Dr Yemeserach Dental Clinic

Dr Yemeserach Dental Clinic Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dr Yemeserach Dental Clinic, Medical and health, Addis Ababa.

27/09/2020
Enkuan le berehan mesekelu aderesachehu
28/09/2019

Enkuan le berehan mesekelu aderesachehu

የጥርስ መቦርቦር(በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)የጥርስ መቦርቦር የሚከሰተው በአፋችን ውስጥ የሚገኙ ጀርሞች (ባክቴሪያ) ጥርሳችንን የሚያበሰብሱ አሲዶችን በሚያመነጩበት ጊዜ ነው፣ ይህም በ...
26/01/2019

የጥርስ መቦርቦር
(በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

የጥርስ መቦርቦር የሚከሰተው በአፋችን ውስጥ የሚገኙ ጀርሞች (ባክቴሪያ) ጥርሳችንን የሚያበሰብሱ አሲዶችን በሚያመነጩበት ጊዜ ነው፣ ይህም በጥርሳችን ላይ የተቦረቦሩ ቀዳዳዎችን (Cavities) እንዲፈጠሩ ያደርጋል። የተቦረቦሩ ጥርሶች ህመም ከማስከተል ባለፈ ለኢንፌክሽን ያጋልጣሉ።

✔ የጥርስ መቦርቦር እንዴት ይከሰታል?

- በጥርስ ላይ ተለጥፈው የሚቀሩ ምግቦች ካልተፀዱ ይከማቹና የባክቴሪያዎች መራቢያ እና ምግብ ይሆናሉ። ባክቴሪያዎች በሚመገቡ ጊዜ ከውስጣቸው አሲድን ይረጫሉ፣ ይህም ጥርሳችን እንዲቦረቦርና እንዲበሰብስ ያደርጋል።

✔ ለጥርስ መቦርቦር የሚያጋልጡ ሁኔታዎች

- ጥርስን በሚገባና በመደበኛ ሁኔታ አለማፅዳት
- ጣፋጭነት የበዛባቸው ምግቦች ማዘውተር
- የፍሎራይድ እጥረት መኖር
- የስኳር ህመም ተጠቂ መሆን
- በህመም ወይንም በተለያዩ መድሀኒቶች ምክንያት የአፍ ድርቀት ሲኖር
- ሲጋራን ማጤስ ናቸው።

✔ የጥርስ መቦርቦር የሚያስከትላቸው ምልክቶች

- የጥርስ ህመም ስሜት
- በተጎዳው ጥርስ አካባቢ የድድ ማበጥ
- መጥፎ የሆነ የአፍ ጠረን መኖር
- በጥርስ ላይ ነጭ፣ ግራጫ፣ ቡኒ ወይንም ጥቁር ቀለማት የያዙ የተቦረቦሩ ቦታዎች መኖር ናቸው።

✔ የጥርስ መቦርቦርን እንዴት መከላከል ይቻላል?

* ጥርስዎን በቀን ውስጥ ቢያንስ ሁለት ጊዜ (ከቁርስ በኃላ እና ከመተኛትዎ በፊት) የፍሎራይድ ኬሚካል ባለው የጥርስ ሳሙና መታጠብ።

* በማንኛው ግዜ ምግብ ከተመገቡ በኃላ አፍዎን በንፁህ ውሀ በሚገባ መጉመጥመጥ

* ከእንቅልፍ በፊት ጥርስዎን ከታጠቡ በኃላ ምንም አይነት ምግብ አለመመገብ

* ጣፋጭ የበዛባቸው ምግቦችን ከምግብ ፕሮግራም ውስጥ ማስወገድ

* ልጆች ለጥርስ መቦርቦር ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ስለሆነ ሁሌም ስለ ጥርስ ፅዳት አጠባበቅ ማስተማር

* የጥርስ ሀኪምዎ ጋር በዓመት አንድ ጊዜ በመሄድ ጥርስዎን በባለሞያ ማሳጠብና ማስመርመር

ማሳስቢያ:
------------

የጥርስ ህመም ሲሰማዎ ጊዜ ሳይሰጡ ወደ ሀኪም መሄድን አይዘንጉ ምክንያቱም የህመም ስሜቱ ከጥቂት ጊዜ በኃላ በራሱ ሊጠፋ ቢችልም የጥርስ መቦርቦር ግን ያለ ህመም ሊቀጥል ይችላል። በአፋጣኝ ህክምና ካልተደረገ ጥርስዎን እስከማጣት ሊያደርስዎ ይችላል።

ለወዳጅዎ ያካፍሉ
ጤና ይስጥልኝ
Image:

Health and Medical Articles, Information covering diseases and conditions, skin infections, symptoms, causes and treatment.

Address

Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr Yemeserach Dental Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram