Dr. Ashebir Medium Clinic-AMC, Wolaita Sodo

Dr. Ashebir Medium Clinic-AMC, Wolaita Sodo We stand for your health! Your Home!

30/03/2022

ከወሊድ በዃላ ደም መፍሰስ(POSTPARTUM HEMORRHAGE) ።

ከወሊድ በዃላ የደም መፍሰስ(postpartum hemorhage) ምንድን ነው?

✓ከወሊድ በዃላ ደም መፍሰስ (Postpartum hemorrhage )የምንለው በመደበኛ (vaginal birth ) የምትወልድ እናት >=500ml ወይም በቀዶ ጥገና ለወለደች እናት ደግሞ >=1000ml ወይም የ Hematocrit መጠን ከመነሻ(baseline) >10 % ሲወርድ ወይም የፈሰሰው ደም እጅግ ወሳኝ የሆኑት የአንድን ሰው ጤንነት የሚገለፁልን መሰረታዊ መለኪያዎች(vital signs) መሆን ከሚገባው በላይ ወይም በታች እንዲሆን ካደረገው ነው።

ምክንያቶቹ ምን ምን ናቸው?
✓ከወሊድ በዃላ የሚፈጠር ደም መፍሰስ ዋነኛው ምክንያት ልጅ ከተወለደ በዃላ የማህፀን ወደ ቦታ አለመመለስ(Uterine atony)፣በማህፀን አካባቢ አደጋ(trauma)፣በምጥ ጊዜ በማህፀን በር እና በብልት አካባቢ መሰንጠቅ(cervical and vaginal laceration)፣የደም መርጋት ችግር(Coagulopathy)፣ኢንፌክሽን(infection)፣የእንግዴ ልጅ ከማህፀን ሳይወጣ ሲቀር(retained placenta) ዋነኛዎቹ ሲሆኑ ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች ተጋላጭነትን የሚጨምሩት ምክንያቶች ለምሳሌ በእርግዝና ጊዜ የደም ግፊት፣የደም ማነስ ችግር፣የህፃኑ ክብደት መሆን ከሚገባው በላይ መሆን፣ከአንድ በላይ ፅንስ መፀነስ ይጠቀሳሉ።

እናቶች ምን አይነት ምልክት ሊያሳዩ ይችላሉ?
✓እነዚህ እናቶች በፈሰሰው ደም መጠን ምልክት ሲያሳዩ ከነዚህም መካከል ከመጠን በላይ በብልት የደም መፈሰስ፣የድካም እና የማዞር ስሜት፣ብርድ ብርድ ማለት፣የታችኛው የሆድ አካል ላይ የህመም ስሜት፣የልብ ምት መጨመር፣የሰውነት መገርጣት፣የደም ግፊት መቀነስ፣እራስን መሳት፣የሽንት መጠን መቀነስ

እነዚህን እናቶቻችን እንዴት እናክማቸው?
✓ዋናው እና ትኩረት መስጠት ያለብን መከላከል ላይ ሲሆን ይህንንም ዋንኛው አንድ እናት ጤና ተቋም ሄዳ ነው መውለድ ያለባት ከዛም ልትወልድ ሶስተኛ ደረጃ ምጥ ላይ እያለች ያለው የህክምና ስርአት (Active management of third stage of labor) በብቁ የጤና ባለሙያ መሆን አለበት።
✓እጅግ በጣም ወሳኙ ነገር እያንዳንዱ ሆስፒታል የ PPH protocol ሊኖረው ይገባል።ከዚህ በተጨማሪ ሁሉን ያማከለ ባለሙያ(multidisciplinary team) ሁልጊዜም ዝግጁ ሆነው መቀመጥ አለበት።
✓ከዚያም ይህ ችግር በሚያጋጥምበት ጊዜ እረዳታ በአፋጣኝ መጠየቅ(Shout for help) እንለዋለን።
ወዲያውን የመጀመሪያ እርዳታ ማግኘት ስላለባት ወዲያውኑ እናትዬዋን በጀርባ አሰተኝተን ኦክስጅን ካስፈለጋት መስጠት፣በዚህ ሰአት ሁለት የደም ስር መሰመር ማድረግ(secure bilateral iv line) እና በ protocol መሰረት በቂ የደም ዝውውር እስኪኖራት ድረስ ፈሳሽ እየሰጠን በዚህ መሀል ወዲያውኑ ደም መፍሰሱ መቆም ስላለበት መንስኤውን ለማወቅ መሞከር እና ሚፈሰውን ደም ማቆም ይጠቅብናል።
✓ምክንያቱ ከታወቀ ደም መፍሰሱን በprotocol መሰረት ማከም ለምሳሌ ማህፀን ማሳጅ(uterine massage) ማድረግ፣መድሀኒቶች ለምሳሌ Oxytocine,Tranxemic Acid እንደ አስፈላጊነቱ መስጠት ፣ማህፀን ላይ መጠንኛ ግፊት በማድረግ መጫን(Bimanual compression)፣ሆድ ላይ ያለውን ትልቁን የደም ቧንቧ መጫን(Aortic compression)፣ማህፀንን በቀዶ ጥገና ማውጣት(Hysterectomy)፣የቀረ ወይም ያልወጣ የእንግዴ ልጅ (retained placenta) ካለ ማውጣት፣ኢንፌክሽን ካለ ፀረ ባክቴሪያ መስጠት ዋና የህክምና አካል ናቸው።

እኛ ሀገር ላይ በብዛት የጤና ተቋም በሌለበት ቦታ በተለይ በገጠሪቷ ኢትዮፕያ ላይ ልጅ የሚወለደው በቤት ውስጥ ስለሆነ የህክምና ተቋም ላይ የሚመጡት አማራጭ ሲጠፋ እናብዙ ደም ከፈሰሰ በዃላ ነው።ይህም እነደ ባህል ያልቀረ ነገር ግን የብዙ እናቶቻችን ሂወት አሁንም ድረስ እየቀጠፈ ስለሆነ ባለንበት ቦታ ሁሉም እናቶች የጤና ተቋም መጥተው እንዲወልዱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መሰራት አለበት ብዬ አምናለሁ።
©ሰላም ለናንተ ይሁን!!

Address

Wolaita Sodo, Back Of Stadium(near To Bus Station)
Sodo

Telephone

+251994141248

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr. Ashebir Medium Clinic-AMC, Wolaita Sodo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Dr. Ashebir Medium Clinic-AMC, Wolaita Sodo:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram