14/08/2025
ብጉር
ምንነት: በብዙ ምክንያት የቆዳ ቀዳዳወች ሲደፈኑ በሚመጣ የቆዳ መቆጣት የሚመጣ ችግር ነው::
ምክንያቶች:
- የፊት ቆዳ ቅባት መብዛት እና የቆዳ ቀዳዳዎችን መድፈን
- ለአቅመ አዳም ወይም ሄዋን ሲደረስ የሚመነጭ አንድሮጅን ሆርሞን መብዛት
- ፒ. አክኔ የሚባል ባክቴሪያ
- ቤተሰብ ተመሳሳይ ችግር መኖር
- ጣፋጭ እና ወተት ያላቸው ምግቦች ያስብሳሉ
- የተለያዩ የፊት ቅባቶች እና ኮስሞቲክሶች ያስብሳሉ
ከጠቅላላው ህዝብ 85% የሚሆነው በዕድሜው በሆነ ጊዜ በብጉር ይያዛል::
ምልክቶች
ማሳከክ የሌለው ሽፍታ: መግል የሚይዙ ሽፍታወች ወይም ዕባጮች
በብዛት ብጉር ፊት ላይ: ደረት ወይም ጀርባ ላይ ይወጣል
ሴቶች ላይ ሆርሞናል ብጉር ከሆነ የወር አበባ መዛባት: ፊት ላይ ፀጉር መብዛት: የድምፅ መወፈር
ህክምና
- የተለያዩ የሚቀቡ እና የሚዋጡ መድሀኒቶች አሉ
- የሚወጡትን ሽፍታወች በዕጅ አለመነካካት
- ፊትን የሚሸፍኑ ቅባቶች: ኮስሞቲክሶች: እና የፊት ማስክ አለመጠቀም
- የፊትን ቅባት በተለያዩ የብጉር ሳሙናወች እና መታጠቢያወች መቀነስ
- በገላ እና በተለይ በልብስ ሳሙና ፊትን አለመታጠብ
- ፀሀይ መከላከል
- የመጨረሻ ደረጃ ላይ ከደረሰ አይሶትሪትኖይን የሚባል የሚዋጥ መድሀኒት ያስፈልገዋል:: አይሶትሬቲኖይን ፍቱን የሆነ የብጉር መድሀኒት ሲሆን በክሊኒካችን ማግኘት ይችላሉ።
- ብጉር ሲድን የሚተወው ጠባሳ ክሊኒካችን ቢመጡ በማይክሮ ኒድሊንግ እንዲሁም በደርማአብሬዥን መታከም ይችላል::
ዶ/ር ዳዊት ዮሐንስ
የቆዳና የአባላዘር ቺፍ ስፔሻሊስት
አድራሻ ቦሌ ቡልቡላ ማርያም ማዞሪያ ፀሀይ ህንፃ
ስልክ 0912050354