28/06/2025
ሠላም ዶ/ር። ልጀ ከተወለደ 1ወር ሆኖታል። ከ9 ቀኑ ጀምሮ ህክምና እየተከታተለ ነው። የምርመራ ውጤቱ biliary atresia ያሳያል ሰርጀሪ ሊያስፈልገው ይችላል ብለውኛል።ምን ይሻለኛል?(የወላጅ ጥያቄ)
🌡ውድ ጠያቂያችን ልጅዎ biliary atresia እንዳለበት ማወቅ ለእርስዎ ከባድ፣ ግራ የሚያጋባ እና ስሜታዊ የሚያደርግ ሊሆን እንደሚችል እንረዳለን።
🌡ምናልባት እነዚህ ጥያቄዎች በውስጥዎ ሊመላለሱ ይችላሉ፡
"ይህ ማለት ምን ማለት ነው? በኛ ስህተት የመጣ ነው? ምን ብናደርግ ይሻላል? ቀጥሎ ምን ሊሆን ይችላል? ወዘተ "
🌡ላረጋግጥልዎ የምፈልገው እርስዎ ብቻዎን አይደሉም - ብዙ ወላጆች ልጆቻቸው ተመሳሳይ ችግር ያጋጠማቸው እንዳሉ እና ችግሩ መታከም እንደሚችል ነው።
🌡ከዚህ በታች ለምነሱ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ሁኔታውን ለመረዳት፣ ምን አይነት ምልክቶች እንደሚኖሩት፣ እንዴት እንደሚታከም እና ከሁሉም በላይ ደግሞ ተስፋ እንዲሰጡዎት ይረዳዎታል ብለን እናስባለን።
✍ጥያቄ 1: Biliary Atresia ምንድን ነው?
🌡Biliary atresia አዲስ በሚወለዱ ሕፃናት ላይ ያልተለመደ የሐሞት ቦይ(Biliary System) ችግር ሲሆን በጉበት ውስጥ ቆሻሻን ለማስወገድ የሚረዱት የሐሞት ቱቦዎች ሲዘጉ ወይም ሳይፈጠሩ ሲቀሩ የሚከሰት ችግር ነው።
🌡ይህም ሐሞት በጉበት ውስጥ ይጠራቀማል፣ ወደ ሰውነት ይሰራጫል(ሰውነት ቢጫ ይሆናል) እና በጊዜ ሂደት ጉበት ላይ ጠባሳን ያስከትላል።
🌡ከዛም ጉበትን ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ያደርጋል!
✍ጥያቄ 2: የሐሞት ፍሰት ለምን ጠቃሚ ነው?
💊ሐሞት ከተመረተ ከ2 ሳምንታት በላይ የሚቆይ ሲሆን ስብን ለመፍጨት እና ቆሻሻን ለመሸከም የሚረዳ ከጉበት የሚመረት ፈሳሽ ነው።
💊በተዘጋ የሞት ቱቦ ምክንያት በትክክል መፍሰስ በማይችልበት ጊዜ ጉበት ላይ ይጠራቀማል ፣ ጉበት ያብጣል እና ይጎዳል።
💊 በመጨረሻም ካልታከመ ጉበት ይደክማል።
✍ጥያቄ 3: መንስኤው ምንድን ነው?
💉ትክክለኛው መንስኤ አይታወቅም
💉 በእርግዝና ወቅት ወላጆች ካደረጉት ወይም ካላደረጉት ነገር ጋር የሚገናኝ አይደለም።
💉ከዘር የሚተላለፍ ወይም ተላላፊ ችግርም አይደለም።
✍ጥያቄ 4: የሚታዩ ምልክቶች ምን ምን ናቸው?
🩺ከ2 ሳምንታት በላይ የሚቆይ የቆዳ ቢጫ መሆን
🩺ፈዛዛ ግራጫ ወይም ነጭ ሰገራ
🩺ጠቆር ያለ ቢጫ ሽንት
🩺የሆድ መነፋት
🩺የሰውነት ክብደት አለመጨር
✍ጥያቄ 5: ሕክምናው ምንድን ነው?
💉ብቸኛ ሕክምናው ቀዶ ጥገና ነው
💉ይህም "Kasai Procedure" ተብሎ ይጠራል( የሐሞት ቱቦዎችን በትንሹ አንጀት መተካት)
💉 በምርመራ ከተረጋገጠ ከ3 ወር እድሜ በፊት በትክክል ከተሰራ ውጤቱ አሪፍ ይሆናል።
✍ጥያቄ 6: ወላጆች ምን ማድረግ አለባቸው?
💊የሕክምና ምክሮችን በጥብቅ መከታተል
💊መደበኛ ክትትል እና የደም ምርመራዎችን በተገቢው ጊዜ ማድረግ
💊የኢንፌክሽን ምልክቶችን ማወቅ ና ቶሎ እንዲታከሙ ማድረግ
💊የሰውነት ብጫነትን ወይም የሰገራ/የሽንት ቀለም ለውጦች መከታተል
💊እንደ ባለሙያ ምክር ትክክለኛውን አመጋገብ መከተል
💊በጣም ከተጨነቁ የስነ ልቦና ድጋፍ ለማግኘት እርዳታ መጠየቅ ምንም ችግር የለውም።
ያስታውሱ፡
🌡ብቻዎትን አይደሉም
🌡ብዙ ቤተሰቦች በዚህ ሁኔታ ውስጥ አልፈዋል
🌡ወቅቱን የጠበቀ ህክምና፣ ድጋፍ እና እንክብካቤ እንዲደረግላቸው በማድረግ የመትረፍ እድል አላቸው።
ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ እንሰራለን!!!
አዘጋጅ:
ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ:
የህፃናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም
Dr. Saleamlak Tigabie:
MD, Pediatric Surgeon, FCS-ECSA
👉ለበለጠ መረጃ ፣ ቀጠሮ ለመያዝ እና ነፃ የምክር አገልግሎት :
📱0911441651
👉Gmail: saleamlaksati@gmail.com
👉(በግል ለማናገር፣ ፎቶ ለመላክ)
https://t.me/DrSaleamlakT
https://www.facebook.com/ዶር-ሳለአምላክ-ጥጋቤ-Pediatric-Surgeon-100878625359706/