19/11/2024
እንግድህ ነገሮቹ ዘገዩ ማለት ጭራሽ አይሆኑም ማለት አይደለም።ይህን ያልነዉ ዝም ብለን አይደለም፣በቅድምያ እንኳን ደስ አላችሁ የቦርቻና የአከባብዉ ህዝብ በሙሉ።ምክንያቱም ፣ከዘህ በፊት የይርባ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የውኃ ችግር እየተወራና በውኃ ምክንያትእየተባለ የትዬለሌ ማሽኖች አገልግሎት ሳይሰጡ መቆየታቸዉና፣ጥራት ያለዉ የጤና አገልግሎት ለመስጠት የውኃ ችግር ትልቅ ማነቆ ሆኖ መቆየቱ ያለውም የነበረውም ያወቀው ሀቅ ነው።እሰይ!ጊዜ የማይፈታዉ ነገር የለምና ቀንና ወራት እንድሁም ዓመታት እያስቆጠረ ይሄው በዛሬው ዕለት በይርባ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ረጅም መንገድ ስጓዝ ከርሞ በዛረዉ ዕለት ኩልል ያለ ውኃ ይሄው ከች አለ።እንኳን ደስ አላችሁ፣ይህ ቀን ሁላችንም ስንናፈቅ የቆየነው ነበረ ሆኖም፣ሁላችንም በዓይናችን አየን። ለዝህም የቦርቻ ወረዳ ማህበረሰብና የይርባ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተጠቃም ወረዳዎች እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ ከዝህ ጎን ለጎን ሳላደንቀው የማላልፈው ነገር ብኖር አንድ አለ፣እሱም ከዝህ በፊት ነገሮች ስዋሹ፣ፖለትካ ነው ስንል ቆይተናል።ሆኖም አልተሳሳትንም ፣ከዝህ በፊት ዛሬ ነገ ስሉ የነበሩ የፖለትካ ስርዓቶች እልባት ያልሰጠውን፣አሁን የነበረው፣የፖለትካ ስርዓት እንድሁም፣መንግስትን ስመሩ የነበሩ ቁርጠኛ አመራሮች እልህ አስጨራሽ ውጤት ስለሆነ፣ወረዳውን እየመሩ ያሉትን ክቡር አስተዳዳሪ አቶ ወሰን ብርሃኑን እንኳን ደስ አለወት እያልኩ፣ላመሰግኖት፣ከመቀነጫዬ ብድግ ስል፣ማሞካሸት ብቻ ሳይሆን፣የቦርቻ ህዝብ ስምንም ጭምር ይዤ መሆኑን ስገልጽ በታላቅ ደስታ ነው።ቦርቻ ።።።።ይቻላል ምንጭ YPH Broad cast.