03/05/2025
ያለመውለድ ችግር(መካንነት) #7ዋና ዋና ምክንያቶች
ጥንዶች ጋብቻ ከፈፀሙ በኋላ በቀጣዩ የህይወት ምዕራፍቸው የሚጠብቁት ነገር ልጅ መውለድ ነው።አንድ ሴት ምንም የመውለድ ችግር ሳይኖርባት እና የወሊድ መከላከያ ሳትጠቀም በአንድ ወር ውስጥ የማርገዝ እድሏ 20% ሲሆን 6 ወር ውስጥ 60% እንዲሁም በ1 ዓመት 85% ነው። ለሁለት አመት ቢሞክሩ ደግሞ 95% የማርገዝ እድል አላቸው።
15% የሚሆኑ ጥንዶት በአንድ አመት ውስጥ ምንም አይነት የወሊድ መከላከያ ሳይጠቀሙ ቋሚ የግብረስጋ ግንኙነት እያደረጉ የማርገዝ ችግር ያጋጥማቸዋል።ይህም መካንነት ወይም ያለመውለድ ችግር አጋጥሟቸዋል ተብሎ ህክምና ይጀመርላቸዋል።
የሴቷ እድሜ ከ35 አመት በላይ ከሆነ ለ6ወር ሙከራ አድርጋ እርግዝና ካልተፈጠረ የመካንነት ህክምና መጀመር አለባት።
መውለድ ያለመቻል እጅግ በርካታ ምክንያቶች ሲኖሩት አንዳንዶቹ ወደ 20% የሚሆኑት ይህ ነው የሚባል ምክንያት የላቸውም።
ያለመውለድ ችግር(መካንነት) ዋናዋናዎቹ ምክንያቶች እነሆ
1. ከወንድ በኩል የሚኖር መካንነት
(male factor infertility)
እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ መሰረት 20% የሚሆነው ያለመውለድ ችግር(መካንነት) ከወንድ በኩል የሚኖር ነው።ይህም በጭንቅላት ውስጥ የሚመረት ሆርምሞን ማነስ(),በዘር ፍሬ ላይ የሚያጋጥም ሰፐርም የማምረት ችግር(primary testicular defect in spermatogenesis), የወንድ የዘር ትቦ መዘጋት, እንዲሁም ምክንያቱ የማይታወቅ የወንድ መካንነት(idiopathic male infertility) ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
ከ70-80% የሚሆነው በወንዶች በኩል የሚያጋጥም መካንነት በዘር ፍሬ (te**es) በተለያዩ ምክንያቶች ዘር ያለማምረት ችግር የሚመጣ ነው። ይህም በዘር(genetics)፣በኢንፌክሽን፣በአደጋ፣ጨረር መጋለጥ፣ለሙቀት መጋለጥ እንዲሁም የሆርሞን ማነስ ምክንያት ሊሆን ይችላል።
2.በሴቶች ላይ እንቁላል የመለቀቅ ችግር
(ovulatory dysfunction)
25% የሚሆነው ያለመውለድ ችግር(መካንነት) ምክንያት የእንቁላል ያለመለቀቅ ችግር ነው።አንዲት ሴት ስትወለድ ከ1-2 ሚሊየን የሚጠጉ እንቁላሎች በኦቫሪ ውስጥ ይኖራሉ።አነዚህ እንቁላሎች እድሜዋ አየጨመረ ሲሄድ እየቀነሱ ይመጣሉ።እርግዝና እንዲፈጠር እንቁላል ከኦቫሪ ወደ ማህፀን ግድግዳ
መለቀቅ አለበት ይህ የመለቀቅ ሂደት በተለያየ ሆርሞኖች ቁጥጥር ስር የወደቁ ናቸው።የእነዚህ ሆርሞኖች መዛባት እንቁላል እንዳይለቀቅ ሊያደርጉ ይችላሉ።
PCOS፣ከአንጎል የሚመነጭ ሆርሞን ማነስ፣የፕሮላክቲን መብዛት፣የታይሮይድ ሆርሞን ማነስ/መብዛት እንደምክንያትነት ይጠቀሳሉ።
3.የማህፀን ቱቦ መዘጋት
በግራና በቀኝ በኩል የሚገኙ እንቁላል አስተላላፊ ትቦዎች በተለያየ ምክንያት ሊዘጉ ይችላሉ። በሰርጀሪ፣በኢንፌክሽን፣ከማህፀን ውጭ በሚያጋጥም እርግዝና እንዲሁም በሆድ እቃ ውስጥ በሚያጋጥም ጠባሳና መጣበቅ ሊዘጋ ይችላል።
4.በማህፀን ግድግዳ ላይ የሚያድግ እጢ
በማህፀን ግድግዳ ላይ የሚፈጠር እጢ እንቁላልና ስፐርም ሴል እንዳይገናኙ እንዲሁም እርግዝና ከተፈጠረ በኋላም ምቹ ሁኔታ እንዳይኖር ሊያደርጉ ይችላሉ።
5.የማህፀን አፈጣጠር ችግር
በተፈጥሮ ለሁለት የተከፈለ ማህፀን(septated uterus) ተደጋጋሚ ውርጃ እንዲኖር ሊያደርግ ይችላል።
6.ኢንዶሜትሪዮሲስ(endometriosis)
ጠባሳና መጣበቅን በመፍጠር የማህፀን ትቦ እንዲዘጋ እንዲሁም በኦቫሪ ውስጥ እጢ(endometrioma) በመፈጠር የእንቁላል ማምረት ሂደትን በማወክ መካንነትን ሊያመጣ ይችላል።
7.የዘረ መል(chromosome)ችግር
Turn