Hakim-bet.com

  • Home
  • Hakim-bet.com

Hakim-bet.com We promote health and health related issues by providing fresh, unbiased and credential information

9ኙ የማንጎ የጤና በረከቶችየፍራፍሬዎች ሁሉ ንጉስ እየተባለ የሚሞካሸው ማንጎ እጅግ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች ሲኖሩት፥ በዋናነት ግን የሚከተሉትን የጤና በረከቶች ይዟል።1. ካንሰርን ይከላከላ...
18/04/2024

9ኙ የማንጎ የጤና በረከቶች

የፍራፍሬዎች ሁሉ ንጉስ እየተባለ የሚሞካሸው ማንጎ እጅግ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች ሲኖሩት፥ በዋናነት ግን የሚከተሉትን የጤና በረከቶች ይዟል።

1. ካንሰርን ይከላከላል፣ጥናቶች እንደሚሳዩት ከሆነ ማንጎን መመገብ ከአንጀት፣ ከጡት፣ከደም እና ከፕሮስቴት ካንሰር ለመጠበቅ ይረዳል።

2. የኮሌስትሮል መጠንን ይቀንሳል፣ማንጎ የኮሌስቴሮል መጠንን መቀነስ የሚችሉ
ንጥረ ነገሮችን በውስጡ በከፍተኛ ሁኔታ ይዟል።

3. ለቆዳ ጤንነት ተመራጭ ነው፣ማንጎን በመመገብም ሆነ ፊትን በመቅባት የቆዳዎን ጤንነት ማሻሻል ይችላሉ።

4. የኩላሊት ጠጠርን ይቀንሳል፣ማንጎን አዘውትሮ መመገብ ጣፋጭ ጣዕምን ከማግኘት ባላፈ በኩላሊታችን ውስጥ ጠጠር እንዳይፈጠር ማድረግ ይቻላል።

5. ለአይን ጤንነት ፍቱን ነው፣ማንጎ ቫይታሚን ኤ በውስጡ ስለሚይዝ የአይን የማየት ጥራትን ይጨምራል።

6. የምግብ መፈጨት ሂደትን ያፋጥናል፣እንደ ፓፓዬ ሁሉ ማንጎም የምግብ መፈጨትን
ስርአት ያፋጥናል።

7. የማስታወስ ችሎታችን ለማሳደግ፣ማንጎ ግሉታሚን የተሰኘ እና የማስታወስ ችሎታችንን የሚያሳድግ እንዲሁም አንድን ስራ በትኩረት ለመስራት የሚያስችል ንጥረ ነገርን አምቆ ይዟል በውስጡ። በተለይም ህፃናት እና ታዳጊዎች አዘውትረው ቢመገቡት በፈተና ወቅት ትኩረታቸውን ለመሰብሰብ በእጅጉ ይረዳቸዋል።

8. በሽታ የመከላከል አቅማችንን ያጎለብታል፣ቫይታሚን እና ቫይታሚን በተጨማሪ ሌሎች
የተለያዩ ንጥረ ነገሮች በሽታን የመከላከል አቅማችንን ያዳብራሉ።

9. በሰውነታችን የስኳር መጠንን ለማስተካከል፣የማንጎ ፍሬው ብቻ ሳይሆን ቅጠሉም ለጤና
ጠቃሚ ነው።

እባኮን ይህን ጠቃሜ መረጃዎች share በማድረግ ለወገኖ እንዲደርስ

ይተባበሩን Hakim-bet.com

የነጭ ሽንኩርት የጤና ጥቅሞችo በነጭ ሽንኩርት ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር በፈንገስ ምክንያት ለሚከሰቱ የቆዳ ሕመሞች መድኃኒትነት አለው፡፡• በከፍተኛን ደረጃ ባክቴሪያንና ቫይረሶችን የማጥፋት...
15/04/2024

የነጭ ሽንኩርት የጤና ጥቅሞች
o በነጭ ሽንኩርት ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር በፈንገስ ምክንያት ለሚከሰቱ የቆዳ ሕመሞች መድኃኒትነት አለው፡፡
• በከፍተኛን ደረጃ ባክቴሪያንና ቫይረሶችን የማጥፋት ብቃት ያለው የምግብ ዓይነት ነው፡፡
o ነጭ ሽንኩርት በውስጡ የደም መርጋትን የሚከላከል ንጥረ ነገርን ይይዛል፡፡ የደም ግፊት መጨመርን ይከላከላል፡፡
o ከዕድሜ መጨመር የተነሳ የሚከሰት የደም ቧንቧ ጥበትን የመከላከል ጥቅም ያለው ነጭ ሽንኩርት ይህንን በማድረግ በደም ቧንቧ ጥበት ምክንያት የሚከሰት የልብ ሕመምን ይከላከላል፡፡
o በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የኮሌስትሮል መጠን በመቀነስ በደም ቧንቧ ላይ የሚገኘውን የስብ መጠን እንዲቀንስ ያድርጋል፡፡
o ሰውነታችን በአለርጂ እንዳይጠቃ የማድረግ አቅምም አለው፡፡ በሰውነት ላይ ለሚወጣ ሽፍታና በአንዳንድ ነፍሳት ምክንያት የሚወጣንን ሽፍታም ይከላከላል፡፡
o ነጭ ሽንኩርት በጉንፋን የመያዝ ሁኔታን በከፍተኛ ደረጃም ይቀንሳል፡፡ከተያዝንም በኋላ እንዳይበረታብንና ቶሎም እንድንድን ይረዳል፡፡
o ነጭ ሽንኩርት በሰውነታችን የሚመነጨውን የኢንሱሊን መጠን መጨመርና በደም ውስጥ የሚገኙትን የስኳር መጠን በመቆጣጠር ለስኳር ሕመም ጠቀሜታነት ይሰጣል፡፡
• የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት ጥርሳችንን በሚያመን ቦታ ላይ በማድረግ ባክቴሪያዎችን ማጥፋትና ሕመምን የመቀነስ ጥቀም አለው፡፡

