Gazer Primary Hospital

Gazer Primary Hospital Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gazer Primary Hospital, Health & Wellness Website, Jinka.

GPH is found in South Ethiopia Region Ari zone Gazer town administration , Started at Nov 10/2010 EC a 17km from Jinka town.The Gazer hospital is found 1568 meter above sea level and located at latitude of 5.89˚N and longitude of 36.58˚

28/11/2025

ከማህበረሰቡ በጤና ተቋም ግቢ ለሚኖሩት ለወላድ እናቶች የሚደረግ የድጋፍ ስነ ሥርዓት
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን በጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

‎ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን በጋዘር ከተማ አስተዳደር የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ  የሆስፒታሉ RRT ቡድን እስካሁን በሆስፒታሉ ውስጥ እየተሰራው ባለው ስለ Marberg Virus (MVD...
28/11/2025

‎ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን በጋዘር ከተማ አስተዳደር የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ የሆስፒታሉ RRT ቡድን እስካሁን በሆስፒታሉ ውስጥ እየተሰራው ባለው ስለ Marberg Virus (MVD) መከላከል እና መቆጣጠር ዙርያ ላይ ከአባላቱ ጋር ያለበትን ሁነታ ገመገመ።

‎ ህዳር 19/2018_ጋዘር

‎ የ PHEM Focal እና የ RRT ቡድን ፀሃፊው አቶ ጣለው ዛሬ ህዳር 19/2018 ዕለታዊ የቅድሜ መከላከል ሥራዎችን ርፖርት አቅርበው ከዚያ ውስጥ በሙቀት መለኪያ መሳሪያ (Thermometer) ከተለኩት ውስጥ ከ38°C በላይ የሆኑት 2 ታካሚዎች ብቻ ስሆኑ እነዚህም ሌላ ምልክት ስለለላቸው በሌላ ህክምና ታክመው መውጣታቸውን በርፖርት ተገልጿል።ሌሎች የመከላከል ሥራዎችን ባለሙያዎች በተመደቡበት እየሰሩ እንዳሌ ተቀምጧል።
‎ የሆስፒታሉ ሜድካል ዳይርክተር የሆኑት ዶክተር ወንድሙ ገዛኸኝ በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ያለው ቅድሜ ጥንቃቀ እንዳለ ሆኖ የ Task force አወቃቀሩን በጠበቀ መንገድ መስራት እንደሚገባ አስቀምጧል።
‎ ከአብዛኛው አባላት የተነሳ ጥያቄ ክልሉ ሙያዊ ሥልጤናዎችን በሆስፒታሉ እስካሁን ከ 50 ባለሙያዎችን እና ከ20 በላይ የሚሆኑት የጋራ አገልግሎት ሰጪ ባለሙያዎችን አሰልጥኗል።ይህንን በማመስገን ከሎጅስትክ ጋር ያለው ክፍተት ግን ትኩረት አልተሰጠም ብለዋል።ምክንያቱም ጋዘር ከተማ ከጅንካ ከተማ በ17 ኪ.ሜ ላይ ስለሚገኝ ወረርሽኑ ሆስፒታል ላይ መገኘቱ ስለማይቀር ተቋሙ በራሱ ግዥ ያደረገውን አልኮል፣ሳንታይዘር፣Gloves እና ሌሎች ግብዓቶችን እየተጠቀመ ስለሆኔ ትኩረት እንድሰጥ አቅጣጫ ተቀምጧል።
‎ በስተመጨረሻም የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ እና የ RRT ቡድን ሰብሳቢ አቶ ያዕቆብ ጥላሁን ይሄ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን ዘውትር እየተወያዬ ርፖርት ለሚመለከታቸው አካላት እንደሚያቀርብ አሳስበዋል።

‎ ማርቨርግ ቫይረስን በጋራ እንከላከል፣
‎ ከመነካካት፣ከመጨባበጥ ራሳችን እናግልል።

‎ የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

‎    ዛሬ ህዳር 19/2018 በጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ማቆያ ቤት ውስጥ ለሚኖሩ ወላድ እናቶች የጋዘር ቀበሌ ልዩ ልዩ ድጋፎችን አድርገዋል።‎ በዋናነት እንጨት፣በቁጥር 1...
28/11/2025

‎ ዛሬ ህዳር 19/2018 በጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ማቆያ ቤት ውስጥ ለሚኖሩ ወላድ እናቶች የጋዘር ቀበሌ ልዩ ልዩ ድጋፎችን አድርገዋል።
‎ በዋናነት እንጨት፣በቁጥር 18 የልብስ ሳሙና፣በቆሎ በኩንታል 1፣ የተለያዩ ቅመማ ቅሜሞች እና የጓሮ አታክልት፣ በጥሬ ገንዘብ 8000(ስምንት ሽ ብር) በጋዘር ቀበሌ አስተዳደር በአቶ ተፈሪ አስናቄ በኩል ገቢ ተደርጓል።
‎ የጋዘር ቀበሌ አስተዳደር አቶ ተፈሪ አስናቄ ይህንን ድጋፍ ላስተባበሩት ጤና ኤክስተንሽኖች፣ለልማት ቡድን አመራሮች አመስግነዋል።አያይዘውም ይህ ድጋፍ ቀጣይነት እንድኖረው እና ያልተሳተፉ ልማት ቡድኖች በቀጣይ ገቢ እንድያደርጉ በትኩረት አሳስበዋል።
‎ የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ያዕቆብ ጥላሁን ይህንን ድጋፍ ላደረጉት ለጋዘር ቀበሌ ማህበረሰብ ምስጋና አቅርበዋል።

‎ አንድም እናት በወልድ ምክንያት መሞት የለባትም!!

በጋዘር ከተማ አስተዳደር በጎህ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እና ጎርከር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ላይ የማርበርግ ቫይረስ ለመከላከል ቅድመ ጥንቃቄ እንድያደርጉ ለተማሪዎች ግንዛቤ ተሰጠ።             ...
28/11/2025

በጋዘር ከተማ አስተዳደር በጎህ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እና ጎርከር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ላይ የማርበርግ ቫይረስ ለመከላከል ቅድመ ጥንቃቄ እንድያደርጉ ለተማሪዎች ግንዛቤ ተሰጠ።

ህ ዳ ር 19/2018 ዓ.ም
===== ጋዘር =====
በቅርቡ በጂንካ ከተማ በተከሰተው የማርበርግ (Marburg) ቫይረስ በተከሰተው ምክንያት አስመልክተው ጥንቃቄ እንድያደርጉ ለተማሪዎች ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል።

በዚህም መሰረት የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሜድካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ወንድሙ ገዛኸኝ ለተማሪዎቹ ስለ ማርበርግ (Marburg) ቫይረስ ግንዛቤ ለመስጠት ወደ ት/ቤት በመምጣት ቅድሜ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸውን ሙሉ በዝርዝር በመጠቀስ የግንዛቤ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
✍️መጠንቀቅ ያለባቸው ቦታ የተጠረጠሩ እንስሳትን አለመንካት፣ በቫይረሱ ተሸካሚ ሊሆኑ ስለሚችሉ የሌሊት ወፍ በብዛት ከሚገኝባቸው ዋሻዎች እና የተፈጥሮ ቦታዎች መራቅ።

ምልክቶችን ማወቅ፦ ከፍተኛ ድንገተኛ ትኩሳት፣ ከባድ ራስ ምታት፣ እና የጡንቻ ሕመም የመሳሰሉ የማርቨርግ ምልክቶች በሰው ላይ ሲታዩ ወዲያውኑ በአቅራቢያ ያለ የጤና ተቋም ማሳወቅ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

መረጃው የጋዘር ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮምኒኬሽን ነው።

‎  ዛሬ ህዳር 17/2018 የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስኒዬር ማንጅሜንት አባላቶች ውይይቱ አደረጉ።‎   የኮሚቴው ሰብሳቢ እና የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ያዕቆብ ጥላሁን የዕለቱን ...
26/11/2025

‎ ዛሬ ህዳር 17/2018 የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስኒዬር ማንጅሜንት አባላቶች ውይይቱ አደረጉ።
‎ የኮሚቴው ሰብሳቢ እና የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ያዕቆብ ጥላሁን የዕለቱን አጀንዳ ለአባላቱ አሳውቆ በሰፊው አስተያየት ተሰጥቶበታል።
በዋናነት ከበጀት አጠቃቀም ጋር ተያይዞ(Duty)፤የእናቶች ማቆያ ቤት እድሳት፣የአገልግሎት አሰጣጥ ዙርያ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ በሰፊው ተወያይተዋል።


‎  ዛሬ ህዳር 17/2018 የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስኒዬር ማንጅሜንት አባላቶች ውይይቱ አደረጉ።‎   የኮሚቴው ሰብሳቢ እና የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ያዕቆብ ጥላሁን የዕለቱን ...
26/11/2025

‎ ዛሬ ህዳር 17/2018 የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስኒዬር ማንጅሜንት አባላቶች ውይይቱ አደረጉ።
‎ የኮሚቴው ሰብሳቢ እና የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ያዕቆብ ጥላሁን የዕለቱን አጀንዳ ለአባላቱ አሳውቆ በሰፊው አስተያየት ተሰጥቶበታል ።
በዋናነት የበጀት አጠቃቀምን፣የCBC reagents ግዥ፣የእናቶች ማቆያ ቤት ዕድሳት፣የአገልግሎት አሰጣጥ ዙርያ በሰፊው ውይይት ተደርጎ ተቋጭቷል።



የደቡብ ኣሪ ወረዳ ዋና አስተዳደር ክቡር አቶ ገብሬ ባይስማይ ከደቡብ አሪ ወረዳ የጤና ቦርድ ጋር በልዩ ልዩ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አደረገ፦                ህዳር  13/...
22/11/2025

የደቡብ ኣሪ ወረዳ ዋና አስተዳደር ክቡር አቶ ገብሬ ባይስማይ ከደቡብ አሪ ወረዳ የጤና ቦርድ ጋር በልዩ ልዩ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አደረገ፦

ህዳር 13/2018 ዓ/ም
ጋዘር

የደቡብ ኣሪ ወረዳ ዋና አስተዳደር ክቡር አቶ ገብሬ ባይስማይ
ከደቡብ አሪ ወረዳ የጤና ቦርድ ጋር በልዩ ልዩ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ወቅት በዋናነት በአራት አጀንዳዎች ሲሆን አንደኛው የጤና ቦርድን ማጠናከር ፣ሁለተኛው የባለሙያዎችን ጥቅማ ጥቅም ማስከበር፣ መድሃንትን ጨምሮ ለህብረተሰቡ በበቂ ሁኔታ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት የህክምና ቁሳቁሶችን ማሟላት ያስፈልጋል ተብሏል።

የጤና ቦርድ ማቋቋምና ማጠናከር አስፈላጊነት በየጤና ጣቢያዎች ውስጥ ለሚገጥመን ለየትኛውም የአገልግሎት እጥረትና ችግሮች መፍተሔ አካል ስለሆነ ቦርዱ ትኩረት ሰጥቶ መስራት አለባቸው ተብሏል።ቦርዱም በስም ብቻ ተደራጅቶ የሚቀመጥ ሳይሆን ለህብረተሰባችን ተገቢውን አገልግሎት በመስጠት ማስደሰትና ማርካት ስለሚያስፈልግ የቦርዱ አካል የሆኑትም በቁርጠኝነት ተግቶ መስራት ያስፈልጋል።

ከየጤና ጣቢያ የመጡትም የጤና ጣቢያ ሃላፊዎችም ቦርድ ማቋቀሙን አመስግነው ተጠናክሮ መቀጠል አለብን ብለዋል። ቦርድ ለየትኛውም ተግባር ወሳኝና አስፈላጊ ነው በማለት ነገር ግን በየጤና ጣቢያው ብዙ ችግሮች ወይም እንዳለ አንስቶ ችግሮችን ለመፍታት በቁርጠኝነት መስራት እንዳለባቸው ተስማምተዋል።

ከጥቅማ ጥቅም ጋር ተያይዞ በሁሉም ባለሙያዎች ቅሬታ እንዳላቸውና መንግስት ያገለገሉበትን ጥቅም ብያስከብርላቸው ጥሩ ነው ህብረተሰቡንም በቅንነትና በደስታ እንድያገለግሉ ብደረግ ጥሩ ነው በማለት አሳስበዋል።ከጤና መድህን ጋር ተያይዞው ህብረተሰቡ መዋጮውን በወቅቱና በጊዜ አለማውጣታቸው በበቂ ሁኔታ አገልግሎቱን እንዳያገኙና እኛም አስፈላጊውን አገልግሎት እንዳንሰጥ ማነቆ ሆኗል ብለዋል።

የወረዳው ዋና አስተዳደር ክቡር አቶ ገብሬ ባይስማይም በማጠቃለያው የህዝባችንን ከፍተኛ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች ብኖርም የህይወት ጉዳይ ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጡ ተግባር በመሆኑ በተቻለ መጠን በዚህ አመት የባለሙያዎችን ጥቅማ ጥቅም ፣የህኪምና አገልግሎት ቁሳቁሶችን በማሟላት የህዝባችንን መልካም አስተዳደር ጥያቄዎን ለመፍታት በቁርጠኝነት እንሰራለን ብለዋል።በቀጣይም አድሱ የማርበርግ በሽታ ዙሪያ ህዝባችንን የማንቃት ስራ ላይ የጤና ኬላዎች፣ጤና ጣብያዎችና የቀበሌው መዋቅር ጋር ተቀናጅቶ በትኩረት ልሰራ ይገባልም ተብለዋል። የበስተመጨረሻ የተግባርና የሥራ ስምርት በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል።

መረጃው የ ደቡብ አሪ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ነዉ 🙏

22/11/2025
‎በቅርብ ጊዜ በአከባቢያችን በጂንካ ከተማ ስለተከሰተው የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ምንነት ለጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች እና ለጤና ጣቢያ ኃላፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ። ‎  ==...
21/11/2025

‎በቅርብ ጊዜ በአከባቢያችን በጂንካ ከተማ ስለተከሰተው የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ምንነት ለጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች እና ለጤና ጣቢያ ኃላፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ።
‎ ===== 12/03/2018 ዓ.ም =====
‎ ጋዘር

‎ ✍️ ሰሞኑን በአከባቢያችን በጅንካ ከተማ የተከሰተው የማርበርግ ቫይረስ በሽታ በቀጣይ በልዩ ትኩረት መሰረት በሚገባቸው ዋና ዋና ነጥቦች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለባለሙያዎች የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከዓለም አቀፍ ጤና ድርጅት እና ኣሪ ዞን ጤና መምሪያ እንድሁም ጤና ጽ/ቤት ጋር በመቀናጀት ለጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች እና ጤና ጣቢያ ኃላፊዎች ተሰጥቷል ።

‎✍️ በስልጠናው ላይ የተገኙት የደቡብ ኣሪ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ደይሲ እንደተናገሩት በቅርቡ በአከባቢያችን በጅንካ ከተማ የተከሰተውን የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ስለ ቫይረሱ ምንነት ጤና ባለሙያዎች እና ጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ያላቸውን ግንዛቤ የማሳደግ እንዲሁም የቅድመ ጥንቃቄ ዝግጅት ሥራዎችን መስራት አንዱ ሲሆን የቅድመ ጥንቃቄና የግንዛቤ ሥራዎቹ እስከታችኛው ማህበረሰብ ድረስ መውረድ እንዳለበት በማስቀመጥ አሁንም ህዝባችን ከበሽታው ጋር ተያይዞ የተሳሳተ አልቧልታ ለሚወሩ ወሬዎች ጆሮ ሳይሰጡ ከጤና ሚኒስቴር የሚቀመጡ አቅጣጫዎችን በመከተል የጤና ባለሙያዎችን መልዕክት ተግባራዊ ማድረግ ግዴታ መሆኑንም አስገንዝበዋል ።

‎✍️ በስልጠናው የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ምንነት ፣ ምልክቶች ፣ መተላለፊያ መንገዶች ፣ ልየታ ፣ ምርመራና መደረግ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች ላይ ግንዛቤ የተሰጠ ሲሆን በቀጣይም ስልጠናዎች እስከ ታችኛው የህብረተሰብ አካላት የሚሰጥ ይሆናል ። በሽታው ከሟች ቤተሰብ በቅርብ ንክክ የነበራቸው በጤና ታመው ክትትል እየተደረገላቸው በመሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ከራስ ይጀምራልና ጥንቃቄ እናድርግ መልዕክታችን ነው
‎ መረጃውን ከደቡብ ኣሪ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ገፅ ላይ ነዉ የተወሰደው
‎ 12/03/2018

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዕለታዊ ሁኔታህዳር 11/ 2018 በተጨማሪም ሶስቱ በህክምና ላይ ያሉ ታማሚዎች ከዚህ በፊት ከተገለፀው ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጂንካ ከተማ በለይቶ ማቆያ የነበሩ ሲ...
20/11/2025

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዕለታዊ ሁኔታ
ህዳር 11/ 2018
በተጨማሪም ሶስቱ በህክምና ላይ ያሉ ታማሚዎች ከዚህ በፊት ከተገለፀው ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጂንካ ከተማ በለይቶ ማቆያ የነበሩ ሲሆኑ በተመሳሳይ ቦታም የህክምና ክትትላቸውን እያደረጉ ይገኛሉ።
Marburg Virus Disease Daily update
Ethiopia
November 20/ 2025

የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከልና መቆጣጠር ተግባራትን የሚጋዙ የህክምና መሳሪያዎችና መድኃኒቶች ድጋፍ ተደረገበደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተከሰተውን የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከልና ...
20/11/2025

የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከልና መቆጣጠር ተግባራትን የሚጋዙ የህክምና መሳሪያዎችና መድኃኒቶች ድጋፍ ተደረገ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተከሰተውን የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከልና መቆጣጠር ተግባራት የሚጋዙ የህክምና መሳሪያዎችና መድኃኒቶች ድጋፍ ወርልድ ቪዥን እና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አድርገዋል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ ድጋፉን በተቀበሉበት ወቅት የተደረገው ድጋፍ የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽን መከላከልና መቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ከፍተኛ እገዛ እንዳለው ገልፀው ድጋፉን ያበረከቱትን ወርልድ ቪዥን እና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበርን በክልሉ ሕዝብ፣ መንግሥትና በቢሮው ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ወርልድ ቪዥንን በመወከል ድጋፉን ያስረከቡት በወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ፕሮግራም ማናጀር አቶ አለማየሁ ብርሃኑ በበኩላቸው ድርጅታቸው አንግበው ከተነሳባቸው ዓላማዎች አንዱ ለድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ መስጠት መሆኑ ገልፀው ለጊዜው ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚገመትና ድጋፉ ቀጣይነት እንደሚኖረው አብራርተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበርን በመወከል ድጋፉን ያስረከቡት የማህበሩ ተወካይ ወ/ሮ ሰሚራ አበራ ማህበሩ ከ5.3 ሚሊየን በላይ የህክምና መገልገያዎችንና መድኃኒቶች ድጋፍ ማድረጉ ገልፀው ድጋፉ ቀጣይነት ይኖረዋል ብለዋል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትውት ዋና ዳይሬክተር አቶ አጉኔ አሾሌ በበኩላቸው የተደረገው ድጋፍ ማርበርግ ቫይረስ ወረርሽን ለመከላከል ወሳኝ መሆናቸውን በመገልጽ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በተቋማችን ዛሬ የ 'Hepatitis at birth' ክትባት ተጀምሯል።ከዚህ በፊት  እናቶች ገና እንደወለዱ ለጨቅላ ህፃናቶች BCG እና OPv 0 ይሰጥ ነበር።አሁን በተጨማሪ የ Hepatiti...
19/11/2025

በተቋማችን ዛሬ የ 'Hepatitis at birth' ክትባት ተጀምሯል።
ከዚህ በፊት እናቶች ገና እንደወለዱ ለጨቅላ ህፃናቶች BCG እና OPv 0 ይሰጥ ነበር።አሁን በተጨማሪ የ Hepatitis ክትባት እንደተወለዱ እንዲሰጥ ባለሙያዎች ሰልጥነው ዛሬ የጋዘር መ/ደ/ ሆስፒታል የክትባት ክፍል ኃላፊዋ ስስተር ባደገች ልባኔ አገልግሎቱን ለተገልጋዮች መስጠት ጀምራለች።

የዜጎች ጤና ለሀገር ብልፅግና

የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል!

Address

Jinka

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gazer Primary Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Gazer Primary Hospital:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram