13/11/2025
ቫይራል ሄሞራጂክ ፌቨር (Viral Hemorrhagic Fever) ምንድነው?
በተለያዩ ቫይረሶች የሚነሱ የተለያዩ ህመሞች ሰብስብ ሆኖ ትኩሳት : መድማት እና የአካል ክፍሎች መዳከም (Organ Failure) የሚያስከትል ነው።
የቫይራል ሄሞራጂክ ፌቨር (Viral Hemorrhagic Fever) ቀድሞው የሚታዩ እና ችላ መባል የሌለባቸው ምልክቶች ምንድናቸው?
° ከፍተኛ ትኩሳት :
° በአፍ ወይም በአፍንጫ መድማት :
° የህመም ስሜት :
° ማስመለስ ወይም ማስቀመጥ።
ቫይራል ሄሞራጂክ ፌቨር (Viral Hemorrhagic Fever) መተላለፍያ መንገዶች ምንድናቸው?
° ከታመመ ሰው ወይም እንስሳ በመነካካት :
° ከታመመ ሰው ወይም እንስሳ የሰውነት ፈሳሽ በመነካካት።
ቫይራል ሄሞራጂክ ፌቨር (Viral Hemorrhagic Fever) እንዴት መከላከል ይቻላል?
° ምልክት ከታየበት ማንኛውንም ሰው ጋ ንክኪ በሚኖር ጊዜ የራስ መከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም
° ሁል ጊዜ እጅ በሳሙና መታጠብ ወይም ሳኒታይዘር መጠቀም :
° የምንመገበው ስጋ በደንብ ማብሰል
° ምልክት ያለበት ሰው ወደ አቅራብያ የጤና ተቋም መውሰድ
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በ 8335 እና 952 ነፃ የስልክ መስመር ይደውሉ።
ረዳት ሜዲካል ፕላዛ
ቦሌ : አአ