Ethio Bette-ኢትዮ ቤት

Ethio Bette-ኢትዮ ቤት የኢትዮ ቤትን ገጽ ላይክ በማድረግ ፈጣን የጤና መረጃዎችን ያግኙ:: This page is intended to give best health tips to audience.

Happy Easter !!🐣
04/20/2025

Happy Easter !!🐣

Happy New year!!!
01/02/2025

Happy New year!!!

የደም ግፊት በሽታ መነሻ፣ ምልክትና መከላከያዎች    የደም ግፊት በሽታ የተለመደ ችግር ሲሆን የደማችን ጉልበት/ሀይል ከአርተሪ (የደም ቧንቧ) ግድግዳ ጋር ሲነፃፀር በጣም ከፍተኛ ሲሆን የሚ...
09/28/2024

የደም ግፊት በሽታ መነሻ፣ ምልክትና መከላከያዎች



የደም ግፊት በሽታ የተለመደ ችግር ሲሆን የደማችን ጉልበት/ሀይል ከአርተሪ (የደም ቧንቧ) ግድግዳ ጋር ሲነፃፀር በጣም ከፍተኛ ሲሆን የሚከሰት ህመም ነው ይህም እንደ ልብ ህመም አይነት የጤና ችግር ያስከትላል። የደም ግፊት ልባችን በምትረጨው የደም መጠን እና ደም በአርተሪዎቻችን ውስጥ ሲያልፍ የመቋቋም ኃይል ይወሰናል። ብዙ ደም ልባችን በረጨች መጠን አርተሪያችን (ደም መልስ) ይጠባል ከዚያም የደም ግፊታት መጠናችን ይጨምራል ማለት ነው። ምንም አይነት ምላክት ሳይኖረው ለአመታት የደም ግፊት መጠናችን ከፍተኛ ሊሆን ይችላል ይህም የደም ቧንቧዎቻችንን ይጐዳቸዋል።

ያልተቆጣጠርነው ከፍተኛ የደም ግፊት ለከባድ የጤና ችግር የመጋለጥ እድላችንን ይጨምራል ለዚህም የልብ ድካምና የደም መርጋት ተጠቃሾች ናቸው። የደም ግፊት ከብዙ አመታቶች በፊት የነበረ በሽታ ሲሆን በማንኛውም የእድሜ ክልል ያሉ ሰዎችን ያጠቃል። ከፍተኛ የደም ግፊት በቀላሉ የሚታወቅ በሽታ ሲሆን በሽታው እናዳለብን ካወቅን ሀኪምዎን በማማከር በቀላሉ መቆጣጠር ይቻላል።

✔ የደም ግፊት በሽታ መነሻዎች!

ሁለት አይነት የደም ግፊት በሽታዎች አሉ፦
1. የመጀመሪያ የደም ግፊት
አብዛኞቻችን አዋቂዎች የደም ግፊት መነሻ ምክንያት አይታወቅም። የዚህ አይነቱ የደም ግፊት የመጀመሪያ ደረጃ ይባላል የሚከሰተውም ቀስ በቀስ ከረጂም አመታት ቆይታ በኃላ ነው።
2. ሁለተኛ የደም ግፊት
አንዳንድ ሰዎች ከፍተኛ የደም ግፊት ከተች በተጠቀሱት ምክንያቶች ያጋጥማቸዋል። ይህ አይነቱ የደም ግፊት ሁለተኛ ደረጃ የደም ግፊት ይባላል በድንገት የሚከሰት ሲሆን ከመጀመሪያ ደረጃ የደም ግፊት ዓይነት የበለጠ ከፍተኛ የደም ግፊት በሽታ ያስከትላል።

✔የተለያዮ ሁኔታዎች እና መድሃኒቶች ለሁለተኛ ደረጃ የደም ግፊት ያጋልጡናል እነሱም፦

★ የኩላሊት ችግር
★ የአድሬናል ዕጢ እብጠት
★ የታይሮይድ ችግር
★ ጥቃቅን የደም ቧንቧዎች ችግር
★ አንዳንድ መድሃኒቶች
★ በህግ የተከለከሉ መድሃኒቶች (ኮኬይን፣ አምፊታሚን)
★ የአልኮል ሱሰኝነት
★ የእንቅልፍ ችግር

✔ የደም ግፊት ምልክቶች!

አብዛኛውን ጊዜ የደም ግፊት በሽታ ተጠቂ ሰዎች የደም ግፊት መጠናቸው በአስደንጋጭ ሁኔታ እስከሚጨምር ድረስ ምንም አይነት የበሽታው ምልክት አይታይባቸውም። ጥቂት ሰዎች በመጀመሪያ የበሽታው ደረጃ ላይ ከባድ የራስ ምታት፣ የተምታታ ንግግር እና ከወትሮው የተለየ የአፍንጫ መድማት ያጋጥማቸዋል። እነዚህ ምልክቶች የደም ግፊት መጠናቸው ለህይወታቸው አስጊ እስከሚሆን ድረስ ላይታዮ/ላይከሰቱ ይችላሉ። የደም ግፊት መጠንዎን መለካት እንደማንኛውም የህክምና ቀጠሮ ልንወስደው ይገባል።

ከ18 ዓመታችን ጀምሮ ቢያንስ በ2 ዓመት አንድ ጊዜ እንድንለካ ይመከራል። የደም ግፊትዎን ሲለኩ በሁለቱም ክንድዎ መለካት አለብዎት የደም ግፊት በሽታ ካለብዎት ወይም የልብ ችግር ካለብዎት በተደጋጋሚ መለካት ተገቢ ነው። በተወሰነ የጊዜ ልዮነት የጤና ምርመራ የማያደርጉ ከሆነ በፋርማሲና በተለያዮ ቦታዎች በሚገኙ የደም ግፊት መለኪያ መሳሪያዎች እንዲለኩ ይመከራል።

✔ የደም ግፊት መከላከያ መንገዶች!

※ ጤናማ የሰውነት ክብደት
ከመጠን ያለፈ ውፍረት ከ2-6 እጥፍ በደም ግፊት የመያዝ እድላችንን ይጨምራል።
※ በየጊዜው እንቅስቃሴ መስራት
የሰውነት እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሰዎች ከ 20―50% ከማያደርጉት ሰዎች የመያዝ ዕደላቸውን ይቀንሳል። እንቅስቃሴ ሲባል ማራቶን መሮጥ አይጠበቅብንም በየቀኑ የሚደረግ ትንሽ እንቅስቃሴ በቂ ነው።
※ የጨው አጠቃቀማችንን መቀነስ
የደም ብዛት ያለባቸው ሰዎች ጨው መጠቀማቸውን ሲያቆሙ የደም ግፊት መጠናቸው ይቀንሳል። ጨው መጠቀም ም ማቆም የደም ግፊት መጠናችን እንደይጨምር ያደርጋል።
※ አልኮል መጠጦችን አለመጠጣት/መቀነስ
ብዛት ያለው አልኮል መጠጣት የደም ግፊታችን እንዲጨምር ያደርጋል። የደም ግፊታችንን ለመቀነስ የሚወስድትን የአልኮል መጠን ገደብ ማስቀመጥ ተገቢ ነው።
※ ጭንቀትን መቀነስ
ጭንቀት የደም ግፊት መጠናችንን እንዲጨምር ያደርገዋል ከጊዜ ቆይታ በኃላ ለደም ግፊት በሽታ መነሻ አንድ ምክንያት ይሆናል።

✔ሌሎች የምግብ ይዘቶች የደም ግፊት በሽታን ለመከላከል ይረድናል ከነዚህም መካከል፦

※ ፖታሲየም
በፖታሲየም የበለፀጉ ምግቦች በደም ግፊት በሽታ ከመያዝ ይከላከላሉ። ፖታሲየም ከተለያዮ አትክልትና ፍራፍሬዎች፣ ከእንሰሳት ተዋጽኦዎች እና ከአሳ እናገኛለን።
※ ካልሲየም
አነስተኛ የካልሲየም መጠን የሚጠቀሙ የህብረተሰብ ክፍሎች በደም ግፊት የመያዝ ዕድላቸው ይጨምራል። ካልሲየም ከወተት፣ እርጐና አይብ እናገኝዋለን።
※ ማግኒዚየም
የማግኒዚየም መጠናቸው አነስተኛ የሆኑ ምግቦች መመገብ የደም ግፊት መጠናችንን ይጨምራል። የጤና ባለሙያዎች እንደሚመክሩት ተጨማሪ ማግኒዚየም የደም ግፊትን ለመከላከል/ለመቀነስ መውሰድ አይመከርም ከመደበኛ ምግባችን የምናገኝው በቂ ስለሆነ።
※ የአሳ ዘይት
ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ የምናገኝው ከአሳ ሲሆን የደም ግፊትን በመከላከል ይረዳናል።
※ ነጭ ሽንኩርት
የደም ግፊት መጠንን እና ኮሌስትሮልን በማስተካከል ከፍተኛ ሚና ይጫዎታል። የካንሰር በሽታን ይከላከላል።

መልካም ጤንነት!!

ለበለጠ የጤና መረጃ ይህን ገጽ ላይክ ያድርጉ https://www.facebook.com/EthioBette

Happy Ethiopian new year!
09/11/2024

Happy Ethiopian new year!

7የነጭ ሽንኩርት ጥቅሞች (Benefits of Garlic)@ኢትዮቤት    #ኢትዮቤት  #   1.ነጭ ሽንኩርት ጤናን ለመጠበቅ! አሊሰን የተባለ ለጤና ጠቃሚ የሆነ ንጥረ ነገር ይዟል፤ ጥንታዊ ...
02/13/2024

7የነጭ ሽንኩርት ጥቅሞች
(Benefits of Garlic)

@ኢትዮቤት #ኢትዮቤት #

1.ነጭ ሽንኩርት ጤናን ለመጠበቅ!
አሊሰን የተባለ ለጤና ጠቃሚ የሆነ ንጥረ ነገር ይዟል፤ ጥንታዊ ግሪካዊያን፣ ግብፃውያን ፣ባቢሎናዊያን ነጭ ሽንኩርትን በጥሬው በመመገብ ጤናቸውን ይጠብቁ ነበር።