27/03/2024
በአሁን ወቅት በብዛት ከባዕድ ነገር ጋር ተቀይጠው ከሚሽጡ የምግብ ግብዓቶች መካከል ማር አንዱ ነው ። ወይ ከጤናችን አልሆንን ወይ ከገንዘባችን አልሆንን። ለመሆኑ አንድን ማር ንጹ ማር መሆኑ...
25/03/2024

በአሁን ወቅት በብዛት ከባዕድ ነገር ጋር ተቀይጠው ከሚሽጡ የምግብ ግብዓቶች መካከል ማር አንዱ ነው ። ወይ ከጤናችን አልሆንን ወይ ከገንዘባችን አልሆንን። ለመሆኑ አንድን ማር ንጹ ማር መሆኑን በምን እናውቃለን? አያስቡ በቤትዎ በቀላሉ ይህን ሊያረጋግጡ የሚችሉበትን 3 ፈጣን መላዎች እናካፍሎ
1, የማር ወለላ ሙከራ - በአንድ ሳህን ውስጥ ጥቂት ማር ይውሰዱ፣ በላዩ ላይ ውሃ ይጨምሩበት እና በሰዓት አቅጣጫ( ከቀኝ ወደ ግራ )ያማስሉት። ባለ ስድስት ጎን የማር ወለላ ሸካራነት ከተፈጠረ ንፁህ ማር ነው።
2, ንጹ ማር ከአውራ ጣት ጋር ይጣበቃል - በአውራ ጣትዎ ላይ አንድ ማር ጠብታ ያስቀምጡ፣ የማይጣበቅ እና የሚንጠባጠብ ከሆነ ንጹህ ማር አይደለም።
3. ይመልከቱ እና ያሽትቱ - ንፁህ ማር ሁል ጊዜ ደመናማ ነው ። አያብረቀርቅም እና የአበባ ጠረን አለው ። ንፁህ ያልሆነ ማር ግን የሚያብረቀርቅ ፣ ግልፅ እና የሸንኮራማ ሽሮፕ ጠረን ሊሰጥ ይችላል።
እባክዎን ይህን የጤና መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ share ያድርጉ? እናመሰግናለን!
© Hakim-bet.com

8ቱ የቅርንፉድ የጤና ጥቅሞች ዛሬ ኢንዶኔዥያ ለአለም ካበረከተቻቸው የህፀዋት አይነቶች መካከል ስለ ቅርንፉድ  የጤና ጠቀሜታ እናካፍላችኋለን።የቅርንፉድ ተክል የዛፍ ዝርያ አይነት ሲሆን ሞቃታ...
13/03/2024

8ቱ የቅርንፉድ የጤና ጥቅሞች
ዛሬ ኢንዶኔዥያ ለአለም ካበረከተቻቸው የህፀዋት አይነቶች መካከል ስለ ቅርንፉድ የጤና ጠቀሜታ እናካፍላችኋለን።
የቅርንፉድ ተክል የዛፍ ዝርያ አይነት ሲሆን ሞቃታማና ርጥበት ያለበት ቦታ ይስማማዋል፤ ዘሩን ለማብቀል ከ1-2 ወር ይፈጃል፤ የመጀመሪያውን አበባ ለማበብ 5-6 አመት ሊወስድበት ይችላል፡፡ ዛፉ ዘገምተኛ አበቃቀል ያለው ሲሆን ሙሉ በሙሉ ምርት ለመስጠት ከ10 አመት በላይ ይፈጃል፤ በሃገራችን ጥብቅ ደኖችና ቤተክርስቲያኖች አካባቢ እስከ እድሜው 300 አመት የሆነው ዛፍ ሊገኝ ይችላል፡፡
ቅርንፉድ ፍሬውን በመዝራት የሚበቅል ሲሆን ፍሬው ሳይደርቅ (ወዲያው እንደተለቀመ) መሆን አለበት፡፡ ከቅርንጫፉ ግንጣይ ወስዶ ማባዛት የሚቻል ቢሆንም ተመራጩ ዘዴ ዘሩን መጠቀም ይሆናል፡፡ ለመሆኑ ይሄን ያህል ያወራንለት ቅርንፉድ ምን ያህል የጤና ጠቀሜታ ይኖረው ይሆን። ታዋቂው ሄልዝ ላይን ዶትኮም በድረ-ገጹ ላይ የለጠፈውን የቅርንፉድን የተረጋገጡ ሳይንሳዊ የጤና በርከቶች እናካፍላችሁ።
1. ጠቃሚ የምግብ ንጥረ ነገሮችን ይዟል
2. መርዛማ ነገሮችን ከሰውነታችን ያስወግዳል
3. ካንሰርን ለመከላከል ይረዳል
4. ባክቴሪያዎችን ይገድላል
5. የጉበት ጤናን ያሻሽላል
6. የደም ስኳር መጠንን ለማስተካከል የረዳል
7. የአጥንትን ጤንነት ይጠብቃል
8. የጨጓራ ቁስለትን ይቀንሳል
እባክዎን ይህን መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ ይተባበሩን? እናመሰግናለን!
©Hakim-bet.com

የቴምር የጤና በረከቶች1. ስብና ኮልስትሮል፡- ከየትኛውም የኮልስትሮል ዓይነቶች የጸዳና በጣም አነስተኛ የስብ መጠን ያለው መሆኑ ክብደት መቀነስ ለሚፈልጉ ተመራጭ ነው፡፡2. ፕሮቲን፡- ቴምር...
11/03/2024

