08/09/2025
#ስለ #ጡት #ካንሰር #ምን #ያህል #ያውቃሉ ?
በዓለም አቀፍ ደረጃ በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር ህመሞች እስከ 31.9 በመቶውን የሚይዘው የጡት ካንሰር
በኢትዮጵያ ሴቶችን ከሚያጠቁ የካንሰር በሽታዎች ቀዳሚው የጡት ካንሰር ነዉ።
👉 የጡት ካንሰር ሁኔታ
• የጡት ካንሰር ማለት በጡት ቲሹ ውስጥ የሚወጡ ከባድ እና በቁጥጥር ውስጥ ያልሆኑ ሕዋሶች መብዛት ነው።
• ይህ ካንሰር በአብዛኛው ሴቶችን የሚያጠቃ የካንሰር አይነት መሆኑን ገልጸዋል።
👉 ለጡት ካንሰር አጋላጭ ምክንያቶች
ምንም እንኳን ማንኛውም አይነት ካንሰር መነሻው በውል ባይታወቅም አጋላጭ የሆኑ ምክንያቶች አላቸው ።
ከእነዚህም መካከል፡-
• የቤተሰብ ታሪክ (እንደ እናት፣ እህት ወይም ሴት ልጅ)፣ የዕድሜ መጨመር (ከ40 ዓመት በላይ መሆን)፣ ጡት አለማጥባት፣ የመጀመሪያ ልጅን ዘግይቶ መውለድ፣ የአካል ክብደት መጨመር፣ የስብ ክምችት መብዛት፣ የሆርሞን መጋለጥ (ለረጅም ጊዜ ለኤስትሮጅን መጋለጥ)፣ የአልኮል መጠጥ ማብዛት፣ ሲጋራ ማጨስ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ በዋናነት የሚጠቀሱ የጡት ካንሰር አጋላጮች ናቸዉ ።
👉 የጡት ካንሰር በአብዛኛው እነማንን ያጠቃል?
• የጡት ካንሰር ሁሉንም የዕድሜ ክልልና ጾታ እንደሚያጠቃ ፤ በተለይም በአብዛኛው በዕድሜ ከ40 እስከ 60 ዓመት በላይ የሆኑትን ያጠቃል ።
• የጡት ካንሰር በስፋት በሴቶች ላይ ቢከሰትም፤ አልፎ አልፎ በወንዶች ላይም ይከሰታል ።
👉 ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
• በጡት ላይ የሚከሰት እብጠት፣ ደም የቀላቀለ ፈሳሽ ከጡት መውጣት፣ የጡት ቆዳ ወደ ውስጥ መሰርጎድ፣ የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መግባት፣ የጡት ቆዳ መልክ መቀየር እንዲሁም መሸብሸብ፣ የጡት መጠን እኩል አለመሆን፣ የንፍፊት እብጠት የመሳሰሉት ከጡት ካንሰር ምልክቶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው ።
👉 ለጡት ካንሰር ላለመጋለጥ ምን ማድረግ ይገባል?
• የጡት ካንሰርን ለመካላከል ቢያንስ የሚታወቁ የጡት ካንሰር አጋላጭ የሆኑት ላይ መሥራት ይገባል።
ለአብነትም ጤናማ የሆነ እንቅስቃሴ እና ክብደትን ማስጠበቅ፣ ከፍተኛ የአልኮል መጠጥን መገደብ፣ ጡት ማጥባት ፣ ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች መደበኛ ጡት ምርመራ ማድረግ፣ የራስ የጡት ምርመራ ማድረግ እና ሌሎችንም ።
👉 ሕክምናውስ?
• የጡት ካንሰር ሕክምና ብዙ ባለሙያዎቸን የሚያሳትፍ መሆኑን ፤ የተለያዩ ሕክምናዎች አሉት።
ከሕክምናዎቹ መካከልም፤ ቀዶ ጥገና፣ ራዲዮቴራፒ፣ ኬሞቴራፒ፣ የሆርሞን ሕክምናን ጨምሮ ሌሎችም በዋናነት ይሰጣል ።