2.ነጭ ሽንኩርት አንደ አልሚ ምግብ!
ነጭ ሽንኩርት ከፍተኛ የሆነ አልሚ ምግብ ቢሆንም ትንሽ መጠን የሆነ ካሎሪ (calories) ይዟል፤ 28 ግራም ነጭ ሽንኩርት፦ 23% ማግኒዝየም፣ ቫይታሚን ሲ 15%፣ ሌሊዬም 6%፣ ፋይበር 1 ግራም በውስጡ ይዟል።

3.ነጭ ሽንኩርት በሽታን በመከላከል!
ጥናቶች አንደሚያመለክቱት በቀን 2.56 ግራም መመገብ የጉንፋን በሽታ በሰውነታችን ላይ የሚቆይበትን ቀናት በመቀነስ እና በጉንፋን የመያዝ እድላችን ይቀንስልናል።

4.ነጭ ሽንኩርት የደም ግፊትን ለመከላከል!
የልብ ችግር፣ እራስን መሳት፣ የደም ግፊት እነዚህ በአለማችን ላይ በገዳይነታቸው የሚታወቁ በሽታዎች ናቸው። ነጭ ሽንኩርት አዘውትረው የተመገቡ ሰዎች ከለሌቹ በተሻለ ሁኔታ የደም ግፊት በሽታ መከላከል ችለዋል።

5.ነጭ ሽንኩርት በደማችን ውስጥ ያለውን ቅባት ለመቀነስ!
በሰውነታቸው ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የኮሌስትሮል (cholestrol) መጠን ያለባቸው ሰዎች ነጭ ሽንኩርት በመመገብ ከ10–15% መቀነስ ይችላሉ።

6.ነጭ ሽንኩርት እንደ ፀረ–ኦክሲዳንት!
ከዚህም በተጨማሪም የመርሳት በሽታ (Alzheimer) እንዲሁም እራስን የመሳት በሽታ (Dementia) የመከላከል አቅም አለው። የደማችንን ቅባት (Cholesterol) እና የደም ግፊታች ከመከላከል በተጨማሪ የአንቲ ኦክሲዳንት ባህሪ ስላለው እንደ የመርሳት ችግር እንዲሁም እራሳችንን እንዳንስት ይከላከልናል።

7.ነጭ ሽንኩርት ለረጂም እድሜ!
መቸም እድሜያችንን ለመጨመር በሰው እንደማይቻለን ሁላችንንም እናውቃለን ነገር ግን ለሞት ሊዳርጉን የሚችሉ በሽታዎች፦ እንደ ደም ግፊት፣ የልብ በሽታ፣ ተላላፊ ለሆኑ በሽታዎች በመከላከል ጤናችን ተጠብቆ እረጂም ዕድሜ እንድኖር ይረዳናል።

መልካም ጤንነት!!

ለበለጠ የጤና መረጃ ይህን ገጽ ላይክ ያድርጉ www.Facebook.com/EthioBette

የተልባ ፍሬ በምን መልኩ ለጤና ይጠቅማል?     #የተልባፍሬተልባ በእኛ ማህበረሰብ ውስጥ ለብዙ ጤና ነክ ችግሮች ፍቱን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ዛሬ ከእኛ ጋር በሳይንስ የተረጋገጡ የተልባ ጥቅ...
02/08/2024

የተልባ ፍሬ በምን መልኩ ለጤና ይጠቅማል?
#የተልባፍሬ

ተልባ በእኛ ማህበረሰብ ውስጥ ለብዙ ጤና ነክ ችግሮች ፍቱን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ዛሬ ከእኛ ጋር በሳይንስ የተረጋገጡ የተልባ ጥቅሞችን እናያለን፡፡ ከታች የምንዘረዝራቸው ጥቂቶቹን ነው፡፡

የተልባ ፍሬ

ለብዙ ዘመናት የተልባ ፍሬ ጤናን በመጠበቅ ላይ ሲያግዘን ኖሯል፡፡ እንደውም በአንዳንድ ሀገራት “ እጅግ አስፈላጊ “ በመባል ይታወቃል፡፡ በአሁኑም ጊዜ ስለ ተልባ ብዙ ጥናቶችና ምርምሮች እየተደረጉ ስለሆነ ተመራጭነቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ ጨምሯል፡፡

በሳይንስ የተረጋገጡ 10 የተልባ ፍሬ የጤና ጥቅሞች፤

1. የተልባ ፍሬ መጠቃሚ የምግብ ይዘቶች የተሞላ ነው፡፡

ከጥንታዊ ስልጣኔ ጀምሮ የተልባ ፍሬ ጠቃሚ ከሚባሉት ውስጥ ይመደባል፡፡ ቡናማ እና ወርቅማ አይነቶች አሉ፤ ሁለቱም ተመሳሳይ ጠቀሜታ አላቸው፡፡

አንድ የሻይ ማንኪያ የተልባ ፍሬ በውስጡ ተመጣጣኝ የሆነ የካሎሪ፣ ፕሮቲን፣ ካርቦሐይድሬት፣ ፊይበር፣ ቅባት፣ ኦሜጋ 3፣ ቪታሚን ቢ 1፣ ቢ 6፣ ፎሌት፣ ካልሺየም፣ አይረንእና ማንግኒዢየም ይዘት አለው፡፡

ለጤና የሚጠቅመው በተለይ በኦሜጋ 3 እና ፋይበር ይዘቱ ነው፡፡

2. የተልባ ፍሬ በኦሜጋ 3 የበለፀገ ነው፡፡

በተለይ የስጋ እና የወተት ተዋዕፆ ለማይወስዱ ሰዎች የተልባ ፍሬ ሁነኛ የኦሜጋ 3 ምንጭ ነው፡፡ መሰል የምግብ ይዘት ያላቸው የልብን ጤንነት ለመጠበቅ እና ጭንቅላት ውስጥ ደም እንዳይፈስ እንደሚረዱ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

3. የተልባ ፍሬ ካንሰርን ሊከላከል የሚችል ውህድ አለው፡፡

እነዚህ ውህዶች የአንታይኦክሲዳንት እና ኤስትሮጅን ባህሪ ስላላቸው በካንሰር (እንደ የጡት ካንሰር እና የፕሮስቴት ካንሰር) የመያዝ እድልን በመቀነስ ጤንነትን ይጠብቃሉ፡፡

4. የተልባ ፍሬ ከፍተኛ የፋይበር መጠን ይይዛል፡፡

ተልባን የእለት ተእለት ምግቦት ውስጥ ማስገባት የምግብ መፈጨትን ከማሳለጡ በላይ የምግብ መፈጨት ላይ የሚሳተፉ አትን ጤንት ያሻሽላል፡፡

5. የተልባ ፍሬ የደም ውስጥ ኮሌስትሮል መጠን ይቀንሳል፡፡

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ በቀን 3 የሻይ ማንጂያ ተልባ ለወራት መመገብ የመጥፎ ኮሌስትሮል መጠንን እጅጉን በመቀነስ ጥሩ የሚባለውን ኮሌስትሮል ይጨምራል፤ ይህም እድሜአቸው ከ45 በላይ የሆኑ ሴቶች ላይ ጎልቶ ታይቷል፡፡ ይህም የሚሆነው በተልባ ውስጥ ያለው ፋይበር ከሃሞት ጨው ጋር በሚጣበቅበት ጊዜ ከሰውነት ስለሚወገድ ነው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ የልብን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል፡፡

6. የተልባ ፍሬ የደም ግፊትን ሊያስተካክል ይችላል፡፡

ተልባ የደምግፊትን እንደሚቀንስ ብዙ ጥናቶች አሳይተዋል፡፡ በቀን 3 የሻይ ማንኪያ ተልባ መመገብ ለዚህ ይረዳል፡፡ ተያይዞም የሌሎች ተጓዳኝ በሽታዎች ተጋላጭነትን ይቀንሳል፡፡

7. ከፍተኛ የፕሮቲን መጠን ይይዛል፡፡

ተልባ በጣም ጥሩ የሚባል የፕሮቲን ምንጭ ነው፡፡ በዚህም ምክንት የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም በመጨመር፣ ኮሌስትሮልን በመቀነ፣ ካንሰርን በመከላከል እና በፀረ-ፈንገስ ባህሪው ወደር አይገኝለትም፡፡ የስጋ ተዋፅዖ ለማይወስዱ ሰዎች ተመራጭ ነው፡፡

8. የተልባ ፍሬ የደም ውስጥ ስኳር መጠንን ለማስተካከል ይረዳል፡፡

በአለምአቀፍ ደረጃ የስኳር በሽታ ዋነኛ የጤና ችግር እየሆነ መጥቷል፡፡ የስኳር በሽተኞች መደበኛ አመጋገባቸው ላይ ከ1-2 የሻይ ማንኪያ ተልባ ቢያንስ ለአንድ ወር ቢጨምሩ በአስገራሚ ሁኔታ የስኳር መጠናቸው ይቀንሳል፡፡ ይህም የሆነው የተልባ ፍሬ በውስጡ ባለው የማይሟሟ የፋይበር መጠን ምክንያት ነው፡፡

9. የተልባ ፍሬ የሰውነትን ክብደት ለመቀነስ ሊረዳ ይችላል፡፡

በተለይ በየሰዓቱ ምግብ መብላት ለለመዱ ሰዎች ተልባን (ከ1-2 የሻይ ማንኪያ) በመጠጦ ላይ በየቀኑ መጨመር የረሐብ ስሜትን ያርቃል፡፡ ምክንያቱም በተላባ ውስ ያለው የሚሟሟ የፋይበር አይነት በጨጓራ የምግብ መፈጨትን ሲያዘገይ፤ የረሐብን ስሜት እና የምግብ ፍላጎትን ይቀንሳል፡፡

10. የተልባ ፍሬን የተለያዩ የምግቦች አይነቶች ውስጥ ሊጨመር ይችላል፡፡

የተልባ ፍሮ ከብዙ የምግብ አይነቶች ጋር ይሄዳል፡፡ ይህም በየቀኑ እንዲወሰድ ያስችለዋል፡፡

ለምሳሌ፤

- የመጠጥ ውሃ ውስጥ መጨመር

- ሰላጣ ሲሰራ የተልባ ዘይት መጠቀም

- ለቁርስ የሚመገቡት አጃ ወይም ገብስ ላይ የተፈጨ ተልባ መጨመር

- የሚወዱት የእርጎ አይነት ውሰስጥ መጠቀም

- የሚጋግሩት ኩኪስ፣ ኬክ እና ዳቦ ላይ መጨመር

- ከሙዝ ወይም የሚወዱት ፍራፍሬ ጋር አብሮ ፈጭቶ መጠጣት

- ከስጋ ጋር አብሮ መቀቀል ወይም መጥበስ

ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!

መልካም ጤንነት!!!
ለበለጠ የጤና መረጃዎች ይህን የፌስቡክ ፔጅ ላይክ ያድርጉት!
WWW.Facebook.com/Ethiobette

መልካም የገና በአል🎄🎉🎈
01/06/2024

መልካም የገና በአል🎄🎉🎈

👁️ የአይን ማቃጠል፤ ከማቃጠልስ ጀርባ ያለው ምስጢር ምንድን ነው 🔥 #የአይንማቃጠል       #ኢትዮቤትበዓይንዎ ውስጥ ያለው የማቃጠል ስሜት ህይወትዎ ትንሽ አስደሳች እንዳይሆን እያደረግዎት...
11/13/2023

👁️ የአይን ማቃጠል፤ ከማቃጠልስ ጀርባ ያለው ምስጢር ምንድን ነው 🔥
#የአይንማቃጠል
#ኢትዮቤት

በዓይንዎ ውስጥ ያለው የማቃጠል ስሜት ህይወትዎ ትንሽ አስደሳች እንዳይሆን እያደረግዎት ይሆን? መንስኤው ምን ሊሆን እንደሚችል እና እንዴት እፎይታ ማግኘት እንደሚችሉ እንመልከት! 🕵️‍♂️

🔥 የአይን ማቃጠል ምንድን ነው? 🔥

የአይን ማቃጠል ልክ እንደ ቃሉ ነው - በአንዱ ወይም በሁለቱም ዓይኖች ውስጥ የማቃጠል ወይም የመንደድ ስሜት ሲሆን፤ የዕለት ተዕለት ኑሮዎን እና እንቅስቃሴዎችዎን ሊያስተጓጉሉ ይችላሉ። ይህም በጣም ቀላል የሆኑትን ስራዎች እንኳን ለማከናወን ፈታኝ ያደርገዋል።

🤔 መንስኤዎች 🤔

በርከት ያሉ ምክንያቶች ወይም መንስኤዎች የአይን ማቃጠልን ሊያመጡ ይችላሉ። ለምሳሌ:-

🔹አለርጂ፡- እንደ የአበባ ዱቄት ወይም የቤት እንስሳ ፀጉር ያሉ አለርጂዎች የአይን ማቃጠል ሊያስከትሉ ይችላሉ።

🔹የአይን መድረቅ፡- በቂ ያልሆነ እንባ ማምረት ወይም ፈጣን ትነት ዓይኖችዎን እንዲደርቁ እና እንዲያበሳጩ ሊያደርግ ይችላል።

🔹የሚያቃጥሉ ነገሮች፡- እንደ የጽዳት መጠበቂያዎች ማጽጃ፣ ሽቶ ወይም ክሎሪን ያሉ በየዕለቱ የምንጠቀምባቸው ምርቶች ውስጥ ያሉ ኬሚካሎች አነሳሽ ወይም ቀስቃሽ ሊሆኑ ይችላሉ።

🔹ዝቅተኛ የእርጥበት መጠን፡- ደረቅ የቤት ውስጥ አየር በተለይም በሞቃት ቦታዎች ከአይንዎ እርጥበትን ሊወስድ ይችላል።

🔹ኢንፍላሜሽን፡- እንደ ብለፈራይተስ ወይም ኦኩላር ሮዜሺያ (blepharitis or ocular rosacea) ያሉ ሁኔታዎች የአይን ማቃጠል ሊያስከትሉ ይችላሉ።

🔹ለአልትራቫዮሌት ጨረር መጋለጥ፡- ለፀሀይ ብርሀን ወይም አርቲፊሻል ዩቪ ጨረሮች ከመጠን በላይ መጋለጥ ፎቶኬራቲትስ ወይም ሰንበርንድ አይስ ሊያስከትሉ ይችላሉ።

🔹ኢንፌክሽኖች፡- የአይን መቅላት (ፒንክ መሆን) (conjunctivitis) ወይም አይንን የሚያጠቁ ሽንግልስ በተጨማሪ መንስኤ ሊሆን ይችላል።

🔹ተጓዳኝ የጤና ችግሮች፡- እንደ ሲዎግረን ሲንድረም ወይም ተርጂየም (Sjögren's Syndrome or Pterygium) ያሉ ሁኔታዎች ለዓይን ማቃጠል አስተዋፅዖ ያደርጋሉ።

