
15/07/2025
📆 ሀምሌ 8 ፣ 2017 ከሚሴ፤
ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በዛሬው እለት ቀበሌን ከአር ነጻ መሆኑን በማረጋገጥ አስመረቀ። 🟢
የደዋ ጨፋ ወረዳ በበጀት አመቱ ከገርቢ ቀበሌ በመቀጠል በዛሬው እለት የወረዳው የብልጽና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አህመድ ሃሰን እና የጤና ፅ/ቤት ሃላፊዎች ፣ ሌሎች የወረዳና የቀበሌ አመራሮች የዞንና የወረዳ ከፍተኛ ባለሙያዎች ፣ የሃገር ሽማግሌዎችና አባ ገዳዎች ፣ የሴቶች ልማት ህብረቶች ፣ ወጣቶች ፣ በተገኙበት የጭረት ወልባታ ቀበሌን ሙሉ በሙሉ ከአይነ-ምድር የፀዳ መሆኑን በማረጋገጥ ከአር ነፃ ቀበሌ በመሆን በዛሬ እለት ሀምሌ 8 ቀን 2017 ተመርቋል።