27/01/2026
የነጭ ሽንኩርት ጥቅሞች !
ነጭሽንኩርት፡-
1. በነጭ ሽንኩርት ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር በፈንገስ ምክንያት ለሚከሰቱ የቆዳ ሕመሞች
መድኃኒትነት አለው፡፡
2. በከፍተኛን ደረጃ ባክቴሪያንና ቫይረሶችን የማጥፋት ብቃት ያለው የምግብ ዓይነት ነው፡፡
3. ነጭ ሽንኩርት በውስጡ የደም መርጋትን የሚከላከል ንጥረ ነገርን ይይዛል፡፡ የደም ግፊት
መጨመርን ይከላከላል፡፡
4. ከዕድሜ መጨመር የተነሳ የሚከሰት የደም ቧንቧ ጥበትን የመከላከል ጥቅም ያለው ነጭ
ሽንኩርት ይህንን በማድረግ በደም ቧንቧ ጥበት ምክንያት የሚከሰት የልብ ሕመምን
ይከላከላል፡፡
5. በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የኮሌስትሮል መጠን በመቀነስ በደም ቧንቧ ላይ የሚገኘውን የስብ
መጠን እንዲቀንስ ያድርጋል፡፡
6. ሰውነታችን በአለርጂ እንዳይጠቃ የማድረግ አቅምም አለው፡፡ በሰውነት ላይ ለሚወጣ ሽፍታና
በአንዳንድ ነፍሳት ምክንያት የሚወጣንን ሽፍታም ይከላከላል፡፡
7. ነጭ ሽንኩርት በጉንፋን የመያዝ ሁኔታን በከፍተኛ ደረጃም ይቀንሳል፡፡ከተያዝንም በኋላ
እንዳይበረታብንና ቶሎም እንድንድን ይረዳል፡፡
8. ነጭ ሽንኩርት በሰውነታችን የሚመነጨውን የኢንሱሊን መጠን መጨመርና በደም ውስጥ
የሚገኙትን የስኳር መጠን በመቆጣጠር ለስኳር ሕመም ጠቀሜታነት ይሰጣል፡፡
9. የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት ጥርሳችንን በሚያመን ቦታ ላይ በማድረግ ባክቴሪያዎችን ማጥፋትና
ህመምን የመቀነስ ጥቀም አለው፡፡
ለዚህ የነጭ ሽንኩርት መጥፎ ጠረን መላ ሲያፈላልጉ የነበሩት የምግብ ሳይንቲስቶች ምስጋና ይግባቸውና ጥረትና ድካማቸው የሰመረላቸው ይመስላል፡፡ ለነጭ ሽንኩርት መጥፎ ጠረን አገኘን ያሉትን መፍትሔ፣ አቅርበዋል።
ሳይንቲስቶች መፍትሔ ነው ያሉት ዘዴ በዚሁ ገጽ ቀርቧልና ይሞክሩት፡፡ አሁን ወደተነሳንበት የነጭ ሽንኩርት ጥቅም ትንታኔ እንመለስ፡፡
እውነቱ ግን፣ ነጭ ሽንኩርት “የቅመሞች ንጉሥ” (King of the herbs) የሚለው ቁልምጫና ቅጽል፣ የሚገባው መሆኑ ነው፡፡ ትኩስ የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት፣ በጠረኑ ብቻ 20 ሳ.ሜ ርቀት ላይ ያለ ቫክቴሪያ ይገድላል፡፡ ይህ ቅመም፣ ለበሽታ መከላከያ አቅም ግንባታ፣ ለምግብ መፈጨት፣ ለነርቭ ሲስተም፣ ለመተንፈሻና ለቆሻሻ ማስወገጃ ሲስተም ይረዳል፡፡ እንዲሁም፣ ለልብ፣ ለሳንባ፣ ለፀጉርና ለዓይን ጤንነት በጣም ጥሩ ጥቅም ይሰጣል፡፡
ነጭ ሽንኩርት የበሽታ መከላከያ አቅምን ከፍ የሚያደርገው፣ አሊሲን (Allicin ) በተባለው ፈጣን ንጥረ ቅመሙ (ingredient) አማካይነት ነው፡፡ አንዳንድ ጥናች ደግሞ ነጭ ሽንኩርትን ከሆድ ካንሰር መቀነስ ጋር አያይዘውታል፡፡ ጉንፋን ወይም ኃይለኛው የጉንፋን ወረርሽን (ፍሉ) ሲይዝ ነጭ ሽንኩርት መብላት (መጠቀም) የበሽታውን የመቆያ ጊዜ በግማሽ ይቀንሳል፡፡ ምን ይኼ ብቻ? የነጭ ሽንኩርት ጥቅም በርካታ ስለሆነ፣ ከገበታዎ እንዳይጠፋ ካደረጉ ዘየዱ ማለት ነው፡፡ ጥሬውን ቢበላ ግን ይመረጣል፡፡