👩‍⚕️ እፎይታ ማግኘት 👩‍⚕️

ሕክምናው እንደ መንስኤው ይወሰናል። የጤና ባለሙያዎችን ማማከር የመጀመሪያው እርምጃ ነው።
የጤና ባለሙያዎች የሚከተሉትን ሊመክርዎት ይችላሉ፡-

🔸አንቲ-ሂስታሚን (Antihistamine):- መንስኤው ወይም ቀስቃሽ ነገሮቹ አለርጂዎች ከሆኑ።

🔸ቤቢ ሻምፑ (Baby Shampoo)፡- ለ ብለፈራይተስ (Blepharitis) የዐይን ሽፋኖቻችሁን በውሃ እና በቤቢ ሻምፑ በቀስታ ማጽዳት።

🔸የአይን ጠብታዎች:- ለድርቀት የማለስለሻ ጠብታዎች ወይም ሰው ሰራሽ እንባ መጠቀም።
🔸ዓይንን መታጠብ፡- የሚያቃጥሉ ወይም ኢሪታንት ነገሮችን ለማስወገድ።

🔸ሙቅ ወይም ቀዝቃዛ ኮምፕረስ:- የተለያዩ ሁኔታዎች የሚያመጡትን የአይን ምቾት ማጣትን ያስወግዳል።

🚫 መከላከል ቁልፍ ነው 🚫

ሁልጊዜ ከመንስኤዎቹ መራቅ ባይቻልም፤ የሚከተሉትን ማድረግ ይቻላል:-

▪️ለአለርጂዎች መጋለጥን ይቀንሱ።
▪️አይኖችዎን ከማሸት ይቆጠቡ።
▪️ከሽቶ-ነጻ ምርቶችን ይምረጡ።
▪️የእጅ ንጽህናዎን ይጠብቁ።
▪️አይኖችዎን ከፀሀይ እና ብናኝ ቆሻሻዎች ይጠብቁ።
▪️እንደ የዓይን ጠብታዎች ወይም ፎጣዎች ያሉ የግል ዕቃዎችን በጭራሽ ለሌሎች አያጋሩ።

👁️ እርዳታ የሚያስፈልግዎት መቼ ነው 👁️

የዓይን ሕመምን ችላ አትበሉ! ማቃጠሉ ከቀጠለ ወይም እንደ ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የእይታ ለውጦች ወይም ሽፍታ ካሉና ሌሎች ምልክቶችን ካስተዋሉ የጤና ባለሙያዎችን ያማክሩ።

አይኖችዎ TLC ይገባቸዋል። እፎይታ ለማግኘት እርዳታ ከመጠየቅና ያለውን ማንኛውም ሁኔታን ከመናገር ወደኋላ አይበሉ! 🌟 #ኢትዮቤት

መልካም ጤንነት!!

ለበለጠ የጤና መረጃ እና ምክር ይህንን ገጽ ይወዳጁ::
www.Facebook.com/EthioBette

የጠቆረ ከንፈር ለማቅላት የሚረዱ ዘዴዎች✔ ከንፈር እንዲጠቁር የሚያደርጉ ምክንያቶች፦★ ከፍተኛ ለሆነ የፀሃይ ጨረር መጋለጥ★ በአለርጂ ተጠቂ ከሆኑ★ ጥራታቸውን ያልጠበቁ የከንፈር ቅባቶችን መ...
11/04/2023

የጠቆረ ከንፈር ለማቅላት የሚረዱ ዘዴዎች

✔ ከንፈር እንዲጠቁር የሚያደርጉ ምክንያቶች፦

★ ከፍተኛ ለሆነ የፀሃይ ጨረር መጋለጥ
★ በአለርጂ ተጠቂ ከሆኑ
★ ጥራታቸውን ያልጠበቁ የከንፈር ቅባቶችን መጠቀም
★ ሲጋራ ማጨስ
★ አልኮል ከመጠን በላይ መጠጣት እና ጫት መቃም
★ የሰውነታችን ሆርሞኖች አለመጣጣም ናቸው።

✔ የጠቆረ ከንፈር ለማቅላት የሚረዱ ዘዴዎች፦

※ ሎሚ፦ ሎሚ የሞቱ ሴሎችን ለማንሳት እና የጠቆረ ቆዳን ለማከም ይረዳናል

አዘገጃጀት፦ ሎሚውን በመጭመቅ ማታማታ ከአንድ እስከ ሁለት (1-2) ወር ከንፈር መቀባት።

※ ፅጌሬዳ አበባ፦ ፅጌሬዳ አበባ የጠቆረ ቆዳን ለማከም ይረዳናል

አዘገጃጀት፦ ፅጌሬዳ አበባ በማዘጋጀት በአነስተኛ ውሃ ላይ መዘፍዘፍ እና ማቆየት ከዛም ውሃው ውስጥ ማር ወይም ወተት በመደባለቅ መቀባት ይህን በቀን ውስጥ ከ3-4 ጊዜ እየደጋገሙ ይቀቡ።

※ የወይራ ዘይት፦ የወይራ ዘይት ከንፈር በቂ የሆነ እርጥበት እንዲኖረው በማድረግ እንዲለሰልስ ያደርገዋል

አዘገጃጀት፦ ማታ ላይ ሁልጊዜ የወይራ ዘይቱን ከንፈራችንን መቀባት።

※ ስኳር፦ ስኳር የሞቱ የቆዳ ሴሎችን ቀርፎ በማንሳት አዲስ ከንፈር እንዲኖሮት ያደርጋል

አዘገጃጀት፦ ሶስት (3) የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ስኳር በማዘጋጀት በላዩ ላይ ሁለት (2) የሻይ ማንኪያ ቅቤ በመጨመር ማዋሃድ ከዛም ከንፈሮን ማሳጅ እያደረጉ ይቀቡ ይህንንም በሳምንት በተደጋጋሚ ያድርጉ።

※ ኩከምበር፦ ኩከምበር የጠቆረ ቆዳን ለማከም ይረዳናል

አዘገጃጀት - ኩከምበር ቆርጦ በማዘጋጀት በቁራጩ ከንፈርን ማሸት ይህንንም በቀን 1 ጊዜ ያድርጉ

※ ማር፦ ማር ማታ ላይ በስሱ በመቀባት ማሳጅ ማድረግ ከዛም ጠዋት ላይ ለብ ባለ ውሃ መታጠብ

※ እንጆሬ፦ እንጆሬውን በመቁረጥ ማታ መቀባት ከዛ ከ1 ሰአት በኋላ ወይም አሳድሮ መቀባት

★ ማሳሰቢያ

ምንጊዜም ማታማታ ከንፈር ላይ የተቀቡትን ሊፒስቲክ ወይም ቻፒስቲክ ሙሉ ለሙሉ ማጥፋት ይልመዱ፣ ከለር ያላቸውን ሊፒስቲኮች አያዘውትሩ በተጨማሪም በቀን ውስጥ በቂ ውሃ ይጠጡ።

መልካም ጤንነት!!

ለበለጠ የጤና መረጃ ይህን ገጽ ይወዳጁ
www.facebook.com/EthioBette

Happy Ethiopian New year!!!
09/11/2023

Happy Ethiopian New year!!!

ስለ ነጭ የደም ሴል ቁጥር መጨመር ማወቅ ያሉብን ነገሮች    ነጭ የደም ሴሎች የደም ወሳኝ ክፍሎች ናቸው።  የነጭ ደም ሴሎች ሚና ኢንፌክሽንን ወይም በሽታን ለመዋጋት ሲሆን ለአጠቃላይ ደህን...
05/18/2023

ስለ ነጭ የደም ሴል ቁጥር መጨመር ማወቅ ያሉብን ነገሮች



ነጭ የደም ሴሎች የደም ወሳኝ ክፍሎች ናቸው። የነጭ ደም ሴሎች ሚና ኢንፌክሽንን ወይም በሽታን ለመዋጋት ሲሆን ለአጠቃላይ ደህንነት እና ጤንነት በጣም አስፈላጊ ናቸው።

ከፍ ያለ ነጭ የደም ሴል ቁጥር የበሽታ መከላከል ስርዓታችን ኢንፌክሽኑን (በሽታን) ለማጥፋት እየሰራ መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡

በተጨማሪም የአካል ወይም የስሜት ጭንቀት ምልክት ሊሆን ይችላል። በተለይ የደም ካንሰር ያለባቸው ሰዎችም ከፍተኛ የነጭ የደም ሴሎች ቁጥር ሊኖራቸው ይችላል።

ዝቅተኛ ነጭ የደም ሴል ቁጥር የአካል ጉዳት ወይም ሁኔታ በሚኖርበት ወቅት ነጭ የደም ሴሎች ከሚመረቱበት ፍጥነት በበለጠ ሴሎቹ እየሞቱ መሆኑን ወይም ሰውነት በጣም ጥቂት ነጭ የደም ሴሎች እያመረተ መሆኑን ሊያመለክት ይችላል።

ነጭ የደም ሴሎች ከሁሉም የደም ሴሎች ውስጥ 1 ከመቶ (1%) የሚሆኑት ሲሆኑ በሽታ የመከላከል ስርዓት ውስጥ ለመደበኛ ተግባር እጅግ በጣም አስፈላጊ ናቸው። ነጭ የደም ሴሎችም ሉኪዮሳይት (Leukocyte) በመባል ይታወቃሉ።

የአጥንት መቅኒ (Bone Marrow) ያለማቋረጥ ነጭ የደም ሴሎችን ያመርታል። በሰውነት ውስጥ ኢንፌክሽን ወይም በሽታን ለመዋጋት አስፈላጊ እስከሚሆኑ ድረስ በደም እና በሊንፋቲክ ስርዓቶች ውስጥ ይቀመጣሉ።

ከፍተኛ ነጭ የደም ሴል ቁጥር ትክክለኛ መጠን ከአንድ ላቦራቶሪ ወደ ሌላው ሊለያይ ይችላል። ነገር ግነወ በአጠቃላይ ለአዋቂዎች በማይክሮ ሊትር ደም ውስጥ ከ 11,000 በላይ ነጭ የደም ሴሎች (ሉኪዮሳይቶች) ሲሆን የነጭ የደም ሴሎች ቁጥር ጨመረ ይባላል።

☑️ ከፍ ያለ የነጭ የደም ሴል ቁጥር ምክንያቶች ምንድናቸው?

