Online Doctor ኦንላይን ዶክተር

  • Home
  • Online Doctor ኦንላይን ዶክተር

Online Doctor ኦንላይን ዶክተር Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Online Doctor ኦንላይን ዶክተር, Doctor, .

19/03/2025

ስኪዞፍሬኒያ (Schizophrenia)

- ሀሰተኛ እምነቶች (delusions)፡ በጠንካራ መልኩ የተሳሳቱ ሃሳቦችን ማመን።

- ሃሰተኛ ስሜቶች (hallucinations)፡ የሌሉ ነገሮችን ማየት፣ መስማት ወይም መሰማት።

- ያልተደራጀ ንግግር፡ ሃሳቦችን በግልጽ ማስተላለፍ አለመቻል።

- ያልተደራጀ ባህሪ፡ ወጥነት የሌለው ወይም ያልተጠበቀ እንቅስቃሴ።

- ሃሳባዊ ግራ መጋባት፡ ሰዎች እውነታን ከፈጠራ ለይተው ማወቅ ይቸግራቸዋል።

19/03/2025

Common Types of Delusions

-Persecutory : they are going to get me.
(ሌሎች ሰዎች "ሊጎዱኝ ነው" ወይም ጉዳት ለማድረስ እያቀዱ ነው የሚል እምነት)

-Reference : Everyone is looking at me.
(በዙሪያቸው ያሉ ነገሮች፣ ሁኔታዎች ወይም የሌሎች ሰዎች ድርጊቶች ከራሳቸው ጋር የተለየ ግንኙነት አላቸው ብለው ማሰብ)

- Grandiose delusions :I am the richest person in the world. (ስለራሳቸው ልዩ ችሎታ፣ ሀብት ወይም ዝና ያልተረጋገጡ እምነቶች)

- Guilt:it’s my fault there are so many people unemployed. (በዓለም ውስጥ ለሚከሰቱ አሉታዊ ክስተቶች ወይም ሁኔታዎች ኃላፊነት አለብኝ የሚል የተሳሳተ እምነት)

-Nihilism: I am dead ( እኔ፣ የእኔ አካል፣ ወይም ዓለም አይኖርም የሚል እምነት)

የጀርባ ሕመም እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የኅብረተሰባችን ክፍል እያጠቃ የሚገኝ የሕመም ዓይነት ነው፡፡ በአብዛኛው ይህ ሕመም በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ የተለመደ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ ...
03/02/2023

የጀርባ ሕመም

እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የኅብረተሰባችን ክፍል እያጠቃ የሚገኝ የሕመም ዓይነት ነው፡፡ በአብዛኛው ይህ ሕመም በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ የተለመደ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ ግን በወጣትነት የዕድሜ ክልል ባሉ ሰዎች ላይም እየተበራከተ ይገኛል፡፡

► የጀርባ ሕመም ለምን ይከሰታል፧የጀርባ ሕመም ከማንኛቸውም የሰው ጀርባን ከሚሰሩ የሰውንት ክፍሎች ሊነሳ ይችላል፡፡
እነዚህም፤
የጀርባ ጡንቻዎች መሳሳብ (መሸማቀቅ)
ከባድ ዕቃን ያለአግባብ ለማንሳት መሞከር
ድንገተኛ የሆነ ከፍተኛ እንቅስቃሴ
የዲስክ መንሸራተት
የመገጣጠሚያ ላይ ኢንፌክሽን
የአጥንት መሳሳት

► የጀርባ ሕመም ከዕለት ተዕለት የኑሮ ሁኔታችን ጋር ይያያዛል፡፡ከባድ ዕቃን በመግፋት ወይንም በመጎተትከባድ ዕቃን በመሸከም ወይም በማንሳትለብዙ ሰዓት በመቆም
ለብዙ ሰዓታት አጎንብሶ መቀመጥያለ ዕረፍት ለብዙ ሰዓታት መኪና ማሽከርከር

► የጀርባ ሕመምን እንዴት መከላከል ይቻላል፧የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፡፡ ኤሮቢክስ የሚባለውን የስፖርት ዓይነት መሥራት የሰውነታችንን አቅም ከመጨመር ባለፈ ክብደታችንን በመቀነስ የጀርባ ሕመም ይከላከላል፡፡
ሲጋራ ማጤስን ማቆም፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ሲጋራን የሚያጤሱ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ ለጀርባ ሕመም ተጋላጭ ናቸው፡፡
የሰውንት ክብደት መቀነስ፡፡ የሰውነት ክብደታቸው የጨመረ ሰዎች የጀርባ ሕመም ይኖርባቸዋል፡፡
የተስተካከለ አቀማመጥ፡፡ በምንቀመጥበት ጊዜ ጀርባችንን የሚደግፍ እና እጃችንን የምናሳርፍበት ቀጥ ያለ አቀማመጥ መያዝ፡፡
የተስተካከለ አቋቋም፡፡ በምንቆምበት ጊዜ የሰውነት ክብደታችን በሁለቱም እግሮቻችን በእኩል መጠን እንዲያርፍ ማድርግ እና ቀጥ ብለን ሳንቆለመም መቆም፡፡
ክብደት ያላቸውን ዕቃዎች በአግባቡ ማንሳት፡፡ ክብደት ያላቸውን በምናነሳበት ጊዜ ክብደቱን ከወገባችን፨ከጀርባችን ይልቅ በእግሮቻችን ላይ እንዲያርፍ ማድርግ ተገቢ ነው፡፡ ዕቃዎችን በምናንቀሳቅስበት ጊዜ ከመጎተት ይልቅ መግፋትተመራጭ ነው፡፡
ጫማ፡፡ የጀርባ ሕመም እንዳይሰማን የምንጫማቸው ጫማዎች ምቹ ሊሆኑ ይገባል፡፡
መኪና በምንሽከረክርበት ወቅት ጀርባችንን መደገፍ፡፡ ለረጅም ሰዓት የምናሽከረክር ከሆነ በየማሃሉ ከመኪና በመውረድ ሰውነትን ማንሳሰቀስና ዕረፍት መውሰድ ተገቢ ነው፡፡
የአልጋ ፍራሽ ምቾት፡፡ የምንተኛበት የአልጋ ፍራሽ ቀጥ ያለ መሆን አለበት፡፡
የጀርባ ሕመም ከባድ የሆኑ የጤና ችግሮች ምልክት ሊሆን ስለሚችል በቀላሉ ሊመለከቱት አይገባም፡፡በመሆኑም ከዚህ በታች የሚጠቀሱት ተጫማሪ ምልክቶች ካሉ ወደ ሕክምና ማዕከል በመሄድ መመርመር ያስፈልጋል፡፡እነዚህም፤
በድንገተኛ የመኪና አደጋ ወይንም መውደቅን ተከትሎ የመጣ የጀርባ ሕመም
ከወር በላይ የቆየ እና እየባሰ የመጣ የጀርባ ሕመም
በሕመም ማስታገሻ እና ዕረፍት በመውሰድ ለውጥ የማያመጣ የጀርባ ሕመም
ከወገብ በታች የመደንዘዝ ስሜት
ደም የቀላቀለ ሽንት መኖር
ከፍተኛ ትኩሳት መኖር እና ሆድ ሕመም መሰማት ናቸው፡፡
ጤና ይስጥልኝ

Address


Telephone

+8618689528508

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Online Doctor ኦንላይን ዶክተር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Online Doctor ኦንላይን ዶክተር:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Practice
  • Claim ownership or report listing
  • Want your practice to be the top-listed Clinic?

Share