የቴምር የጤና በረከቶች
1. ስብና ኮልስትሮል፡- ከየትኛውም የኮልስትሮል ዓይነቶች የጸዳና በጣም አነስተኛ የስብ መጠን ያለው መሆኑ ክብደት መቀነስ ለሚፈልጉ ተመራጭ ነው፡፡
2. ፕሮቲን፡- ቴምር በፕሮቲንና አስፈላጊ ማዕድናት የበለጸገ መሆኑ ለሰውነት እጅጉን ጠቃሚ ያደርገዋል፡፡
3. ቫይታሚን፡- በቫይታሚን የበለጸገ ነው ቴምር፡ ፡ ከቫይታሚን ዓይነቶች ቢ1፣ ቢ2፣ ቢ3፣ ቢ5፣ ኤ1 እና ሲ ንም አካትቶ ይዟል፡፡
4. ሀይል እና ጉልበት፡- ቴምር ቀላል የማይባል የሀይል ክምችት ስላለውም ንቁና በሀይል የተሞላን እንድንሆን ያስችለናል፡፡
5. ፖታሲየምና ካልሲየም፡- ቴምር የፖታሲየም ክምችቱ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህም በልብ በሽታ እንዳንጠቃና አካላችን ውስጥ ያለው የኮልስትሮል መጠን እንዲቀንስ ይረዳል፡፡ ቴምር በአንጻሩ አነስተኛ የሶዲየም መጠን ነው ያለው፡፡ ብዙ ፖታሲየምና ትንሽ ሶዲየም ደግሞ ለጤናማ የነርቭ ስርዓት ወሳኝ ነው፡፡
6. ብረት፡- ቴምር በብረትና በፍሎሪን የበለጸገ መሆኑ ደግሞ ብረቱ የብረት ማዕድን እጥረት ላለባቸው ሰዎች፣ ፍሎሪኑ ደግሞ ጥርስን ከመበስበስ ይከላከላል፡፡
7. ድርቀት፡- ለድርቀትም ቢሆን ውሃ ውስጥ የተነከረ ቴምር መመገብ ፍቱን እንደሆነ ይታወቃል፡፡
8. ሰውነትን ማጽዳት፡- በአልኮል መጠጣት ሳቢያ ሰውነት ውስጥ የሚከማቸውን መርዛማ ኬሚካሎች ከሰውነታችን ውስጥ በማስወገድም ይረዳል፡፡
9. ካንሰር እና የዓይን ችግር፡- የዓይን ህመም ችግርንና የሆድ ነቀርሳ (ካንሰር)ን ለማከምም ብቃት እንዳለው ይታወቃል – ቴምር፡፡
10. የቆዳ ችግር፡- ቴምር የቆዳ ችግሮችን በማስወገድም መልካም ዝና አለው፡፡ ጸጉርን በማፋፋት የጸጉር መሳሳትንም ይከላከላል፡፡
በርከት ያሉ ቪታሚኖችን እና ማዕድናትን በመያዙ ለጤናችን በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ይነገርለታል። ሀይል ሰጪ፣ ፋይበር፣ እንዲሁም ካልሺየም፣ አይረን፣ ፎስፈረስ፣ ሶዲየም፣ ፖታሲየም፣ ማግኒዚየም፣ እና ዚንክ ሚኔራሎች በቴምር ውስጥ የሚገኙ በመሆኑ ቴምርን ለጤና ጠቃሚ ያደርጉታል።
ስለዚህም ቴምርን አዘውትረን መመገብ ለጤናችን ከሚሰጠው ጠቀሜታዎች ውስጥም፦
• የሆድ ድርቀትን ይከላከላል፡- ቴምር በባህሪው የማለስለስ ባህሪ ስላለው ምግብ በአንጀታችን ውስጥ በቀላሉ እንዲዘዋወር በማድረግ የሆድ ድርቀት ለመከላከል ይረዳል። ለዚህም ይረዳን ዘንድ ቴምሩን በውሃ ውስጥ ዘፍዝፈን በማሳደር ጠዋት ላይ መመገብ ይመከራል።
• ለአጥንት ጤንነት እና ጥንካሬ፡- በቴምር ውስጥ የሚገኙት ማዕድናት ለአጥንታችን ጥንካሬ እና ጤንነት እጅጉን ጠቃሚ እንደሆኑ ይነገራል። ቴምር እንደ ሴሌኒየም ማንጋኒዝ፣ ኮፐር እና ማግኒዚየም ማእድናትን በውስጡ በመያዙም ለአጥንት ጤናማ እድገት እና ጥንካሬ ጠቃሚ ነው።
• ደም ማነስን ይከላከላል፡- ቴምር በውስጡ በያዘው ከፍተኛ የምግብ ማዕድናት ንጥረ ነገሮች ክምችት የደም ማነስ ችግር ላለባቸው ሰዎች እጅጉን ጠቃሚ ነው።
• አለርጂን ይከላከላል፡- ቴምርን ከሌሎች ለየት የሚያደርገው አለርጂን ለመከላከል የሚረዳውን ሰልፈር ንጥረ ነገር በውስጡ በመያዙ ነው። ስለዚህም ቴምርን አዘውትረን የምንመገብ ሰዎች ለተለያዩ አይነት አለርጂዎች የመጋለጥ እድላችን እጅጉን እንዲቀንስ እንደሚያደርገው ይነገርለታል።
• ለነርቭ ጤንነት፡- በቴምር ውስጥ የሚገኙት ቪታሚኖች የተስተካከለ እና ጤናማ የነርቭ ስርዓት እንዲኖረን ስለሚያደርግም ለጤናችን ጠቃሚ ያደርገዋል።
• ለልብ ጤንነት፡- ቴምር ለልባችን ጤንነት በርካታ ጠቀሜታዎች ስላሉት ተመራጭ ያደርገዋል። ቴምር የልብ ጤንነትን ይጎዳል የሚባለውን የኮሌስቴሮል መጠን የመቀንስ እቅም ስላለው ለድንገተኛ የልብ ህመም እንዳንጋለጥ በመርዳትም ለልባችን ጤንነት ጠቀሜታ አለው።
• ስንፈተ ወሲብን ይከላከላል፡- ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ቴምር በውስጡ በያዘው ንጥረ ነገሮች አማካኝነት የሰዎችን የወሲብ ፍላጎት ከፍ እንዲል እና የወሲብ ፍራቻ ላለባቸው ሰዎች ድፍረትን እንዲያገኙ በማድረግ ስንፈተ ወሲብን ለመከላከል ይረዳል።
• በእርግዝና እና ወሊድ ወቅት ተመራጭ ምግብ ነው፡- ቴምር በእርግዝና ወቅት ለጽንሱ ጤንነት ብሎም በወሊድ ጊዜ ምጥ አስቸጋሪ እንዳይሆንና የተሻለ የማማጥ አቅም እንዲኖረን ያስችላል።
• የአዕምሯችንን ጤንነት ያሳድጋል፡-ጥናቶች በቴምር የምናገኘው ቫይታሚን ቢ6 የተሻለ የአዕምሮ ተግባራት እንዲኖርና ሰዎች በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘገቡ ማገዙን ተናግረዋል።

በተመገብነው ምግብ እንዴት ልንመረዝ እንችላለንየሆድ ጭብጠትና መንጓጓት እንዲሁም ጩኸት ፣ተቅማጥ፣ማስታወክ፣የምግብ ፍላጎት ማጣት ፣መጠነኛ ትኩሳት፣ድካምና ማቅላሽለሽ ካጋጠሞት በርግጥም በተመገ...
26/02/2024

በተመገብነው ምግብ እንዴት ልንመረዝ እንችላለን

የሆድ ጭብጠትና መንጓጓት እንዲሁም ጩኸት ፣ተቅማጥ፣ማስታወክ፣የምግብ ፍላጎት ማጣት ፣መጠነኛ ትኩሳት፣ድካምና ማቅላሽለሽ ካጋጠሞት በርግጥም በተመገቡት ምግብ ተመርዘዋል፡፡
በምግብ ለመመረዛችን ምልክቶቹ እንደ ኢንፌክሽን አይነቱ ይለያያል፡፡ ምልክቶቹ የሚታዩበት የጊዜ መጠንም እንደ ኢንፌክሽኑ መነሻ ይለያያል፡፡ ብዙን ጊዜ ከአንድ ሰዓት እስከ ሃያ ስምንት ቀናት ሊዘልቅ ይችላል፡፡

ለሕይወታችን በጣም አሰጊ የሚባለው የምግብ መመረዝ ምክንያቶቸ ከሆኑት ውሰጥ ከሦስት ቀናት በላይ የዘለቀ ተቅማጥ፣የሰውነት ሙቀት መጠን ከ101.5 ዲግሪ ፋራናይት በላይ መሆን ፣ለማየትም ሆነ ለመናገር መቸገር፣ከፍተኛ የሆነ መጠማት ( አፍ እስኪ ደርቅ ድረስ) ፣አነስተኛ ሽንትና በሽንቱ ውስጥ ደም መታየት ናቸው፡፡

የምግብ መመረዝ(Food poison) ዋነኛ ምክንያቶች ሦስት ናቸው፡፡ በባክቴሪያ ምድብ ውስጥ E.COLI፣ Listeria እና Salmonella ተጠቃሽ ናቸው ፡፡ በፓራሳይት በኩል Tox oplasma ተጠቃሽ ሲሆን በቫይረስ በኩል ደግሞ Norovirus፣ Sapovirus፣ Rotavirus፣ Astrovirus እና Hepatitsa A ይታወቃሉ፡፡

ብዙን ጊዜ በምግብ የምንበከለው ያልበሱሉ ምግቦች በመመገብ፣ ምግብ አብሳዮች፣ አቅራቢዎችና ተመጋቢዎች እጃቸውን ምግብ ከማዘጋጀታቸው፣ ከማቅረባቸውና ከመመገባቸው በፊት በአግባቡ ያለመታጠብ ችግር ነው፡፡

ስጋ፣ አሣ፣ እንቁላልና ወተትና የወተት ተዋህጾ ምግቦች በአብዛኛው ለምግብ ብክለት ተጋለጭ ምግቦች ሲሆኑ ህጻናት፣ወጣቶች፣ ነፍሰጡር ሴቶችና አረጋውያን ብዙን ጊዜ ለመግብ ብከለት ተጋለጭ ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ የዚህ ዋነኛ ምክንያት ተደረጎ የሚወሰደው የተፈጥሮ በሽታን የመከላከል አቅማቸው ያልዳበረ እና የተዳከመ በመሆኑ ነው፡፡

በምግብ ከተመረዝን በኃላ ወደ ቀድሞ ጤናችን ለማገገም ማድረግ የሚጠበቅብን ጠቃሚ ምክሮች
1. የፍራፍሬ ጭማቂዎችን መውሰድ፡- ድርቀትንና ድካማችንን ያሰወግዳል፡፡
2. ያለሐኪም ማዘዣ የሚሸጡ መድኃኒቶች Imodium እና Pepto-bismol ብንወስድ ተቅማጡንና ማቅለሽለሹን ይቆጣጠሩልናል፡፡
3. ካፊን ያለባቸውን እንደ ቡና፣ሻይና ለስላሳ መጠጦች አይውሰዱ፡፡
4. ቀለል ያሉና መጠነኛ ቅባት ያለባቸውን ምግቦች ይመገቡ፣ የተፈጨ አጃ፣ሩዝ፣ሙዝ፣ድንችና የተቀቀሉ አትክልቶችን ይውሰዱ፡፡
5. መመገብ ከሌለብዎ ምግቦች ውስጥ ወተትና የወተት ተዋፆዎች፣ ከፍተኛ ስኳር ያለባቸው ምግቦች፣ቅመም የበዛባቸውና የተጠበሱ ምግቦችን ከገበታዎ ያስወግዱ፡፡
6. አልኮልና ኒኮቲን የበዛባቸውን መጠጦች አይውሰዱ፡፡

መልካም ልምምድ መልካም የጤና ጊዜ ይሁንልዎ!
ውድ ቤተሰቦቻችን ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን አጫጭር የጤና መረጃዎች በሞባይል ስልካችሁ በየቀኑ እንዲደርሳችሁ በ6655 ላይ ok ብላችሁ ላኩ!!!

ረጅም ዕድሜ ለመኖር እነዚህን 20 ምግቦች ከገበታዎ ያርቁ1. ማርጋሪን2. የተቀነባበሩ ስጋዎች3. የለስላሳ መጠጦች4. ሰው ሰራሽ ማጣፈጫዎች5. በጥልቀት የሚጠበሱ ምግቦች6. ማይክሮዌቭ የተዘ...
20/02/2024

ረጅም ዕድሜ ለመኖር እነዚህን 20 ምግቦች ከገበታዎ ያርቁ
1. ማርጋሪን
2. የተቀነባበሩ ስጋዎች
3. የለስላሳ መጠጦች
4. ሰው ሰራሽ ማጣፈጫዎች
5. በጥልቀት የሚጠበሱ ምግቦች
6. ማይክሮዌቭ የተዘጋጀ ፈንዲሻ
7. በቆርቆሮ የታሸጉ ምግቦች
8. በፍጥነት የሚዘጋጁ ኑድሎች
9. ነጭ ዳቦ
10. በሰው ሰራሽ መልኩ የተዘጋጁ አኩሪ አተር
11. ጣፋጭ ጥራጥሬዎች
12. አይስክሬም
13. የታሽጉ የፍራፍሬ ጭማቂዎች
14. ማስቲካ ማኘክ
15. ሃይል የሚሰጡ መጠጦች
16. እርጎ
17. የኦቾሎኒ ቅቤ
18. በቅዝቃዜ ሰንሰለት ውስጥ የቆዩ ምግቦች
19. ፒዛ
20. ዶናትና ሌሎች የታሸጉ ምግቦች

ስለ ሳንባ ቲቢ ልናውቃቸው የሚገቡ እውነታዎችጥያቄ፡- የሳንባ ቲቢ በምን ይተላለፋል?መልስ፡- የሳንባ ቲቢ ቲበር ክሎሲስ በተባለ ረቂቅ ባክቴሪያ አማካኝነት በትንፋሽ  የሚተላለፍ በሽታ ነው፡፡...
19/02/2024

ስለ ሳንባ ቲቢ ልናውቃቸው የሚገቡ እውነታዎች

ጥያቄ፡- የሳንባ ቲቢ በምን ይተላለፋል?

መልስ፡- የሳንባ ቲቢ ቲበር ክሎሲስ በተባለ ረቂቅ ባክቴሪያ አማካኝነት በትንፋሽ የሚተላለፍ በሽታ ነው፡፡

ጥያቄ፡- በሽታው እንዴት ሊይዘን ይችላል?

መልስ፡- በሽታው በዋናነት የሚተላለፈው በበሽታው የተያዘ ሰው ሲስል፣ሲያስነጥስ፣ወይም ሲነጋገርየቲቢ ባክቴሪያ አየር ውስጥ ሊሰራጩ ይችላሉ፡፡ማንኛውም በቅርብ ያለ ሰው ባክቴሪያዎቹን ከአየር ጋር ወደ ውስጥ በመሳብ ሊያስገባ ይችላል፡፡ ነገር ግን የሳንባ ቲቢ በመጨባበጥ፣አብሮ በመብላት፣ በልብስ እንዲሁም የቤት ዕቃዎችን በጋራ በመጠቀም አይተላለፍም፡፡

ጥያቄ፡- የሳንባ ቲቢ ሰውነታችንን የሚጎዳው በምን አይነት መንገድ ነው?

መልስ፡-አብዛኛው ጊዜ የሳንባ ቲቢ የሚጎዳው ሳንባችንን ሲሆን ከእሱ በተጨማሪ አንጎላችንን፣ ማንቁርታችንን፣ አጥንታችንን እና ኩላሊታችን ይጎዳል፡፡

ጥያቄ፡- በሳንባ ቲቢ የተያዘ ሰው የሚያሳያቸው ምልክቶች ምንድን ናቸው?

መልስ፡- 3 ሳምንት ወይም ከዚያ በላይ የሚቆይ ሳል፣ክብደት መቀነስ፣የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ማታ ማታ ላብ፣ትኩሳት፣ብርድ ብርድ ማለት፣ድካም ወይም አቅም ማነስ፣ደረት ላይ ሕመም እና ሲስሉ ደም ወይም ቡናማ ቀለም ያለው አክታ መታየት ናቸው፡፡

ጥያቄ፡- በሳንባ ቲቢ ለተጠረጠረ ሰው የሚደረግለት ምርመራ ምንድን ነው?

መልስ፡- 1ኛ. የማንቱ የቆዳ ምርመራ አድርጎ ሰውነትዎ ውስጥ የሳንባ ቲቢ መኖሩን ማወቅ ይቻላል፡፡ ባክቴሪያዎቹ የተደበቁ ቢሆንም፡፡

2ኛ. የደረት ራጅ (ኤክስ ሬይ) አንስቶ ባክቴሪያዎቹ ሳንባዎን ጎድተው እንደሆነ ይታወቃል፡፡

3ኛ. የአክታ ምርመራ ማድረግ ባክቴሪያዎች ሳንባዎት ውስጥ እየተባዙ መሆኑን ያሳያል፡፡

ጥያቄ፡- ለሳንባ ቲቢ የሚሰጥ ሕክምና ምን አይነት ነው?

መልስ፡- የሳንባ ቲቢ ባክቴሪያዎች ጠንካራ ሲሆኑ ለረጅም ጊዜ በሰውነታችን ውስጥ ተደብቀው መኖር ይችላሉ፡፡ ስለሆነም ሕክምናው ለ6 ወራት የሚሰጥ ሲሆን የሚታዘዝሎትን መድኃኒት በአግባቡ ከወሰዱ ከበሽታው ፈፅሞ ይፈወሳሉ፡፡ ይህ የሚሆነው ግን ለ6 ወራት የታዘዘሎትን መድኃኒት በየቀኑ ምንም ሳያቋርጡና ሰዓት ሳያዛንፉ ከወሰዱ ብቻ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች መድኃኒቱን በጀመሩ ጥቂት ወራት ውስጥ የበሽታው ምልክቶች በፍጥነት ስለሚጠፉ ፈፅሞ የተሻላቸው ስለሚመስላቸው መድኃኒታቸውን ያቋርጣሉ፡፡ ይሄ ደግሞ በሽታው ተመልሶ እንዲመጣ ስለሚያድርግና ከዚያም በኃላ የሚደረግላቸው ሕክምና እጅግ ውስብስብና ከባድ ስለሚሆን ከወዲሁ ሊጠነቀቁ ይገባል፡፡

ጥያቄ፡- የሳንባ ቲቢን እንዴት መከላከል ይቻላል?

መልስ፡- የሳንባ ቲቢ በአብዛኛው የሚተላለፈው በትንፋሽ ስለሆነ በተለይ በበሽታው የተያዘው ሰው ሲስል፣ሲያስነጥና ሲናገር አፉና አፍንጫውን በመሀረብ አልያም በክንዱ መሸፈን አለበት፣አክታውንም የትም ቦታ መትፋት የለበትም፣ በአጠቃላይ በሽታውን ለመካላከል ታማሚው ያለበት ቤት መስኳትና በር መክፈት ያስፈልጋል፡፡ ሕዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች ለምሳሌ ትራንስፖርት ላይ መስኮቶች መከፈት ይኖርባቸዋል፡፡ መስኮት መክፈት ዋነኛ ጥቅሙ አየር በቀላሉ ገብቶ ባክቴሪያዎቹ ወደ ውጭ እንዲወጡ በማድረግ ሲወጡ ፀሀይ በቀላሉ ካገኛቸው ስለሚሞቱ ነው፡፡

እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ share በማድረግ ይተባበሩን!

ምስጋናችን ከልብ ነው!

© Hakim-bet.com

ሞሪንጋ ( ሺፈራሁ) ባለ ዘረፍ ብዙ መድኃኒተ እፅከሰሜን ሕንድ ለዓለም የተበረከተው የሞሪንጋ ተክል ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት ጀምሮ ለጤና ጠቃሜታ ሲውል የነበረ ምስጉን ተክል ነው፡፡ የሞሪንጋ...
12/02/2024

ሞሪንጋ ( ሺፈራሁ) ባለ ዘረፍ ብዙ መድኃኒተ እፅ

ከሰሜን ሕንድ ለዓለም የተበረከተው የሞሪንጋ ተክል ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት ጀምሮ ለጤና ጠቃሜታ ሲውል የነበረ ምስጉን ተክል ነው፡፡ የሞሪንጋ ተክል በአልሚ ምግቦች፣ በቫይታሚኖችና በአሚኖ አሲዶች የበለጸገ በመሆኑ ለሰውነታችን የሚፈለገውን ሁሉ በሟሟላት ተመልሶ እንዲታደስና አስፈላጊውን ኃይል እንዲያገኝ የሚያደርግ ችሎታ ያለው ተክል ነው፡፡ ይህን የተገነዘቡት ምዕራብአዊያን በተጨመሪ ምግብነት (supplementary food) አድርገው በመውሰድ በዱቄትና በኪንኒን መልክ አዘጋጅተው ለገበያ እስከማቅረብ ደርሰዋል፡፡

የሞሪንጋን ቅጠል ዱቄት በማንኛውም የእለት ተዕለት ምግባችን ውስጥ በመጨመር ልንመገበው እንችላለን፡፡ በተለያዩ የሾርባ ምግቦች ውስጥ በመጨመር፣በሻይ መልክ በፈላ ውሃ በጥብጦ በመጠጣት እና በጁስ ዓይነት በንፁህ ውሀ በጥብጦ አቀዝቅዞ በማንኛውም ሰዓትና ጊዜ መጠጣት ይቻላል፡፡

በሳይንስ የተረጋገጡ የሞሪንጋ የጤና ጥቅሞች

1. የተፈጥሮ የሰውነት ኃይል ያጎለብታል፡፡

2. የሰውነት በሽታ የመቋቋም ችሎታን ያጠናክራል፡፡

3. የሰውነት ቆዳን ጤንነት ይጠብቃል፡፡

4. የደም ግፊትን ይቆጣጠራል፡፡

5. በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ያስተካክላል፡፡

6. ራስ ምታትንና ማይግሬይንን ያስወግዳል፡፡

7. በእሪህና በመሳሰሉት የሚከሰት የህመም ስቃይን ያስታግሳል፡፡

8. የሰውነት እጢዎችን ሁኔታ ይቆጣጠራል፡፡

9. የጨጓራ አልሰርና የመሳሰሉትን ይፈውሳል፡፡

10. የሰውነት ጡንቻዎችን በማዝናናት የተስተካከለና ጤናማ የለሊት እንቅልፍ እንዲኖረን ይረዳል፡፡



በሳይንስ የተረጋገጡ የሞሪንጋ የምግብ ይዘት ጥቅሞች



1. ከብርቱካን ከሚገኘው ቫይታሚን ሲ ሰባት እጅ የበለጠ

2. ከካሮት ከሚገኘው ቫታሚን ኤ አራት እጅ የበለጠ

3. ከስፒናች ከሚገኘው ብረት ሦስት እጅ የበለጠ

4. ከወተት ከሚገኘው ካልስየም አራት እጅ የበለጠ

5. ከሙዝ ከሚገኘው ፖታስየም ሦስት እጅ የበለጠንጥረ ነገር ይዟል፡፡

እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን!

ምስጋናችን ከልብ ነው!

© Hakim-bet.com

ፎሜንቴሽንፎሜንቴሽን ማለት በሚፈላ ውሀ ተነክሮ የተጨመቀ ወይም በእንፋሎት የሞቀ ጨርቅ በአንድ የሰውነት ክፍል ላይ በማድረግ እርጥበት ያለበት ሙቀት መስጠት ነው፡፡ ፎሜንቴሽን በደንብ የመስጠ...
06/02/2024

ፎሜንቴሽን

ፎሜንቴሽን ማለት በሚፈላ ውሀ ተነክሮ የተጨመቀ ወይም በእንፋሎት የሞቀ ጨርቅ በአንድ የሰውነት ክፍል ላይ በማድረግ እርጥበት ያለበት ሙቀት መስጠት ነው፡፡ ፎሜንቴሽን በደንብ የመስጠቱ ምልክት ጨርቁ ከተነሣ በኋላ ቆዳ ቀይ ሆኖ ሲታይ ነው፡፡

ፎሜንቴሽን ለመስጠት የሚያስፈልጉ መሣሪያዎች

አንድ ጎድጓዳ የብረት ድስት ወይም የሚፈላ ውሃ የያዘ የተጣደ ትልቅ ማንቆርቆሪያ ፎሜንቴሽን የሚሰጥባቸው ስድስት ጨርቆች ጥቂት ፀጉራም ፎጣዎች ማድረቂያ ፎጣ አንሶለ እንደ በረዶ የቀዘቀዘ ውሀ የያዘ ትልቅ ጎድጓዳ ሣህንና ጠረፔዛ ያስፈልጋል፡፡

ፎሜንቴሽን የሚስፈልጋቸው ጥቅሞች

1. በጉሮሮና በደረት በላይኛው ክፍል ላይ ሲሰጥ በጉሮሮ በሽታ ፣በቶንሲላይቲስ፣በሳል፣በብሮንካይቲስና በሳንባ ውስጥ በደም መቋጠር ምክንያት የሚመጣውን ስቃይ ለማስታገስ ይረዳል፡፡

2. ታካሚው ያመመው ኩላሊቶቹን የሆነ እንደሆነ ወይም የጀርባ ወይም የወገብ ቁርጥማት ያለበት እንደሆነ ፎሜንቴሽን በጫንቃ ላይ ቀብቶ በሚውልበት ላይ መደረግ አለበት፡፡

3. በሕብለ ሠረሰር ላይ የሚደረግ ፎሜንቴንሽን እንቅልፍ ስለሚያስይዝ ሙቀቱ መጠነኛ መሆን አለበት ፡፡

4. በጉልበት ላይ የሚደረግ ፎሜንቴሽን በሠረሠር ላይ እንደሚሰጠው ሆኖ መታጠፍ ይገባዋል፡፡ጨርቁም በመታጠፊያው ሥር ይዘረጋና ጫፍና ጫፉን ወደ ላይ ስቦና መልሶ አንደኛው ሌላውን እንዲያለብሰው አድርጎ ይጠመጠማል፡፡

5. አንዳንድ ጊዜ በአይንና በሌላም አነስተኛ የሰውነት ክፍል ላይ ፎሜንቴሽን ማድረግ ያስፈልግ ይሆናል፡፡ከሠላሳ እስከ አምሳ ጊዜ የታጠፈ ሻሽ ( ፋሻ) በጣም በሞቀ ውሃ ነክሮና ጨምቆ ሕክምናውን ለመስጠት ይቻላል፡፡

ልብ ይበሉ! ፎሜንቴሽን በሚሰጥበት ጊዜ በሽተኛውን ብርድ እንደማያገኘው እርግጠኛ ካልሆኑ በቀር ይህን ሕክምና አለመስጠት ነው ሙቅ ውሀ በያዘ ላስቲክ ሙቀት ሊሠጥ ይችላል፡፡

እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን!

© Hakim-bet.com

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hakim-bet.com posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your practice to be the top-listed Clinic?

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram