Biiroo Aadaf Turiizimi oromiyaa

Biiroo Aadaf Turiizimi oromiyaa Informations de contact, plan et itinéraire, formulaire de contact, heures d'ouverture, services, évaluations, photos, vidéos et annonces de Biiroo Aadaf Turiizimi oromiyaa, Centre de ressources contre le SIDA, Paris.

Barataa Biyyaaf  Abdii  Boruu Ta`e  Deggeruun Biyya Ijaaruu dha.==Humna waloo qindeessuun hojii tajaajila lammummaa hojj...
19/09/2024

Barataa Biyyaaf Abdii Boruu Ta`e Deggeruun Biyya Ijaaruu dha.
==
Humna waloo qindeessuun hojii tajaajila lammummaa hojjechuun erga jalqabeen asitti rakkoon hawaasaa waloon furamuun daa`imman, barattoota harka qalleeyyiifi haati hiyyeessaa baay`een fayyadamoo ta`aa jiru. Abbootiin qabeenyaafi dhaabbileen addaa addaas akka Oromiyaatti gumaacha taasisaa jiru.

Haaluma kanaan Godina Qellem Wallaggaa Aanaa Anfillootti Abbaan Qabeenyaa Obbo Ismaa`el_Hashiim jedhamu barattoota harka qalleeyyii ta'aniif meeshalee deggersa barnootaa qarshii miiliyoona 3fi kuma 400'n deeggersa taasisanii jiru.

Obbo Ismaa'el kana malee aanichatti mana harka qalleeyyii ijaaruu, manneen barnootaaf meeshaalee barnootaa addaa addaa arjoomuu fi hojilee tajaajila lammummaa gara garaa irratti hirmaachuun hawaasa naannoo isaaniif tajaajila lammummaan gumaacha gochaa turaniiru.
Abbootiin qabeenyaa biroos naannoo isaanitti hojii misoomaa adda addaa keessatti qooda fudhachuu akkasumas harka qalleeyyii deeggaruun dirqama lammummaa qaban bahachuun guddina biyyaaf tumsuu qabu.

Odeeffannoo Dabalataa Argachuuf
Facebook:
https://www.facebook.com/oromiabc
------
Telegram: https://t.me/Oromiacommunicationaffairsbureau
------
Twitter: twitter.com/OromiaBureau
------
YouTube:
https://www.youtube.com/
------
TikTok: tiktok.com/
------
Website: https://www.oromiacommunication.gov.et/
------
kallachaOromia: https://m.facebook.com

24/03/2024
24/03/2024
23/03/2024
"ለወሰን እና የማንነት ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እየተሰራ ነው"- የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘው ተሻገር********************የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አገኘው ተ...
28/02/2024

"ለወሰን እና የማንነት ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እየተሰራ ነው"- የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘው ተሻገር
********************

የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አገኘው ተሻገር ለወሰን እና የማንነት ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ገለጹ።

አፈጉባኤው ይህን ያሉት፤ የፌደሬሽን ምክር ቤት እና የፌደራል ፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ በተፈራረሙበት ወቅት ነው።

የስምምነት ሰነዱ ሁለቱ ተቋማት የሀብት ማፈላለግ፣የአቅም ግንባታ እና የምርምር ስራዎችን በጋራ ለመስራት ያስችላቸዋል ተብሏል።

አፈጉባኤ አገኘው ተሻገር ሁለቱ ተቋማት የደረሱት ስምምነት፤ የወሰን እና የማንነት ጥያቄዎችን በዕውቀት እና በምርምር ለመመለስ አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል።

በስምምነቱ መሰረት የሚሰሩ ጥናቶች ሕገ መንግስቱን የመተርጎም እና ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል ስራዎችን በቀላሉ ለመፈፀም እንደሚያግዝም ተናግረዋል።

የፌደራል ፍትሕ እና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ደግፌ ቡላ፤ የፌደራል ስርዓቱን ለማጠናከር እና የዳበረ ዴሞክራሲን እውን ለማድረግ በስምምነቱ መሰረቱ ተቋማቱ በጋራ ይሰራሉ ብለዋል።

የሁለቱ ተቋማት የጋራ ስምምነት የመንግስታት ግንኙነትን ማጠናከር፣በሕገ መንግስታዊነት እና በሕግ የበላይነት ላይ የአቅም ግንባታ በመስራት በክልል እና በፌደራል ደረጃ ተቀራራቢ የሕግ አተረጓጎም እንዲኖርም ያግዛል ተብሏል።

በንብረቴ ተሆነ

28/02/2024

ሀሰተኛ ሊብሬና ታርጋ በማውጣት ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት ያደረሱ እስከ 25 ዓመት በሚደርስ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉሙሩክ ስርዓት ሳይፈጽሙ ሀሰተኛ የተሽከርካሪ ሊብሬና ታርጋ በማወጣት ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት ያደረሱ ግለሰቦች እስከ 25 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ።

የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ወንጀል ችሎት ተከሳሾቹ ጥፋተኛ በተባሉባቸው ተደራራቢ ክሶች መነሻ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየት መርምሮ ነው ዛሬ በዋለው የችሎት ቀጠሮ ተከሳሾቹን በጽኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ የወሰነው።

ተከሳሾች የኦሮሚያ ክልል የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ሰበታ ቅርጫፍ ሰራተኛ የነበሩት ለሚ በየነ እና ያይላል ንጋቱ እንዲሁም በግል ስራ የሚተዳደሩት መሪማ ጀማል፣ ጌታቸው ንጉሴ እና ቃልኪዳን አሰፋ ናቸው።

የኦሮሚያ ክልል የፍትህ ቢሮ የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ የተሳትፎ ደረጃ ጠቅሶ ተደራራቢ ክሶችን አቅርቦባቸው ነበር።

ይህም ያቀረበው ክስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 እና አንቀጽ 33 እና የሙስና አዋጅ 881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ ቁጥር 1 እና 2፣ አንቀጽ 33 እና የጉሙሩክ አዋጅን አንቀጽ 167 ንዑስ ቁጥር 1፣ አንቀጽ 168 ንዑስ ቁጥር 1 እንዲሁም አዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀጽ 29 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) እና ንዑስ ቁጥር 2 (ለ) ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል የሚል ነበር።

በተለይም 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች በ2015 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ሰበታ ቅርጫፍ ባለሙያነት ሲሰሩ ከ3ኛ እስከ 5ኛ ተራ ቁጥር ከተጠቀሱ ግለሰቦች ጋር በመመሳጠር ከህግና አሰራር ውጪ የጉሙሩክ ስርዓት ያልተፈጸመባቸው በአካል ያልቀረቡ ሶስት ቪ8 ተሽከርካሪዎች የታርጋ ቁጥር፣ ሊብሬና ቦሎ የተለያዩ የማረጋገጫ ሰነዶች እንዲወጣላቸው ማድረጋቸውን ዐቃቤ ሕግ በክሱ አመላክቷል።

ጌታቸው ንጉሴና ቃልኪዳን አሰፋ የተባሉ ተከሳሾች ደግሞ የጉሙሩክ ስርዓት ያልተፈጸሙባቸው፣ ከሰበታ ቅርንጫፍ የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ በህገወጥ መንገድ የወሰዱትን የተሽከርካሪ የማረጋገጫ ሰነዶችን ለባንክ በማቅረብ 26 ሚሊየን ብር ብድር መውሰዳቸው በክሱ ላይ በዝርዝር ሰፍሯል።

በአጠቃላይ በተጠቀሰው መልኩ በተፈጸመ ህገወጥ ተግባር መንግስት ላይ ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው በዐቃቤ ሕግ ተደራራቢ ክስ ተመስርቶባቸው ነበር።

ተከሳሾቹ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ ከደረሳቸውና በንባብ ከተሰማ በኋላ ወንጀሉን አልፈጸምንም በማለት የሰጡትን የዕምነት ክህደት ቃል ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ ስድስት የሰው ምስክር ቃልና የተለያዩ የሰነድ ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።

ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መርምሮ ተከሳሾቹ በተከሰሱባቸው ድንጋጌዎች እንዲከላከሉ ብይን የሰጠ ቢሆንም ተከሳሾቹ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢ መንገድ መከላከል ባለመቻላቸው ተከላከሉ በተባሉበት ድንጋጌ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየትን ከግምት ውስጥ በማስገባት ተከሳሾቹን በጽኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።

በዚህም የኦሮሚያ ክልል የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ሰበታ ቅርጫፍ ሰራተኛ የነበሩት 1ኛ ተከሳሽ ለሚ በየነን በ23 ዓመት ከ6 ወራት ጽኑ እስራትና በ225 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ የተወሰነ ሲሆን፥ 2ኛ ተከሳሽ ያይላል ንጋቱን ደግሞ በ18 ዓመት ጽኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ተወስኗል።

በግል ስራ የሚተዳደሩት 3ኛ ተከሳሽ መሪማ ጀማልን በሚመለከት በ22 ዓመት ከ6 ወራት ጽኑ እስራትና 335 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ የወሰነው ፍርድ ቤቱ፥ 4ኛ ተከሳሽ ጌታቸው ንጉሴ ደግሞ በ25 ዓመት ጽኑ እስራትና በ175 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።

ፍርድ ቤቱ 7ኛ ተከሳሽ ቃልኪዳን አሰፋን በሚመለከት በ12 ዓመት ጽኑ እስራትና በ60 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።

ከተከሳሾች ላይ የተያዙ ተሽከርካሪዎች ለመንግስት ገቢ እንዲሆኑ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

በታሪክ አዱኛ

ወንድሜ ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ በኬንያ ላደረጉልን ደማቅ አቀባበል አመሰግናለሁ። ሰፋ ያሉ ጉዳዮችን ያካተተው የዛሬው ውይይታችን የቆየውን ትስስራችንን ያጠናከረ ብቻ ሳይሆን የወደፊት ቁልፍ የ...
28/02/2024

ወንድሜ ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ በኬንያ ላደረጉልን ደማቅ አቀባበል አመሰግናለሁ። ሰፋ ያሉ ጉዳዮችን ያካተተው የዛሬው ውይይታችን የቆየውን ትስስራችንን ያጠናከረ ብቻ ሳይሆን የወደፊት ቁልፍ የትብብር መስኮችንም የለየ ነበር። የጋራ አንድ ርዕይ እና እጣፈንታ እንዳላቸው ጎረቤቶች በጋራ ለመስራት ያለን ቁርጠኝነት ተጠናክሯል።

I extend my heartfelt gratitude to my brother, President William Ruto, for his gracious welcome to Kenya. Our comprehensive discussions today have not only strengthened our existing ties but also highlighted key areas for future collaboration. As neighbors sharing a unified vision and destiny, our commitment to working together remains steadfast.

Adresse

Paris

Site Web

Notifications

Soyez le premier à savoir et laissez-nous vous envoyer un courriel lorsque Biiroo Aadaf Turiizimi oromiyaa publie des nouvelles et des promotions. Votre adresse e-mail ne sera pas utilisée à d'autres fins, et vous pouvez vous désabonner à tout moment.

Partager