18/02/2025
የቁጫ ሕዝብ ሲተርት "እፍረት ከሌለ እህል አይታጣም" ይላል። ተረቱም ለሆዳም የተተረተ ነበር !!!
====+=+++++++++
የጋሞ ዞንና የቁጫ መዋቅር አመራሮች በተለይም ከ6ቱ ቀበሌያት የተውጣጡና የነሱ ተላላኪዎች በቁጫ ሦስቱ መዋቅሮች ውስጥ ምን እየሠሩ ነው?
1. ሕዝቡን የዱቡሻ ባህል ነው ብለው የመቃብር አፈር በጥብጠው አጠጥተዋል፣
2. የኃይማኖት መሪዎችንና ተከታዮቻቸውን በኃይል ለጣዖታቸው አሰግደዋል፣
3. የሕዝቡን ሀብትና ንብረት ያለምንም ሕግ መሠረት ዘርፈዋል፣
4. ለጣዖታቸው አልሰግድም ያለውን እጅና እግር ሰብረዋል፣
5. ራስህን ቁጫ ነኝ ትላለህ ብለው ከቤቱ፣ ሀብቱና ንብረቱ አፈናቅለዋል፣
6. የማኅበራዊ ማግለልን ፈፅመዋል፣
7.በሕዝብ ተወካዮች ላይ የግድያ ሙከራ ፈፅመዋል፣
8. ሌሎች በሰው ልጅ ላይ ሊፈፀሙ ቀርቶ ሊታሰቡ የማይገቡ ተግባራትን ፈፅመዋል።
ከላይ በተጠቀሱትና በሌሎች ሲዖላዊ ድርጊቶቻቸው ለተጎዳውና በሕይወት ላለው የቁጫ ሕዝብ ያበረከቱት አስተዋፅዖ:-
1. የሰላምበር ከተማን አመዳም ማድረግና በስሙ የማምለኪያ አፀድ ወይም ጣዖት መትከል፣
2. የሰላምበር ከተማን ከየትኛውም የፈርጅ ደረጃ እንዲወጣ ማድረግና ለማዘናጊያና ገንዘብ ዝርፊያ በመብራት ስም ዘመቻ መክፈት፣
3. የሰላምበር ከተማ ሕዝብ በሰቆቃና በግዳጅ የጣዖት አምልኮ ውስጥ እንዲገባ ተደርጎ ገንዘቡን እየተዘረፈ ግን በንፁህ ውኃ እጦት እንዲሰቃይ ማድረግ፣
4. በቁጫ አልፋ ወረዳ የጫባ ሦንባ ቀበሌ በሠራው ዳስ ምረቃ ላይ የዞኑን ዋና አስተዳዳሪን ጨምሮ በ20 መኪና ከ100 በላይ ሰው መታደምና የሕዝቡን ጥሪት መበዝበዝ፣
5. ሦስቱንም የቁጫ መዋቅሮች ከየትኛውም ልማት ዳር ማውጣትና የሕዝቡን ኪስ ማራቆት፣
6. በየወሩ ዞኑ በሚያመርተው ዋንጫ ቢንበሻበሽም ምንም የሚጨበጥና የሚዳሰስ ነገር መጥፋት፣
7. የሕዝብና የመንግሥት እንዲሁም የከተማና የገጠር መሬት መቸብቸብና መክበር፣
8. በሕገወጥ ቅጥር የ6 ቀበሌያት ሰዎችን መቅጠርና ከሌሎች የቁጫ መዋቅሮች ለወጉ ማኖ ማስነካት፣
9. የመንግሥት ሠራተኛውን ሆነ ብሎ ማስራብ፣ ከሥራ ማፈናቀል፣ ከደመወዝና ደረጃ ዝቅ ማድረግ፣
10. በሁሉም ተቋማት ሙስናና ብልሹ አሠራር መደበኛ ሥራ ማድረግ፣
11. ሌሎች ኢሰብዓዊ ተግባራትን እየፈፀሙ መኖራቸውን ለመደበቅና አጀንዳ ለማስቀየስ እንዲሁም ከተጠያቂነት ለመዳን በመከጀል የ2005 ነጠላ ዜማ "ደባል አጀንዳ" የሚል ማቀንቀን ይገኙበታል።
ይህንን ሁሉ ኢሰብዓዊ እና ኢሞራላዊ ድርጊት የፈፀሙት የብልፅግና ፓርቲ አባላትና አመራሮች ነን በሚል ነው። ነገር ግን የብልፅግና ፓርቲ እንደዚህ አይነት የወረደ ተግባር ፈፅሞ እኔ የብልፅግና ፓርቲ አባል ነኝ የሚለውን አላውቅም እያለ ነው።
ስለዚህ በቁጫ በሦስቱ መዋቅሮች ግልፅ የሆነ የሕግ ተጠያቂነት እንዲሰፍን ይጠበቃል።
አብረው ያስተኟቸውና የቀበሯቸው የቁጫ መዋቅሮች!
የብልፅግና ተሀድሶ/Reform/ ያነሳቸው ይሆን? የምናየው ይሆናል፥ ይጠበቃልም።