Ibsa

Ibsa �Life is a Short

20/01/2025
20/01/2025
ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፓርቲ
20/01/2025

ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፓርቲ

የአገሪቱ የውጭ ዕዳ መጠን ወደ 31 ቢሊዮን ዶላር አሻቀበ‼️የአገሪቱ የውጭ ዕዳ መጠን በሰኔ ወር 2016 ዓ.ል. ከነበረበት 28.8 ቢሊዮን ዶላር ወደ 31 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱን የገንዘ...
20/01/2025

የአገሪቱ የውጭ ዕዳ መጠን ወደ 31 ቢሊዮን ዶላር አሻቀበ‼️

የአገሪቱ የውጭ ዕዳ መጠን በሰኔ ወር 2016 ዓ.ል. ከነበረበት 28.8 ቢሊዮን ዶላር ወደ 31 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱን የገንዘብ ሚኒስቴር በቅርቡ ባወጣው የሩብ ዓመት አጠቃላይ የመንግሥት የዕዳ ሰነድ አመላክቷል።

ለዚህ እንደምክንያት የተጠቀሰዉ ገበያ መር የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተግባራዊ መደረጉና በተጠቀሱት ሦስት ወራት ውስጥ መንግሥት ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ድርጅት (IMF) እና ዓለም ባንክ በድምሩ 1.6 ቢሊዮን ዶላር ብድር የተለቀቀለት በመሆኑ ነዉ ተብሏል።

የዕዳ ሰነዱ እንደሚያሳየዉ የውጭ ምንዛሪ ለውጡ ከመደረጉ አንድ ወር በፊት ማለትም በሰኔ 2016 ዓ.ል. የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት በገንዘብ (በዶላር) ሲሰላ 207 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን በ2017 ዓ.ል. መስከረም ወር መጨረሻ ላይ ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር ወርዷል።

የአገሪቱ ጂዲፒ በዶላር ሲተመን ያሽቆለቆበት ምክንያትም ገበያ መር የውጭ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት በሐምሌ ወር 2016 ዓ.ል. ተግባራዊ በመደረጉ እንደሆነ ሰነዱ ያስረዳል።

በዚህና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች በሰኔ ወር 2016 ዓ.ል. የአገሪቱን ጂዲፒ 32.9 በመቶ ይዞ የነበረው አጠቃላይ የመንግሥት የአገር ውስጥና የውጭ ዕዳ (Public Debt) በመስከረም ወር 2017 ዓ.ል ወደ 50.3 በመቶ ማሻቀብ የሪፖርተር ዘገባ ያሳያል።

የብልፅግና ፓርቲ የአፋር ህዝብን ታሪክ በጋራ ተጠቃሚነት እንደ አዲስ የፃፈ ፓርቲ ነው፡- አቶ አወል አርባ ****************የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የብልፅግና ፓ...
27/11/2024

የብልፅግና ፓርቲ የአፋር ህዝብን ታሪክ በጋራ ተጠቃሚነት እንደ አዲስ የፃፈ ፓርቲ ነው፡- አቶ አወል አርባ
****************

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የብልፅግና ፓርቲ የአፋር ህዝብን በታሪክ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ እንደ አዲስ የፃፈ ፓርቲ መሆኑን ገለጹ።

በአፋር ክልል የብልፅግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት ምስረታ "የሀሳብ ልዕልና ለሁለተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ሀሳብ ተከብሯል።

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር አወል አርባ የብልፅግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልክት፤ዜጎችን በድሞክራሲ ስርኣት ላይ የነበራቸውን ጥያቄዎችን ፣ የጋራ ተጠቃሚነት፤የመልካም አስተዳደር ላይ ሲነሱ የነበሩ ጥያቄዎች በተግበር በመፍታት በላፉት አምስት ዓመታት የሚታዩ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል።

የብልፅግና ፓርቲ አፋር ክልል ቅርጫፍ ፅሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሃመድ ሁሴን፤ አፋር በሀገር ጉዳይ ላይ የዳር ተመልካች የነበረበት ስርዓት አልፎ አሁን ላይ በሀገራዊ ጉዳዮች የሚሳተፍበት በብልፅግና አካታችነት የተገኙ ስለ መሆናቸው አንስተዋል።

የብልፅግና ፓርቲ በጥልቅ ተሃድሶ ከለውጡ በፊት ለ27 ዓመታት የልተተገበሩ የእኩልነት እና የጋራ ተጠቃሚነት ጅምሮች በ17 ቀናት ተግባራዊ ለማድረግ አቅም ያለው ፓርቲ ስለ መሆኑ ያሳያ ነው ሲሉ አቶ መሃመድ ሁሴን ገልፀዋል።

በመርሐ-ግብሩ የክልል ፣ የዞን እና ከተለያዩ ወረዳዎች የመጡ አመራሮች ተገኝተዋል።

27/11/2024

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ibsa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Ibsa:

  • Want your practice to be the top-listed Clinic?

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram