Wolkite University Comprehensive Specialized Hospital

  • Home
  • Wolkite University Comprehensive Specialized Hospital

Wolkite University Comprehensive Specialized Hospital Wolkite University Comprehensive Specialized Hospital

መጋቢት 10/2018 ዓ.ምየወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛ ዒድ አል ፊጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ፤ በዓ...
19/03/2026

መጋቢት 10/2018 ዓ.ም
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛ ዒድ አል ፊጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ፤ በዓሉም የሰላም፣ የጤና፣የፍቅር እና የመተሳሰብ በዓል እንዲሆን መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡
ዒድ ሙባረክ!

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ተማሪዎች ማህበር ከኢትዮ ጤና አሊያንስ እና ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕረሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጋር በመተባበር በጉብሬ አባ ፍራንሶ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤ...
16/03/2026

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ተማሪዎች ማህበር ከኢትዮ ጤና አሊያንስ እና ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕረሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጋር በመተባበር በጉብሬ አባ ፍራንሶ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚገኙ ሴት ተማሪዎች እና በሆስፒታላችን ውስጥ ላሉ ታካሚዎች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ልገሳ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም በተሳካ ሁኔታ አካሂደዋል።
ፕሮግራሙ በማህበረሰባችን ውስጥ የሴቶችን የጤና ግንዛቤ የሚያበረታቱ የንፅህና መጠበቂያ ፓዶችን እና የልብስ ማጠቢያ ሳሙናዎችን በማቅረብ ወጣት ልጃገረዶችን ለመደገፍ ያለመ ነው።
ይህንን ተነሳሽነት በገንዘብ በመደገፍ እና ፕሮግራሙን እውን ለማድረግ ላደረጉት የአስተዳደር አካላት ልባዊ ምስጋናችንን መግለጽ እንወዳለን።
ይህንን ፕሮግራም ለማደራጀት እና ተግባራዊ ለማድረግ ጊዜያቸውን እና ጉልበታቸውን ለሰጡ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ተማሪዎች ማህበር አባላት እና የሆስፒታሉ አመራሮች ሁሉንም እናመሰግናለን።
Wokite university medical students association in collaboration with Ethio health alliance and Wolkite University Comprehensive Specialized Hospital successfully conducted a pad donation and awareness program for female students at Gubre Aba Franso High School and for patients at our Hospital.
The program aimed to support young girls by providing sanitary pads and laundry bar soaps promoting women’s health awareness in our community.
We would like to express our sincere gratitude to the administrative bodies that supported this initiative financially, making this program possible.
We are also grateful to all wolkite university medical student association member and the hospital leaders who dedicated their time and effort to organize and implement this program.

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በጉብሬ ክ/ከተማ ከሚገኙ ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር በመተባበር በህክምና ላይ ለሚገኙ ታካሚዎች እና አስታማሚዎች ታላቁን የረመዳን ወር ም...
12/03/2026

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በጉብሬ ክ/ከተማ ከሚገኙ ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር በመተባበር በህክምና ላይ ለሚገኙ ታካሚዎች እና አስታማሚዎች ታላቁን የረመዳን ወር ምክንያት በማድረግ የኢፍጣር ፕሮግራም አከናውኗል፡፡

እንኳን ደስ ያላችሁ፤ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለመጀመርያ ጊዜ እስፔሻሊስት ሀኪሞችን በውስጥ ደዌ (Internal Medicine) ትምህርት ክፍል 6 እና በህፃናት...
10/03/2026

እንኳን ደስ ያላችሁ፤ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለመጀመርያ ጊዜ እስፔሻሊስት ሀኪሞችን በውስጥ ደዌ (Internal Medicine) ትምህርት ክፍል 6 እና በህፃናት (Pediatrics) ትምህርት ክፍል 5 ተፈታኞች ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በመጡ ልምድ ባላቸው ሀኪሞች ተፈትነው በአመርቂ ውጤት አጠናቀዋል። ለመምህራን እና ለተመራቂ ሀኪሞች እንኳን ደስ ያላችሁ። በቅርብ ቀናት የቀዶ ህክምና እና የማህፀንና ፅንስ ረዚደንት ሀኪሞች የምናስመርቅ ይሆናል።

‹‹50ኛ ዓመት የሴቶች ድምፅ ለእኩልነት እና ለበለፀገች ኢትዮጵያ›› በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ115ኛ ጊዜ በሃገር አቀፍ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማ...
09/03/2026

‹‹50ኛ ዓመት የሴቶች ድምፅ ለእኩልነት እና ለበለፀገች ኢትዮጵያ›› በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ115ኛ ጊዜ በሃገር አቀፍ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በድምቀት ተከበረ፡፡
በእለቱም ወደ ሆስፒታሉ ለመጡ ታካሚዎች የሴቶች እኩልነትና መብት ማረጋገጥ እንዲሁም በሁሉም ዘርፍ ሴቶችን ማበረታታት የማህበረሰቡ እና የተቋማት ትልቅ ሀላፊነት መሆኑን የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጠ፡፡

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የመጨረሻ ዓመት ለውስጥ ደዌ (Internal Medicine) እና ለህፃናት ሕክምና (Pediatrics) ስፔሻሊቲ ሃኪሞች የተግባር ፈተ...
09/03/2026

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የመጨረሻ ዓመት ለውስጥ ደዌ (Internal Medicine) እና ለህፃናት ሕክምና (Pediatrics) ስፔሻሊቲ ሃኪሞች የተግባር ፈተና በዛሬው ዕለት እየተሰጠ ይገኛል።
ለፈተናው የተቀመጡ ሪሲደንስ ሃኪሞቻችን ሁሉ መልካም ውጤት እንመኛለን።

‹‹የሲቲ ስካን ምርመራ›› ምንነት እና ጥቅሞች ሲቲ ስካን (CT- scan) በጥራት እና በፍጥነት በመስራት የተዋጣለት ማሽን ነው፡፡ ሲቲ ስካን በሰውነታችን ውስጥ በርካታ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን...
06/03/2026

‹‹የሲቲ ስካን ምርመራ›› ምንነት እና ጥቅሞች
ሲቲ ስካን (CT- scan) በጥራት እና በፍጥነት በመስራት የተዋጣለት ማሽን ነው፡፡
ሲቲ ስካን በሰውነታችን ውስጥ በርካታ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን ከነሱም መካከል የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው
1. በአደጋ ጊዜ የተከሰተ የደም ስር እና አጥንት ጉዳት ካለ መኖሩን እና መጠኑን ለማወቅ ይጠቅመናል።
2. የተለያዩ በሽታዎችን ለመመርመር እና ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ ያገለግላል። ለምሳሌ በሰውነታችን ውስጥ የሚወጡ እጢዎች እና ካንሰር እባጮችን ለማየት ፣ ኢንፌክሽን ካለ ለማየት፣ እና የሳንባ ጤና እክሎችን ለማወቅ ያስችለናል።
ለምርመራ የተለያዩ ናሙናዎችን ከሰውነታችን በትክክል ለመውሰድ ይጠቅመናል፡፡
3. የደም መርጋት ወይም መፍሰስ እንዲሁም የልብ ጤና ችግሮች ካሉ ለማየት ይጠቅመናል።
በተጨማሪም ህክምና ላይ ላለ ሰው የህክምና ለውጡን ለማወቅ እና ክትትል ለማድረግ እንጠቀመዋለን ።
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለማህበረሰቡ ከሚሰጣቸው ዘርፈ ብዙ የህክምና አገልግሎቶች ውስጥ የራዲዮሎጂ ምርመራ ክፍል አንዱ ነው፡፡
በራዲዮሎጂ ምርመራ ክፍል ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች፡-
 የአልትራሳውንድ ምርመራ (ultrasound)
 ራጅ (digital x-ray) ምርመራ
 የሲቲ ስካን ምርመራ (CT-SCAN) የመሳሰሉት አገልግሎቶችን በራዲዮሎጂስት ሃኪም እና በራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂስት ባለሙያዎች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

በወልቂጤ ዩኒቨርሰቲ ኮምፕሬሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እየተሰጠ የነበረው የነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና አገልግሎት በስኬት ተጠናቀቀ።ሆስፒታሉ ከእንግሊዝ ሃገር ከመጡ የአይን ስፔሻሊስ...
27/02/2026

በወልቂጤ ዩኒቨርሰቲ ኮምፕሬሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እየተሰጠ የነበረው የነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና አገልግሎት በስኬት ተጠናቀቀ።
ሆስፒታሉ ከእንግሊዝ ሃገር ከመጡ የአይን ስፔሻሊስት ሃኪሞች ጋር በመተባበር ለ5 ተከታታይ ቀናት ህክምናው ሲሰጥ የቆየ ሲሆን በአገልግሎቱም ከ200 በላይ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ታካሚዎች ተጠቃሚ ሆነዋል። ህክምናውን ያገኙ ታካሚዎች በተደረገላቸው የህክምና አገልግሎት መደሰታቸውን ገልፀው በሆስፒታሉ ቆይታቸው ለተደረገላቸው መልካም አቀባበል እና እንክብካቤ እንዲሁም የህክምና አገልግሎት ለሰጡአቸው ለአይን ስፔሻሊስት ሃኪሞች እና ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ወልቂጤ ዩኒቨርሰቲ ኮምፕሬሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

‹‹ታላቅ ደስታ እና ምስጋና ከታካሚ አንደበት››ምስኪያ አህመድ ትባላለች የቀቤና ልዩ ወረዳ የወሸርቤ ቀበሌ ነዋሪ ናት፤ ነገሩ እንዲህ ነው፤በእርግዝናዋ ወቅት ሁለት ወር ከአስራ አምስት ቀናት...
27/02/2026

‹‹ታላቅ ደስታ እና ምስጋና ከታካሚ አንደበት››
ምስኪያ አህመድ ትባላለች የቀቤና ልዩ ወረዳ የወሸርቤ ቀበሌ ነዋሪ ናት፤ ነገሩ እንዲህ ነው፤በእርግዝናዋ ወቅት ሁለት ወር ከአስራ አምስት ቀናት ጀምሮ እርግዝናዋ እንደ ወትሮው ምቾት እንዳልተሰማት እና ትቸገር እንደነበር በመግለፅ እስከ 6ኛ ወር ድረስ በወሸርቤ ጤና ጣቢያ ክትትል ስታደርግ መቆየቷንም ትናገራለች፤ እዛው በክትትልዋ ወቅት አልትራሳውንድ ተነስታ የጤና ባለሙያዎች ወ/ሮ ምስኪያን ላለማስደንገጥ ሲባል እርግዝናዋ 3 መንትያ ልጆች ናቸው ላለማለት 2 መንታ ልጆች ናቸው ብለው ሲነግሩኝ ፈጣሪ የፈቀደው ይሁን በማለት እራሷን እንዳበረታታች ትናገራለች፡፡ ለ2ኛ ጊዜ በሌላ ቀን ድጋሚ አልትራሳውንድ ስነሳ ግን ውጤቱ እንደቀድሞው መንታ ልጅ የሚል ቃል ሳይሆን እንደውም ሶስት መንትያዎች እንደሆኑ ተነገረኝ፤እንደገና ለማረጋገጥ ስል ወደ ወልቂጤ ከተማ መጥቼ ፌነት መካከለኛ ክሊኒክ አልትራሳውን ስነሳ በድጋሚ 3 መንትያዎች መሆናቸውን አረጋገጡልኝ ያለችው ምስኪያ ትልቅ መደናገጥ እና ፍረሃት እንደገጠማትም ትገልፃለች፡፡
ቀጥሎም ፌነት ክሊኒክ ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እንድሄድ መክረውኝ ቀጥታ እዚህ መጣሁ ሃኪሞች እና የጤና ባለሙያዎችም በጥሩ ሁኔታ ተቀብለውኝ ክትትል እና ልዩ እንክብካቤ እያደረጉልኝ ለአንድ ሳምንት እዚሁ ሆስፒታል አልጋ ይዤ ቆየሁኝ ስትል ሃሳቧን የገለፀች ሲሆን ከዚያም በፊት ስፈራ እና ስጨነቅ የነበረው ሁሉ ጠፍቶ የመውለጃ ጊዜዬን መጠባበቅ ጀመርኩኝ፤ቀጥሎም ከአንድ ሳምንት በኋላ ለመውለድ የተወሰኑ ጊዜያት እንደሚቀሩኝ ሃኪሞች ነግረውኝ ወደ ቤቴ ተመለስኩኝ እያለች ወ/ሮ ምስኪያ ሃሳቧን ቀጠለች ከዚያም በየሳምንቱ ክትትሏን እዚሁ ሆስፒታል አደረገች፡፡የመውለጃ ጊዜዋ ሲደርስ ቀጥታ እዚሁ ሆስፒታል መጥታ በጥሩ አቀባበል እና መስተንግዶ አቆይተውኝ የመውለጃ ጊዜዬ ደርሶ በቀዶ ህክምና የካቲት 14/2018 ዓ.ም ሶስት መንትዮችን ለመታቀፍ በቃሁኝ፡፡
ወ/ሮ ምስኪያ ስትናገር በዚህ ሁሉ የረዳኝን ፈጣሪዬን አመሰግናለሁ! ቀጥሎም የሆስፒታሉ ሃኪሞች፣ የጤና ባለሙያዎች እና የሆስፒታሉ ሰራተኞችን እኔን ከተቀበሉኝ ጊዜ ጀምሮ እስከ መውለጃዬ ቀን ለተደረገልኝ ልዩ እንክብካቤ ምስጋናዬን ማቅረብ እፈልጋለሁ ያለችው ምስኪያ አሁንም በሆስፒታሉ ልዩ ትኩረት እና እንክብካቤ እየተደረገላት ትገኛለች፡፡
በመጨረሻም ወ/ሮ ምስኪያ ከቀዶ ህክምናዋ በኋላ ወደ ፅኑ የጨቅላ ህፃናት ክትትል ክፍል ውስጥ በጥሩ ሁኔታ እንክብካቤ እየተደረገላት እና ህፃናቶቹም በጥሩ ጤንነት እንደሚገኙ በጨቅላ ህፃናት ክትትል ክፍል የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች ጠቅሰው የህፃናቶቹ ሁኔታ ያለ ጊዜያቸው የተወለዱ በመሆናቸው ክብደታቸው 2.3፣1.9 እና 1.5 ኪ.ግ መሆናቸውንም ባለሙያዎች ገልፀዋል፡፡
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

‹‹ታላቅ የደስታ ስሜት እና የምስጋና መልእክት ከታካሚ አንደበት››ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አባት ያሲን መሃመድ ይባላሉ በቸሃ ወረዳ የፌቅ ጠረቅ ወድሮ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው፡፡አንድ አይኔ ማየት ...
27/02/2026

‹‹ታላቅ የደስታ ስሜት እና የምስጋና መልእክት ከታካሚ አንደበት››
ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አባት ያሲን መሃመድ ይባላሉ በቸሃ ወረዳ የፌቅ ጠረቅ ወድሮ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው፡፡አንድ አይኔ ማየት ካቆመ ድፍን አምስት አመት አስቆጥሯል፤ በማለት ለማየትም ሲቸገሩ እንደሰነበቱ ገልፀው አሁን ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ባመቻቸው የነፃ የህክምና አገልግሎት እኔም ተጠቃሚ በመሆኔ እጅግ ደስ ብሎኛል ያሉት አባት ለተደረገላቸው የህክምና አግልግሎትና ልዩ እንክብካቤ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የአቶ ያሲን መሃመድ አስታማሚ ወጣት ነኢማ ረሻድ ትባላለች በአካባቢያችን በፌቅ ጠረቅ ወድሮ ቀበሌ ይህን እድል አግኝተው የተመለሱ ሰዎች አይተን ለማንኛውም እድላችን እንሞክር ብለን ከረፈደ ነው የመጣነው ያለችው ነኢማ እንደመጣን ግን መልካም አቀባበል ተደርጎልን አገልግሎቱን ማግኘት በመቻላችን በጣም ተደስቻለሁ በማለት አስተያየቷን ሰጥታ ለተደረገላቸው የህክምና አገልግሎት እና እንክብካቤ የአይን ሃኪሞችን እና ባለሙያዎችን አመስግናለች፡፡

‹‹ታላቅ የደስታ ስሜት እና የምስጋና መልእክት ከታካሚ አንደበት››ናስር አማን ይባላሉ  የቸሃ ወረዳ ዱቢሳ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው፤ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላዝድ ሆስፒታል የአይን...
27/02/2026

‹‹ታላቅ የደስታ ስሜት እና የምስጋና መልእክት ከታካሚ አንደበት››
ናስር አማን ይባላሉ የቸሃ ወረዳ ዱቢሳ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው፤ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላዝድ ሆስፒታል የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ይሰጣል የሚል በሆስፒታሉ ድረ-ገፅ የተለቀቀውን መልእክት ከልጄ ሰምቼ ነው የመጣሁት ብለዋል፤ታዲያ እኚህ አባታችን ካሁን በፊት አይናቸው እየታመመ ስራ ለመስራትም ሲቸገሩ ለብዙ አመታት እንደቆዩ በመግለፅ አሁን ግን ይህን መልካም እድል ለመጠቀም በመብቃቴ ደስታዬ ወደር የለውም ብለው አስተያየት ሰጥተው ይህንን እድል ላመቻቸላቸው የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና ህክምናውን ላደረጉላቸው የአይን ሃኪሞች እንዲሁም የጤና ባለሙያዎችን አመስግነዋል፡፡ ፡፡
አስታማሚያቸው ወጣት ሳዳም ናስር ይባላል አባቴን ለማሳከም ስመጣ ብዙ የምቸገር እና አገልግሎቱም በቶሎ የሚሳካ መስሎ አልታየኝም ነበር፤ ነገር ግን ያለምንም ውጣ ውረድ እና እንግልት ይህን ትልቅ እድል አግኝተን መጨረሳችን እጅግ አስደስቶኛል በማለት ሆስፒታሉንና አጠቃላይ በሆስፒታሉ የህክምና አገልግሎት ለሰጡት የአይን ሃኪሞች እና የአይን ክፍል ባለሙያዎችን አመስግኗል፡፡ በቀጣይም ተመሳሳይ የሆነ እድል ለሌሎችም የሚመቻችበት ሁኔታ ቢኖር መልካም እንደሆነ አስተያየቱን ሰጥቷል።

በአጥንትና መገጣጠሚያዎች ላይ የሚያጋጥሙ ውስብስብ የጤና ችግሮችን ለመቅረፍ እና ለህብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንዲቻል በባህላዊ መንገድ የሚሰጡ ህክምናዎች ዘመናዊ የህክምና ሳይንስ...
26/02/2026

በአጥንትና መገጣጠሚያዎች ላይ የሚያጋጥሙ ውስብስብ የጤና ችግሮችን ለመቅረፍ እና ለህብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንዲቻል በባህላዊ መንገድ የሚሰጡ ህክምናዎች ዘመናዊ የህክምና ሳይንስ መርሆዎችን በተከተለ እና በማይጣረስ መልኩ መሆን እንዳለበት ተገለጸ።
ዜጎች በተለያዩ ምክንያቶች ለሚያጋጥማቸው የአካል ጉዳት የጤና እክል በተገቢው መንገድ ማከም እንዲቻል ባህላዊ የአጥንት ህክምና ባለሙያዎች ፣ በተለያዩ የጤና ተቋማት ለሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች እና ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን የኢትዮጵያ የአጥንት እና መገጣጠሚያ ሃኪሞች ማህበር ከቦሳድ ፕሮጀክት እንዲሁም ከወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጋር በመተባበር ለሶስት ቀናት የቆየ ስልጠና በወልቂጤ ከተማ ሰጥቷል።
ቦሳድ ሃገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ቡድን በሃገራችን በተለምዶ ከሚከሰቱ የአጥንት እና መገጣጠሚያ ጉዳቶች ጋር በተያያዘ በሚመጡ የተለያዩ ውስብስብ የጤና ችግሮች ከዘመናዊ የህክምና ሳይንስ ጋር በማጣጣም የተለያዩ ሙያዊ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል።
ማህበሩ በዘመናዊ እና በባህላዊ የአጥንት ህክምና መሃል ያሉ ልዩነቶችን ለማጥበብና ዘመኑ የደረሰበትን የህክምና ሳይንሰ በተከተለ መልኩ ህክምናውን እንዲሰጡም በትኩረት እየሰራ ይገኛል።
የአጥንት ህክምና ጥንቃቄ ከልተደረገለት ለውስብስብ የጤና ችግር የሚያጋልጥ እንደሆነ የህክምና ባለሙያዎች ጠቁመዋል።
በስልጠና መድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ የሃላፊው ተወካይ ጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶች ጥራት እና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ባዴ በአጥንትና መገጣጠሚያዎች ላይ የሚያጋጥሙ ውስብስብ የጤና ችግሮችን ለመቅረፍ እና ለህብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንዲችል በባህላዊ መንገድ የሚሰጡ ህክምናዎች ዘመናዊ የህክምና ሳይንስ መርሆዎችን በተከተለ እና በማይጣረስ መልኩ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።
ዘመናዊ ህክምና ከመሰጠቱ አስቀድሞ ሃገር በቀል እውቀትን መሰረት በማድረግ ባህላዊ የአጥንትና የመገጣጠሚያ ህክምና ሲሰጥ እንደነበር ያስታወሱት አቶ አለማየሁ ተጠያቂነት ያለበት አሰራር ለመዘርጋት እና ወቅቱ የደረሰበትን የህክምና አገልግሎት ለመስጠት በዘመናዊ የህክምና ሳይንስ መደገፍ ይገባልም ብለዋል።
ባህላዊ የአጥንት ስብራትና ውልቃት ህክምና የሚሰጡ ወጌሻዎች ተጠያቂነት ባለው መልኩ ስራዎችን ለመስራት ህጋዊ ፍቃድና ምዝገባ ማድረግ አለባቸውም ብለዋል።
በመድረኩ በዘመናዊና በባህላዊ የአጥንትና የመገጣጠሚያ እንዲሁም የውልቃት ህክምና መካከል ያሉ ችግሮችን በተመለከተ የተለያዩ ወርክ ሾፖች በዶክተር አብረሃም ገብሬ፣ በዶክተር ዳንኤል እንዳለ፣ በዶክተር ቶሎሳ ዲንሳ እና በዶክተር ደሳለኝ ታሉ ቀርበው በተሳታፊያን ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአጥንትና መገጣጠሚያ ትምህርት ክፍል የፕሮጀክቱ ስልጠና አስተባባሪ አቶ አንዷለም የኋላሸት በበኩላቸው የባህላዊ የአጥንት ህክምና አግኝተው ለተወሳሰቡ የጤና ችግር የተጋለጡ የማህበረሰብ ክፍሎችን ዘመናዊ ህክምና እንዲያገኙ የሚቻልበትን ሁኔታ ማመቻቸትና ግንዛቤ መፍጠር የቦሳድ አላማ መሆኑን ገልጸዋል።
ባህላዊ ህክምና ከሚሰጡ ባለሙያዎች እርስበርስ የመታዋወቅና ተግባራቸውን ከዘመናዊ ህክምና ጋር አስተሳስሮ መስጠት እንዲቻል መሰል ስልጠናዎች ፋይዳቸው የጎላ መሆኑን የጠቆሙት ደግሞ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአጥንትና የመገጣጠሚያ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሃኪም ዶክተር አብረሃም ገብሬ ናቸው።
በመድረኩ የተገኙት የባህላዊ ህክምና የሚሰጡ ባለሙያዎች (ወጌሻዎች) በሰጡት አስተያየት ስልጠናው መካሄዱ በሙያው ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት እድል የሚፈጥር ስለመሆኑ አንስተዋል።
ታካሚዎች አገልግሎት ለማግኘት ሲመጡም በአቅም ልክ ህክምና መስጠት ከአቅም በላይ ሲሆን ደግሞ ተጨማሪ የጤና ጉዳት እንዳያስከትል ወደ ዘመናዊ ህክምና ተቋም መላክ ከኛ ይጠበቃልም ብለዋል አስተያየት ሰጪዎቹ።

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolkite University Comprehensive Specialized Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Wolkite University Comprehensive Specialized Hospital:

  • Want your practice to be the top-listed Clinic?

Share