Dr. DEBOL

Dr. DEBOL TEAM DEBOL

Medicine's Creativity & Leadership Hub! Medical

OFFICIAL STATEMENT  The Ethiopian Health Professionals' Students' Association (EHPSA)  Expresses deep concern over the p...
03/06/2025

OFFICIAL STATEMENT

The Ethiopian Health Professionals' Students' Association (EHPSA)

Expresses deep concern over the prolonged and unaddressed challenges facing health professionals, interns, and students across Ethiopia.

EHPSA calls upon all responsible bodies—including the government, the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC), the Ethiopian Health Professionals Movement (EHPM), the Ethiopian Health Professionals Association (EHPA), and other stakeholders—to engage in immediate, open, and constructive dialogue.

We urgently demand:
1. The release of all detained students, interns, and health professionals.
2. Swift and concrete action to address the legitimate grievances of health workers, ensuring their voices are heard and respected.
3. Protection of the fundamental rights of all healthcare professionals to advocate for their profession, their patients, and systemic improvements without fear of retaliation.

This is a pivotal moment for Ethiopia’s healthcare system. The future of our nation’s health depends on fairness, dialogue, and meaningful reform.




 #ዜናመሠረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከማይወክሉን ግለሰቦች ጋር ውይይት ሊያደርጉ ነው በማለት የጤና ባለሙያዎች ቅሬታቸውን አሰሙ (መሠረት ሚድያ)- በርካታ ቀናትን ካስቆጠረው የጤና ባለሙያዎች የስ...
03/06/2025

#ዜናመሠረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከማይወክሉን ግለሰቦች ጋር ውይይት ሊያደርጉ ነው በማለት የጤና ባለሙያዎች ቅሬታቸውን አሰሙ

(መሠረት ሚድያ)- በርካታ ቀናትን ካስቆጠረው የጤና ባለሙያዎች የስራ የማቆም አድማ ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቅርብ ቀናት ከተወሰኑ ባለሙያዎች ጋር ውይይት ሊያደርጉ መሆኑ ታውቋል።

(መሠረት ሚድያ)- በርካታ ቀናትን ካስቆጠረው የጤና ባለሙያዎች የስራ የማቆም አድማ ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቅርብ ቀናት ከተወሰኑ ባለሙያዎች ጋር ውይይት ሊያደር.....

⚓ስደትሀገር ትታህ ሆድ ሲብስህጥረህ ግርህ ሲያጥር ኪስህ፣ለሰው ኖረህ ስትጎል ከስውትመኛለህ ሀገር መተው፣ሀገር ያለህ ሰው የሚያውቅህሆድ ቢብስህ ጠፍቶ ሃቅህ፣ሀገር ትተህ ብትሰደድሌላ ሀገር ብ...
03/06/2025

⚓ስደት

ሀገር ትታህ ሆድ ሲብስህ
ጥረህ ግርህ ሲያጥር ኪስህ፣

ለሰው ኖረህ ስትጎል ከስው
ትመኛለህ ሀገር መተው፣

ሀገር ያለህ ሰው የሚያውቅህ
ሆድ ቢብስህ ጠፍቶ ሃቅህ፣

ሀገር ትተህ ብትሰደድ
ሌላ ሀገር ብትወደድ፣

መክሊትህ ነው አይግረምህ
ለይ እ'ኮ ነው ያንተ ስምህ፣

ሀግር ህመማን ዘንግታ
ብትሸኝህም ተረጋግታ፣

ዳር ላይ ጥላ ያንተን ብሶት
ባይሰማት ድሃ ሲሞት፣

አንተ የአቅምህን ስትሞክር
እሷን ብለህ ስ'ጠነክር፣

የኔ ያልካት ይችህ ሀገርህ
ፌዝ ከሆነባት መቸገርህ፣

ያንተ ማጣት ካልተሰማት
ምንም አይደል ስትተውህ ብትተዋት።

©️ Dr. Elias Samuel Matheos (internist)

©️EHSM

03/06/2025

⚓️

"ይሄ ለተወሰኑ የስፔሻሊቲ ዶክተሮች መኖርያ ተብሎ የሚሰጥ የጥቁር አምበሳ ዶርሚተሪ ነዉ። ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ዉስጥ ያልደረሳቸዉ ዉጪ ተከራይተው ይኖራሉ። ግን በ10ሺ ብር ደሞዝ አዲስ አ...
03/06/2025

"ይሄ ለተወሰኑ የስፔሻሊቲ ዶክተሮች መኖርያ ተብሎ የሚሰጥ የጥቁር አምበሳ ዶርሚተሪ ነዉ። ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ዉስጥ ያልደረሳቸዉ ዉጪ ተከራይተው ይኖራሉ። ግን በ10ሺ ብር ደሞዝ አዲስ አበባ ላይ ተከራይተው መኖር ስለሚከብድ እዚ ዶርም ለመግባት በወረፋ ነዉ ።"

TASH Residents

For Other Health Professionals from your colleague Will you continue to be silent when the government offers selective s...
03/06/2025

For Other Health Professionals from your colleague

Will you continue to be silent when the government offers selective salary increases to doctors, ignoring the rest of the health workforce yet again?

I have served as a Health Officer in Ethiopia for over a decade. Today, I write not only out of deep concern, but with profound disillusionment and frustration.

Ethiopian health professionals — including nurses, health officers, laboratory technologists, midwives, and others — continue to endure systemic neglect and chronic underpayment. Despite the essential and often life-saving nature of our work, our wages are grossly insufficient to meet even the most basic human needs: food, shelter, and clothing. Many of us are living in financial destitution, grappling daily with the harsh realities of survival.

In response to this worsening crisis, a number of health professionals have chosen to take a stand — demanding fair treatment, dignity, and recognition. Yet, alarmingly, a large portion of our colleagues remain silent. This passivity, in the face of such glaring injustice, is both disheartening and damaging.

Why are you silent?
Why do you only raise your voice when the grievances of doctors are addressed — but remain indifferent to the shared suffering we all endure?
Will you continue to be silent when the government offers selective salary increases to doctors, ignoring the rest of the health workforce yet again?

Let us be clear: even doctors — those who have studied for 7 years and beyond, including specialists with over a decade of education and training — are fully aware of the potential consequences of their protest. They risk disciplinary action, revocation of their professional licenses, dismissal from employment, and even imprisonment. Yet, despite these real threats, they have found the courage to speak up.

So I ask you — those who studied for 3 or 4 years — what exactly are you afraid of?
If those with more at stake are willing to take a principled stand, what excuse remains for silence?

This movement is not solely about doctors. It concerns all of us — every individual who forms the backbone of Ethiopia’s healthcare system. Whether you are a nurse, a health officer, a midwife, or a technician, you are equally undervalued, overworked, and underpaid.

Remaining silent in the face of oppression does not preserve your safety — it simply delays the inevitable, and weakens our collective voice. By failing to stand together, we embolden the system that exploits us.

The time for hesitation has passed. The time for unity is now. We must rise — not only for our own welfare, but for the integrity and future of our profession.

From Dandena

የሕዝብ እና የመንግስት አጀንዳ እንደዚኛው ዘመን የተራራቀበት ጊዜ የነበረ አይመስለኝም።  የሕዝብ አንኳር አጀንዳ:➖➖➖➖➖➖➻ ዳቦ➻ የኑሮ ውድነት ➻ በከተሞች የቤት አቅርቦት እጥረት ➻ የደ...
03/06/2025

የሕዝብ እና የመንግስት አጀንዳ እንደዚኛው ዘመን የተራራቀበት ጊዜ የነበረ አይመስለኝም።

የሕዝብ አንኳር አጀንዳ:
➖➖➖➖➖➖

➻ ዳቦ

➻ የኑሮ ውድነት

➻ በከተሞች የቤት አቅርቦት እጥረት

➻ የደሞዝ ማስተካከያ

➻ የተቋማት ዝቅጠት እና ሙስና

➻ የግብር ጭማሪ እና ተደጋጋሚ መዋጮ

➻ የማዳበሪያ ዋጋ

➻ ዘላቂ ሰላም

➻ ሁሉን አካታች ምክክር

የመንግስት አንኳር አጀንዳ
➖➖➖➖➖➖➖

➻ የኮሪደር ልማት

➻ ሎጅ እና ሪዞርት

➻ አዲስ ቤተመንግሥት

➻ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ

➻ የድሮን ትርዒት

➻ አረንጓዴ አሻራ

➻ የቅርሶች ዕድሳት

➻ የውትድርና ምልመላ

➻ ከራስ ጋር ንግግር ወ [ ምክክር ]

➖➖➖➖➖➖➖

በሕዝቡ እና በመንግሥት አጀንዳ መካከል ባለው ሰፊ ልዩነት እና ርቀት ምክንያት የሁለቱን አካላት አጀንዳዎች ማስታረቅያ እና መገናኛ ቦታ ማበጀት አዳጋች ነው። በሁለቱ ጫፍ ያሉት አጀንዳዎች እንዴትም ቢጎተቱ እና ቢገፉ ወደ መሐል መንገድ መምጣት አይችሉም። ለመንግስት ኮሪደር እና ሪዞርት የቅድሚያ ቅድሚያ የሚያገኙ [ የህልውና ] ጉዳዮች ናቸው። ለሕዝቡ ደግሞ ከዳቦ ጥያቄ፣ ከኑሮ ውድነት እና ከሰላም የበለጠ አንገብጋቢ ጉዳይ የለም።

ቆይ ግን እንዲህ ቢደረግስ...

ምናልባት ሕዝቡ ዳቦ...ዳቦ ማለቱን ትቶ በአንድ ድምፅ:

[ ኮሪደር ሕይወቴ - ነይልኝ በሞቴ ] ብል

እስካሁን ባየነው አካሄድ መንግስታችን ደግሞ ሕዝቡ ያልጠየቀወን መመለስ እና መስራት ስለሚወድ..የሕዝቡን [ ኮሪደርዬ ] ማለት ተንተርሶ እሱ በተራው [ዳቦ...ዳቦ..] ማለት ይጀምር ይሁን😐

እስኪ እንሞክረው...

የኔ ነፍስ ነገር.. ጣፋጭ ልክ እንደ ማር
በምላስ ይላስ እንጂ እንዳትረግጠው በእግር
እውነትም ድንቅ ነው.. የዚህ ዘመን ተዐምር
በሞቴ! ቅመሱት ይህን ውብ ኮሪደር...🤗


ዶ/ ር M. From South ethiopia.

ምክር ቤቱ ሁለት የብድር ስምምነቶችን አጸደቀየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 33ኛ መደበኛ ስብሰባው ሁለት የብድር ስምምነቶችን አጽድቋል፡፡የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ...
03/06/2025

ምክር ቤቱ ሁለት የብድር ስምምነቶችን አጸደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 33ኛ መደበኛ ስብሰባው ሁለት የብድር ስምምነቶችን አጽድቋል፡፡

የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በአረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት መካከል ለተቀናጀ የውጤታማ ግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት ለወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡

በማብራሪያቸውም፣ ብድር ስምምነቱ በግብርና ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለማስፋፋት፣ የባለሙያዎችን አቅም ለመገንባት፣ የመስኖ አውታሮችና እና የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲሁም ወጣቶች በግብርና ኢንዱስትሪው ዘርፍ ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚያስችል ስምምነት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለሴቶች እና ልጃ-ገረዶች ጤና የተቀናጀ ፣ ጠንካራ እና በፈጠራ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የቀረበውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን አስመልከቶ ገለጻ አቅርበዋል::

ስምምነቱ በጤናው አገልግሎት ዘርፍ ጥራት እና ተደራሽነትን ለማስፋት፣ በሴቶች ቅድመ-ወሊድ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ችግሮችን ለመፍታት፣ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ ምቹ የጤና ተቋማትን ለመገንባት እና የጤናውን ዘርፍ ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ስምምነት መሆኑን አቅርበዋል፡፡

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በአረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት መካከል ለተቀናጀ የውጤታማ ግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት ለወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ በቀረበ ረቂቅ አዋጅ አሳታፊነትን እና ተጠቃሚነትን በተመለከተ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጉዳዮች የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታው እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ምላሽ አቅርበዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ግብርና ላይ ያተኮሩ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለማልማት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አብራርተው፣ የተገኘውን የልማት ሀብት በአግባቡ አሳታፊነቱ እና ተጠቃሚነቱ ተጠብቆ ስራ ላይ እንደሚውል ክትትል እና ቁጥጥር ይደረግበታል ብለዋል፡፡

ምክር ቤቱም የብድር ስምምነት ረቂቅ አዋጆቹን አዋጅ አድርጎ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

(መናኸሪያ ሬዲዮ)

ምኞት አይከለከል!⚓ ሰሞኑን አሜሪካዊው ቢሊየነር Bill Gates ወደ 200ቢሊየን የሆነውን ሀብቱን በበጎ አድራጎት ስራ ላይ በተለይ በጤናና ትምህርት ዘርፍ ላይ እንዲያውሉ ለአፍሪካ አገራት...
03/06/2025

ምኞት አይከለከል!

⚓ ሰሞኑን አሜሪካዊው ቢሊየነር Bill Gates ወደ 200ቢሊየን የሆነውን ሀብቱን በበጎ አድራጎት ስራ ላይ በተለይ በጤናና ትምህርት ዘርፍ ላይ እንዲያውሉ ለአፍሪካ አገራት እንደሚረዳ ቃል ገብቷል።

⚓ Gates foundation በሚባለው የምግባረ ሰናይ ድርጅታቸው ስም...ወዲያው ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት ለ Bill Gates የአገሪቱን የመጨረሻ ክብር ምልክት የሆነውን “የክብር ኒሻን” ሸለመ ተባለ።

ያው መንግስት ለትምህርትና ለጤናው ዘርፍ ከሰጠው ትኩረት አንፃር የንሻን ሽልማቱ ግራ የሚያጋባ ይመስለኛል🤔።

ምናልባት የተዘጉ ትምህርት ቤቶችንና ስራ ያቆሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ለማደራጀት የታሰበ ነገር ያለ ይመስለኛል።

የሰሞኑ የጤና ባለሙያዎች ጥያቄ በ Bill Gates ጣልቃ ገብነት ሊፈታ ይሁን? እኔ እንጃ ምኞት እንደሆነ አይከለከል!!

©️ዶ/ር አሻግሬ ገ/ሚካኤል
(Pediatric surgeon)

ተው ጊዜ  ተመለስ  ይበቃል ያለፈውእንባው የደረቀን  ደም አንባ  አትበለው !✓✓  ያልተባለ አያውሩ ፤ ያልተጠየቁትንም አይመልሱ ! ✓✓ሙያችን በገንዘብ ይተመን ያለው ማነው ?ጤና ባለሙያው ...
03/06/2025

ተው ጊዜ ተመለስ ይበቃል ያለፈው
እንባው የደረቀን ደም አንባ አትበለው !

✓✓ ያልተባለ አያውሩ ፤ ያልተጠየቁትንም አይመልሱ ! ✓✓

ሙያችን በገንዘብ ይተመን ያለው ማነው ?

ጤና ባለሙያው የጠየቀውን 1ኛ ጥያቄ ከሆነ እየመለሱ ያሉት ፣ ጥያቄው መሰረታዊ ፍላጎታችን ማለትም ምግብ ፣ መጠለያ ፣ ልብስ የሚሸፍን ክፍያ ይከፈለን ነው። አሁንስ ግልጽ አይደለም?
...

በታላቅ ራዕይ እና ወኔ 24 ከባድ የትምህርት ዓመታትን ያሳለፋ ስፔሻሊስት ሐኪሞች ሳይቀር በ 12,765 ብር ግሮስ ደመወዝ ( 35% ታክስ እና ጡረታ ሳይቆረጥ ) መኖር ከበደን ፡ " ራበን " ብለው ሲማፀኑ ማየት ፤ ሰው ሁነህ ካየኸው እንደ ሀገር አሳፋሪ እና ሐኪምነትን የድህነት መታወቂያ ያደረገ ፤ በክፍያው ምክንያት ሐኪም ነኝ ብሎ መናገር የሚያሸማቅቅ ፤ በስራ ላይ ያሉት ሙያውን የመረጡበትን ቀን ያስረገመ ፤ ሐኪም የመሆን ራዕይ የሰነቁ ተተኪ የጎበዝ ተማሪዎችን ህልም የሚያጨልም ሐውልት ተሰርቷል !
..

ጊዜ ጨካኝ ነውና ራበን ብሎ የተማፀነን ጤና ባለሙያ እናንተ ለሀገር ያላችሁ ጠቀሜታ እዚህ ግባ የሚባል ስላልሆነ ስለእናንተ አያገባንም ፤ ችግራችሁም አያስጨንቀንም ፤ ካልፈለገ እዚህ ሀገር ጤና ባለሙያ አለመኖር ይችላል ፤ ስለቀጣይ ትውልድስ ምን አስጨነቀን ፤ እኛ እንብላ እናንተ አግሱ ፡ ጤና ባለሙያ እርካታ ይብላ ፣ እርካታ ይጠጣ ፣ ቤት ኪራይ እርካታ ይክፈል ፣ ትራንስፓርትም እርካታውን ተጫምቶ በእግሩ ይጓዝ የሚል ይዘት ያለው መልስ እየተፈራረቀ ነው ።
...

ተው ጊዜ ተመለስ ይበቃል ያለፈው
እንባው የደረቀን ደም አንባ አትበለው !

Dr. Astewale Tesfie
ACCPM Final year Resident

03/06/2025

ሆስፒታሎች ውስጥ ለሚታየው ክፍተት ማህበረሠቡ የሚወቅሰው እየራበው የሚሰራውን ሀኪም ቢሆንም...ሆስፒታሎች ጋር የተያያዘ ውሳኔ እና ግዢ...በተያያዘም ለሙስና የተጋለጡ አካላት👇

የሆስፒታል ቦርድ ከ5-7 አባላት ሲኖሩት እነርሱም

1) የከተማው ከንቲባ (ሰብሳቢ)
2) የወረዳው አስተዳዳሪ (ም/ሰብሳቢ)
3) የሆስፒታሉ CEO (ቀጥታ የፖለቲካ ተሿሚ)
4) የአካባቢው ማህበረሰብ ተወካይ (01)
5) የሴቶች ተወካይ (01)
6) ከስታፍ ተወካይ (ብዙ ጊዜ አይካተትም)

ለዛም ነው ባለሙያውን/ሀኪሙን የለፋበትን አለመክፈል ፣ ምሬቱን ማፈን ፣ ከፍ ሲልም ማሳሰር እና ማሰቃየት ቀላል የሆነላቸው። ሆስፒታሎችም ህክምናውን በማይረዱ አካላት በሚወሰነው ውሳኔ እየተራቆቱ ያሉት።

መፍትሄው ቀጥታ በ Vertical structure በጤና ሚኒስተር ከላይ እስከታች በቦርድ እንዲመራ ማድረግ ነው። ሀኪሞችን በወረዳ አስተዳዳሪዎች ምሬት ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ እንዲሁም ተቋማቱ በቀላሉ ለሙስና የተጋለጡ በማድረግ ከማንወጣው ቀውስ ውስጥ ከቶናል። መፍትሄውም ግልፅ ነው!

(Inbox)

⚓️ 94% የጤና ባለሙያው የጤና ሚኒስተር ስለሚመለምላቸው ባለሙያዎች እውቅና እንደሌለው በ12 ሰዓታት ውስጥ የተካሄደ 10ሺ ባለሙያ የተሳተፈበት Poll ያሳያል። ⚓️የሚሰበሰቡ ሰዎች የስብሰ...
03/06/2025

⚓️ 94% የጤና ባለሙያው የጤና ሚኒስተር ስለሚመለምላቸው ባለሙያዎች እውቅና እንደሌለው በ12 ሰዓታት ውስጥ የተካሄደ 10ሺ ባለሙያ የተሳተፈበት Poll ያሳያል።

⚓️የሚሰበሰቡ ሰዎች የስብሰባ ፣ ውይይት እና ድርድር ልዩነቱን አልተረዱም። በስብሰባ የሚመለስ ጥያቄ አይኖርም። ከመላሹ በኃላ አስተያየት መስጠት ስለማይቻል በስብሰባ። እንደተለመደው ተሰድቦ ከመውጣት ውጭ።

⚓️እነዚህ ተዘጋጅተዎል የተባሉ 6% ባለሙያውን የሚወኩሉ አካላት ላይ እንኳ አስተያየት እንዳይሰጥ...94%ቱ ባለሙያው በጤና ሚኒስተር ፌስቡክ ገፅ የሚለጠፋ ምስሎች ስር ያለው የአስተያየት መስጫ ተቆልፎባቸዎል።

⚓️6%ቶች ምናለ ተሰድባችሁ ባታሰድቡን!

⚓️ ጥያቄያችን ግልፅ እና አለም ያወቀው ነው። የምንፈልገው ግልፅ መልስ ነው።

⚓️እዚህ ግባ የማይባል መልስ ይዛችሁ ባለሙያውን አዎርዳችሁ ስትመለሱ ግን አስተውሉ መንግስት ለአለም አቀፍ ሚዲያዎች እና ኢምባሲዎች ፕሮፓጋንዳ ይሰራባችኃል።

⚓️በየት በኩል እንግባባ ወገን!

⚓️ለማንኛውም 94%ቱ ህይወት ስታድኑ ኖራችኃል...አሁን ቆራጥ ውሳኔ ለመወሰን እና ራሳችሁን ለማዳን በተጠንቀቅ ቁሙ!

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr. DEBOL posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Dr. DEBOL:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Practice
  • Claim ownership or report listing
  • Want your practice to be the top-listed Clinic?

Share