Dr. Abrham Mulugeta Obstetrician and Gynecologist

Dr. Abrham Mulugeta Obstetrician and Gynecologist Obstetrician & Gynecologist | Women’s Health Specialist

Dedicated to providing comprehensive, evidence-based care for women at every stage of life.

15/04/2026

በምጥ ወቅት "የእንሽርት ውሃ መደፍረስ" ምንድነው? ማወቅ ያለባችሁ 3 ወሳኝ ነጥቦች!

Meconium Stained Amniotic Fluid" during labor: 3 things every mom MUST know!

12/04/2026

በምጥ ለመውለድ የሚረዱ 5 ቁልፍ እንቅስቃሴዎች! 🤰✨

​ጤናማ እና ቀለል ያለ የወሊድ ጊዜ እንዲኖርዎት ይፈልጋሉ? በሳይንሳዊ መንገድ የተረጋገጡ እና የዳሌ ጡንቻዎችን በማዝናናት ፅንሱ ትክክለኛ ቦታ እንዲይዝ የሚረዱ 5 ዋና ዋና ስፖርቶችን በዚህ ቪዲዮ አቅርበናል፦

​1️⃣ ፈጣን እርምጃ (Brisk Walking)

2️⃣ ስኳትስ (Deep Squats)

3️⃣ የኳስ ላይ እንቅስቃሴ (Stability Ball)

4️⃣ የዳሌ እንቅስቃሴ (Pelvic Tilts)

5️⃣ የቢራቢሮ ስትሬች (Butterfly Stretches)

11/04/2026

በኦፕራስዮን ምን ያህል ጊዜ መዉለድ ይቻላል!?

08/04/2026

06/04/2026

በእርግዝና የመጨረሻ ሳምንታት: ቴምር መመገብ ምጥን ያቀላል?? በምጥ የመዉለድን እድልንስ ይጨምራል?

02/04/2026

and infertility!? 🤔

Postpill እና መሃንነት፦ እውነታውና ስጋቱ!"ፖስትፒል ደጋግሜ ብወስድ መሃን እሆናለሁ?" የሚለው ጥያቄ በብዙ እህቶቻችን ዘንድ ትልቅ ጭንቀት ነው። ዛሬ ይህንን ጉዳይ በሳይንሳዊ መንገድ ...
02/04/2026

Postpill እና መሃንነት፦ እውነታውና ስጋቱ!

"ፖስትፒል ደጋግሜ ብወስድ መሃን እሆናለሁ?"

የሚለው ጥያቄ በብዙ እህቶቻችን ዘንድ ትልቅ ጭንቀት ነው። ዛሬ ይህንን ጉዳይ በሳይንሳዊ መንገድ እንፈትሸዋለን።

✅ እውነታው ምንድን ነው?
ፖስትፒል (Postpill) በውስጡ የያዘው 'Levonorgestrel' የተባለ ሆርሞን ሲሆን፣ ስራው እንቁላል የሚወጣበትን ጊዜ ለጥቂት ቀናት ማዘግየት ብቻ ነው። ሆርሞኑ በሰውነታችን ውስጥ አይቆይም፤ ወዲያውኑ ተፈጭቶ ስለሚወጣ ማህፀን ወደ መደበኛ ስራው ይመለሳል።

ስለዚህ ኪኒኑ ራሱ በቀጥታ መሃንነት አያመጣም።

⚠️ ታዲያ ስጋቱ የት ጋር ነው?

አደጋው ያለው በሁለት በተዘዋዋሪ ምክንያቶች ነው፦
1. የቱቦ መዘጋት (Tubal Scarring): ፖስትፒል የምንወስደው ጥንቃቄ የጎደለው ግንኙነት ሲኖር ነው። ይህ ደግሞ ለኢንፌክሽኖች (STIs) ያጋልጣል። ኢንፌክሽኑ ወደ ላይ በመውጣት የማህፀን ቱቦን ካቆሰለና ጠባሳ ካመጣ ለዘላቂ መሃንነት ሊዳርግ ይችላል።

2. ከማህፀን ውጭ እርግዝና (Ectopic Pregnancy): ኪኒኑ ሳይሰራ ቀርቶ እርግዝና ከተከሰተ፣ ፅንሱ ከማህፀን ውጭ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው። ይህ ደግሞ በድንገተኛ ቀዶ ጥገና ቱቦው እንዲወጣ ሊያደርግ ይችላል።
💡 የዶክተር ምክር፦
ፖስትፒል ለድንገተኛ አደጋ እንጂ እንደ መደበኛ መከላከያ የሚያገለግል አይደለም። ለጤናችሁ ዋስትና የሚሆን ዘላቂ እና አስተማማኝ የወሊድ መከላከያ ዘዴዎችን ይጠቀሙ።

👨‍⚕️ ዶ/ር አብርሃም ሙሉጌታ (Senior OBGYN)
ለተጨማሪ የጤና መረጃዎች ቻናላችንን ይቀላቀሉ!

31/03/2026

30/03/2026

በእርግዝና ወቅት ሊወገዱ የሚገቡ 3 ዋና ዋና የምግብ አይነቶች! ብዙ ጊዜ እናቶች "ምን ልመገብ?" ብለው ይጠይቃሉ፤ ነገር ግን ከምግብ ምርጫ እኩል "ምን አይነት ምግቦችን ላስወግድ?" የሚለ...
29/03/2026

በእርግዝና ወቅት ሊወገዱ የሚገቡ 3 ዋና ዋና የምግብ አይነቶች!

ብዙ ጊዜ እናቶች "ምን ልመገብ?" ብለው ይጠይቃሉ፤ ነገር ግን ከምግብ ምርጫ እኩል "ምን አይነት ምግቦችን ላስወግድ?" የሚለውን ማወቅ ለፅንሱ ደህንነት ወሳኝ ነው።

​በጥናት እና በህክምና መመሪያዎች መሰረት ሊጠነቀቁባቸው የሚገቡ 3 ዋና ዋና ነጥቦች፦
​1️⃣ ጥሬ ወይም በደንብ ያልበሰሉ የእንስሳት ተዋፅኦዎች (Raw/Undercooked foods)
​ምክንያቱ፦ ጥሬ ስጋ (ክትፎ)፣ አሳ ወይም በደንብ ያልበሰለ እንቁላል እንደ Salmonella እና Toxoplasmosis ያሉ ተዋሲያን ሊኖሩባቸው ይችላሉ።
​ጉዳቱ፦ እነዚህ ባክቴሪያዎች በእናትየው ላይ ከባድ ህመም ከመፍጠራቸውም በላይ በፅንሱ የሰውነት አካል እድገት ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ።
​⚠️ መፍትሄ፦ ስጋም ሆነ እንቁላል በደንብ መብሰሉን ያረጋግጡ።
​2️⃣ ያልፈላ ወተት እና ለስላሳ አይቤዎች (Unpasteurized Dairy)
​ምክንያቱ፦ ያልፈላ (Unpasteurized) ወተት እና ከእሱ የሚዘጋጁ አይቤዎች Listeria የተባለ ባክቴሪያ ሊኖራቸው ይችላል።
​ጉዳቱ፦ ይህ ባክቴሪያ የእንግዴ ልጅን (Placenta) ሰንጥቆ የመግባት አቅም ስላለው ፅንስ ማስወረድ ወይም ያለጊዜ መውለድን ሊያስከትል ይችላል።
​⚠️ መፍትሄ፦ ሁልጊዜ ወተት መፍላቱን እና አይቤዎች በንፅህና መዘጋጀታቸውን ያረጋግጡ።
​3️⃣ ከፍተኛ ሜርኩሪ ያላቸው አሳዎች (High-Mercury Fish)
​ምክንያቱ፦ አንዳንድ የአሳ አይነቶች ከፍተኛ የሜርኩሪ መጠን ይይዛሉ።
​ጉዳቱ፦ ሜርኩሪ በፅንሱ የአንጎል እና የነርቭ ስርአት እድገት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ሊያሳድር ይችላል።
​⚠️ መፍትሄ፦ አሳ ለጤና ጠቃሚ ቢሆንም፣ የሚገዙት አሳ አይነት ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል።

ዶ/ር አብርሃም
ማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት
+251926272535
ሻሸመኔ: ፈያ ጠቅላላ ሆስፒታል

28/03/2026

Dr.Abrham Mulugeta (Obstetrician and Gynecologist @ Shashemene)

26/03/2026

# postpartum

Address

Shashemene

Website

https://t.me/pregnancyandbirthsafty, http://abrham.obgyn/, https:

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr. Abrham Mulugeta Obstetrician and Gynecologist posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share