
07/08/2025
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ትኩረት የሚሹ የሃሩራማ አከባቢ በሽታዎች የምርምር እና ስልጠና ማዕከል ከ ጋር በመተባበር የ2ተኛወን ዙር የመማህበረሰብ አቀፍ የመድኃኒት እደላ ሽፋን ጥናት (Post MDA Coverage Validation Survey for IoT Districts) የመስክ ስራው በተሳካ ሁኔታ እየሰራ ይገኛል።
የክረምቱ አየር አስቸጋሪ ቢሆንም በጤና ሚንስቴር እና ክልል ጤና ቢሮ አማካኝነት የሚተገበረው የአንጀት ጥገኛ ትላትል እና ብላሃርዚያ በሽታ ስርጭትን ለመግታት ታልሞ በተለዩ አከባቢዎች እየተሰጠ የቆየው የማህበረሰብ አቀፍ መድሃኒት እደላ ሽፋን ምን እንደሚመስል ለማወቅ ከአርባ ምንጭ ዩንቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተወጣጡ ባለሙያዎች ነባራዊ ሁኔታውን በመቋቋም በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች በሚገኙ በተመረጡ ወረዳዎች መረጃውን በተሳካ ሁኔታ እየሰበሰቡ ይገኛሉ።