሳጃ አጠቃላይ  ሆስፒታል የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራ  ተጠናክሮ ቀጥሎዋል።  ነሐሴ:- 8/2017 ዓ/ም  በዛሬው ዕለት ከሆስፒታሉ  ደረጃ ለውጥ ጋር ተያይዞ ተቋሙን ለአገልግሎት ም...
14/08/2025

በየም ዞን በሳጃ አጠቃላይ ሆስፒታል የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሎዋል።

ነሐሴ:- 8/2017 ዓ/ም

በዛሬው ዕለት ከሆስፒታሉ ደረጃ ለውጥ ጋር ተያይዞ ተቋሙን ለአገልግሎት ምቹ፣ሳቢና ውብ ለማድረግ በሳጃ ከተማ አስተዳዳር እና በግለሰብ ባለሃብት ድጋፍ ተደርጎ ኮረት የማንጠፍ ስራ ተከናውኗል ።

ለስራው መሳካት ከተማ አስተዳደሩ ካደረገው ድጋፍ ባሻገር ወጣት ባለሀብት ኢንጅነር ሳሙኤል ወንድሙ በሙያቸው ከመደገፍ ጎን ለጎን ገልባጭ መኪና ተባብሯል ።

ኮረት የማንጠፍ ስራው ላይ የሆስፒታሉ ሰራተኞች ተሳትፎ በማድረግ የበጎ አድራጎት ስራውን አከናውኗል።

ይህ በሆስፒታሉ እየታዬ ያለው የመደጋገፍ እና የመተባበር እሴት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል።

የመጨረሻም የሆስፒታሉ አመራሮች እና አስተባባሪ አካላት ለተደረገው በጎ ድጋፍ የሳጃ ከተማ አስተዳደርን እና ኢንጅነር ሳሙኤል ወንድሙን አመስግኗል ።

ምንጭ -ሆስፒታሉ የአገልግሎት ጥራት ዪኒት

07/08/2025

ማስታወቂያ
________

ለጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1362/2017 ማስፈፀሚያ በተዘጋጁ ረቂቅ መመሪያዎች ላይ የባለድርሻ አካላት እና የሕዝብ አስተያየት ለመሰብሰብ የወጣ ማስታወቂያ፡

በጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1362/2017 አንቀጽ 58(2) በተሰጠው ስልጣን መሠረት የጤና ሚኒስቴር ለአዋጁ ማስፈፀሚያ ይሆኑ ዘንድ የሚከተሉትን መመሪያዎች አዘጋጅቷል፡፡

1) የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና አተገባበር መመሪያ፤
2) የኃይጅን እና የአካባቢ ጤና አጠባበቅ መስፈርችን እና ግዴታዎችን ለመደንገግ የወጣ መመሪያ፤
3) የጤና አገልግሎት ይዘት ያለዉ ማስታወቂያ ዘገባ እና የኪነጥበብ ስራ አዘገጃጀትና አሰረጫጨት መመሪያ፤
4) የተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ አተገባበር ሥርዓት መመሪያ፤
5) የጤና ፋይናንስ ሥርዓት አተገባበር መመሪያ፤
6) በመሳሪያ ላይ ብቻ የተመሰረተ የአተነፋፈስ ሥርዓት የሚቋረጥበትን አግባብ ለመወሰን የወጣ መመሪያ፤
7) የምግብና መጠጥ እና ጤና ነክ ተቋማት ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ መመሪያ፤
8) የጤና የተግባር ትምህርት አሰጣጥ መመሪያ፤
9) የጤና መረጃ አስተዳደር ሥርዓትን ለመዘርጋት የወጣ መመሪያ፤

ከላይ በተዘረዘሩት ረቂቅ መመሪያዎች ላይ አስተያየት መስጠት የሚፈልግ፡-

1) ማንኛውም ባለድርሻ አካል የጽሑፍ አስተያየት ለሚኒስቴሩ እንዲያቀርብ የሚጠይቀው ደብዳቤ በደረሰው በ 15 ቀናት ውስጥ፤
2) ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ በሚኒስቴር መ/ቤቱ ድህረ-ገፅ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ፤

በጤና ሚኒስቴር ድህረ-ገፅ https://www.moh.gov.et/en/node/532 ላይ አስተያየት መስጫ ቅፅ የትኛው ረቂቅ መመሪያ ላይ አስተያየት መስጠት የምትፈልጉ የረቂቅ መመሪያውን ስም በመጥቀስ አስተያየቱን ሞልቶ መላክ ወይም በሚኒስቴር መ/ቤቱ የሕግ ክፍል በአካል በመገኘት ማስገባት የሚችል መሆኑን እያሳወቅን የረቂቅ መመሪያዎቹን ቅጂ ከሚኒስቴሩ ድህረ-ገፅ ላይ በነፃ ማውረድ የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

በሆስፒታሉ  #የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ ሥራ ሲከናወን ውሏል*********************************************(ሳጃ፤ሐምሌ ፣ 29/2017ዓ.ም)ሳጃበሳጃ አጠቃላይ ሆስፒታ...
05/08/2025

በሆስፒታሉ #የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ ሥራ ሲከናወን ውሏል
*********************************************

(ሳጃ፤ሐምሌ ፣ 29/2017ዓ.ም)

ሳጃ

በሳጃ አጠቃላይ ሆስፒታል የክረምት ወራት በጎ አድራጎት ሥራ በሆስፒታሉ ሲከናወን ውሏል።
ከነዝህም ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ከመለየትና ከማከም ጎን ለጎን የአከባቢ ፅዳት እና ያቆረ ውሀን የማፋሰስ ሥራ ተከናውኗል።

በተለይም ቁጥሩ እየጨመረ የመጣውን የደም ግፊት በሽታን በማስተማር፣ በመለካት እና ማህበረሰቡ የራሱን ጤና እንዲጠብቅ ከማሳወቅ በተጨማሪ ምርመራ እና ህክምና ተከናውኗል።

በመቀጠል ማህበረሰቡ ያለበትን አከባቢ ፅዱ እና ለጤና ምቹ እንዲሆን ከአከባቢ ፅዳት ሥራዎች ጎን ለጎን እየጣለ ካለው ዝናብ አንፃር የወባ ወረርሽኝ እንዳይከሰት በሆስፒታሉ አከባቢ ያቆረ ውሀ የማፍሰስ ሥራ ተከናውኗል ።

ማህበረሰቡ በየአካባቢው ያቆረ ውሀን በማፍሰስ እራሱን ከወባ በሽታ እንዲከላከል እና ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲሳተፍ በማለት የበጎ አድራጎት አባላት ጥሪ አድርገዋል።

18/07/2025
17/07/2025

Address

Yem Saja
Saja
2212009

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Central Ethiopia Region Yem Zone Saja General Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category