
11/12/2024
#ለጨቅላ ህፃን ልጅ ማልቀስ ምክንያት የሆኑ ነገሮች
1. ቅዝቃዜ ወይም ሙቀት ከተሰማቸው
2. ሸንተው ወይም ተፀዳድተው ምቾት ሲነሳቸው
3. የእርሀብ ስሜት ሲሰማቸው
4. እንቅልፋቸው መጥቶ ለመተኛት አመች ነገር ከሌለና ሰውነታቸውን የሚበላቸው ወይም የጎረበጣቸው ነገር ካለ
5. ሰው ሲለያቸውና ፍቅር ሲነፈጉ
6. የለመዱትንና የፈለጉትን ሲያጡ ነው። ስለዚህ ለልጀዎ ማልቀስ ምክናየት ሊሆን የሚችለው ከዚህ በለይ ከተዘረዘሩት ውስጥ ነው። ከዚህ በለይ የተዘረዘሩት ምክናየቶች ለልጅዎ ማልቀስ ምክናየት እንዳልሆነ እርግጠኛ ከሆኑ ወይም እንደተስተካከሉ ካረጋገጡ ልጅዎ የሚያለቅሰው አሞት ሊሆን ስለሚችል በአቅራቢያ ወደሚገኝ የጤና ተቋም መውሰድ ያስፈልጋል።
#ልጅዎትን እንቅልፍ አልወስድ ብሎ ካስቸገረዎ ደግሞ የሚከተሉትን ያድርጉ
1. ከላይ የተዘረዘሩ 6 ነገሮችን ያስተውሉ
2. ሰውነቱን እሽት አርገው ለብ ባለ ውሀ ይጠቡና በባዝሊን ጀርባ እና እግሩን ይሹ
3. አየሩ ቀዝቀዝ ያለ ከሆነ በስርአቱ በልብስ ይጠቅሉ። ሞቃታማ ከሆነ ግን ልብስ አያብዙበት።
4. ከታጠበ በሗላ የምግብ ፍላጎት ስለሚጨምር በደንብ ያጥቡት።
5. መታጠቡና መጥባቱ ደግሞ ለጥልቅ እንቅልፍ ስለሚረዳው የተስተካከለና ፀጥታ የተሞላበት ቦታ ላይ አብረውት ገደም ይበሉ። ይሄን ጊዜ በቀላሉ መተኛትና የእንቅልፍን ጥቅምም በስርአቱ ማግኝት ይችላል።