19/07/2025
💀ድምጽ አልባው ገዳይ :ካርቦን ሞኖክሳይድ :የከሰል ጪስ💀
🚨 **ንቁ ሁኑ!** ካርቦን ሞኖክሳይድን (CO) ማየት፣ ማሽተት ወይም መቅመስ የማይቻል አደገኛ መርዝ ነው! 😷
❓የከሰል ጪስ ወይም ካርቦን ሞኖክሳይድ ለምን ገዳይ ሆነ?
👉 ካርቦን ሞኖክሳይድን ወደ ውስጥ ስትተነፍሱ ወደ ደም ውስጥ ይገባና በቀይ የደም ሴሎች ውስጥ ከሚገኘው ሄሞግሎቢን ጋር ፍጥነት ይጣበቃል። ማለትም ከኦክስጂን ይልቅ ቀድሞ ቦታ ይይዛል
👉ሄሞግሎቢን ኦክስጅንን በመላ ሰውነት ተሸክሞ የሚያጓጉዝ እጅግ ጠቃሚ መርከብ ነው ብላችሁ ማሰብ ትችላላችሁ
👉ይሄን መርዘኛ ጪስ እጅግ አደገኛ የሚያደርገው ከኦክስጅን ይልቅ ከሄሞግሎቢን ጋር ከ200-250 እጥፍ የመጣበቅ አቅም ያለው መሆኑ ነው ! ይህ ማለት:
✅ወሳኝ የአካል ክፍሎች(በተለይ አንጎል እና ልብ) ለመስራት የሚያስፈልጋቸውን ኦክስጅን እንዳያገኙ ያደርጋል።
✅ኦክስጅን ከሌለ የወሳኝ አካል ክፍሎች ህዋሳት በፍጥነት መሞት ይጀምራሉ፣ ይህም ከባድ የአካል ጉዳት፣ ራስን መሳት እና በመጨረሻም ለሞት ይዳርጋል
🚨🚨በከሰል ጭስ የመመረዝ ምልክቶች ምንድናቸው 🚨
😵 የመጀመሪያ አከባቢ ግልጽ ምልክቶች የሉትም:-
💥ራስ ምታት፣ ማዞር፣ ማቅለሽለሽ፣ ድካም ግራ መጋባት ሊከሰት የሚችል ሲሆን ተጠቂው በፍጥነት ስለማያስተውለው አደጋው የከፋ ሊሆን ይችላል።
---
🛠️ እራስዎን/ዎን ከCO መመረዝ እንዴት መጠበቅ ይችላሉ?
✅ ቢቻል ከሰልን በቤት ውስጥ በጭራሽ አይጠቀሙ!
✅ ሙሉ በሙሉ ሳይቀጣጠል ወይም በቂ አየር ዝውውር በሌላቸው ቦታዎች ፈጽሞ መጠቀም አይገባም
✅ ለተከፈቱ መስኮቶች/በሮች በጣም ቅርብ አድርጎ ማስቀመጥ አስፈላጊ ነው
✅ ቢቻል የከሰል ጭስ ቤት ውስጥ እየተጠራቀመ መሆኑን ማስጠንቀቂያ ምልክት የሚሰጡ መሳሪያዎችን (አላርም) በተለይ በመኝታ ክፍሎች አቅራቢያ በመግጠም ይጠቀሙ 🔊
✅ የጋዝ ምድጃ ወይም የጋዝ ማብሰያ ለማሞቂያ በጭራሽ አይጠቀሙ
✅ምልክቶቹን ይወቁ
✅ይሄ ችግር በሚያጋጥም ጊዜ በፍጥነት በር እና መስኮት መከፋፈት ወይም ወደ ውጪ መውጣት ያስፈልጋል
---
🌍 ንቁ እንሁን ደህንነታችንን እንጠብቅ!
ከዚህ ድምጽ አልባ ገዳይ ጪስ ለመጠበቅ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እናድርግ። 📢
#ካርቦንሞኖክሳይድ #የህዝብደህንነት #ድምጽአልባውገዳይ #የከሰልጪስ
etana