የነጭ የደም ሴሎች መጨመር ሉኪዮሳይቶሲስ (Leukocytosis) በመባል ይታወቃል። ለሚከተሉት ሁኔታዎች ምላሽ ለመስጠት የነጭ ደም ሴል ቁጥር ይጨምራል-

🔺 ኢንፌክሽን
🔺 የበሽታ መከላከል አቅም መቀነስ
🔺 መድሃኒቶች (ኮርቲሲቶይደሮችን ጨምሮ)
🔺 የአጥንት መቅኒ በሽታቨወይም የበሽታ መከላከል መታወክ
🔺 ድንገተኛ ወይም ሥር የሰደደ የሊምፎሳይቲክ ሉኪሚያ (Lymphocytic Leukoma) ያሉ የካንሰር በሽታዎች
🔺 የሰውነት መቆጣት (Inflammation)
🔺 የሰውነት ጉዳት ወይም ቁስለት
🔺 ስሜታዊ ወይም አካላዊ ጭንቀት
🔺 የጉልበት ሥራ
🔺 እርግዝና
🔺 ሲጋራ ማጨስ
🔺 የአለርጂ ምላሾች
🔺 ከመጠን በላይ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ

እንደ ደረቅ ሳል ወይም ቲቢ ያሉ የተወሰኑ የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች የነጭ የደም ሴሎችን መጠን እንዲጨምሩ ሊያደርግ ይችላል።

☑️ ከፍ ያለ የነጭ የደም ሴል ብዛትዎን ለመቀነስ ምን ዓይነት ምግቦች መመገብ አለብዎት?

የሚመገቡት ምግብ በነጭ የደም ሕዋስ ብዛትዎ ላይ ተጽዕኖ አለው። የነጭ ደም ሴል ቁጥር እንዲቀንስ ለማድረግ ከፍተኛ ስብ፣ ካሎሪ የበዛባቸው፣ ስኳር እና ጨው ያሉ ምግቦችን (እንደ ፈጣን ምግቦች ያሉ) ከመብላት ይቆጠቡ።

እንደ ቫይታሚኖች ሲ እና ኢ ፣ ፋይበር ፣ ካልሲየም ፣ የዓሳ ዘይቶች ፣ ሞኖ-ያልተሟሉ ቅባቶችን እና ዝቅተኛ የግሊኬሚክ መረጃ ጠቋሚ ያሉ ከፍተኛ የፀረ-ሙቀት አማቂዎች የሆኑ ምግቦችን ዓላማ አድርገው ይመገቡ።

እብጠትን በመቀነስ ላይ ተፅእኖ እንዳላቸው የተረጋገጡ አንዳንድ ምግቦች መካከል፤ ነጭ ሽንኩርት፣ ወይን፣ ቅጠላቅጠሎች እና ቅመሞች፣ አኩሪ አተር፣ ፕሮቲን፣ ለውዝ፣ የወይራ ዘይት፣ ጥቁር እና አረንጓዴ ሻይ እና ሆምጣጤ ይገኙበታል። በየቀኑ ቢያንስ ስድስት ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን ለመመገብ ያቅዱ፣ ይህም የነጭ የደም ሴል መጠንዎ ለማስተካከል ጠቃሚ ናቸው።

☑️ ወደ ዶክተር መቼ መሄድ አለብን

ከፍ ያለ ነጭ የደም ሴል ቆጠራ ብዙውን ጊዜ ዶክተርዎ ቀድሞውኑ ያጋጠመዎትን ሁኔታ ለመመርመር የሚያግዙ ምርመራዎችን ሲያዝዝ የቁጥሩ መጨመር በቀላሉ ይታወቃል። የምርመራው ውጤት ብዙም ያልተጠበቀ ግኝት ወይም በአጋጣሚ የተገኘ ይሆናል።

እነዚህ ውጤቶች ምን ማለት እንደሆኑ ከሐኪምዎ ጋር ይነጋገሩ። ከፍ ያለ ነጭ የደም ሴል ቁጥር፣ ከሌሎች ምርመራዎች ውጤት ጋር ተያይዞ የበሽታዎን መንስኤ አስቀድሞ ሊያመለክት ይችላል። ወይም ሐኪምዎ ሁኔታዎን የበለጠ ለመገምገም ሌሎች ምርመራዎችን ሊጠቁም ይችላል።

መልካም ጤንነት!!

ለበለጠ የጤና መረጃ ገጻችንን ይወዳጁ
EthioBette

Happy new year
12/31/2022

Happy new year

Address

Addis Ababa
West Vancouver, BC
V3R5X8

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Bette-ኢትዮ ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Ethio Bette-ኢትዮ ቤት:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram